ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተጨማሪ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጅግጅጋ ገብተዋል።
በሶማሌ ክልል በሚኖራቸው ቆይታም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል መባሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።