ቀጥታ፡

ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የአውሮፓ ህብረት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከአዲሱ የአውሮፓ ህብረት የትብብር ኃላፊ ጌራልድ ሃልተር ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል።

ውይይቱ ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት በሰላም፣ ደህንነት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አቅም ግንባታ፣ የምግብ ዋስትና እና በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።

ሁለቱ ወገኖች አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬታሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት እ.አ.አ 2008 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሁለቱ ተቋማት እ.አ.አ ሜይ 2025 ላይ በጅቡቲ የጋራ ምክክር ያደረጉ ሲሆን በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም