ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ ፒኤስጂ ባርሴሎናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ መርሃ ግብር ፒኤስጂ ከመመራት ተነስቶ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በሉዊስ ካምፓኒስ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌራን ቶሬስ በ19ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ባርሴሎና መሪ ሆኗል።

ሴኒ ማዩሉ በ38ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል የወቅቱን የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂን አቻ አድርጓል።

ጎንዛሎ ራሞስ በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል የፈረንሳዩን ቡድን አሸናፊ ሆኗል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጣም አዝናኝ እና ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነበር።


 

በሌሎች ጨዋታዎች አርሰናል በጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ ጎሎች ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማንችስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ከሞናኮን ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። አርሊንግ ሃላንድ ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል።


 

ጆርዳን ቴዜ በጨዋታ እና ኤሪክ ዳየር በፍጹም ቅጣት ለሞናኮ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ቢልባኦን 4 ለ 1፣ ናፖሊ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።

ቪያሪያል ከጁቬንቱስ ሁለት አቻ ሲለያዩ ባየር ሌቨርኩሰን እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

አስቀድመው ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ ዩኒየን ሴይንት ጊሎይስን 4 ለ 0፤ ካራባግ ኤፍሲ ኮፐንሃገንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም