ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል
Nov 4, 2025 35
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2017 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በፎርቹና አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። አርሰናል በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን በርካታ የግብ እድሎችንም ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ውድድር ፎርማት ደረጃን በ12 ነጥብ መምራት ጀምሯል። መድፈኞቹ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም። ተቀይሮ የገባው የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን በ15 ዓመት 308 ቀናት በመጫወት በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ወጣት ተጫዋች ሆኗል። በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስላቪያ ፕራግ በሁለት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው መርሃ ግብር ናፖሊ እና ኢንትራክት ፍራንክፈርት ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል 
Nov 4, 2025 38
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በፎርቹና አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። አርሰናል በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን በርካታ የግብ እድሎችንም ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ውድድር ፎርማት ደረጃን በ12 ነጥብ መምራት ጀምሯል። መድፈኞቹ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም። ተቀይሮ የገባው የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን በ15 ዓመት 308 ቀናት በመጫወት በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ወጣት ተጫዋች ሆኗል። በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስላቪያ ፕራግ በሁለት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው መርሃ ግብር ናፖሊ እና ኢንትራክት ፍራንክፈርት ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ነው
Nov 4, 2025 104
ወላይታ ሶዶ/ጂንካ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ። የባህር በር የማግኘት ጥያቄው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የአንድን ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራትን የተሰሚነት ተፅዕኖ በአዎንታዊ መልኩ እንደሚያሳድገው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይገልፃሉ። የባህር በር ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ዕድልን ከማስፋቱም ባሻገር የአንድን ሃገር ዳር ድንበር ተከብሮ እንዲኖር የሚኖረው ሚና ቀላል አይደለም። ይህና ሌሎች ጉዳዮች ከግምት ሲገቡ ኢትዮጵያ በተሸረበባት ሴራና በልዩ ልዩ በደሎች ከባህር በር እንድትርቅ የተደረገበት ሁኔታ እጅግ የሚያስቆጭ ጉዳይ ነው። ሆኖም አሁን በኃላፊነት ላይ ያለው መንግስት የበርካታ አመታት የህዝቡ ቁጭት የነበረውን የባህር በር ባለቤትነት አጀንዳን የህልውና ጉዳይ በማድረግ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው እያደረገ ያለበት ሁኔታ ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሃሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ እንዲሁም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄና እያደረገች ባለችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተመለከተ ኢዜአ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ቆይታ አድርጓል። ምሁራኑ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አበሻ ሺርኮ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ካሉ ተጨባጭ እውነታዎች አንፃር ህጋዊና በግልጽ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው የህልውና ጉዳይ ሆኖ ህጋዊነትን፣ ታሪክንና መልክዓ ምድርን መሰረት በማድረግ የጋራ ተጠቃሚነትን በማለም የተነሳ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል የሰላምና ደህንነት ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ወንድሙ አዴ፤ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና መቆየቷ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የወጣችበት ምክንያት ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት ያልተገኘለትና ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው መሆኑም ለሁላችንም ጥያቄ ሆኗል ብለዋል። የባህር በር የማግኘቱ ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ የሆነ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ሲሉ የህግ ምሁራን ተናግረዋል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በጅንካ ከተማ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የህግ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የህግ አማካሪና አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ሙሉአለም ኃይለማርያም፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ እውነታን የያዘ በመሆኑ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል። በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የባህላዊ መብቶች የቃል ኪዳን ስምምነት ላይ ሁሉም ሀገራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል ። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን የመጠቀም ታሪካዊ፣ ህጋዊ፣ መልካአ ምድራዊ መብት ያላት መሆኑን አስረድተዋል። ሌላኛው ዐቃቤ ህግ እና የህግ አማካሪ ቢንያም አያሌው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሚያሳየው የሀገሪቱ ስልጣኔና ሌሎች የመንግስት አደረጃጀቶች በዘመናት መካከል ከባህር በር ተለይተው የማያውቁ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ህጋዊ መሰረት በሌለበት መንገድ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ በህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ ህጋዊ ስምምነት እስከሌለ ድረስ የባህር በር ባለቤት የመሆን መብቷ የተከበረ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የሚታይ

‎ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ ነው
Nov 4, 2025 99
‎አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ዜጎች የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምኅዳር እየፈጠረ የሚገኝ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ ልማት መርሃ ግብር አካል መሆኑ ይታዎሳል። በ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት የተጀመረው መርሃ ግብርም ዜጎች መሠረታዊ ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት የሚያዳብሩበትን የበይነ-መረብ (ኦንላይን) የስልጠና ምኅዳር ፈጥሯል። በተነሳሽነቱም በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ፣ በአንድሮይድና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልጠና መስኮች ዜጎች ያለምንም ክፍያ ባሉበት ቦታ በበይነ-መረብ የስልጠና እንዲከታተሉ እያደረገ ይገኛል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳው የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነትም ዜጎች በዲጂታል ዓለም ውስጥ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ፤ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች የመንግስትን አገልግሎቶች በማሳለጥ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። የ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳ ቁልፍ የዜጎች ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት ልማት መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ትግበራ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ በመገንባት በቁልፍ መሳሪያነት እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠና ከጀመረበት አንስቶም በፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ፣ ዳታ ሳይንስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊያን ላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ነው ብለዋል። በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ ከሚገኙ ዜጎች ውስጥም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው ሰርትፊኬት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል። የኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብሩም የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መርሃ ግብሩም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል በማፍራት አገልግሎት አሰጣጦችን በማዘመን በር እንደከፈተም ገልጸዋል። በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት መጨረሻም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎችን 4 ሚሊየን ለማድረስ ከክልልና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ኢትዮጵያዊያንም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናን ባሉበት ቦታ በመመዝገብ የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት አቅማቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃን የልማት አጀንዳቸው የትኩረት ማዕከል ሊያደርጉ ይገባል- ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ 
Nov 4, 2025 100
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃና እንክብካቤን እንደ ልማት አጀንዳ በመያዝ መስራት እንደሚገባቸው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው ላለፉት ሁለት ቀናት በባለሙያዎች ደረጃ ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል።   “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” በመሪ መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎችና ቀጣይ እርምጃዎች የሚመክር ነው። የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ከጸጋ ባሻገር የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፣ የምግብ ዋስትና እና የባህል ማንነት መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። ብዝሃ ህይወት እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች የዓለም ተፈጥሮ ሀብት ዘቦች ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል። ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የእንስሳትና እጽዋት መኖሪያ ቦታ መውደም እና የተለያዩ ዝርያዎች መጥፋት የብዝሃ ህይወት ሀብቶች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አፍሪካውያን ብዝሃ ህይወትን የአህጉሪቱ የልማት አጀንዳ ምሰሶ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ነው ያሉት። በአጀንዳ 2063 የበለጸገች እና ሰላማዊ አፍሪካን የመፍጠር ህልም ሊሳካ የሚችለው በዜጎች ትጋትና በዘላቂ አካባቢ ጥበቃና አስተዳደር መሆኑንም አመልክተዋል። አህጉራዊ አጀንዳዎችን ለማሳካት የፖሊሲ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ እንዲሁም ወጣቶችና ሀገር በቀል ማህበረሰቦችን በብዝሃ ህይወት ጥበቃ የመሪነት ሚና እንዲወጡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት ንግግራቸውን ወደ ተጨባጭ ስራ እና ወደሚለካ ውጤት በመቀየርና የአካባቢ ስነ ምህዳርን በመጠበቅ መጻኢውን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ እንዲሰሩ አስገንዝበዋል። አፍሪካን በዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ እና ዘላቂ አጠቃቀም መሪ እናድርጋት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ነገር እናስረክብ ሲሉም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል። በጉባኤው ላይ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ ነገ በመሪዎች ደረጃ በሚደረግ ስብሰባ ይጠናቀቃል። ጉባኤው ለአፍሪካ ብዝሃ ህይወት መመናመን፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ብክለት የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊና ታሪካዊ ተቀባይነት ያለው ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው - አምባሳደር ጥሩነህ ዜና
Nov 4, 2025 86
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትን የማስመለስ ጥያቄ ሕጋዊና ታሪካዊ ተቀባይነት ያለው ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን አንጋፋው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ጥቅምት 18/2018 ዓ/ም ማካሄዱ ይታወቃል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ያለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ አካል የነበረውን የባሕር ጠረፍ ለማጣት 30 ዓመት በላይ የወሰደውን ያህል የትግል ታሪክ አሁን ላይ ወደ ባሕር በር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመት እንደማይወስድባት አጽንኦት ሰጥተዋል። የቀይ ባሕር ባለቤትነትን ጥያቄ ለመፍታት የተረጋጋ፣ የሰከነና በውይይት ላይ የተመሰረተ አካሄድ መከተል ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለማጣት የፈጀውን ያህል ለመመለስ አይፈጅም ብለዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድም ሕጋዊና ተቋማዊ መሠረት የሌለው የሚያስቆጭ የብሔራዊ ጥቅም ስብራት አካል መሆኑን አስረድተዋል። አንጋፋው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ ሕጋዊና ታሪካዊ ቅቡልነት የሌለው ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው ታሪኳ የባሕር በር ባለቤትነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር ብትሆንም በታሪካዊ ጠላቶች ሴራ ከቀይ ባሕር እንድትገለል መደረጉን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚጋልቧቸውና ህጋዊ መሰረት የሌላቸው አካላት ምንም አይነት የህዝብ ምክክር ሳያደርጉ የባሕር በርን ያህል ግዙፍ የብሔራዊ ጥቅም አንኳር ጉዳይ ማሳጣታቸውን አስታውሰዋል። በህዝብ የተመረጠ ሕጋዊ የመንግስት አስተዳደር ባልነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተገለለችበት መንገድ ጉልህ ዓለም አቀፍ የሕግ ጥሰት የተፈጸመበት የታሪክ ስብራት መሆኑንም አስገንዝበዋል። የአሁኑ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ህዝባዊ መሠረት ያለው የጋራ ተጠቃሚነት መርህን የተከተለ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። በዚህም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የማስመለስ አካሄድ በታሪካዊ ዳራ የተደገፈ ሕጋዊ መሠረትና ተቀባይነት ያለው መሆኑን አስረድተዋል። መንግስትም የኢትጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማስመለስ እየተከተለ የሚገኘው በሳል የዲፕሎማሲ አካሄድ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከጥንተ አክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የቀይ ባሕር ቀጣናን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ የባሕሩ ባለቤትና ተጋሪ ሀገር እንደነበረችም ነው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ያስታወሱት። በፖለቲካ ሴራ ከአካባቢው እንድትርቅ መደረጉ የቀይ ባህር ቀጣና የአሸባሪዎች መናኸሪያ በመሆን ለቀጣናው ሰላምና ደኅንነት መታወክ መንስኤ እየሆነ መጥቷል ብለዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ መሆኑና ብሔራዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ ባለፈ የቀጣናውን ደኅንነት በማስጠበቅ ለዓለም አቀፍ የሚተርፍ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። ኢትጵያውያን፣ የቀጣናው ሀገራትና የዓለም ህዝብ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ምክንያታዊ ጥያቄ በጎ ምላሽ እንዲያገኝ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአውሮፓ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እንዲሳተፉ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል-ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
Nov 4, 2025 114
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መሰማራት ለሚፈልጉ የአውሮፓ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረም በፈረንሳይ ፓሪስ ተካሄዷል። ኢትዮጵያ በፎረሙ ላይ የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቿ የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማሳለጥ ረገድ እየተወጡት ያለውን ሚና አቅርባለች። በዘመናዊ ሎጅስቲክስ እና የትራንስፖርት መሰረተ ልማት የተደገፉት የኢኮኖሚ ዞኖች ለባለሀብቶች የአሰራር ሂደቶችን የሚያቀላጥፉ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ እና የተቀናጁ የኢንዱስትሪ አገልግሎቶችን እንደሚሰጡ ተመላክቷል። በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ ለባለሀብቶች ምቹ ምህዳርን ለመፍጠር እና የንግድ ስራ ምቹነት ለማሻሻል ያላትን ቁርጠኝነት፣ የህግ ማዕቀፍ ግልጽነትና ተጠያቂነት እና የመንግስት-የግል አጋርነቶች አስመልክቶ ለፎረሙ ተሳታፊዎች ገለጻ ተደርጓል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የኢንዱስትሪ ማዕከላት ብቻ ሳይሆኑ የኢንቨስትመንት፣ ኢኖቬሽን እና ንግድ መግቢያ በሮች ናቸው ብለዋል። መንግስት መሰረተ ልማትን በማቅረብ፣በመደገፍ እና አጋርነትን በማጠናከር ባለሀብቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል። የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሞቱማ ተመስገን ዘመናዊ መሰረተ ልማት፣ ተአማኒነትን ያላቸው መገልገያዎች እና ፍላጎትን ያማከሉ ልዩ አገልግሎቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን አመልክተዋል። ግባችን ኢትዮጵያን የዘላቂ ኢንቨስትመነት መዳረሻ ማድረግ፣ እድገትን ማረጋገጥ እና ለሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን ምቹ እድሎችን መፍጠር ነው ብለዋል። በውይይቱ ላይ የግሎባል አፍሪካ ሎጅስቲክስ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሃይም ኮንፎርቲ፣ የጀርመን የንግድ ባንክ ኬኤፍደብሊው አይፔክስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሪን ሙልደር እና የዓለም አቀፉ የምህድስና አማካሪ ድርጅት ሲስትራ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ሉዊስ ዴቪድ የዓለም ኢንቨስትመንት አዝማሚያዎች እና ቀጣናዊ የሎጅስቲክስ ልማትን አስመልክቶ ሀሳባቸውን አጋርተዋል። በፎረሙ ላይ የተሳተፉ የአውሮፓ ባለሀብቶች እና የንግድ መሪዎች የኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በማኑፋክቸሪንግ፣ሎጅስቲክስ እና ንግድ ዘርፍ ያሉ ስትራቴጂካዊ እድሎችን ለማስፋት የሚያግዙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያጠናክሩም መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን የጥፋት እቅድ በማምከን ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን- የመንግስት ሰራተኞች
Nov 4, 2025 111
ወልዲያ ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች ገለጹ። "የውጭ ባዳ እና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የውይይት መድረክ አካሂደዋል።   በውይይቱ መድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሲሳይ አለሙ እና አቶ አበራ አብርሃ፤ ለኢትዮጵያ መልካም ነገር የማያስቡ እና የማይመኙ ታሪካዊ ጠላቶች በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለጥፋት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም የውስጥ ባንዳዎችን ተልእኮ ፈፃሚ በማድረግ የልማት ስራዎች እንዲደናቀፉ እና በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲደፈርስ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ጭምር ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።   የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ አሰፋ፤ የባንዳዎችና ባዳዎች የጥፋት ሙከራና እንቅስቃሴ በሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ እና በጸጥታ ሃይሉ ጥብቅ ቁጥጥር እየመከነ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት የህዝቡ በተለይም የመንግስት ሰራተኛው እገዛና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው-ምሁራን
Nov 4, 2025 141
ድሬደዋ፤ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦በአሻጥር ያጣነውን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ። የባሕር በር ጉዳይ የሕልውናና ሀገርን የማስቀጠል ተቀዳሚ አጀንዳ መሆኑንም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የመንግሥት አቋምና አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ የተደረገበት መንገድ እና ውሳኔ ተፈትሾ ተጨባጭ ማስረጃ መታጣቱን ማንሳታቸው ይታወሳል። የባሕር በር ጉዳይ የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጥረቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን በጉዳዩ ላይ አነጋግሯል። የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ ሐይሉ እንዳሉት፥ በአሻጥር ያጣነው የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ወቅታዊ፣ጊዜው የሚያስገድደንና የዜጎች ሁሉ ቀዳሚ አጀንዳ ነው ብለዋል።   ሀገራችን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄዋ በታሪክም ሆነ በአለም አቀፍ ህጎች ተቀባይነት ያለው የሕልውና ጥያቄ ነው ያሉት ደግሞ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምሕር አቶ ዋኬና አፍካላ ናቸው። ይህን ታሪካዊና ሕጋዊ መብቷን በዲፕሎማሲያዊ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ ለማግኘት መንግስት የጀመራቸው ተግባራት እና ውሳኔዎች ወሳኝ እርምጃ መሆናቸውን አንስተዋል።   ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ ሐይሉ አክለው እንደገለፁት፥ ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተነጠለችበት መንገድ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ የሚመላለስ አሁናዊ የሕልውና ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል። የሀገርን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ፣ዕድገትና ሕልውና ለማረጋገጥ የመንግስት አቋምና እየተጓዘበት ያለው መንገድ ትክክለኛና ወቅታዊ ነው ብለዋል። ከ130 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ እና ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት አገር ባሕር ተዘግቶባት ሕልውናዋን ማስቀጠል አይቻልም የሚሉት ደግሞ መምሕርና የአፍሪካ ቀንድ ፀሐፊ አቶ ዋኬና አፍካላ ናቸው። የባሕር በር ጥያቄን በአለምአቀፍ ሕጎችና በጋራ የመልማት ተቀዳሚ ዲፕሎማሲያዊ መርሕ ከዳር ለማድረስ የተቀናጀ ጥረቱ መጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ተንሳይ፥ የሕልውና ጥያቄ የሆነውን የባሕር በር የማግኘት ጉዞ በማሳካት ረገድ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ጭምር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ብለዋል። በተለይም የኢትዮጵያን መልማትና ማደግ ባገኙት አጋጣሚ የሚያጠለሹት ግብፅን የመሳሰሉ ታሪካዊ ባላንጣ ሀገራትን መልዕክቶች በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ በማጋለጥ የሀገራችንን በጋራ የመልማት ተቀዳሚ መርሕን ማሳወቅ ላይ መረባረብ ይገባናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን እንዳትጠቀም የሚከለክል ሕግ የለም
Nov 4, 2025 113
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን እንዳትጠቀም የሚከለክል ሕግ እስከሌለ ድረስ ቀይ ባሕርን ለመጠቀም ጥያቄ ማንሳቷ ሕጋዊ መሠረት እንዳለው ተገለጸ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህርና ተመራማሪ ኪዳኔ ደያሳ፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት እያደረገች ያለውን ሂደት ከሕግ አንጻር በቅርብ እንደሚከታተሉ አንስተዋል። በዚህም መሠረት የባሕር በር አልባ የተደረገችው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ የባሕር መዳረሻ የማግኘት መብት እንዳላት ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ቀይ በሕርን እንዳትጠቀም የሚከለክል ሕግ የለም ብለዋል። ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት የነበረው አሰብ ወደብ በአልጀርስ ስምምነት ላይ እንኳን ምን መሆን እንዳለበት በግልጽ የተገለጸ ነገር አለመኖሩንም አስረድተዋል። የአልጀርስ ስምምነት ሲፈረምም ሀገራቱ ይገባኛል በሚሉት ድንበር ላይ ብቻ ማተኮሩን አውስተዋል። ስለዚህ አሰብ ወደብንና ቀይ ባሕርን ኤርትራ የኔ ብላ እንድትጠቀምና ኢትዮጵያ አንዳትጠቀም ተብላ እንድትከለከል የሚያደርግ ሕጋዊ መሠረት አለመኖሩን ነው ያረጋገጡት። በሌላ በኩል ከዓለም አቀፍ ንግድ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ ከፍተኛ ባሕር የሚባል የሁሉም የሆነ ሀብት መባሉን ጠቁመው፤ ይህን ሃብት ለመጠቀም የባሕር በር የግድ ያስፈልጋል ብለዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ በዚህ አማራጭም ቀይ ባሕርን የመጠቀም መብት እንዳላት መዘንጋት የለበትም ነው ያሉት። በአጠቃላይ ከላይ በተገለጹት መነሻዎች መሠረት ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ያነሳችው ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕጋዊ መሠረት እንዳለው በአጽንኦት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት የነበረው አሰብ ወደብና ቀይ ባሕር ወደ ኤርትራ እንዲጠቃለል የተደረገበት አግባብን የሚያሳይ ማስረጃ አለመገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ መናገራቸው ትክክል መሆኑንም ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ካለችበት የኢኮኖሚ፣ የሕዝብ ቁጥርና ዘርፈ-ብዙ ዕድገት አኳያ ለወጪና ገቢ ንግድ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ነው ያስረዱት።
የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነት እና አቅም ያለው ሰራዊት ተገንብቷል- ሜጀር ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ 
Nov 3, 2025 223
ጅማ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦ የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነት እና አቅም ያለው ሰራዊት መገንባቱን የሀገር የመከላከያ ሰራዊት የሰላም ማስከበር ማእከል ኃላፊ ሜጀር ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ ገለጹ። የዳሎል ማዕከላዊ እዝ አባላት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች "እንዳይደገም መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ሃሳብ የጥቅምት 24ቱን ጥቃት በተለያዩ ዝግጅቶች አስበውታል።   በዚሁ ሁነት ላይ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰላም ማስከበር ማእከል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ፤ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር የሚያስችል ዝግጁነትና የተሟላ አቅም የገነባ መሆኑን ገልጸዋል። የሰራዊቱ ወትሮ ዝግጁነትና የግዳጅ አፈፃፀም ብቃት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ከሀገርም ባለፈ ለሌሎች ሃገራት የጀግንነት መገለጫ እና የሰላም ተምሳሌት የሆነ ብቁ ሰራዊት ተገንብቷል ብለዋል። የሀገርን ክብርና ሉአላዊነት ለማስከበር የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነትና ጠንካራ አቅም ያዳበረ ሰራዊት መገንባቱን አንስተው ለማንኛውም ግዳጅ ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። የዳሎል ማእከላዊ እዝ አባላትም በተሰማሩበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ በጀግንነት ውጤታማ ተልእኮዎችን በመፈፀም የሚታወቁ መሆኑን አንስተው ይህንኑ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።   የዳሎል ማእከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው ጥቅምት 24ን ማስታወስ ያስፈለገው ሰራዊቱ ለሀገር የከፈለውን መስዋእትነት ለማሳየትና መሰል ጥፋቶች በቀጣይ እንዳይደገሙ ትውልዱ እንዲማርበት በማሰብ ነው ብለዋል።   የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር አንድነት እና ሰላም መረጋገጥ በጽናትና በጀግንነት መቆሙን ገልጸው ለቀጣይም የላቀ ዝግጁነት ያለው መሆኑን አረጋግጠዋል። በዚሁ መድረክ ላይ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት በጅማ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር ንጉሱ አደም (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጀግንነት ጸንቶ የቆመ፣ የሀገር ህልውና መሰረት ብሎም የዓለም የሰላም ማስከበር ተምሳሌት መሆኑን አንስተዋል። የሀገሩን ዳር ድንበር ከማስከበር አልፎ በተለያዩ ሃገራት በሰላም ማስከበር ተልእኮ የተመሰከረለት ጠንካራ ሰራዊት መሆኑን አስታውሰው በዚህም ክብርና አድናቆት ሊቸረው ይገባል ብለዋል። በጅማ ከተማ በተካሄደው መርሀ ግብር ላይ የሰራዊቱ አባላትና ከፍተኛ መኮንኖች፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በመጠበቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ተዘጋጅተናል- ሰልጣኝ የሕግ አስከባሪዎች 
Nov 3, 2025 232
ገንዳ ውኃ፤ ጥቅምት 24/2018 (ኢዜአ):-የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በመጠበቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መዘጋጀታቸውን በምዕራብ ጎንደር ዞን የተመደቡ አዲስ የአድማ መከላከልና መደበኛ ፖሊስ አባላት ገለጹ። ሰልጣኝ የሕግ አስከባሪዎቹ ወደ ዞኑ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ከሰልጣኞቹ መካከልም የአድማ መከላከል ፖሊስ ሙሐመድ ሱሌማን በሰጠው አስተያየት፤ ሀገርንና ሕዝብን ለማገልገል በነበረው ፍላጎት ወደ ፖሊስ ተቋም በመቀላቀል ተገቢውን ፖሊሳዊ ስልጠና መውሰዱን ተናግሯል።   በስልጠና ቆይታው ያገኘውን እውቀትና ፖሊሳዊ ጥበብ በመጠቀም የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በመጠበቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የድርሻውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል። ኮንስታብል ዳዊት ሞላ በበኩሉ፤ የተሰጠውን ሀገራዊና ሕዝባዊ አደራ ለመወጣት አበክሮ እንደሚሰራ ገልፆ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሁሉ የበኩሉን ሚና በመወጣት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እንደሚተጋ ተናግሯል።   ሰልጣኞቹ የተጣለባቸውን ሕዝባዊ አደራ ታማኝነትን በጠበቀ አግባብ ለመወጣት መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ተወካይና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ መሰንበት መልካሙ እንደገለጹት፤ ሰልጣኝ የሕግ አስከባሪዎች ሰላምን ለማፅናት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተገቢው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል።   የዞኑ ሕዝብ ሰላም ወዳድና የልማት አርበኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሕብረተሰቡ ለፀጥታ አካሉ ተልዕኮ ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል። መከላከያ ሰራዊት የ504ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ቾምቤ ወርቁ በበኩላቸው፤ ሰራዊቱና የክልሉ የፀጥታ ኃይል የጥፋት ኃይሎችን ተልዕኮ በቅንጅት በማምከን አኩሪ ገድል እየፈፀሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።   ሰላምን የማፅናትና የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባር እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በቀጣይም በሕዝቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የባንዳ ስራ ላይ የተሰማሩ ኃይሎች ከሀገር ክህደት ተግባራቸው ሊቆጠቡ ይገባል - ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
Nov 3, 2025 239
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦ የባንዳ ስራ ላይ የተሰማሩ ኃይሎች ከሀገር ክህደት ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ። የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ጥቃት የሚዘከረው የተፈጸመው አሳዛኝ ድርጊት መቼም እንዳይደገም ለማስታወስ መሆኑንም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ገልጸዋል። የመከላለከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ የተፈጸመበት ጥቃት አምስተኛ ዓመት ዝክረ ሰሜን ዕዝ "እንዳይደገም መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ተከብሯል።   ከአምስት ዓመት በፊት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የጀግናው መከላከያ ሰራዊት አካል የሰሜን ዕዝ ክህደት እንደተፈፀመበት ይታወቃል። በመርሃ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌሎች ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ጥቅምት 24 ቀን የሰሜን ዕዝ ዝክረ ሰማዕታት ቀን ነው። የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ዳር ዳር ድንበር በማስከበር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኑንም አውስተዋል። የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለትግራይ ክልል ምሽግና አጥር እንደነበር ገልጸው፤ እስከ አሁን ከሰሜን ዕዝ ውጪ በራሱ ዜጎች ጥቃት የደረሰበት አጋጣሚ እንዳልተፈጠረ ተናግረዋል። የመከላከያ ሰራዊት ከራሱ ቀንሶ በትግራይ ብዙ ትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማትና የግብርና ልማት እንዳከናወነ ገልጸው፣ ጥቅምት 24 ቀን የተፈጸመው ድርጊት ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ነጥብ ነው ብለዋል። የሰሜን ዕዝ ጥቃት መቼም እንደማይረሳ ገልጸው፤ ቀኑ የሚዘከረው መቼም እንዳይደገም መሆኑን አንስተዋል።   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ዕለቱን ሲያስታውሱ፤ መንግሥት በወቅቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተለኮሱ ግጭቶችን ለማብረድ የሚታትርበት እንጂ የጦርነት ዝግጁነት እንዳልነበረው አውስተዋል። መንግሥት ሁልጊዜም ለሰላማዊ መንገድ በሩን ክፍት ማድረጉን ጠቁመው፤ ከትላንት ባለመማር የሚደረግ ፉከራ መቆም አለበት ብለዋል። የቀድሞው ህወሓት ጥቂት አባላት የታጠቁ ኃይሎችን በመደገፍ፣ ሀገር ለማፍረስ ከጎረቤት ሀገር ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በዲ.ዲ.አር የተሰባሰቡትን በመበተን የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት እየጣሱ መሆኑንም ገልጸዋል። የባንዳ ስራ ላይ የተሰማሩ እነዚህ ህዝቡን የማይወክሉ ኃይሎች ከሀገር ክህደት ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ተናግረዋል። የመከላከያ ሰራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን በበኩላቸው፤ ከአምስት ዓመት በፊት በሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላት ላይ የተፈፀመው ጥቃት በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ደባ መሆኑን ጠቁመዋል። ዝክረ ሰሜን ዕዝ ወቅቱን በሚመጥን መልኩ እየተከበረ ነው ብለዋል። የተፈጸመው ጥቃት እንዳይደገም መቼም አንረሳውም ያሉት ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው፣ ጥቃቱን ለመመከት ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ የሰራዊቱ አባላትን ለማስታወስ እና ለተጋድሏቸው ዕውቅና ለመስጠት እንደሚዘከር ገልጸዋል።
ከምክር ቤቱ የመጨረሻ ዓመት የሥራ ዘመን ምን ይጠበቃል?
Nov 3, 2025 192
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦ ከ6ኛው ዙር ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጨረሻ ዓመት የሥራ ዘመን የሚጠበቁ ጉዳዮች ምንድ ናቸው? 6ኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ዘንድሮ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሕገ-መንግስቱ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ሕግ ያወጣል፣አስፈጻሚ ተቋማትን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል። የፓርላማ ዲፕሎማሲ እንዲሁም የህዝብ ውክልና ሥራዎችን ያከናውናል። ምክር ቤቱ ባለፉት አራት ዓመታት ሀገራዊ ለውጡን የበለጠ የሚያሳልጡና የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የምክር ቤቱ አባላት ያነሳሉ። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የምክር ቤቱ አባላት በቀሪ የሥራ ጊዜያቸው የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ከምክር ቤቱ አባላት መካከል መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) በተያዘው ዓመት ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ የሚያደርገው ውይይት ነው ብለዋል።   ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሥብራት ለመጠገንና ነባር ችግሮችን በምክክር የመፍታት ባህል ለማዳበር መፍትሄ እንደሚያመጣ እንደታመነበትም ነው ያነሱት። ምክር ቤቱ በቀሪ የሥራ ዘመኑ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባና ችግሮች በምክክር መፍትሄ እንዲያገኙ አበክሮ ይሰራል ብለዋል። የፓርላማ ወዳጅነት ቡድኖች ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ የገለጹት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አባል ሳዲቅ አደም ናቸው።   በፓርላማ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች የሚያስከብሩና የሀገሪቷን የልማት ፍላጎትን የሚያስረዱ ጉዳዮች ላይ በስፋት ይሰራል ብለዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው በተያዘው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን አስታውሰዋል።   የምክር ቤቱ አባላትም በመጨረሻ ዓመት የሥራ ጊዜያቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች በተሻለ ፍጥነትና ፈጠራ እውን እንዲሆኑ የተለየ ድጋፍና ክትትል ያደርጋሉ ብለዋል። ለሚቀጥለው ምክር ቤት አስቻይ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የ5ኛ ዓመት የምክር ቤት አባላት ድርሻ መሆኑንም አንስተዋል።
የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች ለከተማቸው እድገትና ሰላም መስፈን በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን  እየተወጡ ነው
Nov 2, 2025 302
ጎንደር ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ):-ለጎንደር ከተማ እድገትና ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በጎንደር ከተማ የንግዱ ማህብረሰብ አባላት ገለጹ፡፡ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በአካባቢ ሰላምና ልማት ዙሪያ የከተማው የንግዱ ማህበረሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ አካሂደዋል፡፡   ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ አብዱራህማን ሰኢድ ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ዳር እንዲደርሱና ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። በተለይም በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም ለማጽናትና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት መሳተፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ተሾመ ንጉሱ በበኩላቸው እንደ አንድ የንግዱ ማህበረሰብ አባል ህብረተሰቡን የሚያማርሩ ህገወጦችን በማጋለጥ መንግስት ለሰላም መስፈን የሚያደርገውን ጥረት ይበልጥ ለማገዝ እንደሚተጉ አስረድተዋል። የንግዱ ማህበረሰብ የግብር ግዴታውን በመወጣት ለሀገር እድገት የሚያበረክተውን ሚና ማጠናከር እንደሚገባውም ጠቁመዋል።   በምንከፍለው ግብር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን በማየታችን ተደስተናል፤ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻዬን ለማበርከት ዝግጁ ነኝ ያሉት ደግሞ አቶ ጀማል ቃሲም ናቸው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ጥሩዬ አታክልት እንደገለጹት በከተማው ሰላም መረጋገጡ የንግድ እንቅስቃሴው እንዲነቃቃ አስችሏል።   ይህም የንግዱ ማህበረሰብ ሰርቶ በሚያገኘው ልክ የመንግስትን ግብር በታማኝነትና በወቅቱ እንዲከፍል ምቹ መደላድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ የንግዱ ማህበሰረብም በሰላም ግንባታ እያበረከተ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡ በምክክር መድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከስድስት ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ማህበራዊ
በዞኑ የተጀመረውን የሥርዓተ ምግብ ሞዴል መንደር ምስረታ ለማስፋፋት ይሰራል
Nov 4, 2025 75
ደብረ ብርሃን፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተጀመረው የሥርዓተ ምግብ ሞዴል መንደር ምስረታ ውጤታማ በመሆኑ ወደሌሎች ዞኖች ለማስፋፋት እንደሚሰራ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በዞኑ አንጎለላና ጠራ ወረዳ የስርዓተ ምግብ ሞዴል መንደር ምርቃትና የስንዴ ክላስተር ልማት የመስክ ምልከታ ዛሬ ተካሂዷል። በቢሮው የሥርዓተ ምግብ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ሙጬ በዚህ ወቅት እንደገለጹት የስርዓተ ምግብን በማሻሻል ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠርና እድገትን ለማፋጠን እየተሰራ ነው። በክልሉ ትርፍ አምራች በሆኑ ወረዳዎችና ዞኖች ጭምር በአመለካከት ምክንያት የመቀንጨርና የመቀጨጭ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚስተዋል አስታውሰዋል። ይሄን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት በሰሜን ሸዋ ዞን የተጀመረው የሥርአተ ምግብ ሞዴል መንደር ምስረታ ውጤታማ በመሆኑ ወደሌሎች ዞኖች ተሞክሮውን ለማስፋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ታደሰ ማሙሻ በበኩላቸው እንዳሉት ስርዓተ ምግብን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በዚህም በሰባት ወዳዎች 4 ሺህ 200 እናቶችን በስርዓተ ምግብ ፕሮግራም በማቀፍ ስርአተ ምግብን የሚያሻሽሉ ምርቶችን እንዲያመርቱና ልጆቻቸውን እንዲመግቡ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጎልባ ቀበሌ 60 እናቶች የስርዓተ ምግብ መስፈርትን አሟልተው በመገኘታቸው ዛሬ መመረቃቸውንም ተናግረዋል። የተመረቁት እናቶች አትክልት፣ እንቁላል፣ ወተትንና በንጠረ ነገር የበለጸጉ የምግብ አይነቶችን አምርተው በመጠቀም ያላቸውን ልምድ ለሌሎች ወረዳዎች እንዲያካፍሉ ይደረጋል ብለዋል። የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመ በአስተሳሰብ ችግር ምክንያት አርሶ አደሮች በሴፍትኔት ፕሮግራም ሲረዱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። አሁን ላይ የአመለካከት ለውጥ በማድረግ ካመረቱት ምርት ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ጤናማና አምራች ትውልድ ለመገንባት እያደረጉት ያለው ጥረት ውጤት ማምጣቱን ተናግረዋል። ከፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች መካከል ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጀማው እንደገለጹት በጓሯቸው አትክልት ማልማታቸውና ዶሮና ላሞችን ማርባታቸው ለልጆቻቸው የተመጣጠነ ምግብ ለመስጠት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። ይህም ሕፃናት ጤናቸው እንዲጠበቅ፣ ጠንካራ እንዲሆኑና በትምህርታቸውም ውጤታማ እየሆኑ እንዲመጡ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ወይዘሮ ማርታ ሸንቁጤ በበኩላቸው በባለሙያዎች የሚሰጣቸውን የክህሎት ትምህርት ተጠቅመው የቤተሰባቸውን የአመጋጋብ ሥርአት በማሻሻላቸው የልጆቻቸው የእድገትና የጤና ሁኔታ መሻሻሉን ተናግረዋል።  
ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ2 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ ነው 
Nov 4, 2025 91
ደሴ ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦በደሴ ከተማ የሚገኘው ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ2 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ። የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ እንደገለጹት፣ ሆስፒታሉ በዓይን ሞራ ግርዶሽ የተጠቁ ወገኖችን ለማገዝ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና መስጠት ጀምሯል።   በአገልግሎቱ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ወሎ፣ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብ እንዲሁም ከሰሜን ሸዋ ዞኖችና አጎራባች ክልሎች ለሚመጡ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ። ሕክምናው ከኪውር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር እየተሰጠ ሲሆን የታካሚዎች የትራንስፖርትና የምግብ ወጪ በመሸፈን ሕክምናውን እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የሆስፒታሉ የዓይን ሕክምና ክፍል ኃላፊና የነጻ ሕክምናው አስተባባሪ አቶ እንዳልክ ያረጋል፤ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ብዙውን ጊዜ በዕድሜ መግፋት የሚከሰት የጤና ችግር መሆኑን አንስተው፣ በወቅቱ ካልታከመ ለዓይነ ስውርነት እንደሚዳርግና ሆስፒታሉም ይህን ለመታደግ በዘመቻ ነጻ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።   በቀን እስከ 400 ሰዎች ሕክምናውን እንደሚያገኙ ጠቁመው፤ ለዚህም 9 የዘርፉ ስፔሻሊስት ዶክተሮችን ጨምሮ ከ100 በላይ የዓይን ሐኪሞችና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን አስረድተዋል። የነጻ ሕክምናው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አቶ ተሾመ እሸቴ በሰጡት አስተያየት ለዓመታት የዓይን ብርሃናቸውን በማጣታቸው ተቸግረው ቆይተዋል። በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ሕክምና ሁለቱም ዓይኖቻቸው ማየት በመጀመራችው መደሰታቸውን ጠቅሰው፤ "እየተመራሁ መጥቼ እራሴን ችዬ መንቀሳቀስ ጀመርኩ" ብለዋል።   ሌላኛዋ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ወይዘሮ መሬማ ማህሙድ በበኩላቸው፣ በሕክምናው የሁለቱም ዓይኖቻቸው ሙሉ ብርሃን በመመለሱ ዳግም የተወለዱ ያህል ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታሉ ባለፉት ዓመታት በዘመቻ ብቻ 19ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት መስጠቱን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን እንግልትን አስቀርቶልናል-  ተገልጋዮች
Nov 4, 2025 72
አርባ ምንጭ ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን እንግልትን በማስቀረት የተገልጋዩን እርካታ እያሳደገ መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ተገልጋዮች እንደገለፁት፤ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል እየሰጠ ያለው ከወረቀት ንክኪ ነፃ አገልግሎት የተገልጋዩን ማህበረሰብ እንግልት ማስቀረት አስችሏል። ከሆስፒታሉ ህክምና ተገልጋዮች መካከል ከቡርጂ ዞን የመጡት አቶ ደበበ ጮታ በሆስፒታሉ የረጅም ግዜ ተገልጋይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።   አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ በሚመጡበት ወቅት የአገልግሎት አሰጣጡ መዘመን የተገልጋይን የጊዜና የገንዘብ ብክነት ማስቀረት እንዳስቻለ ተናግረዋል። ሆስፒታሉ የተገበረው ከወረቀት ንኪክ ነፃ አገልግሎትና የባለሙያዎች ትህትና አስደሳች መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ የምስራች ጉጃ ናቸው።   የሆስፒታሉ የአገልግሎት ቅልጥፍና ከአንዱ ክፍል ወደ ሌላው ያደርጉት የነበረን እንግልት ማስቀረቱንና በመድኃኒት አቅርቦት ረገድም መሻሻል መኖሩን ጠቁመዋል። የሆስፒታሉ ምድረ ግቢም ውብና ሳቢ መሆኑ ለታካሚዎች ተጨማሪ የፈውስ እቅም እንደሆነም አስረድተዋል። በሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያ ዶክተር ወንድይፍራው ከበደ ሆስፒታሉ በህክምና ባለሙያዎችና መሣሪያዎች በበቂ ሁኔታ መደራጀቱን ጠቅሰው ህሙማንን በአክብሮትና በእንክብካቤ እያገለገልን እንገኛለን ብለዋል።   የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አምባቸው ዱማ በበኩላቸው በሆስፒታሉ የታካሚዎችን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን በማዘመን ሙሉ በሙሉ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል። ይህም በካርድ ፍለጋና በሌሎች ምክንያቶች ይፈጠር የነበረውን እንግልት ያስቀረ መሆኑን ጠቅሰዋል።   በተጨማሪም ታካሚዎች ቤታቸው ሆነው የህክምና የምክር አገልግሎትና ቀጠሮ የሚይዙበት ነፃ የስልክ መስመር መዘጋጀቱን ስረድተዋል። ሆስፒታሉ የአንጎል ቀዶ ህክምናን ጨምሮ በተለያየ ዘርፍ ስፔሻሊስት የሆኑ ሐኪሞችን የያዘና ኤም አር አይን ጨምሮ በዘመናዊ የህክምና መሣሪያዎች የተደራጀ በመሆኑ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚላኩ ታካሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ገልጸዋል። በአካባቢው በሌሎች ሆስፒታሎች የማይሰጡ የቃጠሎና የኦክሲጅን ህክምናዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በ1961 ዓ.ም የተመሰረተው የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከጋሞ፣ ከጎፋ፣ ከባስኬቶ፣ ከጋርዱላ፣ ከኮንሶ፣ ከቡርጂ፣ ከኮሬ፣ ከአሪ እና ከደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም ከከፊል ኦሮሚያ እና ከሲዳማ ክልሎች ለሚመጡ ተገልጋዮች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሻሻል ምቹ የመማር ማስተማር ምኅዳር ፈጥሯል  
Nov 4, 2025 87
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሻሻል ምቹ የመማር ማስተማር ምኅዳር መፍጠሩን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች ገለጹ። በ2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተገበረው የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት መሰረት እየጣለ ይገኛል። መርሃ ግብሩም ባለፉት ዓመታት ምቹ የመማር ማስተማር ምኅዳር በመፍጠር በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ስኬት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተገልጿል። የቡርቃ ዋዩ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አዲሱ ግዛው፤ መርሃ ግብሩ በተማሪ ምገባ አገልግሎትና ትምህርት ጥራት ላይ ምቹ የመማር ማስተማር ምኅዳር ፈጥሯል ብለዋል።   መርሃ ግብሩም የህዝብና መንግስትን ትብብር በማጠናከር የትምህርት ቤቶችን ግብዓት በማሟላት በተማሪ ቁጥርና በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ እንዲመዘገብ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ ማድረጉንም ነው የገለጹት። የእንጦጦ ማርያም ቅድመ አንደኛ፣ መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ኢፋ ሀይሌ፤ መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን ከክፍል ወደ ክፍል የማለፍ ውጤታማነት እያሻሻለ ነው ብለዋል።   በተጨማሪም በመርሃ ግብሩ የቤተ-መጽሐፍትና የምርምር ክፍሎችን የቁሳቁስ ፍላጎት በማሟላት ተማሪዎች ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያቀናጀ ዕውቀት እንዲጨብጡ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)፤ የትምህርት ለትውልድ ሀገር አቀፍ መርሃ ግብር ምቹ የመማር ማስተማር ምኅዳርን በመፍጠር ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ነው ብለዋል።   በቅድመ አንደኛና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ በምገባ መርሃ ግብር፣ መምህራንን በማብቃትና የትምህርት ቤቶችን ቁሳቁስ በማሟላት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን እያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል። የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት በማሟላት በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ጉልህ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ነው
Nov 4, 2025 104
ወላይታ ሶዶ/ጂንካ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ። የባህር በር የማግኘት ጥያቄው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የአንድን ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራትን የተሰሚነት ተፅዕኖ በአዎንታዊ መልኩ እንደሚያሳድገው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይገልፃሉ። የባህር በር ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ዕድልን ከማስፋቱም ባሻገር የአንድን ሃገር ዳር ድንበር ተከብሮ እንዲኖር የሚኖረው ሚና ቀላል አይደለም። ይህና ሌሎች ጉዳዮች ከግምት ሲገቡ ኢትዮጵያ በተሸረበባት ሴራና በልዩ ልዩ በደሎች ከባህር በር እንድትርቅ የተደረገበት ሁኔታ እጅግ የሚያስቆጭ ጉዳይ ነው። ሆኖም አሁን በኃላፊነት ላይ ያለው መንግስት የበርካታ አመታት የህዝቡ ቁጭት የነበረውን የባህር በር ባለቤትነት አጀንዳን የህልውና ጉዳይ በማድረግ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው እያደረገ ያለበት ሁኔታ ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሃሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ እንዲሁም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄና እያደረገች ባለችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተመለከተ ኢዜአ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ቆይታ አድርጓል። ምሁራኑ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊና ትክክለኛ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አበሻ ሺርኮ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ካሉ ተጨባጭ እውነታዎች አንፃር ህጋዊና በግልጽ የቀረበ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው የህልውና ጉዳይ ሆኖ ህጋዊነትን፣ ታሪክንና መልክዓ ምድርን መሰረት በማድረግ የጋራ ተጠቃሚነትን በማለም የተነሳ በመሆኑ ተገቢ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል የሰላምና ደህንነት ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ወንድሙ አዴ፤ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና መቆየቷ ብዙ ዋጋ አስከፍሏል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የወጣችበት ምክንያት ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት ያልተገኘለትና ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው መሆኑም ለሁላችንም ጥያቄ ሆኗል ብለዋል። የባህር በር የማግኘቱ ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ ህጋዊ ጥያቄ በመሆኑ ተገቢ የሆነ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ሲሉ የህግ ምሁራን ተናግረዋል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በጅንካ ከተማ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የህግ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በመልክአ ምድር፣ በህግም ይሁን በታሪክ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የህግ አማካሪና አቃቤ ህግ የሆኑት አቶ ሙሉአለም ኃይለማርያም፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በየትኛውም መመዘኛ እውነታን የያዘ በመሆኑ ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አስረድተዋል። በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የባህላዊ መብቶች የቃል ኪዳን ስምምነት ላይ ሁሉም ሀገራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል ። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን የመጠቀም ታሪካዊ፣ ህጋዊ፣ መልካአ ምድራዊ መብት ያላት መሆኑን አስረድተዋል። ሌላኛው ዐቃቤ ህግ እና የህግ አማካሪ ቢንያም አያሌው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደሚያሳየው የሀገሪቱ ስልጣኔና ሌሎች የመንግስት አደረጃጀቶች በዘመናት መካከል ከባህር በር ተለይተው የማያውቁ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ህጋዊ መሰረት በሌለበት መንገድ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ በህግ አግባብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ ህጋዊ ስምምነት እስከሌለ ድረስ የባህር በር ባለቤት የመሆን መብቷ የተከበረ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን 44ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው
Nov 4, 2025 68
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 44 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው የበጋ የመስኖ ልማት ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አካሂዷል። የዞኑ ግብርና መምሪያ አቶ ታደሰ ማሙሻ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የዞኑን የምግብ ሉአላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ለገበያ የሚሆን ለማምረት ትኩረት ተሰጥቷል። ለዚህም 44 ሺህ ኼክታር መሬት በበጋው ወራት በመስኖ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስረድተዋል። በአርሶ አደሮች ተሳትፎ በመስኖ ከሚለማው መሬት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብአትና ገበያን ለማረጋጋት መታቀዱን ተናግረዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅትን ሳይጠብቅ ባሉ የውሃ አማራጮች መስኖን በመጠቀም ስንዴን በዓመት ሁለት ጊዜ በማምረት የምግብ ዋስትናውን እያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል። ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግም መንግስት የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በወቅቱ እያሰራጨና የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ የሲያ ደብርና ዋዩ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን እንዳላማው ፤ በወረዳው 850 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። በወረዳው ከ1 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ እንደሚለማ የተናገሩት ደግሞ የአሳግርት ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ወሰኔ አምበርብር ናቸው። እቅዱን ለማሳካትም የመሬት ልየታ፣ የውሃ መሳቢያ ሞተር አቅርቦትና ሌሎች ዝግጅቶች ተጠናቀው ተግባራዊ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል።
በበጋ መስኖ ለገበያ ጭምር የሚቀርብ ስንዴ በማምረት ተጠቃሚ ሆነናል- አርሶ አደሮች
Nov 4, 2025 66
ጎንደር ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ) ፡- በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለገበያ ጭምር የሚቀርብ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ። በዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ዛሬ በወገራ ወረዳ ባልደርጌ ቀበሌ ተካሂዷል። ከቀበሌው ነዋሪዎች ውስጥ አርሶአደር ተሾመ ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከጀመሩ ሶስት ዓመት እንደሆናቸው ተናግረዋል። በዚህም ሲያገኙት የቆየው ምርት ከፍጆታቸው የተረፈውን ለገበያ በማቅረብ የልጆቻውን የትምህርት ወጪ በመሸፈን ጭምር ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል። ይህንን ለማስፋትም በዘንድሮው የበጋ ወቅት ግማሽ ሄክታር መሬታቸውን በበጋ መስኖ የስንዴ ሰብል ለማዋል የእርሻ ስራ መጀመራቸውን አንስተዋል። ሌላው የቀበሌው አርሶአደር ተስፉ ሙጨ፤ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየተሳተፉ እያገኙ ካሉት ትርፍ ምርት ሽያጭ የገቢ አቅማቸው እያደገ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት በስንዴ ልማቱ ባገኙት ተጨማሪ ገቢ አንድ በሬ መግዛት እንደቻሉ አውስተዋል። በዘንድሮ በጋም ግማሽ ሄክታር መሬታቸውን በሰንዴ ሰብል በመሸፈን 20 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። ። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የስራ ባሕላችንን በመቀየር የድሕነት መውጫ መንገድ ሆኖናል ያሉት ደግሞ ሌላው አርሶ አደር አስረስ መላኩ ናቸው። ከመኸር እርሻ በተጨማሪ በጋውን በመስኖ ስንዴ በማልማት ያገኙት ትርፍ ምርት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነታችን እንዲጨምር ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልናል ብለዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ንጉሴ ማለደ በበኩላቸው ፤ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 20ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ780 ሺህ ኩንታል በላይ ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። ምርታማነቱን ለማሳደግም ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ የስንዴ ዘር የማቅረብ ስራ መጀመሩን ጠቅሰው፤ ከ6ሺህ በላይ ነባርና አዲስ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አስረድተዋል። የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዙ ሌሎች የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች በስፋት ለመተግበር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ላይ አርሶ አደሮችን ጨምሮ የዞኑና የወረዳው አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊና ታሪካዊ ተቀባይነት ያለው ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው - አምባሳደር ጥሩነህ ዜና
Nov 4, 2025 86
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትን የማስመለስ ጥያቄ ሕጋዊና ታሪካዊ ተቀባይነት ያለው ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን አንጋፋው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ጥቅምት 18/2018 ዓ/ም ማካሄዱ ይታወቃል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ያለው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ አካል የነበረውን የባሕር ጠረፍ ለማጣት 30 ዓመት በላይ የወሰደውን ያህል የትግል ታሪክ አሁን ላይ ወደ ባሕር በር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመት እንደማይወስድባት አጽንኦት ሰጥተዋል። የቀይ ባሕር ባለቤትነትን ጥያቄ ለመፍታት የተረጋጋ፣ የሰከነና በውይይት ላይ የተመሰረተ አካሄድ መከተል ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለማጣት የፈጀውን ያህል ለመመለስ አይፈጅም ብለዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድም ሕጋዊና ተቋማዊ መሠረት የሌለው የሚያስቆጭ የብሔራዊ ጥቅም ስብራት አካል መሆኑን አስረድተዋል። አንጋፋው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ ሕጋዊና ታሪካዊ ቅቡልነት የሌለው ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም በፊት በነበረው ታሪኳ የባሕር በር ባለቤትነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር ብትሆንም በታሪካዊ ጠላቶች ሴራ ከቀይ ባሕር እንድትገለል መደረጉን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚጋልቧቸውና ህጋዊ መሰረት የሌላቸው አካላት ምንም አይነት የህዝብ ምክክር ሳያደርጉ የባሕር በርን ያህል ግዙፍ የብሔራዊ ጥቅም አንኳር ጉዳይ ማሳጣታቸውን አስታውሰዋል። በህዝብ የተመረጠ ሕጋዊ የመንግስት አስተዳደር ባልነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተገለለችበት መንገድ ጉልህ ዓለም አቀፍ የሕግ ጥሰት የተፈጸመበት የታሪክ ስብራት መሆኑንም አስገንዝበዋል። የአሁኑ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ህዝባዊ መሠረት ያለው የጋራ ተጠቃሚነት መርህን የተከተለ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። በዚህም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የማስመለስ አካሄድ በታሪካዊ ዳራ የተደገፈ ሕጋዊ መሠረትና ተቀባይነት ያለው መሆኑን አስረድተዋል። መንግስትም የኢትጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማስመለስ እየተከተለ የሚገኘው በሳል የዲፕሎማሲ አካሄድ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከጥንተ አክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የቀይ ባሕር ቀጣናን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ የባሕሩ ባለቤትና ተጋሪ ሀገር እንደነበረችም ነው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ያስታወሱት። በፖለቲካ ሴራ ከአካባቢው እንድትርቅ መደረጉ የቀይ ባህር ቀጣና የአሸባሪዎች መናኸሪያ በመሆን ለቀጣናው ሰላምና ደኅንነት መታወክ መንስኤ እየሆነ መጥቷል ብለዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ መሆኑና ብሔራዊ ጥቅምን ከማስጠበቅ ባለፈ የቀጣናውን ደኅንነት በማስጠበቅ ለዓለም አቀፍ የሚተርፍ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። ኢትጵያውያን፣ የቀጣናው ሀገራትና የዓለም ህዝብ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ምክንያታዊ ጥያቄ በጎ ምላሽ እንዲያገኝ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዎችን በማከናወን አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር እያስተዋወቀ ነው
Nov 4, 2025 145
ሮቤ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፡- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በማከናወን አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር እያስተዋወቀ መሆኑን ገለጸ። ዩኒቨርሲቲው ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ተመራማሪዎችን ያሳተፈ የምርምር ማዕከላት የመስክ ምልከታን ዛሬ አካሄዷል። በመስክ ምልከታው ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ተባባሪ ፕሮፌሰር በዛብህ ወንድሙ እንዳሉት ፤ ተቋሙ የአርሶ አደሩን ችግር ማዕከል ያደረጉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ነው። የስንዴ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልና በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በምርምር ለመለየት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በአርሶ አደሩ አቅራቢያ የምርምር ጣቢያዎችን በመክፈት አርሶ አደሩን ከተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ጋር የማስተዋወቅ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 200 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ ማሳ ላይ በኩታ ገጠም አስተራረስ ለተደራጁ አርሶ አደሮች ዝርያን በማላመድ፣ በአረም ቁጥጥርና በሌሎች ተዛማጅ ተግባራት ዙሪያ ሰፊ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በተጨማሪም ለአርሶ አደሩ የምርጥ ዘር አቅርቦትና ሌሎች የግብርና ድጋፎችን ከማድረግ በተጓዳኝ በእፅዋት በሽታ ቁጥጥርና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ተግባር ተኮር ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑንም አንስተዋል። አርሶ አደሩንና የዘርፉ ባለሙያዎችን ያገናኘው የመስክ ምልከታ የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል። ከምሥራቅ ባሌ ዞን የመጡት አርሶ አደር ዘውዴ ጉታ፤ በስንዴ ሰብል ልማት የመሳተፍ የረጅም ዓመት ልምድ ቢኖራቸውም በምርጥ ዘር አጠቃቀም ልምድ ማነስ ምክንያት በሄክታር ከ20 ኩንታል ያልበለጠ ስንዴ ሲያመርቱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ። ከሦስት ዓመታት ወዲህ ግን በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ያገኙትን የስንዴ ምርጥ ዘር መጠቀም በመጀመራቸው በአንድ ሄክታር እስከ 70 ኩንታል ስንዴ ማምረት መጀመራቸውን አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው በተወሰነ መሬት ላይ እያከናወነ ከሚገኘው የስንዴ፣ የባቄላ፣ የጤፍና የሌሎች የሰብል ዝርያዎች ብዜት ብዙ ልምድ መቅሰማቸውን የገለጹት ደግሞ ከምዕራብ አርሲ ዞን የመጡት ከማል አልይ ናቸው። የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ አርሶ አደር አሚኖ አማን በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በተለያየ ጊዜ ምርጥ ዘርና ሌሎች ድጋፎችን አድርጎልናል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በሚያደርግልን ድጋፍም ምርትና ምርታማነታችንን እያሻሻልን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል። በመስክ ምልከታው ላይ ከባሌ ዞን፣ ምሥራቅ ባሌና ምዕራብ አርሲ ዞን የተውጣጡ አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
‎ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ ነው
Nov 4, 2025 99
‎አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮ-ኮደርስ የዜጎችን ዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና እየተወጣ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ዜጎች የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምኅዳር እየፈጠረ የሚገኝ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ ልማት መርሃ ግብር አካል መሆኑ ይታዎሳል። በ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት የተጀመረው መርሃ ግብርም ዜጎች መሠረታዊ ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት የሚያዳብሩበትን የበይነ-መረብ (ኦንላይን) የስልጠና ምኅዳር ፈጥሯል። በተነሳሽነቱም በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ፣ በአንድሮይድና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልጠና መስኮች ዜጎች ያለምንም ክፍያ ባሉበት ቦታ በበይነ-መረብ የስልጠና እንዲከታተሉ እያደረገ ይገኛል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳው የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነትም ዜጎች በዲጂታል ዓለም ውስጥ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ስዩም መንገሻ፤ የዲጂታል መሠረተ ልማቶች የመንግስትን አገልግሎቶች በማሳለጥ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል። የ5-ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተቀዳ ቁልፍ የዜጎች ዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት ልማት መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮ-ኮደርስ ተነሳሽነት ስልጠናም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ትግበራ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ በመገንባት በቁልፍ መሳሪያነት እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠና ከጀመረበት አንስቶም በፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ፣ ዳታ ሳይንስና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊያን ላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ነው ብለዋል። በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ ከሚገኙ ዜጎች ውስጥም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው ሰርትፊኬት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል። የኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብሩም የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን እያሳደገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። መርሃ ግብሩም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል በማፍራት አገልግሎት አሰጣጦችን በማዘመን በር እንደከፈተም ገልጸዋል። በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት መጨረሻም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎችን 4 ሚሊየን ለማድረስ ከክልልና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ኢትዮጵያዊያንም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናን ባሉበት ቦታ በመመዝገብ የዲጂታል ዕውቀትና ክህሎት አቅማቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የዲጂታል መታወቂያ በተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ የሚያስችል የአገልግሎት ማዕከላትን የማስፋት ስራ እየተከናወነ ነው
Nov 2, 2025 280
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ):-የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን በተለያዩ አካባቢዎች ለማዳረስ የሚያስችል የአገልግሎት ማዕከላት ማስፋት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ገለጹ፡፡ እስካሁን ከ27 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ አስተባባሪ ደጀኔ ገብሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ለሁሉም ነዋሪዎች ዲጂታል መታወቂያን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። የምዝገባ አገልግሎቱን በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ለማዳረስ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የአገልግሎት ማዕከላት በማስፋት ምዝገባ እያካሄደ ነው። በተጨማሪም አገልግሎቱ ወደ ሩቅ አካባቢዎች እንዲደርስ በተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች (Mobile Registration Units) አማካኝነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከአምስት ሺህ በላይ የመመዝገቢያ ማሽኖች አገልግሎት ላይ ናቸው ያሉት አስተባባሪው፤ ከ27 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል ብለዋል። እስከ በጀት ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የመመዝገቢያ ማሽኖቹን ቁጥር ወደ 10 ሺህ በማሳደግ ተደራሽነትን ለማስፋት መታቀዱን ገልጸዋል። በአጠቃላይ በዓመቱ ውስጥ 60 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመዝገብ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማሳካት ጠንካራ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አስረድተዋል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማሳደግ፣ የገንዘብ ማጭበርበርን በመቀነስ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለንን የዲጂታል ክህሎትለማወቅ እየተጋን ነው
Nov 1, 2025 244
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018(ኢዜአ)፡-በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለንን የዲጂታል ክህሎት ለማወቅ እየተጋን ነው ሲሉ በመዲናዋ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ። የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብር የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ ፕሮጀክት ነው። ይህም የቴክኖሎጂ እውቀት በማበልጸግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ብቃት እንዳስጨበጣቸው መርኃ ግብሩን ተከታትለው የጨረሱ ሰልጣኞች በተደጋጋሚ ገልጸውታል።   መርኃ ግብሩ ዜጎች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዳታ ሳይንስ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግና በዌብ ፕሮግራሚንግ ወሳኝ እውቀትንና ክህሎትን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ሳምንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና መውሰድ መቻላቸውን አስታውቀዋል። መንግሥት ያመቻቸውን እድል በመጠቀም ስልጠናውን እየወሰዱ ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ተማሪዎች ተጠቃሽ ናቸው። ተማሪዎቹ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቂ የሆነ የዲጂታል እውቀትና ክህሎት የሚጠይቅ ነው ብለዋል። በኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አቤኔዘር ዘገዬወርቅ ስልጠናው ከመደበኛ ትምህርታችን ጎን ለጎን የዲጂታል አቅማችንን እንድናጎለብት አስችሎናል ብሏል። ከቀረቡት መርኃ ግብሮች መካከል በዌብ ፕሮግራሚንግ እና ዳታ ሳይንስ ስልጠና መውሰዱን ገልጿል። ያገኘው ስልጠና ጊዜው የሚጠይቀውን የዲጂታል እውቀት እንዲገበይ እንዳደረገው በመግለጽ ቀሪዎቹን የኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብሮች በቀጣይ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ጠቅሷል። በስልጠናው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተሻለ ክህሎት ማግኘቷን የገለጸችው ደግሞ የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ህይወት ተስፋሁን ናት። አርቴፌሻል ኢንተለጀንስ በተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራት ትፈልግ እንደነበረ በመጠቆም መርኃ ግብሩ ፍላጎቷን እውን እንድታደርግ እንዳስቻላት ገልጻለች። በኮከበ ጽባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሀናን ኢብራሂም በበኩሏ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ስልጠና መውሰዷ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በቀላሉ ለመረዳት እንዳስቻላት ጠቅሳለች። የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ኪሩቤል ሀብተስላሴ ዲጂታል ቴክኖለጂውን በሚገባ ለመረዳት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሶ ስልጠናው ክህሎቱን ለማጎልበት እንዳስቻለው ተናግሯል።   የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ቢሮው ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ተማሪዎች የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከ2017 ጀምሮ ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎች የኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን አስታውቀዋል። ቢሮው የዲጂታል እውቀትና ክህሎት የተላበሰ ትውልድ ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ስልጠናውን የተከታተሉ ተማሪዎች ወጣቶች ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን የኮደርስ ስልጠናን በመውሰድ ያላቸውን የዲጂታል ህሎት እንዲያጎለብቱ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፖርት
አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል
Nov 4, 2025 35
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2017 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በፎርቹና አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። አርሰናል በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን በርካታ የግብ እድሎችንም ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ውድድር ፎርማት ደረጃን በ12 ነጥብ መምራት ጀምሯል። መድፈኞቹ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም። ተቀይሮ የገባው የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን በ15 ዓመት 308 ቀናት በመጫወት በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ወጣት ተጫዋች ሆኗል። በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስላቪያ ፕራግ በሁለት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው መርሃ ግብር ናፖሊ እና ኢንትራክት ፍራንክፈርት ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል 
Nov 4, 2025 38
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በፎርቹና አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። አርሰናል በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን በርካታ የግብ እድሎችንም ፈጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ውድድር ፎርማት ደረጃን በ12 ነጥብ መምራት ጀምሯል። መድፈኞቹ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም። ተቀይሮ የገባው የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን በ15 ዓመት 308 ቀናት በመጫወት በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ወጣት ተጫዋች ሆኗል። በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስላቪያ ፕራግ በሁለት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው መርሃ ግብር ናፖሊ እና ኢንትራክት ፍራንክፈርት ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃን የልማት አጀንዳቸው የትኩረት ማዕከል ሊያደርጉ ይገባል- ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ 
Nov 4, 2025 100
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ጥበቃና እንክብካቤን እንደ ልማት አጀንዳ በመያዝ መስራት እንደሚገባቸው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው ላለፉት ሁለት ቀናት በባለሙያዎች ደረጃ ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ በሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል።   “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” በመሪ መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎችና ቀጣይ እርምጃዎች የሚመክር ነው። የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ከጸጋ ባሻገር የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፣ የምግብ ዋስትና እና የባህል ማንነት መሰረት መሆኑን አመልክተዋል። ብዝሃ ህይወት እና ተፈጥሯዊ ቅርሶች የዓለም ተፈጥሮ ሀብት ዘቦች ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል። ይሁንና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የእንስሳትና እጽዋት መኖሪያ ቦታ መውደም እና የተለያዩ ዝርያዎች መጥፋት የብዝሃ ህይወት ሀብቶች አደጋ ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አፍሪካውያን ብዝሃ ህይወትን የአህጉሪቱ የልማት አጀንዳ ምሰሶ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ሊያሳዩ ይገባል ነው ያሉት። በአጀንዳ 2063 የበለጸገች እና ሰላማዊ አፍሪካን የመፍጠር ህልም ሊሳካ የሚችለው በዜጎች ትጋትና በዘላቂ አካባቢ ጥበቃና አስተዳደር መሆኑንም አመልክተዋል። አህጉራዊ አጀንዳዎችን ለማሳካት የፖሊሲ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ እንዲሁም ወጣቶችና ሀገር በቀል ማህበረሰቦችን በብዝሃ ህይወት ጥበቃ የመሪነት ሚና እንዲወጡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት ንግግራቸውን ወደ ተጨባጭ ስራ እና ወደሚለካ ውጤት በመቀየርና የአካባቢ ስነ ምህዳርን በመጠበቅ መጻኢውን ጊዜ የተሻለ ለማድረግ እንዲሰሩ አስገንዝበዋል። አፍሪካን በዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ እና ዘላቂ አጠቃቀም መሪ እናድርጋት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ነገር እናስረክብ ሲሉም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል። በጉባኤው ላይ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የመጀመሪያው የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጉባኤ ነገ በመሪዎች ደረጃ በሚደረግ ስብሰባ ይጠናቀቃል። ጉባኤው ለአፍሪካ ብዝሃ ህይወት መመናመን፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ብክለት የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ስራዎች ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው
Nov 4, 2025 129
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ የምታከናውናቸው ተግባራት ከቀጣናው ባሻገር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምሳሌ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የስነ-ምህዳርና ባዮ-ዳይቨርሲቲ ዋና የቴክኒክ አማካሪ ዶለይ ጸሪንግ ገለጹ፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የስነ-ምህዳርና ባዮ-ዳይቨርሲቲ ዋና የቴክኒክ አማካሪ ዶለይ ጸሪንግ ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ስነ-ምህዳርና ብዝሃ ህይወት የታደለች ሀገር ናት ብለዋል፡፡ የብዝሃ ህይወት እና ስነ-ምህዳር ጥበቃ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ወሳኝ ሚና እንደሚያበረክት ጠቁመው፤ ተቋማቸው በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከበርካታ የዓለም ሀገራት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በብሔራዊ ፓርኮች ጥበቃን በማጠናከር እና አዳዲስ ስፍራዎችን በማልማት ለብዙ አይነት የዱር እንስሳትና ዕፅዋት ወሳኝ መኖሪያ እያለማች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በትላልቅ የደን ልማት እያከናወነች ያለው ተግባር ከአፍሪካ ቀንድ አልፎ በዓለም አቀፉ ደረጃ ግንባር ቀደም እንደሚያደርጋት ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ተግባር አስደናቂ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራዎች ቀጣዩን ትውልድ ጭምር ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡   በተለይ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና ከብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ጋር ለማስተሳሰር እየወሰደቻቸው ያሉ እርምጃዎች የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በስነ-ምህዳር እና ብዝኃ-ሕይወት ጥበቃ ረገድ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ከቀጣናው ባሻገር ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያ የምታከናውነውን የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን እንደሚያግዝም አረጋግጠዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በቀጣናው የሚገኙትን ሥነ-ምህዳሮችና የብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ ከመንግሥት፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡   በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ተመራማሪ (ዶ/ር) ፋኑዔል ከበደ በበኩላቸው፤ የዱር እንስሳት ለቱሪዝም መስህብነትና ለሌሎችም ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ የእነዚህን እንስሳት መኖሪያ የመጠበቅ ስራን በትኩረት እየሰራች መሆኑን ጠቁመው በዚህም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡ በዚህም በርካታ የዱር እንስሳት አሁን ላይ ወደ ነባር ቀዬያቸው እየተመለሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እየጨመረ ይሄዳል
Nov 3, 2025 180
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚሄድ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በመካከለኛው፣ምስራቅ እና የደቡባዊ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአየሩ ሁኔታ እንደሚቀያየር አስታውቋል። በደብረ ብርሃን፣አርሲ ሮቤ፣አዳባ፣ደሴ፣ባሌ ሮቤ፣አዲስ አበባ፣አደሌ፣አምባ ማሪያም፣ ኮምቦልቻ፣ አንኮበር በአብዛኛው ቀናቶች ላይ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል። የበጋ ወቅት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑት የደቡብ፣ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል። በሌላ በኩል አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በመካከለኛው፣የምስራቅ እና ደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደሚሄድ የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል። የመኽር ሰብል አብቃይ በሆኑት የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በወሩ ያለው እርጥበት ዘግይተው ለተዘሩት፣ የእድገት ጊዜያቸውን ላልጨረሱ ሰብሎች፣ለቋሚ ተክሎችና ፍራፍሬዎች የውሃ ፍላጎት ለማሟላት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጿል። ያለው እርጥበት ለእንስሳት መኖም አዎንታዊ አበርክቶ እንዳለው ጠቁሟል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበጋ እርጥበት ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው የሚጠበቅ ሲሆን የተቀሩት ተፋሰሶች ዝቅተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል ብሏል። አብዛኛው የባሮ አኮቦ፣ኦሞ ጊቤ፣ገናሌ ዳዋ፣ኦጋዴን፣ በመካከለኛው እና በታችኛው ስምጥ ሸለቆ፣ዋቤ ሸበሌ የተሻለ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ጠቁሟል። አብዛኛው አፋር ደናክል፣አዋሽ፣ተከዜ፣መረብ ጋሽ እንዲሁም አይሻ ተፋሰሶች ላይ ደረቅ የአየር ሁኔታ ጠባይ ተጽዕኖ ስር እንደሚወድቁ የአየር ትንበያ ያሳያል ብሏል።
 የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ቃል ኪዳን እና የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጉዞ 
Oct 31, 2025 319
ብዝኃ ህይወት ሁሉንም ሥነ-ሕይወታዊ ኃብቶች፣ እፅዋት፣ እንስሳትና ደቂቅ አካላት እንዲሁም በውስጣቸው የያዟቸው ዘረ-መሎችና እነዚህ የሚፈጥሯቸውን ውህዶች የሚያካትት ነው። የሁሉም ስርዓተ ምህዳር እና የሰው ልጆች የመኖር መሰረት ነው ብዝሃ ህይወት። እንደ አንዳንድ ጥናቶች ከሆነ በዓለማችን ካሉ ህይወት ካላቸው 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዝርያዎች መካከል 80 በመቶዎቹ ገና ያልተገኙ ናቸው። የዓለም ብዝሃ ህይወት ቁልፍ ጠቀሜታዎች አሉት። የምግብ ምርታማነት፣ ንጹህ ውሃ እና አየር፣ ለርክበብናኝ (ፖሊኔሽን) እና አየር ንብረትን መቆጣጠርን ጨምሮ በርካታ ጠቃሜታዎች እንዳሉት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ብዝሃ ህይወት ከ44 ትሪዮን ዶላር በላይ ወይም የዓለምን ዓመታዊ 50 በመቶ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) ይሸፍናል። የዓለም የብዝሃ ህይወት እና የስነ ምህዳር አገልግሎቶች የበይነ መንግስታት የሳይንስ ፖሊሲ መድረክ ((IPBES) በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በሰው የተለያዩ ተግባራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመሬት አጠቃቀም ምክንያት አንድ ሚሊዮን ገደማ ህይወት ያላቸው ዝርያዎች ሊጠፉ እንደሚችሉ ስጋቱን አስቀምጧል። በዚህ የዓለም ቀውስ ውስጥ አፍሪካ የብዝሃ ህይወት እምቅ ሀብቶች ያላት አህጉር ሆና ተገኝታለች። የብዝሃ ህይወቱ በርካታ እና ጫና መቋቋም የሚችሉ የአይበገሬነት አቅም ያላቸው ናቸው። የዓለም አንድ አምስተኛ እጽዋት፣ አጥቢ እንስሳት እና አዕዋፋት የሚገኙት በአፍሪካ ነው። ከ50 ሺህ በላይ የእጽዋት ዝርያዎች፣ 1 ሺህ 100 አጥቢ እንስሳት፣ 2 ሺህ 500 የአዕዋፋት እና ከ3000 በላይ የአሳ ዝርያዎች ይገኛሉ። የዓለማችን ሁለተኛው ጥብቅ ደን የኮንጎ ጥቅጥቅ ደን፣ የቦትስዋና ኦካንጋቮ ዴልታ፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ስፍራዎች እና የማዳጋስካር ልዩ ስነ ምህዳሮችና ዝርያዎች ከአፍሪካ ዋነኛ ብዝሃ ህይወቶች መካከል ይጠቀሳሉ። የአፍሪካ ብዝሃ የኔዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ ከማሻሻል ባለፈ የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት በዘላቂነት ማስቀጠል የሚችል አቅም ያለው ነው። ይሁንና የአፍሪካ ብዝሃ ህይወቶች ለተለያዩ ፈተናዎች የተጋለጡ ናቸው። አህጉሪቷ በየዓመቱ 3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር ገደማ ደን እንደምታጣ መረጃዎች ያሳያሉ። እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ህዝብ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ህዝብ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ህገ ወጥ አደን ፣ ዘላቂነት የጎደለው የመሬት አጠቃቀም እና ብክለት የአህጉሪቷን ብዝሃ ህይወት ስርዓት እየጎዱ ይገኛሉ። የአፍሪካ ጥብቅ ስፍራዎች ለማስተዳደር በዓመት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያስፈልግ ቢሆንም አንዳንድ ሀገራት በቂ ኢንቨስመንት እየመደቡ አይገኝም። አፍሪካ የሶስትዮሽ ተፈጥሯዊ ቀውሶችን እያስተናጋደች ትገኛለች ማለት ይችላል። የብዝሃ ህይወት መመናመን፣ ብክለት እና የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ናቸው። የአስተዳደር ስርዓት አለመጠናከር፣ የተገደበ የፋይናንስ አቅርቦት እና የአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎች በውሳኔ መስጠት ውስጥ አለመሳተፋቸው በዋናነት የሚጠቀሱ ፈተናዎች እንደሆኑም ይነገራል። የአፍሪካ ሀገራት የብዝሃ ህይወት ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛል። ከነዚህም አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያም ከፍተኛ የብዝኃ ሕይወት ኃብት ካላቸው አገራት መካከል አንዷ ናት። አሁን ላይ አገሪቱ ከ6 ሺህ በላይ የእፅዋት ኃብቶች ያላት ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 600 ወይም 10 በመቶ የሚሆኑት በአገሪቱ ብቻ የሚገኙ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢንስቲትዩት መረጃ ያመለክታል።   ጎን ለጎንም የወፍ ዝርያዎችን ጨምሮ በየብስና በውኃ አካላት ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ ዓይነት ዝርያ ያላቸው በርካታ እንስሳት በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ይሁንና የየብስና የውኃማ አካላት አካባቢ መለወጥ ለእነዚህ ብዝኃ ሕይወት ኃብቶች ሥጋት እየሆነ መምጣቱን ነው ኢንስቲትዩቱ የገለጸው። በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብክለትና ዘለቄታዊ ያልሆነ የተፈጥሮ ኃብት አጠቃቀም ለብዝኃ ሕይወት ኃብቶች መመናመን ምክንያቶች ናቸው። የሕዝብ ቁጥር መጨመርን ተከትሎ ደን ወደ እርሻ መሬትነት መቀየር እንዲሁም መጤ ወራሪ አረሞች ነባር አገር በቀል ዝርያዎች የሚበቅሉበትን ሥፍራ መያዝም ሌላኛው ምክንያት ነው። ይህንንም ተከትሎ ወይራ፣ ዝግባ፣ ቀረሮ፣ ዋንዛ፣ ጥቁር እንጨትና ኮሶ እየተመናመኑ ካሉ የእፅዋት ብዝኃ ሕይወት ዝርያዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ዝርያዎቹ አንዴ ከጠፉ መልሰው የማይገኙ በመሆናቸው ኢንስቲትዩቱ ዝርያዎቹን የማራባትና የማብዛት ሥራ በልዩ ትኩረት እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል። ከእነዚህም በተጨማሪ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውና በኢትዮጵያ ብቻ ያሉ የእፅዋትና እንስሳት ብዝኃ ሕይወት ዝርያዎችን የመጠበቅ ሥራ እየተከናወነ ነው። በዚህም የቀረሮ የእጽዋት ዝርያ የማብዛት ሥራ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የተመናመኑ የዳልጋ ከብቶች ወደ ነበሩበት የመመለስ ሥራም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። በተመሳሳይ "የሸኮ ዳልጋ ከብት" እየተባለ የሚጠራውን ዝርያ የማብዛት እንዲሁም በጣና ኃይቅ የዓሳ ዝርያዎች ላይ ያለውን መመናመን ለመቀልበስም የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ነው ኢኒስቲትዩቱ ያስታወቀው። ጥብቅ አካባቢዎችን የማስፋት፣ የእፅዋት አፀድ ጥበቃ፣ የዘረመልና የማኅበረሰብ የዘር ባንኮችን በየአካባቢው የማስፋት ተግባርም እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብርም የብዝኃ ሕይወትን ከመጠበቅና ከማስቀጠል አኳያ ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ያሏትን የብዝኃ ሕይወት ሃብቶች የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩትም ኃብቶቹን የማንበር (የመጠበቅ)፣ ዘለቄታዊ አጠቃቀምና ፍትሃዊ የጥቅም ተጋሪነት ላይ እየሰራ ይገኛል። በአፍሪካ ብዝሃ ህይወት ሀብቶች፣ እድሎች፣ ፈተናዎች እና ቀጣይ እርምጃዎች የሚመክር ጉባኤ በቦትስዋና ጋቦሮኒ ከጥቅምት 23 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። “የብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት በመጠቀም የአፍሪካን ብልጽግና ማረጋገጥ” የጉባኤው መሪ ቃል ነው። ጉባኤው ለአፍሪካ ብዝሃ ህይወት መመናመን፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ብክለት የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ መስጠት የሚያስችል መድረክ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የዓለም የብዝሃ ህይወት ጥበቃ መሪዎች እና ተመራማሪዎች፣ ሀገር በቀል የማህበረሰብ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። የአፍሪካ ቀዳሚ የብዝሃ ህይወት አጀንዳዎች ምክክር ይደረግባቸዋል። አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ትስስርን ማጠናከር እና ለብዝሃ ህይወት ክብካቤ የፋይናንስ ሀብትን በተቀናጀ ሁኔታ ማሰባሰብ ሌሎች የጉባኤው አጀንዳዎች ናቸው። ኢትዮጵያ እና የጉባኤው አዘጋጅ ቦትስዋን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በብዝሃ ህይወት ጥበቃ እያከናወኗቸው ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ልምዳቸውን ያጋራሉ። እ.አ.አ በ2026 በአርሜኒያ በሚካሄደው 17ኛው የዓለም የብዝሃ ህይወት ጉባኤ (ኮፕ 17) ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካን ድምጽ በጋራ ማሰማት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ይደረጋል። ጉባኤው አንድ ብዝሃ ህይወት የልማት አቅም ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ብልጽግና አረጋጋጭ ሞተር መሆኑ ግልጽ መልዕክት የሚተላለፍበት መድረክ ነው። ፍላጎቶች ተጨባጭ እና መሬት ወደወረዱ መፍትሄዎች ማውረጃ አማራጭ ሆኖም ያገለግላል። በአርሜኒያ ለሚገሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ አፍሪካ ፍትሃዊ የፋይናንስ አቅርቦት እንድታገኝ፣ ሁሉን አቀፍ የብዝሃ ህይወት አስተዳደር እንዲረጋገጥ እና ለፍትሃዊ የጥቅም ተጋሪነት ድምጿን ለማሰማት ስንቅ ለሚሆን የሚያስችል አህጉራዊ መድረክ ጭምር ነው ማለት ይቻላል። በአፍሪካ ያለውን የብዝሃ ህይወት አቅም በውጤታማ የአስተዳደር ስርዓት፣ አካታች የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት ወደ ዘላቂ እድገት ምንጭነት ማሸጋገር እንደሚቻል ጥርጥር የለውም። የአፍሪካ የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራ ለዓለም የብዝሃ ህይወት ግቦች መሳካት ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል። በብዝሃ ህይወት ላይ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ ለአፍሪካ መጻኢ ጊዜ መሰረት እንደመጣል ይቆጠራል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በሄይቲ እና ጃማይካ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው ጎርፍ ሳቢያ የበርካቶች ሕይዎት አለፈ
Oct 31, 2025 273
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ)፡-በሄይቲ እና ጃማይካ የተከሰተው ‘ሃሪኬን ሜሊሳ’ የተሰኘው ወጀብና ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ እስካሁን የ49 ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል። በሄይቲ የ30 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን እና ከ20 በላይ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። እስካሁን ያሉበት ሁኔታ ያልታወቁ ሰዎችን የመፈለጉ ሥራም መቀጠሉን ባለሥልጣናቱ ለአልጄዚራ ገልጸዋል።   ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመላክተዋል። እንዲሁም የአውሎ ነፋሱ ሰለባ በሆነችው ሌላኛው ሀገር ጃማይካ የ19 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል። እስካሁን ከተመዘገቡት በጣም ኃይለኛ የአትላንቲክ አውሎ ነፋሶች አንዱ እንደሆነ የተነገረለት ሃሪኬን ሜሊሳ በሠዓት 295 ኪሎ ሜትር እንደሚከንፍ ተገልጿል። አውሎ ነፋሱ የጃማይካን ምዕራባዊ ክልል በመምታት አስከፊ ጉዳት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።   ሃሪኬን ሜሊሳ በካሪቢያን ቀጣና ኩባ፣ሄይቲ እና ጃማይካ በሰው ሕይወት እንዲሁም በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። ይህን ተከትሎም በካሪቢያን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ውጭ መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል። የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን ለመመለስና አካባቢዎቹንም የማጽዳት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
የአፍሪካ ህብረት የ30 ቢሊዮን ዶላር የአቪዬሽን መሰረተ ልማት የኢንቨስትመንት እቅድ ይፋ አደረገ
Oct 31, 2025 226
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ማዘመንን አላማ ያደረገ የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርጓል። ከጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ የነበረው ሶስተኛው የአፍሪካ መሰረተ ልማት ፋይናንስ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአንጎላ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ጆአኦ ሎሬንቾ፣ የህብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የአየር መንገዶች ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ከጉባኤው ጎን ለጎን በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ አማካኝነት የአህጉሪቷን አቪዬሽን መሰረተ ልማት በፋይናንስ በመደገፍ እና በማዘመን የተቀናጀ የአየር አገልግሎት እና ነጻ እንቅስቃሴን መፍጠር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተከናውኗል። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ በመድረኩ ላይ በአየር ትራንስፖርት ገበያው አማካኝነት የአህጉሪቷን የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ለማዘመን የሚውል የ30 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት እቅድ ዛሬ ይፋ አድርገዋል። እቅዱ አፍሪካ በቀጣይ 10 ዓመት የአቪዬሽን ዘርፉን ለማሻሻል የሚያስፈልጋትን ከ25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በአፍሪካ እ.አ.አ በ2024 160 ሚሊዮን የነበረው የመንገደኞች መጠን እ.አ.አ በ2050 ወደ 500 ሚሊዮን ገደማ እንደሚደርስ የገለጸው ህብረቱ ኢንቨስትመንቱ የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና አቅምን ለማጎልበት እንደሚያስችል አመልክቷል። በኢንቨስትመንት እቅዱ አማካኝነት ገንዘቡ ለአውሮፕላን ማረፊያ፣ አውሮፕላን ጣቢያ እና ጥገና ማዕከላት መሰረተ ልማት፣ የአቪዬሽን ስርዓቶች ማዘመን፣ ለሰው ኃይል ልማት፣ ለቁጥጥር ስራ፣ ለቴክኖሎጂ እና ተጓዳኝ ስራዎች እንደሚውል ተገልጿል። የአፍሪካ ህብረት 10 ቢሊዮን ዶላሩን ከአፍሪካ መንግስታት፣ ከቀጣናዊ የልማት ባንኮች እና ከባለቡዙ ወገን አጋሮች ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቋል። ቀሪው 20 ቢሊዮን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አጋሮች፣ የሉዓላዊ ሀብት ፈንዶች (sovereign wealth funds) እና የጡረታ ፈንዶችን ጨምሮ ከግል እና የተቋማት ኢንቨስተሮች ለማግኘት መታሰቡን ነው ያመለከተው። የሀብት ማሰባሰቡ የሚከናወነው በአፍሪካ ነጻ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ማዕቀፍ ሲሆን የ30 ቢሊዮን ዶላሩ ከእ.አ.አ 2025 እስከ 2035 ለሚተገበሩ ስራዎች የሚውል ነው። የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት እና ኢነርጂ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦጅ አቪዬሽን የትራንስፖርት አማራጭ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ትስስር ስትራቴጂካዊ ሞተር እንዲሁም የአጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ቁልፍ አቅም ነው ብለዋል። በኢንቨስትመንት እቅዱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ልማት መመዘኛዎችን ባሟላ እና ከካርቦን ልህቀት ነጻ በሆነ መልኩ እንደሚገነቡ አመልክተዋል። ህብረቱ ዘመናዊ፣ ውጤታማ እና ዘላቂ የአቪዬሽን ኔትወርክ በመፍጠር ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር፣ የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት ስር እንዲሰድ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንዲያድግ በቁርጠኝነት ይሰራል ነው ያሉት።
ለአህጉሪቷ ለዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው  
Oct 24, 2025 498
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-ለአህጉሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡   በስብሰባው ላይ የአባል አገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በዓሳ ሀብት፣ በገጠር ልማት፣ በውሃ፣ በአካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው የሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም የማላቦ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2014 እስከ 2025) መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው የካምፓላ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2035) ጸድቋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አባል ሀገራት የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም የግብርና ግብዓቶችንና ምርጥ ዘርን መጠበቀ እንዲሁም ብዝሃ ህይወትን ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውሃ ኃብትን ከማሳደግ አኳያም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ - ኒፓድ የግብርና፣ የምግብ ዋስትና እና የአካባቢ ዘላቂነት ዳይሬክተር ኤስቴሪን ፎታቦንግ የካምፓላ አጀንዳ (2026–2035) በአፍሪካ የግብርና-ምግብ ሥርዓቶች ላይ የለውጥ ምዕራፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ገልጸዋል፡፡   ከአጀንዳው ግቦች መካከልም ዘላቂ የምግብ ምርትን፣ አግሮ-ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እና ንግድን ማጠናከር፣ ለግብርና-ምግብ ሥርዓት ለውጥ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስን ማሳደግ ብሎም የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ የካምፓላ አጀንዳ ስትራቴጂ እንዲሳከ ምቹ ሁኔታዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡ የዩጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የአምስተኛው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ ፍሬድ ብዊኖ ክያኩላጋ የካምፓላ አጀንዳ የእንስሳት ሃብትን ማሳደግ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡   በዚህም ለእንስሳትና ለዓሳ እርባታ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የእንስሳት መኖ ማሳደግ፣ ለእንስሳት ጤና እንዲሁም የዘረመል መሻሻልም ከትኩረት መስኮች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ የካምፓላ አጀንዳ የአፍሪካ ግብርና ልማት መርሃ ግብር ታላላቅ ግቦች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ
Oct 24, 2025 389
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፦11ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጥቅምት 14 እስከ 16/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው 11ኛው ጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት፣የዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የጣና ፎረም "አፍሪካ በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች በአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ለሶስት ቀናት የሚመክር ይሆናል። የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ተሳታፊ ሙያተኞች በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮችና በአፍሪካዊ መፍትሔዎች ልምድና ዕውቀታቸውን የሚያካፍሉበት ዝግጅትም ተጠባቂ የፎረሙ የመርሃ ግብር አካል ነው። በፎረሙ ላይ በመሪዎችና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ልዩ መልዕክተኞች ምክክር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ሐተታዎች
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት
Nov 3, 2025 219
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት አጋርነት ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ያላቸው ታሪካዊ ወዳጅነት በርካታ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት በአራተኛው ክፍለ ዘመን እንደጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአክሱም ንጉስ ኢዛና ወቅት ኢትዮጵያ ከምስራቅ ሮም መንግስት ጋር ዲፕሎማሲያዊ እና ሃይማኖታዊ ግንኙነት እንደነበራት ይነገራል። 15ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው በሰነድ የተደገፈ የኢትዮጵያ እና አውሮፓ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ግንኙነቶች የተደረጉበት ወቅት ነው። እ.አ.አ በ1441 የኢትዮጵያ ልዑክ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤት (The Council of Florence) ስብስባ ላይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት እና አውሮፓ መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ግንኙነት እንደሆነ ታሪክ ያወሳል። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑካን ወደ ሮም፣ ቬኒስ እና ሊዝበን ጉብኝቶችን አድርገዋል። ከዛ በኋላ ባሉ ክፍለ ዘመናት በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ሀገራት መካከል በርካታ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ እንቅስቃሴዎች እና የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። እ.አ.አ 1975 ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ማህበረሰብ ጋር ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመረችበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት (በቀድሞ አጠራሩ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ) እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 28 1975 በቶጎ ሎሜ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱ የሎሜ ድንጋጌ እየተባለ ይጠራል። ስምምነቱ ለኢትዮጵያ እና ለአውሮፓ ህብረት ትብብር መሰረት የጣለ ታሪካዊ ሁነት ነው። የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ ትብብር፣ የልማት ድጋፍ እና የወጪ ንግድ የስምምነቱ አበይት ማዕቀፎች ናቸው። የሎሜ ስምምነት አራት ጊዜ ማሻሻያ ተደርጎበታል። ማሻሻያዎቹ ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በፖለቲካ፣ ዴሞክራሲ፣ ኢንዱስትሪ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ቀጣናዊ ትስስርን ጨምሮ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ ማስፋትን ያለሙ ናቸው። እ.አ.አ በ2000 የሎሜ ስምምነት ወደ ኮቶኑ ስምምነት ተሸጋገረ። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በቤኒን ኮቶኑ አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ተፈራረሙ። የኮቶኑ ስምምነት የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ያስቀጠለ ነው። የፖለቲካ ምክክሮች፣ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶች አካቷል። ስምምነቱ ሁለት ጊዜ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ሲሆን እ.አ.አ በ2020 ማዕቀፉ እስከ እ.አ.አ 2024 እንዲቀጥል ተወስኗል። እ.አ.አ በ2023 በሶሞአ በተደረገ ውይይት የድህረ ኮቱኑ ስምምነት የተባለለት ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት እና አውሮፓ ህብረት መካከል ተፈርሟል።ኢትዮጵያ የዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ናት። እ.አ.አ በ2016 የተፈረመው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ስትራቴጂካ ትስስር ማዕቀፍ ስምምነት የበለጠ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ያጸና ነው። የአውሮፓ ህብረት ያቋቋመው የአውሮፓ ቡድን በኢትዮጵያ (Team Europe in Ethiopia) ህብረቱን፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና 21 የህብረቱ አባል ሀገራትን አቅፎ የያዘ ነው። ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት መካከል 21ዱ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ውክልና አላቸው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ሰላም እና ፀጥታ፣ የምግብ ስርዓት፣ ዘላቂ ኢነርጂ ልማት፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የግሉ ዘርፍ ልማት እና ትራንስፖርት ጨምሮ በሌሎች መስኮች ትብብር አላቸው። የአውሮፓ ህብረት በኮቶኑ ስምምነት የነበረውን የአውሮፓ የልማት ፈንድ ድጋፍ በመተካት ከእ.አ.አ 2021 እስከ 2027 የሚቆይ የፋይናንስ ማዕቀፍ እየተገበረ ይገኛል። 629 ሚሊዮን ዩሮ ፈሰስ የሚደረግበት ይህ ማዕቀፍ ከአውሮፓ ህብረት ተቋማት እና አባል ሀገራት አስተዋጽኦ የሚገኝ ሲሆን በየዓመቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለሚከናወኑ ስራዎች የሚውል ነው። ታዳሽ ኢነርጂ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ዘላቂ የስርዓተ ምግብ ግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ የሰው ሀብት ልማት፣ የፍልሰት አስተዳደር እና ሰላም ግንባታ ድጋፍ የሚደረግባቸአው መስኮች ናቸው። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ትብብር ውስጥ የሚጠቀሱ አንኳር ጉዳዮች አሉ። ከቅርቡ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ወደ ቤልጂየም ብራሰልስ በማምራት ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከርና ለማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ከውይይቱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። "ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ" በአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን የሚመራ የአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ ኢኒሼቲቭ ሲሆን ህብረቱ ከተለያዩ ሀገራት በዲጂታላይዜሽን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በስርዓተ ምግብ፣ በጤና፣ በዘላቂ ግብርና፣ በሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በቁልፍ ዘርፎች ያለውን ትብብር እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው። ስምምነቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ ገልጸዋል። በተጨማሪም ስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች እ.አ.አ በ2016 ለተፈራረሙት የስትራቴጂክ ትስስር የጋራ ድንጋጌ አዲስ አቅም እንደሚፈጥርም ተመላክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሳምንት ለ2025 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ ግብር የ90 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት በአዲስ አበባ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው። በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብስባ ላይ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ ከስበሰባው ጎን ለጎን ከአውሮፓ የኢንቨስትመንት ባንክ ከዓለም አቀፍ አጋርነት ዳይሬክተር ቱራያ ትሪኪ ጋር መክረው ነበር። በወቅቱ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP III) ሶስተኛ ምዕራፍ ማስፈጸሚያ የሚውል የ110 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ የሚታወስ ነው። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር ተፈራርመውታል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የ240 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት በመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል። ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን ልማት በተለያዩ ወሳኝ ዘርፎች ለማጠናከር የሚውል ነው። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም የጋራ ምክክር በአዲስ አበባ ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ የጋራ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሁለቱ ወገኖች በህዳር ወር 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተመሳሳይ የጋራ የምክክር መድረክ ማድረጋቸው አይዘነጋም። በ2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት በጤና ዘርፍ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ ያተኮረ የ20 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ዲፕሎማሲያዊ ትስስሩ ሁለቱ ወገኖች በሰኔ ወር 2008 ዓ.ም ከተፈራረሙት የስትራቴጂክ የጋራ ድንጋጌ በኋላ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። ዛሬ በፈረንሳይ ፓሪስ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረሙ የሁለቱን አካላት ግንኙነት ለማጠናከር እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የአፍሪካ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጌዛ ስትራመር፣ የፈረንሳይ የወጪ ንግድ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር መልዕክተኛ ኒኮላስ ፎርሲየር፣ የሜዴፍ ኢንተርናሽናል ምክትል ፕሬዝዳንት ፋብሪስ ላሳች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች እና የንግድ መሪዎች ተገኝተዋል። ፎረሙ በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከርና አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በዝርዝር አስረድተዋል። ሪፎርሙ የግል ኢንቨስመንት መሳብ እና ኢትዮጵያ ከዓለም ኢኮኖሚ ጋር ያላትን ትስስር የበለጠ ማጠናከርን ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ትብብር እያደገ መምጣቱን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ኢንቨስትመንት ፎረም በኢትዮጵያ ተቋማትና በአውሮፓ ኩባንያዎች መካከል በኢኖቬሽን፣ በእሴት መጨመርና የጋራ ብልጽግናን መደገፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጎልበት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም ገልጿል። ፎረሙ የፈረንሳይ ድርጅቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚሰራ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በሚደግፈው ሜዴፍ ኢንተርናሽናል እና በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በአራት የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በአቪዬሽን፤ በታዳሽ ኃይል፤ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት እና በዲጂታል ቴሌኮሙኒኬሽን ላይ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ- የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረምም ይህንን እያደገ ያለ ትብብር ያሳያልም ተብሏል። የኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት ከግማሽ ክፍለ ዘመናት በላይ ጸንቶ የቆየ ወዳጅነት ነው። የሁለቱ ወገኖች ትብብር በአውሮፓ እና አፍሪካ ሀገራት ላለው ግንኙነት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
የብዙዎች ቤት…
Oct 27, 2025 424
እስካሁን በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት ከ81 በላይ የአጥቢ እንስሣት፣ ከ450 በላይ የአዕዋፍ እና ከ400 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች መኖሪያ ነው። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የአዕዋፍ ዝርያዎች በዚህ ሥፍራ ብቻ ይገኛሉ፤ ከአምስቱ መካከል በተለይም የአንዷ ዝርያ ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተመራማሪዎችንና ጎብኚዎች ቀልብ መሳቡ ይጠቀሳል። ከአካባቢው ተፈጥሯዊ አቀማመጥና የአየር ሁኔታ ጋር መጣጣም የቻሉ የቆላ እፅዋት (ዛፎች) በምቾት በስፋት እንደሚገኙበትም ይገለጻል። የተመሠረተው በ1958 ዓ.ም ሲሆን፤ ስፉቱም 591 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፤ በቁጥርም ሆነ በሥብጥር የብዙዎች መኖሪያ የሆነው ይህ ሥፍራ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ይሰኛል። መንግሥት በሰጠው ትኩረት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ እንስሣቱም ሆኑ እፅዋቱ እየኖሩ ነው፤ ከሕገ ወጥ ድርጊትም እንዲጠበቁ ማድረግ መቻሉን የፓርኩ ኃላፊ አደም መሐመድ ለኢዜአ አረጋግጠዋል። በፓርኩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም ለ247 ወገኖች ቋሚ እና ለ2 ሺህ 535 ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ዓመትም በ1 ሺህ 751 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች እንደተጎበኘ ኃላፊው ገልጸዋል።
የክህሎቶች ልማት፤ የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
Oct 15, 2025 811
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ። ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል።   ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው።   የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። አህጉራዊ የንግድ ማዕቀፉ በሙሉ አቅሙ ሲተገበር የአፍሪካ ሀገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ መጠን 50 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያፋጥንና አህጉሪቷ ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ ልካ መልሳ ያለቀላቸውን ምርቶች በከፍተኛ ወጪ ከመግዛት ተላቃ ጥሬ ምርቶቿን በከፍተኛ ጥራት ወደ ማምረት ያሸጋግራታል። ይህ ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር እድል አፍሪካውያን በጋራ እንዲለሙ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያሳድጉ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ እና የማይበገር ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እነዚህ ሁላ ተስፋ ሰጪ አቅሞች የሚቃረን አንድ የማይካድ ሐቅ አፍሪካ ውስጥ አለ ይህ እውነት የአፍሪካን የእድገት አቅም በሚፈለገው መልኩ የሚመግብ የክህሎቶች እና የስራ ክፍተት ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ከ10 እስከ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ። ይሁንና በአህጉሪቷ በዓመቱ የሚፈጠረው መደበኛ ስራ 3 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።   እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ ከአፍሪካ ወጣቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ገደማው ስራ አጥ (Unemployment) ወይም ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) ውስጥ ነው። ይህ ስራ አለማግኘት ያለው በአፍሪካ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ክህሎት ያለው ሰው አጠረን እያሉበት ባሉበት ወቅት መሆኑ ትልቅ ጥያቄን ያስነሳል። በትምህርት ስርዓቱ እና በገበያው ፍላጎት መካከል እንዴት እንደዚህ አይነት አለመጣጣም ሊመጣ ቻለ? የሚል። በትምህርት እና በኢንዱስትሪው መካከል ባለው ያለመተሳሰር ችግር ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምርታማነት (productivity) ታጣላች። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ፈተናው የአቅም ሳይሆን ትምህርት እና ስራን፣ ፖሊሲ እና ተግባርን እና ስልጠናን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተሳሰር መስመር አለመዘርጋቱ ነው። በአፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት እየሰሩ ያሉት ከኢንዱስትሪው ርቀው ነው ማለት ይቻላል ይህም ተመራቂዎች የስራ ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት እና አቅም እንዳይታጠቁ አድርጓል። ሌላኛው ፈተና በአፍሪካ የተንሰራፋው ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ነው። አንዳንድ ጥናቶች የአፍሪካን ኢ-መደበኛ የኢኮኖሚ ድርሻ እስከ 85 በመቶ ያደርሱታል። ይህም ዜጎች ክህሎታቸውን እንዳያሳድጉ እና የብቃት ማረጋገጫን እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል። የአፍሪካን ክህሎት ምህዳር በመቀየር የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር አበይት ትኩረቱ ያደረገ ሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።   “አፍሪካውያንን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያፋጥኑበትን ክህሎቶች ማስታጠቅ” የሳምንቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሁነቱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው። በሁነቱ መክፈቻ ላይ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የልማት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራን፣ ኢኖቬተሮች፣ የወጣት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ተሳትፈውበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክህሎቶች ለሀገራዊ ግቦችና ለአህጉራዊ የ2063 የልማት አጀንዳዎች መሳካት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ናቸው።   ኢትዮጵያ ለክህሎት ልማት በሰጠችው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው ብለዋል። ክህሎት መር የፖሊሲ እርምጃችን ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የስራ ፈጣሪነት ባህልን በንቃት እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እና እድገት እንዲያመጡ የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እያመቻቸ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው የህዝባችንን አቅም ወደ ውጤታማ፣ አሳታፊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ የሥራ ኃይል መለወጥ አለብን ብለዋል።   ክህሎት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የክህሎት ልማት ለአሳታፊ ዕድገትና ለተገቢ የሥራ ዕድሎች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። አባል ሀገራት ሀገራዊ ለውጦችን ከአህጉራዊ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተሻለ፣ ፈጣን እና ይበልጥ አሳታፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የለውጥ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። የፖሊሲ ወጥነትን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ክህሎት ክፍተትን መሙላት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለክህሎት ልማት መጠቀም እና በአጀንዳ 2063 አማካኝነት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ላይ ውይይት ይደረጋል። በሳምንቱ የሚኒስትሮች እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች፣ የክህሎት አውደ ርዕዮች እና የገበያ ትስስር ሁነቶች እንዲሁም የወጣቶች እና የስራ ፈጣሪዎች ፎረም እንደሚካሄድ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፎረሙ የአፍሪካ ኢኖቬተሮች የስራ ውጤቶች ይቀርቡበታል። የክህሎቶች ሳምንት ተሳታፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና በኢኖሼሽን ማዕከላት ውስጥ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ይጎበኛሉ። ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ ክህሎት ልማት አስመልክቶ የጋራ አቋም መገለጫ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።   የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ለአህጉሪቷ የኢንዱስትሪ እና ክህሎት አጀንዳ ተጨባጭ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል። የመጀመሪያው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት እ.አ.አ ኦክቶበር 2024 በጋና አክራ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ክህሎቶች ፈተናዎች ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ምህዳሩን ለመቀየር አህጉሪቷ በዘርፉ አብዮት ያስፈልጋታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን የስነ ህዝብ ትሩፋት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ክህሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል መቀየር ይገባል። ይህን ለማድረግ የተቀናጀ እና አህጉር አቀፍ ጥረት ያስፈልጋል። የሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ስኬት የሚለካው በንግግሮች እና በጋራ መግለጫዎች ሳይሆን ራዕዮቹን በአፍሪካ ትምህርት ተቋማት፣ ስልጠና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች በተጨባጭ በመቀየር እና ውጤት በማምጣት ነው። በዚህ ረገድም መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአፍሪካን የክህሎት ልማት መጻኢ ጊዜ በውድድር፣ በፈጠራ እና አሳታፊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊገነቡ ይገባል። አፍሪካ ወጣቶቿ በክህሎት እና በእውቀት ከታጠቁ አፍሪካ የተለመቻቸውን ግዙፍ እቅዶች እና ትላልቅ ውጥኖች ባጠረ ጊዜ እንዲሳኩ ያስችላል።
 ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ በሀገሩ ህልሙን እውን ያደረገው ወጣት...
Oct 9, 2025 780
ሐረር ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ተወልዶ ያደገው ነስረዲን አህመድ፤ በውጭ ሀገር ሰርቶ መለወጥን በማሰብ ከአመታት በፊት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ እንቅስቃሴ ጀመረ። የመጓዝ እቅዱም ተሳካለትና በዱባይ ለስምንት ዓመታት በስራ ላይ ማሳለፉን ያስታውሳል፤ በበረሃው ምድር ሌት ተቀን በስራ እየደከመ ህይወቱን ሊለውጥለት የሚችል ገንዘብ ለመያዝ ቢጥርም ባሰበው ልክ ሊሳካለት አልቻለም።   በመሆኑም ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ሰርቶ የመለወጥ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ስራ ገባ። ከበረሃው ንዳድ ወጥቶ በሀገሩ ሰርቶና አልምቶ መለወጥን የሰነቀው ነስረዲን በሀረር የንብ ማነብ ስራን ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንደሆነው ያስታውሳል። በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት ሌት ከቀን መስራት ከቻልን የማናሳካው ነገር አይኖርም የሚለው ወጣቱ አሁን በሀገሩና በወንዙ በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን ይናገራል።   የነስረዲን የንብ ማነብ ስራ የተጀመረው በጥቂት ቀፎዎች የነበረ ቢሆንም በስድስት ወራት ውስጥ ግን 50 ቀፎዎች ማድረስ መቻሉን ያስታውሳል። በሀገሬ ህልሜ እውን እየሆነ ነው የሚለው ወጣቱ የንብ ማነብ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ላይ የንብ ቀፎዎቹን 300 ሲያደርስ ለ30 የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ፈጥሯል። በአረብ ሀገር የቆየባቸውን ዓመታት በቁጭት የሚያስታውሰው ነስረዲን መልፋትና መድከም ከተቻለ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ ይላል። ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የስኬት መንገድን ጀምሬያለሁ በቀጣይም ጠንክሬ እሰራለሁ ብሏል።   በቀጣይ ከንብ ማነብም ባለፈ የማር ማቀነባበርያ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የማቋቋም ትልም እንዳለው ተናግሮ ለዚህም እንደሚተጋ አረጋግጧል። በዚሁ የልማት ፕሮጀክት ላይ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ሸዊብ መሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ያለምንም ስራ ተቀምጦ መሽቶ ይነጋ እንደነበር አስታውሶ አሁን እያገኘ ባለው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየረዳ መሆኑን ተናግሯል።   ወጣት በድሪ ሙሳም፤ በነስረዲን ጥረት እርሱን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ስራ የተፈጠረላቸው በመሆኑ ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን አንስቶ በቀጣይ እርሱም የራሱን ተመሳሳይ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል።   በሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የንብ እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢብሳ ዩስፍ፤ የነስረዲን ጥረትና የአጭር ጊዜ ስኬት ለሌሎች ወጣቶችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።   በመሆኑም በክልሉ የማር ምርታማነትን ለማጎልበት በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ የንብ መንደር በመመስረት ዘርፉን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 1691
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ  7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2100
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 2960
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 3066
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር።   ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል።   ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው።   የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው።   ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 980
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 683
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6522
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 4997
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 55857
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 51467
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 32179
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 29691
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 26071
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 24672
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 24383
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 24283
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 55857
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 51467
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 32179
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 29691
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የዳሰነቾች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ''
Oct 30, 2025 805
የዳሰነች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ''ጀለባ'' (በጣፋጩ ሰለሞን ከጂንካ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ዳሰነቾች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በአብሮነት ተጎዳኝተው ይኖራሉ። የብሔረሰቡ አባላት ዋነኛ መተዳደሪያ ከብት እርባታ ሲሆን፤ ከከብት እርባታው ጐን ለጐን በዝቅተኛ ደረጃ በግብርናና በዓሳ ማስገር ስራ ይተዳደራሉ፡፡ ዳሰነቾች በሰሜን ከሐመር፣ በደቡብ ከኬኒያ፣ በምስራቅ ከቦረና በስተ ምዕራብ ደግሞ ከኛንጋቶም ማህበረሰብ ተጎራብተው ይኖራሉ። ዳሰነቾች ከኩሽቲክ የቋንቋ ነገድ የሚመዘዝ ''አፍ ዳሰነች'' የተሰኘ የመግባቢያ ቋንቋም አላቸው። ዳሰነቾች የተለየ የአለባበስ፣ የአጋጌጥ፣ የቤት አሰራር እና የባህላዊ የሙዚቃ ስልተ ምትን ጨምሮ አስደማሚ ባህሎች እና ማራኪ የመልክዓ ምድር አቀማመጥን የታደሉ ናቸው። ዳሰነቾች ከሚታወቁባቸው አስደማሚ ባህሎች ውስጥ አንዱ የሆነው አለመግባባቶችን በውይይት የሚፈቱበት የ''ጀለባ''ስርዓት ተጠቃሽ ነው። ይህ ስርዓት ግጭቱ ቂምና ቁርሾ በማይሻገርበት መልኩ በዘላቂነት የማስወገድ አቅም ያለው ሲሆን የማይናወጥ ሰላምና ወንድማዊ ትስስር እንዲጠናከርም ሚናው የጎላ ነው። ዕሴቱ የዳሰነቾች የአኗኗር ቁመና የሚለካበትና የሚመዘንበት መጻኢንም የሚተለምበትም ጭምር ነው። ስለሆነም በዳሰነቾች ዘንድ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል ነው የሚባለው። የባህሉ ተመራማሪ ሊዮን አርሎት 'ጀለባ'' የተሰኘው ባህላዊ ዳኝነት ከአካባቢው ሰላም አልፎ ለቀጠናው ወንድማማችነት መጠናከር ትልቅ ሚና ያለው የፍትህ ስርዓት መሆኑን ያነሳሉ። በ''በጀለባ'' ስርዓት ባህላዊ የዳኝነት አሰጣጥ እርከኖች እንዳሉ ጠቅሰው፥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ''ኖሞ'' የተሰኙ ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው በማቅናት የግጭቱን መንስኤ በማጣራት ''ቶሎል'' ለተሰኙ ሌሎች ሽማግሌዎች የሚያሳውቁበት አሰራርም አላቸው። እንደ ግጭቱ ቅለትና ክብደት ''ቶሎል'' በተሰኙ ሽማግሌዎች ተለይቶ ቀለል ያለው ''ካባና'' በተሰኙ ዳኞች ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን፥ ጉዳዩ ከበድ ያለ ከሆነ ደግሞ የመጨረሻው ውሳኔ ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች ይሰጣል። ከነፍስ ማጥፋት በስተቀር ሁሉም ውሳኔዎች ''አራ'' በተሰኙ ዳኞች እልባት ያገኛሉ። የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ሲከሰት ግን ጉዳዩን ለመንግሥት አሳልፎ በመስጠት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል ። ነፍስ ያጠፋው ሰው የእርምት ጊዜውን አጠናቆ ማህበረሰቡን ለመቀላቀል ሲወስን ባህላዊ የዕርቅ ስነ-ስርዓት ተዘጋጅቶ በዳይና ተበዳይ ይቅር የሚባባሉበትም ስርዓት እንዳለ የባህሉ ተመራማሪ ይናገራሉ።   በዳሰነቾች ባህል ልዩነቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በዘላቂነት መንገድ የመፍታት ዘመናትን የተሻገረ ድንቅ ዕሴት መኖሩን የሚያነሱት የብሔረሰቡ አባል አሸቴ ነካሲያ፤ “በዳሰነች ብሔረሰብ ቂም መያዝ አሎሎ ተሸክሞ እንደመዞር ይቆጠራል'' ይላሉ። በዳሰነቾች አለመግባባቶች በውይይት የሚፈቱበት ስርዓት እንዳለ ጠቅሰው፥ ''ናብ'' በተሰኘው የዳኝነት ስፍራ አለመግባባቶች ውለው ሳያድሩ እልባት ያገኛሉ ብለዋል። ሌላው የብሔረሰቡ አባል ሎቶያቡስ ሎኪሰሬሬ በበኩላቸው የባህል መሪዎች የተጣላን ማስታረቅ፣ ትውልዱን የመግራትና በስነ-ምግባር የማነፅ ኃላፊነት እንዳላቸው ጠቅሰዋል። ''ማንም ሰው ከባህል መሪዎች ትዕዛዝ አያፈነግጥም'' የሚሉት አቶ ሎቶያቡስ፥ ሁሉም እርስ በእርስ በመከባበር እና ችግሮች ሲኖሩ በውይይት በመፍታት አብሮነቱን ያጠናክራል ብለዋል።   ወጣቱ ለባህል መሪዎች ታዛዥ ነው የሚሉት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ የብሔረሰቡ አባል ሎሲያ ሎብቻ ወጣቶች ለአካባቢው ሰላም ዘብ እንዲቆሙ፣ ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በፍቅር እንዲኖሩ በማስተማር ወጣቱን በስነ-ምግባር የማነፅ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው የዳሰነች ህዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ ከወረዳው አልፎ ለቀጠናው ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። የብሔረሰቡ ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት ትውልዱን በመግራት በስነ- ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲፈጠር እንዳደረገም አስረድተዋል።   የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርና ተመራማሪ አጎናፍር ሰለሞን፤ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቶች ለዘመናዊው የፍትህ ስርዓት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓቶች ቅጣት በመጣል ጥፋተኝነት እንዲሰማ የሚያደርጉ ሳይሆኑ፤ እውነተኛ ይቅርታን የሚያሰፍኑና ለአብሮነት የሚበጁ ዕንቁ ባህሎች እንደሆኑም አብራርተዋል።   ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹ በግለሰብ ተጠቃሚነት ላይ ሳይሆን በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ በመሆናቸው ከዘመናዊው የፍትህ ስርዓት በይበልጥ ለአብሮነት መጠናከር አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎቹም ለሀገራዊ መግባባት ሚናቸው የላቀ በመሆኑ፥ እሴቶቹ ተጠብቀው፣ ለምተውና ጎልብተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ መስራት እንደሚገባም መክረዋል። ሀገራችን ቂምና ቁርሾን የወለዱ ያለመግባባቶች በዘላቂነት በሰለጠነና ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ሁሉንም ያሳተፈ ስራ እየሰራች እንደሆነ ያነሱት መምህርና ተመራማሪው አጎናፍር ሰለሞን ዕሴቶቹ በማህበረሰቡ ዘንድ ካላቸው ተቀባይነት እንዲሁም ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን ከማገዝ አንጻር ጉልህ ሚና ስለሚኖራቸው መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
''ቦር ተራራ'' የየሞች የፈውስ ምድር 
Oct 27, 2025 448
(በእንዳልካቸው ደሳለኝ ከወልቂጤ ኢዜአ ቅርንጫፍ) የም ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ይገኛል። በዞኑ የቦር ተራራ ዋነኛው የመድኃኒት እጽዋት መገኛ እና ምንጭ በመሆኑ የሞች በየዓመቱ ጥቅምት ወርን ጠብቀው በ17ኛው ቀን ከዚህ ተራራ በህብር ሆነው የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ስነ-ስርዓት ያካሂዳሉ፤ ይሰባስባሉም ። የቀደምት የየም አባቶችና እናቶችን በማሳተፍ የሚከወነው የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ከባህር ጠለል በላይ 2 ሺህ 939 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው ቦር ተራራ ላይ ነው። በዚህ ተራራ ላይ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን የሞች ለዓመት የሚያገለግላቸውን የመድኃኒት እጽዋት ይለቅማሉ። ተግባሩንም አዋቂዎች በጋራ ሰብሰብ ብለው ለመድኃኒት የሚውለውን ቅጠል በጥሰው፣ ስር ምሰው፣ አስሰውና መርጠው ይሰበስባሉ። ይህም የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ስርዓት "ሳሞ ኤታ" ተብሎ ይጠራል ። አያምጣውና ህመም ሲከሰት ታማሚውን ሰው ወይም እንስሳን ከበሽታው ለመፈወስ የተዘጋጀው ባህላዊ መድሃኒት በባህላዊ ሃኪም ትዕዛዝ መሰረት በህመሙ ልክ ይታዘዝለታል። መድሃኒቱን ለመጠቀምም የጠቢባን አባቶችን ፈለግ ተከትሎ መፈፀም የግድ ይላል። የሞች አጅግ አስገራሚ እና አስደናቂ የሆኑ የበርካታ አገር በቀል ዕውቀቶች ባለቤት ናቸው ካስባሏቸው እሴቶች መካከል ይህ ለየት ያለው ክዋኔያቸው አንዱ ነው፡፡ አባቶች ታዳጊና ወጣቶችን አስከትለው ወደ ቦር ተራራ በመውጣት የሚፈፅሙት ባህላዊ ክዋኔ በመሆኑም ከትውልድ ወደ ትውልድ ቅብብሎሹን ጠብቆ እስከ አሁን እንዲዘልቅ እድርገውታል።   በየሞች ዘንድ የባህላዊ መድኃኒት አዋቂዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም፤ የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማ ልምድን የቀሰሙት ከአባታቸው መሆኑን በመግለፅ አያታቸው ከቅድመ አያቶቻቸው በመውረስ እዚህ እንዳደረሱት ይናገራሉ። የቦር ተራራ ለመድሃኒት ዕፅዋት ለቀማው የተመረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ቦታው ተራራ በመሆኑ ማንም ያልደረሰባቸው የተለያዩ እፅዋትን ለማግኘት አመቺ ከመሆኑ ጋር ያያይዙታል። በሌላም በኩል ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ መጀመሪያ የምታገኘው ተራራውን በመሆኑና ክረምቱ አልፎ ጥቅምት ሲገባ የተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎችን በብዛት እና በዓይነት ለማግኘት ተመራጭ ወቅት መሆኑም ቦታው የተመረጠበት ሌላኛው ምክንያት ነው ብለዋል። በጥቅምት 17 ለመድኃኒትነት የሚያገለግለው ዕፅዋት ቅጠልም በየፈርጁ ተለቅሞ እና ተቀምሞ ይቀመጣል ሲሉም አስረድተዋል። የተዘጋጀው ባህላዊ መድኃኒትም ለሰው ልጆችና ለቤት እንስሳት ያገለግላል ሲሉም አስረድተዋል፡፡ ይኸው በዚህ ቀን የተለቀመው የመድኃኒት ዕፅዋት ከዚህኛው ጥቅምት 17 እስከሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት 17 ድረስ እንደሚያገለግልም አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡ የባህል መድኃኒት ሰብሳቢዎች እና ተጠቃሚዎች ጊዜውን ጠብቀው ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ቦር ተራራ እንደሚመጡ የሚገልጹት የባህል መድኃኒት አዋቂው ዛሬ ዛሬ እሳቸውን ጨምሮ መድኃኒት ቤቶችን በመክፈት ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ የባህል መድኃኒቶችን በመሸጥ ኑሯቸውን እየመሩ የሚገኙ አያሌ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉም ይናገራሉ። ሌላኛው የባህል መድኃኒት አዋቂው አቶ ወልደመስቀል ጆርጋ በበኩላቸው በየሞች ዘንድ የተዘጋጀው የመድኃኒት ዕፅዋት ጥቅም ላይ የሚውለው ህመም ሲያጋጥም ብቻ ሳይሆን በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል መሆኑን ጠቁመው መድኃኒቶቹም ብቻቸውን እንዲሁም ከምግብ ጋር በመመገብ ለጥቅም እንደሚውሉም አንስተዋል። የየም ምድር የበርካታ የመድኃኒት ዕፅዋቶች መገኛ አካባቢ " የፈውስ ምድር " ነው የሚሉት ደግሞ በየም ባህላዊ መድኃኒት ዙሪያ ጥናት ያደረጉት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የፎክሎር መምህር እና ተመራማሪ ለማ ንጋቱ (ዶ/ር) ናቸው። ከየሞች አያሌ የባህል ዕሴቶች መካከል የባህል መድኃኒት ለቀማና ቅመማ አንዱና ዋነኛው የሀገር በቀል እውቀት ማሳያ መሆኑን ገልፀው የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማ ስነ-ስርዓቱ ከጥንት ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ዛሬ ላይ የደረሰ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡   ማህበረሰቡ የራሱንም ሆነ የእንስሳትን ጤና የመጠበቅ የቆየ ባህል ያለው መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰው የባህላዊ መድኃኒት ለቀማው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፉበት ዓመታዊ ክዋኔ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ሌላው ገራሚው ነገር ይላሉ አጥኚው ታላላቆች ታናናሾቻቸውን አስከትለው የለቀማ ሂደቱን የሚያስረዱበት መንገድ ደግሞ ስርዓቱ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል ትውልድ ተሻጋሪ የሀገር በቀል እውቀት ሽግግር ስርዓት ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጹት። በዚህም ሂደት የሚነገሩ ስነ-ቃሎች መሞጋገስ፣ ጭፈራና ደስታ ይስተናገድባቸዋል። ይህም ማህበራዊ ትስስርን ይበልጥ የሚጠናክሩበትን ሁነት የሚፈጥር ስርዓት ነው። የየም ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሞጋ በበኩላቸው የቦር ተራራ የመጀመሪያውን የማለዳ የፀሐይ ጎህ የሚፈነጥቅበት የንጋት ብርሃን ቀድሞ የሚያገኝ በመሆኑ፥ በዚህ አካባቢ የሚገኙ እጽዋት በሽታን የመከላከልና ፈዋሽነታቸው ከፍተኛ ነው ተብሎ ስለሚታመን ለዚህ ክዋኔ ቦታው መመረጡን ነው የሚገልፁት። ለዚህም ነው የሞች ይህንን ስፍራ ከሌሎች ቦታዎች አስበልጠው የሚወዱት፤ በየዓመቱም ጥቅምት 17 ቀን ወደ እዚህ ስፍራ በማቅናት ለዓመት ፍጆታ የሚያገለግላቸውን መድኃኒትም ይሰበስቡበታል ብለዋል። ጥቅምት 17 በየም ዘንድ ለየት የሚያደርገው ሌላው የመድሃኒት ዕፅዋት ለመልቀም እና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን የለቀማውን ትዕይንት ለመመልከት የሚመጡ ቱሪስቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው ሌላው ትልቁ ትሩፋት ነው ይላሉ። የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማው ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት በመሆኑ፥ ለአብሮነት እና ሃገር በቀል እውቀት ለመቅሰም ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው አቶ መስፍን የገለፁት።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም