አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸፈች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸፈች
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ በፈረንሳይ ላይቪን የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ተካሄዷል።
በሴቶች 3000 ሜትር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ8 ደቂቃ ከ24 ሴኮንድ ከ59 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።
በርቀቱም የ2026 ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።
አለሺኝ ባወቀ ሁለተኛ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስትጨርስ ጣልያናዊቷ ናዲያ ባቶክሌቲ ሶስተኛ ወጥታለች።
በውድድሩ ሂሩት ማስረሻ አምስተኛ፣ ሃዊ አበራ ስድስተኛ፣ የኔዋ ንብረት ዘጠነኛ፣ ብርቱካን ሞላ 10ኛ፣ ሺቶ ጉሚ 11ኛ፣ ፋንታዬ በላይነህ 13ኛ እና አስቴር አረሪ 14ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በወንዶች የ3000 ሜትር ውድድር አትሌት አዲሱ ይሁኔ 7 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ58 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አንደኛ ወጥቷል።
ኬንያዊው ጃኮብ ኪሮፕ ሁለተኛ እና ጌትነት ዋለ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በ1500 ሜትር ሴቶች ብርቄ ኃየሎም እና ሳሮን በርሄ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል።
የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ጆርጂያ ሃንተር ቤል ውድድሩን አሸንፋለች።
ወርቅነሽ መሰለ እና ሐረገወይን ካላዩ 9ኛ እና 10ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በሴቶች 2000 ሜትር ኬና ቱፋ አምስተኛ፣ ባይሴ ቶሎሳ 10ኛ እና ገላ ሐምበሴ 11ኛ ወጥተዋል።
አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሁል፣ ፖርቹጋላዊቷ ሳሎሜ አልፎንሶ እና ፈረንሳያዊቷ አጋት ጉሌሞት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ፅጌ ዱጉሞ ሶስተኛ ወጥታለች። ንግስት ጌታቸው አራተኛ ደረጃን ይዛለች።
የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ኬሊ ሆድኪንሰን አንደኛ ስትወጣ ስዊዘርላንዳዊቷ ኦውድሬይ ዌሮ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
የዓለም አትሌቲክስ እ.አ.አ በ2026 ባወጣው መርሐ-ግብር አማካኝነት በተለያዩ ሀገራተ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።