ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ የ39ኛው የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ ለተመዘገበው ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያሳዩት ቁርጠኝነት በተግባር የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበውን ውጤት የአዲስ አበባ ከተማ በራሷ ትናገራለች ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በማዘጋጀት የአፍሪካ አቋም ለማሳወቅ ማጣቀሻ የሚሆን ሰነድ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ተጽዕኖን በመቋቋምና በሀይል ሽግግር የአፍሪካን ድምጽ የሚያንጸባርቅ አቋም የተያዘበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የበካይ ጋዝ ልቀት ተጽዕኖ ከ4 በመቶ እንደማይበልጥ በማንሳት፤ በብክለት የምትጎዳው ግን የላቀ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራትን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የማገገሚያ ዕቅድ እንዲያወጡ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡