ቀጥታ፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዐርማ ተመረቀ

ሐዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነው የዕዙ ዐርማ የምረቃ መርሐ-ግብር ተከናውኗል።

ዐርማውን የመረቁት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው።

እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የዕዙን የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በሐዋሳ ከተማ ተከፍቷል።

በሌላ በኩል የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የመጽሐፍ ምረቃ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች👉 https://linktr.ee/ENADigital

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም