ቀጥታ፡

አዲስ አበባ በንፅህና አጠባበቅ ረገድ እያከናወነች ያለው ሥራ በአርዓያነት ይጠቀሳል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2018 (ኢዜአ)፡- አዲስ አበባ በውኃና በንፅህና አጠባበቅ ላይ እያከናወነች ያለው ሥራ በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ገለጹ።


 

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ግንባታ እያከናወነች ያለውን ተግባርም አድንቀዋል አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ።

በተጨማሪም ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ እየወሰደቻቸው ያሉ እርምጃዎች ለእድገቷ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።


 

በሌላ በኩል በተለያዩ ከተሞች የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆናቸውን ነው ያስረዱት።

እንዲሁም አዲስ አበባ ከውኃና ንፅህና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም እንደ ትልቅ ማሳያ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።


 

ለአብነትም በርካታ የሕዝባዊ መገልገያ ስፍራዎች እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ መገንባትን ጨምሮ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ እየተሠራ ያለውን ሥራ አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም