ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።

በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ዛሬ ይጀመራል


ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ማንችስተር ሲቲ ከኒውካስትል ጋር በኢትሃድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።



ማንችስተር ሲቲ በ53 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ36 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ውሃ ሰማያዊዎቹ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዘገብ ይጫወታሉ።

በ26ኛ ሳምንት ከሜዳው ውጪ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 ያሸነፈው ኒውካስትል ዩናይትድ ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ ይፋለማል።

ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋል።

በሌላኛው መርሐ-ግብር አስቶንቪላ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድን በቪላ ፓርክ ስታዲየም ያስተናግዳል።

አስቶንቪላ በ50 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ሊድስ ዩናይትድ በ30 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ጨዋታው አስቶንቪላ በዋንጫ ፉክክሩ ለመቆየት፣ ሊድስ ዩናይትድ ከወራጅ ቀጠና ለመራቅ ሶስት ነጥብ ለማግኘት የሚፋለሙበት ነው።



ቼልሲ ከበርንሌይ እና ብሬንትፎርድ ከብራይተን በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። 

ዌስትሃም ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ በለንደን ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም