ቀጥታ፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ -ርዕይ በሐዋሳ ተከፈተ

ሐዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የዕዙን የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በሐዋሳ ከተማ ተከፍቷል።

የፎቶ ዐውደ-ርዕዩን መርቀው የከፈቱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ናቸው።

በዚሁ ዝግጅት ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብዳታ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።


 

በተጨማሪም የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ነዋሪዎች ታድመዋል።

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነው የመጽሐፍ ምረቃ እንደሚከናወንም ተጠቁሟል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመጽሐፉ ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም