ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል
Mar 26, 2026 37
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ ሰብሳቢ ረዳት ዣንግ ሊንግሊንግ ገለጹ። "ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ ናት" በሚል መሪ ሀሳብ ኢንቨስት በኢትዮጵያ' ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ፎረም ላይ ለመሳተፍ የመጡት የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሙዚየም ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ ሰብሳቢ ረዳት ዣንግ ሊንግሊንግ በዚሁ ወቅት፤የሰው ዘር መገኛ የሆነችውን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሙዚየም በመመልከታቸው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸዋል። በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ዘመናዊና የአፍሪካ የውበት ማዕከል ማድረጉን ያደነቁት ሰብሳቢዋ፣ በከተማዋ የታየው ለውጥ እጅግ አስደናቂ መሆኑን ጠቁመዋል። የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ገልጸው፤ በርካታ ቻይናውያን በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ እንደሚገኙና ኮሚቴውም ለዚህ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል:: በቀጣይም ኮሚቴው ስለ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ ለቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድል መፍጠሩም ተናግረዋል። መንግስት የቻይና ባለሀብቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ የፈጠረው ምቹ ሁኔታና እያደረገ ያለው ጥሪ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ሌላኛው የፊልም ዳይሬክተሩ ሱን ካይካይ በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ በሚቆይበት ጊዜ በካሜራው የቀረጻቸውን ምስሎች በማሰባሰብ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ዘጋቢ ፊልም ለማዘጋጀት ማቀዱን ገለጿል። ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው እንቅስቃሴ የተመለከተው የከተማዋ ውበትና ፅዳት እጅግ አስደንቆታል። በቻይና ሄንግዲያን ከተማ የኢትዮጵያን ቡና በማስተዋወቅ ላይ የምትገኘው አርቲስት ሃኦ ሊፒንግ፣ የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ በቤጂንግ በሚያዘጋጃቸው የኢንቨስትመንት ፎረሞች አማካኝነት ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ እውቀት ማግኘቷን ገልጻች። አርቲስቷ ኢትዮጵያ የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን የቡናም መገኛ መሆኗን ካወቀች በኋላ ቡናውን እጅግ በመውደዷ በማስተዋወቅ ስራው ላይ በንቃት እየተሳተፈች እንደምትገኝም ጠቁማለች። ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር በአካል ተገኝታ በመጎብኘቷም የተሰማትን ታላቅ ደስታ ገልጻለች። በቱሪዝም ሚኒስቴር የማይስ ቱሪዝም ሽያጭ ዴስክ ኃላፊ ብዙዓለም ጌቱ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚዬም የአብዛኛው የሰው ዘር ቅሪተ አካል መገኛ በመሆኑ በዓለም ደረጃ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። ጎብኚዎችና ኢንቨስተሮች እንዲህ ያሉ የኢትዮጵያን ቀዳሚነት የሚያሳዩ ስፍራዎችን መመልከታቸው ስለ ሀገሪቷ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ትልቅ በር እንደሚከፍትም አስረድተዋል።
ቱርክዬ ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች
Mar 26, 2026 31
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቱርክዬ ሮማንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን ኢስታንቡል በሚገኘው ቱርፓስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርዲ ካዲኦግሉ በ53ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ቱርክዬ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች። ውጤቱን ተከትሎ ቱርክዬ ወደ ጥሎ ማለፉ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ አልፋለች። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከስሎቫኪያ እና ኮሶቮ አሸናፊ ጋር መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ትጫወታለች። የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ ጥሎ ማለፍ ቀሪ ጨዋታዎች ማምሻውን መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ። በጥሎ ማለፉ የሚያልፉ አራት ሀገራት አስቀድመው በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫ ያለፉ 12 የአውሮፓ ሀገራትን ይቀላቀላሉ።
23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ይካሄዳል
Mar 26, 2026 53
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ከመጋቢት 20 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሐረር ከተማ እንደሚካሄድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ ውድድሩንና ፌስቲቫሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት ለስፖርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት በአዲሱ የስፖርት ፖሊሲ አማካኝነት የባህል ስፖርቶችን ለማልማት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሁነቱ የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊ አንድነት፣ ብዝሃነት እና አብሮነት የሚተዋወቅበት መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ህይወት መሐመድ በበኩላቸው ውድድሩና ፌስቲቫሉ ህብረተሰቡን በባህል ስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ከማድረግም ባሻገር የባህል ስፖርትን ማህበረሰብ አቀፍ የማድረግ አላማ እንዳለው ገልጸዋል። በውድድርና ፌስቲቫሉ ከአፍሪካ ባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን የተጋበዙ የክብር እንግዶች እንደሚታደሙበት ጠቁመዋል። በ11 የስፖርት አይነት በሚካሄደው ውድድርና ፌስቲቫል ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ1500 በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ። ሁነቱ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። ውድድሩና ፌስቲቫሉ "የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ላለው ብርቱ ጥረት እውቅና ልሰጥ እወዳለሁ-ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር)
Mar 26, 2026 70
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ላለው ብርቱ ጥረት እውቅና እንደሚሰጡ የድርጅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር) ገለጹ። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) የሚኒስትሮች ስብሰባ (MC14) ዛሬ በካሜሮን ያውንዴ ይካሄዳል። በሚኒስትሮች ስብሰባው ላይ የድርጅቱ 166 አባል ሀገራት የንግድ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ ነው። የዓለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር 22 ሀገራት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። አንዳንድ ሀገራት አባል ለመሆን ለአስርት ዓመታት ጥረት ማድረጋቸውንና ሌሎች ሀገራት በቅርቡ ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን አመልክተዋል። ከ22 ሀገራት በተጨማሪ የፋሮ ደሴቶች አባል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበች አዲስ ሀገር መሆኗን ጠቁመው፥ጥያቄው ለድርጅቱ አጠቃላይ ምክር ቤት ገና አለመታየቱን ጠቁመዋል። የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን አድካሚ፣ብርቱ ጥረት እና ጽናት የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ አባል ለመሆን እየጣሩ ያሉ ሀገራት ለጠንካራ ስራቸው እና ትዕግስታቸው እውቅና መስጠት እወዳለሁ ብለዋል። ዳይሬክተ ጀነራሏ ባደረጉት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ እውቅና ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ እና ኡዝቤኪስታን እ.አ.አ በ2026 የድርጅቱ አባል እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) የሚኒስትሮች ስብስባ (MC14) እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2026 የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድር ለማጠናቀቅ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን 7ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እ.ኤ.አ በኤፕሪል ወር 2026 ለማካሄድ ኢትዮጵያ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
ብሔራዊ ቡድኑ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል
Mar 26, 2026 65
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ነገ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ታደርጋለች። ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው በሚደረግበት ኤል አብዲ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ማምሻውን አከናውኗል። ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት ልምምዳቸውን ሰርተው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኤል ጀዲዳ ኤል አብዲ ስታዲየም ይከናወናል።
ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ይሳተፋሉ
Mar 26, 2026 123
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ማላቦ ኢኳቶሪያል ጊኒ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ማላቡ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአፍሪካ፣ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ከ5 አስርት አመታት በፊት እ.አ.አ በ1975 በቶጎ በተካሄደው ሎሜ ኮንቬንሽን ነበር የተጠነሰሰው፡፡ በሰኔ ወር በዚያው ዓመት ደግሞ ከአፍሪካ፣ካርቢያን እና ፓሲፊክ የተወጣጡ 46 ሀገራት በፈረሙት የጆርጅታውን ስምምነት መሰረት ድርጅቱ ተመስርቷል። በተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች ያለፈው ድርጅቱ አሁን ላይ 79 ሀገራትን በአባልነት ማካተት የቻለ ሲሆን የተፅዕኖ ደረጃውም በዚያው ልክ እያደገ ነው የመጣው። ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር በተጨማሪ የልማት ፣ዴፕሎማሲ፣ ፖለቲካዊ እና አለም አቀፍ የፍትህ ጉዳዮች የሚንሸራሸሩበት መድረክ እየሆነ መጥቷል። 11ኛው የአፍሪካ፣ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከመጋቢት 18- 20 / 2018 ድረስ የሚቆይ ይሆናል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
በክልሉ ሰላምን ለማዝለቅና ልማትን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሚናውን ሊያጠናክር እንደሚገባ ተመላከተ
Mar 26, 2026 78
ወልዲያ፤ መጋቢት 17/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰላምን ለማዝለቅና ልማትን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሚናውን ሊያጠናክር እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ገለጹ። በወልዲያ ከተማ በሠላምና ልማት ዙሪያ ከነዋሪዎች ጋር የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሄዷል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የህዝቡ የነቃ ተሳትፎና ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህም በክልሉ ሰላምን ለማዝለቅና ልማትን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ እየተወጣ ያለውን ሚና ሊያጠናክር እንደሚገባም አመልክተዋል። የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ በበኩላቸው፤ ጽንፈኛው ቡድን በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በመታገል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የውይይት መድረኩም ይህን ተግባር ለማጠናከርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ለሠላም መደፍረስ መነሻ የሆኑ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ወሬዎችን ለይቶ መዋጋት አለበት ያሉት ደግሞ የመድረኩ ተሳታፊ ያሲን አሰፋ ናቸው። በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህን ለማዝለቅም እያከናወንን ያለነውን ተግባር እናጠናክራለን ብለዋል። የዘላቂ ሠላም ግንባታ ተግባር ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የገለፁት ደግሞ ሌላኛው ተሳታፊ መሐመድ አሚን ናቸው። ለአፍራሽ ሚዲያዎችና ለአላማ ቢስ ትግል ጆሮ ባለመስጠት ዘላቂ ሰላምን እውን በማድረግ የአካባቢያቸውን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ትግል የድርሻቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል። በመድረኩም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በክልሉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ተቀናጅቶ በመስራቱ ለሕዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ማድረስ እየተቻለ ነው
Mar 26, 2026 158
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ተቀናጅቶ በመስራቱ ለሕዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ማድረስ እየተቻለ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ፎረም የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና በቢሮው የተዘጋጀው የተቀናጀ ድረ ገጽ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ ቢሮው የክልሉን መረጃ በበላይነት የማስተዳደር እና መልካም ገጽታን የመገንባት ስራ በትኩረት እያከናወነ ነው። ቢሮው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መተማመን እንዲኖር የማድረግ እንዲሁም የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን የማስተባበር ተግባር እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። በተለይም ባለፉት ዓመታት የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ተቀናጅተው መስራት እንዲችሉ የጋራ ፎረም በመቋቋሙ የጋራ ትርክት ግንባታውን ለማጠናከርና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው መረጃን አቀናጅቶ የሚይዘው ድረ-ገጽም ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደርን፣ በእውነተኛ መረጃ ላይ የተገነባና ተደራሽነቱ አስተማማኝ የሆነ አሠራርን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል። በቴክኖሎጂ ዘመን ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመረጃ አገልግሎት ፈተናዎችን ለመከላከል ቢሮው የመረጃ አስተዳደር ማዕከል በመገንባት አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ድረ ገጹ በየደረጃው ከሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች መረጃ ከመሰብሰብ ባለፈ በሚዲያ፣ በመንግሥት ተቋማትና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንም አስረድተዋል። ድረ ገጹ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግብ አካል መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ቢሮው በሁሉም ረገድ አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር፣ ጥራት ያለውና ወጥ የሆነ መረጃን ለተጠቃሚው ተደራሽ ለማድረግ የጀመረውን ስራ ያጠናክራል ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ፎረሙ በዘርፉ የተናበበ እና የተቀናጀ አሰራር እንዲኖር እድል መፍጠሩን ተናግረዋል። ይፋ የተደረገው ድረ-ገጽም በክልሉ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ተደራሽ በማድረግ የሕዝቡን የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል። በመድረኩም የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የጀመረው የዲጂታል መረጃ አስተዳደር ሥርዓት እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና ቀርቧል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በምርጫው በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ካርድ እየወሰዱ ነው
Mar 26, 2026 112
ጅማ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ መሆናቸውን የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ለዚሁ ተግባር የምርጫ ካርዳቸውን ሲወስዱ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጅማ ነዋሪዎች እንዳሉት በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለሀገራቸው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸው እየተወጡ መሆናቸውን አንስተዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ጌታቸው ወዳጆ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። የምርጫ ካርዳቸውን ከመውሰዳቸው ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጫቸውን በመገናኛ ብዙሃን የሚያቀርቡበትን መድረክ እየተከታተሉ መሆኑን አንስተዋል። ሌሎችም እንደሳቸው በወቅቱ የምርጫ ካርዳቸውን በመውስድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገሪቱ እድገት የሚበጅ ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ እንዲመርጡም መክረዋል። የምርጫ ካርድ መውሰድ ለሀገር እድገት የሚበጅ የፖሊሲ አማራጭ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መሰረት በመሆኑ ካርድ መውሰዱን የገለጸው ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ወጣት ዘሪሁን ጂሀድ ነው። በምርጫ ካርዱም የወጣቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እና የሀገሪቱን እድገት የሚያስቀጥል ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። ሌላኛዋ የጅማ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አለምፀሀይ ፃዲቁ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረው ለህዝብ እና ለሀገር እንዲሁም ለሴቶች ተጠቃሚነት በትኩረት ይሰራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ እንዳቀዱም አክለዋል።
በሶማሌ ክልል ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ይጠናከራሉ
Mar 26, 2026 116
ጅግጅጋ፣ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ከማድረግ ባሻገር ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ወጣቶች ምክር ቤት ገለጸ። በጠቅላላ ምርጫው ለመሳተፍ ከሚያስፈልጉ ጉዳዮች አንዱ የመራጮች ምዝገባን ማከናወን ዋነኛው በመሆኑ በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች በሚባል ሁኔታ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል። ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠቅላላ ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲከናወን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የሶማሌ ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሀመድ አህመድ ኑረ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልሉ ህዝብ በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የምርጫ ካርዱን በወቅቱ እንዲወስድ እየተሰራ ነው። የክልሉ ወጣቶች ምክር ቤትም የወጣቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግና በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ወጣቶች ህገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ዜጎች በምርጫው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለባቸው አመልክተዋል። በተጓዳኝም ወጣቶቹ ቀደም ብለው ሲሳተፉበት የነበረውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማጠናከር በደም ልገሳ፣ አረጋውያንን በመርዳት እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ላይ እየተሣተፉ መሆኑን ጠቁመዋል። ወጣቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም የዲጂታል ክህሎታቸውን የማበልጸግ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ የተጀመሩ ተግባራትም ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ለዚህም ወጣቶቹ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
የምርጫ ካርድ በመውሰድ በድምፃችን የሚመራንን ፓርቲ ለመወሰን ተዘጋጅተናል
Mar 26, 2026 168
ደብረ ማርቆስ ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ) ፡-የምርጫ ካርድ በመውሰድ በድምፃቸው የሚመራቸውን ፓርቲ ለመወሰን መዘጋጀታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ የበኩላቸውን ለመወጣት የሚሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ ቀን ተወስኖ፣ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ስም እንዲሁም የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል ለመወሰን የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት አካሒዷል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ፖሊሲና ስትራቴጂያቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ የምርጫ ክርክርና ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢው አጠቃላይ ምርጫውን በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር በየምርጫ ጣቢያዎቹ ተዘዋውሮ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ያሉ ዜጎችን አነጋግሯል። ከየምርጫ ጣቢያዎቹ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎችም የምርጫ ካርድ በመውሰድ በድምፃቸው የሚመራቸውን ፓርቲ ለመወሰን መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በከተማው ቀበሌ 11 የሚኖሩትና የምርጫ ካርድ ሲወስዱ ያገኘናቸው ወይዘሮ ውባለም ዝይን፤ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የመምረጥ እድል ያገኙ መሆኑን ተናግረው ካርድ በመውሰድ ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመገናኛ ብዙሃን የሚካሄዱ የፓርቲዎችን የክርክር መድረኮች እየተከታተሉ መሆኑን አንስተው ለሀገርና ህዝብ ይበጃል ለሚሉት ፓርቲ ድምፃቸውን እንደሚሰጡም ነው የሚናገሩት። የቀበሌ 10 ነዋሪ የሆኑት አቶ አንተነህ ይርዳው፤ በአምስት አመት አንዴ የሚገኘውን እድል በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመጠቀም የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። የምርጫ ጉዳይ የህዝብ የመወሰን መብት የሚረጋገጥበት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ከወዲሁ የምርጫ ካርድ በመውሰድ እድሉን መጠቀም ይገባል ብለዋል። በመሆኑም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ ከወዲሁ ካርድ በመውሰድ በድምፃቸው የሚመራቸውን ፓርቲ ለመወሰን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ትግስት ዳኘ፤ የመራጭነት ካርዳቸውን በመያዝ ድምፃቸውን ለመስጠት ከወዲሁ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምርጫ ሂደት የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበትና ሀገራዊ ሃላፊነትን የመወጣት ሚና በመሆኑ ለመምረጥ የሁላችንም ዝግጁነት ያስፈልጋል ብለዋል። የምርጫ ካርድ ከመያዝ በተጓዳኝ ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ የበኩላቸውን ለመወጣት የሚሰሩ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎቹ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት እየሰፈነ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Mar 25, 2026 532
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የአማራ ክልል ሰላምና መረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው በክልሉ ሰላምና መረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች፣ከከተሞች እስከ ገጠር ባደረጉት የመስክ ምልከታ የክልሉ ሰላም መሻሻል ማሳየቱን ገልጸዋል። በክልሉ ያለው ሁኔታ ቀደም ሲል በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚነገረው በተለየ መልኩ እጅግ የተረጋጋ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ያለው ችግር ከፀጥታ ስጋት ይልቅ የአስተሳሰብ ግድፈትና በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱ መረጃዎች የፈጠሩት የስነ-ልቦና ጫና መሆኑን ጠቁመዋል። ቁጥራቸው በዛ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለው ሰላማዊ ህይወት መጀመራቸውን ገልጸዋል። በተለይም የታጣቂ አመራር አባላት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እንዲጎበኙ መደረጉን አንስተዋል። በዚህም ታጣቂዎቹ የልማት ስራዎችን የመደገፍ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ነው የተናገሩት። በአሁኑ ወቅት በክልሉ እጅግ የሚያስደንቁ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተው፤ የክልሉ መንግስትና የፀጥታ ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተጠናከሩ መምጣታቸውንም አክለዋል።
ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ መሆን የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Mar 25, 2026 402
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ መሆን የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ዜጎች ለኢትዮጵያ ይጠቅማል የሚሉትን ለመምረጥ አስቀድመው የምርጫ ካርዳቸውን እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በምርጫ ዝግጅት መልዕክታቸው፤ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሕዊና ገለልተኛ ሆኖ መጠናቀቁ የህዝብ ተቀባይነት ማስገኘቱን አስታውሰዋል። ብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ አግኝቶ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የመንግስት ኃላፊነት በመስጠት አስቻይ የፖለቲካ ምኅዳር መፍጠሩን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የተፈጠረው ጤናማ የፖለቲካ ምኅዳርም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት በሀገር ሰላም፣ ልማትና ዕድገት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል። ፓርቲው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሚበጁ አማራጭ ሃሳቦቻቸውን በነጻነት እንዲያቀረቡ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው አንስተዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም መከበርን በተመለከተ የማይናወጥ አቋም ሊኖራቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። ለዚህም የስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ተሞክሮዎችን በመቀመር ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በውጤታማነት ማካሄድ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የብልፅግና ፓርቲም የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባስመዘገባቸው ተጨባጭ ውጤቶች ብቻ በህዝብ ተመራጭ መሆን የሚሻ ፓርቲ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ ፍትሐዊና መልክዓ-ምድራዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም የትውልድና የብሔራዊ ጥቅም አንጓ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ አስረድተዋል። የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ የህዝብን አንድነት ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረትም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትብብር የመስራት ባህልን ማጎልበት እንደሚኖርባቸው አንስተዋል። በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንግስት ለመመስረት የምርጫው ዴሞክራሲዊነት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ ሃሳባቸውን በመገናኛ ብዙሃን ለህዝቡ እያዳረሱ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎችም ድምፅ መስጫ ካርድ መውሰድ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም ሰላማዊ፣ ተዓማኒና የህዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ማህበራዊ
ዩኒቨርስቲው የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ብቁ የሰው ሃይልን በማፍራት ረገድ የድርሻውን እየተወጣ ነው
Mar 26, 2026 51
ደሴ፤ መጋቢት 17/2018(ኢዜአ)፦ ወሎ ዩኒቨርስቲ የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ብቁ የሰው ሃይልን በማፍራት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) ገለፁ። ዩኒቨርሲቲው "ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሕክምና ትምህርትንና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤን ማሻሻል" በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛውን ዓለም አቀፍ የጤና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ተግባር ተኮር ትምህርት በመስጠት ብቁ ባለሙያዎች ማፍራት ላይ እየሰራ ነው። የጤና ተቋማትን በግብዓት በመደገፍ፣ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማካሄድ ህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የበኩሉን መወጣቱን አመልክተዋል። የዛሬው ኮንፈረንስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረጉ የምርምር ስራዎችን በውይይት በሚገኝ ግብዓት በማዳበር ወደ ተግባር ለማሸጋገር መካሄዱን አንስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የልዕለ ሕክምና ካምፓስ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር መታደል አዳነ (ዶ/ር) በበኩላቸው የህክምናውን ዘርፍ ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጋር በማስተሳሰር የፈውስ ምጣኔን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል። በጤና ዘርፉ የሚሰሩ ምርምሮችን በቴክኖሎጂ ተደግፎ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምህርት ቤት መምህር እና ተመራማሪ ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ ናቸው። ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ ትምህርት ጋር በማስተሳሰርና የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመቀመር የህክምናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረጉ ተግባራት ዩኒቨርሲቲዎች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። በጤና ሚኒስቴር የጤና ዘርፍ የሰው ሀብት ልማት ማሻሻያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሳሙኤል በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር፣ ቴክኖሎጂን በማላመድና በማስፋት የጤናውን ዘርፍ ማዘመን ላይ አተኩረው እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። የጤና ተቋማትን ለማዘመንና የህክምና አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ በፓይለንት ደረጃ በተመረጡ የጤና ተቋማት የተጀመረውን ስራ ለማስፋት እንደሚሰራ አስረድተዋል። ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት እየተደረገ ባለው ጥረት የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከፍ ያለ በመሆኑ ሚኒስቴሩ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል። ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
ባህላዊ የግጭት አፈታት የፍትሕ ሥርዓቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ ነው
Mar 26, 2026 53
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የዜጎች ባህላዊ የግጭት አፈታት የፍትሕ ሥርዓቶች ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኝ የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያስላሴ ገለጹ። ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዕውቅና በተሰጣቸው ባህላዊ የፍትሕና የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች ከሶስት ሚልየን በላይ ጉዳዮች መስተናገዳቸውን ተናግረዋል። ''በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የፍትሕ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልቶችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሃሳብ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የፍትሕ ተደራሽነት በአፍሪካ-2026 ጉባኤ ተጠናቋል። በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደው ጉባኤ የአፍሪካን ባህላዊ የማህበረሰብ የፍትሕ ሥርዓቶችን ከመደበኛው የሕግ ማዕቀፍ ጋር ለማቀናጀት ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ ያለመ መድረክ መሆኑ ተገልጿል። በባህላዊ የክርክር መፍቻ ሥርዓቶች ውስጥም የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን በማሳደግ አስተማማኝ የፋይናንስ ሥርዓት ማፈላለግም ሌላኛው የጉባኤው ዓላማ መሆኑ ተመላክቷል። የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያስላሴ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የግጭት መፍቻ ባህላዊ ዕሴቶች መደበኛ የፍትሕ ሥርዓቱን በማገዝ ለሕግ የበላይነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የተደረገው ባህላዊ ፍርድ ቤት ሌሎች ክልሎችም እንደየማህበረሰቡ ዕሴትና ሥርዓት ዕውቅና አግኝቶ ወደሥራ እየገባ እንደሚገኝ አንሰተዋል። በቀጣይም ባህላዊ የግጭት መፍቻ የዳኝነት ዕሴቶችን በሁሉም ክልሎች ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰብ አብሮነትና አንድነት ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ለዚህም የክልሎችን ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አንስተዋል። በማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ያላቸው ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶችም ለዜጎች አፋጣኝ የፍትሕ ምላሽ በመስጠት ለዘላቂ ሰላምና እርቅ ገንቢ ሚና እየተወጡ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታትም በኢትዮጵያ ዕውቅና የተሰጣቸው የግጭት መፍቻ የማህበረሰብ ዕሴቶች ከሶስት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ጉዳዮች መስተናገዳቸውን አስረድተዋል። በጉባኤውም የአፍሪካዊያንን ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዕሴቶች ከመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት ጋር ለማናበብ መፍትሔ አመላካች ልምድና ተሞክሮዎች እንደተገኙበት ተናግረዋል።
የሹዋሊድ ምሽት ሐረር እንደ ጨረቃና እንደ ከዋክብት በሐረሪዎች ውብ ባህል፣ በልዩ ዜማና ትዕይንት የምትደምቅበት ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Mar 26, 2026 51
አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 17 /2018 ( ኢዜአ)፦የሹዋሊድ ምሽት ሐረር እንደ ጨረቃና እንደ ከዋክብት በሐረሪዎች ውብ ባህል፣ በልዩ ዜማና ትዕይንት የምትደምቅበት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን ለሹዋሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የሹዋሊድ ምሽት ሐረር እንደ ጨረቃና እንደ ከዋክብት በሐረሪዎች ውብ ባህል፣ በልዩ ዜማና ትዕይንት የምትደምቅበት ነው። በዓሉ ከባህላዊ ሥነ ሥርዓትነቱ ባለፈ፣ የጥንታዊቷ ጀጎል የታሪክ ዐሻራ፣ የሕዝቦች የአብሮነት መድረክና የኢትዮጵያ የባህል ብዝኃነት ማሳያ ነው። ሹዋሊድ የማኅበራዊ ትሥሥር ድልድይ ነው። ቂም በቀል የሚሻርበት፣ በወጣቱና በአረጋውያን መካከል ያለው የትውልድ ሠንሰለት በምርቃትና በምክር የሚታደስበት፣ እንዲሁም የአብሮነትና የመቻቻል ዕሴቶቻችን በደመቀ ሁኔታ የሚታዩበት ልዩ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው። መንግሥታችን ለሀገራዊ ቅርሶችና ለቱባ ባህላዊ እሴቶች ጥበቃ ልዩ ትኩረት የሰጠው፣ እንደ ሹዋሊድ ያሉ ቅርሶቻችን የቱሪስት መስሕብና የሀገራዊ አንድነታችን ምሰሶ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ጭምር ዕውቅናን ያገኘው ሹዋሊድ፣ የሐረርን ብቻ ሳይሆን የሁላችንንም እንግዳ ተቀባይነትና የከበረ ዕሴት ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና አለው። በድጋሚ ለሐረሪ ሕዝብና ለከተማዋ ነዋሪዎች በሙሉ እንኳን ለሹዋሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የ’አዲስ መሶብ’ ዲጂታል የአንድ ማዕከላት የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ ብልሹ አሰራርን አስቀርተዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 26, 2026 77
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018(ኢዜአ)፦የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ዲጂታል ማዕከላት የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ ብልሹ አሰራርና ሙስናን ማስቀረታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ 4ኛውን የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከላት አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በማስቀረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጡ 240 የአገልግሎት አይነቶችም በዲጂታል ሥርዓት እየተሰጡ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶችንም በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በማስገባት ተገልጋዮች ያለአንዳች እንግልት የሚገለገሉበትን ምቹ ምኅዳር መፍጠር እንደተቻላ አንስተዋል። የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከላትም የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ በማሳደግ ብልሹ አሰራርና ሙስናን ማስቀረት ማስቻሉን አስረድተዋል። በቀጣይም ዜጎች በያሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ተንቀሳቃሽ የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ በሁሉም መስክ በለውጥ ምህዋር ውስጥ ናት ብለዋል። በዚህም የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከላት አስተማማኝ የኃይልና የኔትወርክ አቅርቦት እንዲኖራቸው በማድረግ የዜጎችን የአገልግሎት ፍላጎት በጥራት እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል። የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር)፤ በክፍለ ከተማው ተገንብቶ የተመረቀው የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የታጠቀ ማዕከል ነው ብለዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል
Mar 26, 2026 37
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ ሰብሳቢ ረዳት ዣንግ ሊንግሊንግ ገለጹ። "ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ ናት" በሚል መሪ ሀሳብ ኢንቨስት በኢትዮጵያ' ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ፎረም ላይ ለመሳተፍ የመጡት የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሙዚየም ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያና ቻይና የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ ሰብሳቢ ረዳት ዣንግ ሊንግሊንግ በዚሁ ወቅት፤የሰው ዘር መገኛ የሆነችውን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሙዚየም በመመልከታቸው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸዋል። በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ዘመናዊና የአፍሪካ የውበት ማዕከል ማድረጉን ያደነቁት ሰብሳቢዋ፣ በከተማዋ የታየው ለውጥ እጅግ አስደናቂ መሆኑን ጠቁመዋል። የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑን ገልጸው፤ በርካታ ቻይናውያን በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ እንደሚገኙና ኮሚቴውም ለዚህ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል:: በቀጣይም ኮሚቴው ስለ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ ለቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ሰፊ ዕድል መፍጠሩም ተናግረዋል። መንግስት የቻይና ባለሀብቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ የፈጠረው ምቹ ሁኔታና እያደረገ ያለው ጥሪ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ሌላኛው የፊልም ዳይሬክተሩ ሱን ካይካይ በበኩሉ፤ በኢትዮጵያ በሚቆይበት ጊዜ በካሜራው የቀረጻቸውን ምስሎች በማሰባሰብ ወደ ሀገሩ ሲመለስ ዘጋቢ ፊልም ለማዘጋጀት ማቀዱን ገለጿል። ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው እንቅስቃሴ የተመለከተው የከተማዋ ውበትና ፅዳት እጅግ አስደንቆታል። በቻይና ሄንግዲያን ከተማ የኢትዮጵያን ቡና በማስተዋወቅ ላይ የምትገኘው አርቲስት ሃኦ ሊፒንግ፣ የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነትና የትብብር ኮሚቴ በቤጂንግ በሚያዘጋጃቸው የኢንቨስትመንት ፎረሞች አማካኝነት ስለ ኢትዮጵያ የተሻለ እውቀት ማግኘቷን ገልጻች። አርቲስቷ ኢትዮጵያ የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን የቡናም መገኛ መሆኗን ካወቀች በኋላ ቡናውን እጅግ በመውደዷ በማስተዋወቅ ስራው ላይ በንቃት እየተሳተፈች እንደምትገኝም ጠቁማለች። ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር በአካል ተገኝታ በመጎብኘቷም የተሰማትን ታላቅ ደስታ ገልጻለች። በቱሪዝም ሚኒስቴር የማይስ ቱሪዝም ሽያጭ ዴስክ ኃላፊ ብዙዓለም ጌቱ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚዬም የአብዛኛው የሰው ዘር ቅሪተ አካል መገኛ በመሆኑ በዓለም ደረጃ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። ጎብኚዎችና ኢንቨስተሮች እንዲህ ያሉ የኢትዮጵያን ቀዳሚነት የሚያሳዩ ስፍራዎችን መመልከታቸው ስለ ሀገሪቷ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ትልቅ በር እንደሚከፍትም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ላለው ብርቱ ጥረት እውቅና ልሰጥ እወዳለሁ-ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር)
Mar 26, 2026 70
አዲስ አበባ፤መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ላለው ብርቱ ጥረት እውቅና እንደሚሰጡ የድርጅቱ ዳይሬክተር ጀነራል ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር) ገለጹ። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) የሚኒስትሮች ስብሰባ (MC14) ዛሬ በካሜሮን ያውንዴ ይካሄዳል። በሚኒስትሮች ስብሰባው ላይ የድርጅቱ 166 አባል ሀገራት የንግድ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ ነው። የዓለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር 22 ሀገራት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። አንዳንድ ሀገራት አባል ለመሆን ለአስርት ዓመታት ጥረት ማድረጋቸውንና ሌሎች ሀገራት በቅርቡ ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን አመልክተዋል። ከ22 ሀገራት በተጨማሪ የፋሮ ደሴቶች አባል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበች አዲስ ሀገር መሆኗን ጠቁመው፥ጥያቄው ለድርጅቱ አጠቃላይ ምክር ቤት ገና አለመታየቱን ጠቁመዋል። የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን አድካሚ፣ብርቱ ጥረት እና ጽናት የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ አባል ለመሆን እየጣሩ ያሉ ሀገራት ለጠንካራ ስራቸው እና ትዕግስታቸው እውቅና መስጠት እወዳለሁ ብለዋል። ዳይሬክተ ጀነራሏ ባደረጉት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት በስብሰባው ላይ እየተሳተፈ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ እውቅና ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ እና ኡዝቤኪስታን እ.አ.አ በ2026 የድርጅቱ አባል እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) የሚኒስትሮች ስብስባ (MC14) እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2026 የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድር ለማጠናቀቅ አቅዳ እየሰራች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን 7ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እ.ኤ.አ በኤፕሪል ወር 2026 ለማካሄድ ኢትዮጵያ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው
Mar 26, 2026 58
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ። በዞኑ ቶኬ ኩታዬ ወረዳ የዞኑና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ በተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፣ በ32 ሄክታር መሬት ላይ የሙዝ ችግኝ ተከላ ተጀምሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ እንደገለጹት፤ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የፍራፍሬ ምርትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማቅረብ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች ሰፋፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። የፍራፍሬ ልማቱ በክረምት ዝናብ ብቻ ሳይወሰን በበጋ መስኖም ጭምር በስፋት እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ዓመትም በበጋ መስኖ ወደ 16 ሚሊዮን የሚጠጋ የሙዝ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ፣ እስካሁን በተከናወነው ሥራም ከ100 ሺህ በላይ የሙዝ ችግኝ በ63 ሄክታር መሬት ላይ መተከሉን አስረድተዋል። የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዋዬሳ አላሙ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ በበጋ መስኖ 472 ሄክታር መሬት በሙዝ ምርት ለመሸፈን መታቀዱን ገልጸዋል። የእስካሁኑን ሂደት ከተመለከትን አበረታች ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዕቅዱን ለማሳካት ከወረዳውና ከዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤቶች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የወረዳው አርሶ አደሮች፤ በሙዝ ልማት ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ግንዛቤ ከግብርና ጽሕፈት ቤት ማግኘታቸውንና ከጥራጥሬ ሰብሎች ጎን ለጎን ሙዝ ማልማት መጀመራቸውን ተናግረዋል። የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር ደረጄ ገላልቻ፤ ቀደም ሲል በአካባቢያቸው የሙዝ ምርት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም፣ አሁን ግን ከባለሙያዎች ባገኙት ሥልጠና መሠረት ከሌሎች ሰብሎች በተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማምረት ማቀዳቸውን ገልጸዋል። ሌላው አርሶ አደር ወይዘሮ ዳዊ ጉተታ በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ያመርቱ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን መንግሥት ባመቻቸው ዕድል በመጠቀም በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ሙዝን በክላስተር በማልማት በዓመት ሁለት ጊዜ ለማምረት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት
Mar 26, 2026 67
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በኋላ የታዛቢነት (Observer) ደረጃን አገኝታለች። እ.ኤ.አ በ2006 የውጭ ንግድ ፖሊሲዋን የሚገልጽ ሰነድ ለድርጅቱ አቅርባለች። ሰነዱ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ የወጪና ገቢ ንግድ ሕጎች፣ የቀረጥ፣ ከቀረጥ ውጭ ያሉ የንግድ ገደቦች፣ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ እና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ እና በዓለም ንግድ ድርጅት መካከል የመጀመሪያው የድርድር ምዕራፍ የተጀመረው እ.አ.አ በ2008 ነው። ከእ.አ.አ 2008 እስከ 2012 በቆየው የቴክኒክ ድርድር ሶስት የስራ ቡድን ስብስባዎች ተካሂደዋል። በዚህ ወቅት የነበረው ድርድር በዋናነት ኢትዮጵያ ስለ ንግድ ሥርዓቷ ማብራሪያ የምትሰጥባቸው እንጂ፣ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘት አልቻሉም። ከእ.አ.አ 2012 እስከ 2019 የሁለቱ ወገኖች ድርድር ተቋርጦ ነበር፤ ለሰባት ዓመታት እንዲቋረጥ ያደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ይነሳሉ። በወቅቱ ስልጣን የነበረው የኢህአዴግ መንግስት "የገበያ ውድቀት" አለ ብሎ ያምን ነበር። ስለዚህም እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም እና ኢነርጂ ያሉ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች በመንግስት እጅ መቆየት አለባቸው የሚል አቋም ነበረው። ይህ የመንግስት ጽንሰ ሀሳብ ድርጅቱ የተለያዩ ዘርፎች ለውጭ ክፍት መደረግ አለባቸው ከሚለው አቋም ጋር የሚጣጣም አልነበረም። በዓለም ንግድ ድርጅት የተጠየቁ የንግድ ስርዓትን የማዘመን ስራዎች በሚፈለገው መልኩ አለመሄዳቸውም ለድርድሩ መቆም እንደ ምክንያትነት ይነሳል። የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር በድጋሚ ነፍስ ዘርቷል። መንግስት በተለያዩ ዘርፎች የወሰዳቸው ጠንካራ የንግድ እና ኢኮኖሚ እርምጃዎች ድርድሩ በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀጥል አድርጓታል። መንግስት እንደ ቴሌኮም፣ ባንክ እና ሎጅቲክስ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉ በድርጅቱ እንደ ትልቅ ለውጥ የታየ ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን ሕጎች ከድርጅቱ ህጎች ጋር የማጣጣም ስራም ተከናውኗል። ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደርጎበት ዘመናዊ የንግድ አይነቶች የተካተቱ ሲሆኑ፤ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ መቋቋም የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ላይ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ኢትዮጵያ የሸቀጦች ታሪፍ ቅናሽ ሰነዷን አሻሽላ አቅርባለች። ይህም ኢትዮጵያ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች የምትጥለው ቀረጥ በምን ያህል መጠንና በስንት ዓመት ውስጥ እንደሚቀንስ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገባችውን ቃል በተግባር ያሳየችበት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኢትዮጵያ በተናጠል እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ካናዳ ካሉ ሀገራት እና ከአውሮፓ ህብረት ጋር የገበያ ተደራሽነት ድርድር እያደረገች ነው። በተደረጉት የተናጥል ድርድሮች ላይም ለኢትዮጵያ አባልነት ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከአዕምሯዊ ንብረት ጋር በተያያዘ የፈጠራ ውጤቶችን፣ የንግድ ምልክቶችን እና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሕግና ተቋም መገንባት ላይ ትኩረት ተደርጓል። የጉምሩክ አሰራር የሸቀጦችን ፍሰት ለማሳለጥ የዲጂታል ጉምሩክ አሰራርን የማስፋፋት ስራ በመንግስት በኩል ተከናውኗል። 14ኛው የዓለም የንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብስባ ከመጋቢት 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካሜሮን ያውንዴ መካሄድ ጀምሯል። በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ያውንዴ ገብቷል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ (ዶ/ር) ጋር ያደረጉት ውይይትም በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውይይቱ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አባል አገራት ከ1200 በላይ ለሚሆኑ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቷንና ከ419 በላይ የሕግና የፖሊሲ ይዘቶችን ማሳወቋን ጠቁመዋል። የያውንዴው ስብስባ ለኢትዮጵያ የአባልነት ጉዞ የፖለቲካ ድጋፍን ለማሰባሰብ ያስችላታል። በቅርቡ የድርጅቱ አባል ከሆኑ የአፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት ጋር የቴክኒክ እና የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግም ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል። የያውንዴው ውይይት ኢትዮጵያ በቴክኒክ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ደረጃም ለድርድር ዝግጁ መሆኗን የምታሳይበት ነው። የዓለም የንግድ ድርጅት እ.አ.አ በ1995 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫው ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ነው።ድርጅቱ 166 አባል ሀገራት አሉት። አባል ሀገራቱ የዓለምን 98 በመቶ የንግድ ልውውጥን እንደሚሸፍኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ንግድ ድርጅት በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው አቅምና ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ድርጅቱ ራሱ ገንዘብ የሚያበድር ባንክ ባይሆንም፣ የዓለምን የንግድ “የጨዋታ ሕግ" በመቅረጽ ረገድ ያለው ሚና ትልቅ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል መሆኗ የገበያ እድሏ እንዲሰፋ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ምርቶች በ160+ አባል አገራት ገበያ ውስጥ ያለ አድሎና በዝቅተኛ ታሪፍ እንዲገቡ ዕድል ይሰጣል። ይህ በተለይም ለግብርና ውጤቶችና ለጨርቃጨርቅ ምርቶች ትልቅ በር ይከፍታል። የኢትዮጵያ አባል መሆን ሀገሪቷ ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎችን እንደምታከብር ማረጋገጫ ስለሚሆን፤ ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጨምር ያደርጋል። ኢትዮጵያ አባል መሆኗ ከሌሎች አገራት ጋር የንግድ አለመግባባቶች ቢገጥሟት፣ በድርጅቱ የክርክር መፍቻ መድረክ አማካኝነት መብቷን ማስከበር ትችላለች። ኢትዮጵያ የንግድ አቅሟን ለመገንባት የሚያግዙ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ከድርጅቱ ማግኘት ትችላለች። ኢትዮጵያ በያዘችው ፍጥነት እና ቁርጠኝነት ከቀጠለች እ.አ.አ 2026 የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድሯን የማጠናቀቅ እድሏ ሰፊ ነው። የድርድሩ መጠናቀቅ ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጽደቅ እና የአገር ውስጥ ህጎችን ከድርጅቱ ሕግ ጋር የማጣጣም ስራዎችን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፍ ለሚከናወኑ ስራዎች በር ይከፍታል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል የመሆን ውጥኗ ከ23 ዓመታት በኋላ እውን ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ድርድሩም ወደ መደምደሚያው ምዕራፍ ደርሷል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የመንግስት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ ለማድረግ እያገዘ ነው
Mar 25, 2026 90
ባህር ዳር፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የመንግስት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለመስጠት እያስቻለ መሆኑን የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በብሔራዊ ደረጃ የሚያገኙበት ሕጋዊና መሠረታዊ የመታወቂያ ዓይነት መሆኑም ይታወቃል። የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ለኢዜአ እንዳሉት፤ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዜጎች በየደረጃው ፈጣንና ፍትኃዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እያስቻለ ነው ። በተለይም መታወቂያውን ከባንክና ሌሎች አሰራሮች ጋር በማስተሳሰር ወጥ የሆኑ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በፍትሃዊነት ለማቅረብ እያገዘ መሆኑን ጠቅሰዋል። ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በክልሉ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከማስቻሉ ባሻገር ህገ- ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የራሱ ድርሻ እንዳለውም ጠቅሰዋል። በተያዘው ዓመትም ከ4 ሚሊዮን የሚልቁ ዜጎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ መቻሉንም ነው ያመለከቱት። ፋይዳ የዜጎች ትክክለኛ ማንነት የሚገልፅ መሆኑን አመልክተው ደሕንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከጅማ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ አገልግሎት አግኝተናል
Mar 25, 2026 83
ጅማ፤መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፡- የጅማ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ ለአቅመ ደካሞችም እፎይታን መስጠቱን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ማዕከሉ ስራ ከጀመረ ስድስት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን ነዋሪዎች ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ማዕከል በማግኘታቸው ጊዜና ገንዘባቸውን መቆጠብ ችለዋል። ኢዜአ ካነጋገራቸው የከተማው ተገልጋዮች መካከል አቶ ኑሪ የሱፍ፤ የውኃ እና የመብራት ክፍያዎችን ለመክፈል ከዚህ ቀደም ቀናትን ይወስድባቸው እንደነበር አስታውሰዋል። እሁን ላይ ግን በከተማው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚፈልጉትን ክፍያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ለነዚህ አገልግሎቶች ሲያወጡ የነበሩትን የትራንስፖርት እና ተጨማሪ ወጪዎች ማስቀረታቸውንም ይገልጻሉ። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ሙክታር ኢብራሂም ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ለመሰል አገልግሎት ወደተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በየቀኑ ይመላለሱ እንደነበር ተናግረው አሁን በግማሽ ቀን ውስጥ ተጠናቆልኛል ብለዋል። የጅማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት ከ84 ሺህ በላይ አገልግሎቶችን መስጠቱን የተናገሩት ደግሞ የማዕከሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ ሰለሞን ናቸው። ወደ ማዕከሉ 25 ሴክተሮች የገቡ ሲሆን በሴክተሮቹ 135 አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን ጠቅሰው 103 ሠራተኞች ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም አንስተዋል። ከዚህ በተጨማሪም አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን ያማከለ ምቹ አገልግሎትም እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች ወደ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ቀርበው ከማገልገል በተጨማሪ ልዩ የሊፍት አገልግሎት መዘጋጀቱንም ገልጸዋል። በቀጣይ በከተማዋ በሚገኙ ቀበሌዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት ይበልጥ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቅረብ ታቅዷል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም የማዕከሉን አገልግሎት ተንቀሳቃሽ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አቶ አብዲ ተናግረዋል።
የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ ይሆናል
Mar 24, 2026 264
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል አገልግሎት እስከ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተደራሽ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል የተገልጋዮችን እንግልት በማስቀረት ውጤታማነትን እያረጋገጠ ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት የልደታ ቅርንጫፍን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፈጣን የህዝብ አገልግሎት በዜጎች እና በመንግሥት መካከል ያለውን መተማመን ያጎለብታል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ዘርፉን ለማዘመንና ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ በርካታ ጥረቶችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከነዚህ ጥረቶችና ተነሳሽነቶች መካከል የአዲስ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንዱ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በዚህም በርካታ ብልሹ አሰራሮችንና አላስፈላጊ የደንበኛ ምልልሶችን በማስቀረት ስር-ነቀል ለውጥ ማምጣት መቻሉን አመላክተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከላት የህዝቦችን የጊዜ እና የገንዘብ ብክነት ትርጉም ባለው መልኩ እንዳስቀሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በተገነቡ የ'አዲስ መሶብ' ዲጂታል የአንድ ማዕከላት ከ120 ሺህ በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ አመላክተዋል፡፡ እነዚህ ደንበኞች በሰጡት አስተያየት መሰረት የደንበኞች እርካታ 98 በመቶ መድረስ መቻሉ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡ በተያዘው ወር ብቻ ተጨማሪ ሶስት የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከላት ለመገንባት ታስቦ ወደ ተግባር መገባቱን ያመላከቱት ከንቲባዋ፤ እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስም የከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ አንድ አሰባስቧል ብለዋል፡፡ በ18 ተቋማት እና በ107 አገልግሎቶች ስራ የጀመረው የ'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን ላይ የተቋማትን ቁጥር ወደ 22 እና የአገልግሎቶችን ቁጥር ደግሞ ወደ 140 ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቃው ማዕከል የክፍለ ከተማችንን አገልግሎት አሰጣጥ እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ነው ያሉት ደግሞ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ልዕልቲ ግደይ ናቸው፡፡
የኮደርስ ስልጠና መውሰዳችን ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት ከማግኘት ባለፈ በዘርፉ ብቁ ተወዳዳሪ መሆን አስችሎናል
Mar 24, 2026 112
መቀሌ፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ የኮደርስ ስልጠና መውሰዳችን ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት ከማግኘት ባለፈ በዘርፉ ብቁ ተወዳዳሪ እንድንሆን አስችሎናል ሲሉ በመቀሌ ከተማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ተናገሩ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተመቻቸው የአምስት ሚሊየን የኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና በተለይም ወጣቶች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነው ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን የሚያሳድግ መሆኑ ይታወቃል። የስልጠናው ዓላማ በዘርፉ የዜጎችን አቅም ከመገንባት ባለፈ ኢትዮጵያ በዘርፉ ልማት የጀመረችው እድገትና ማንሰራራት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርግም ነው። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ስልጠናውን እየወሰዱ ከራሳቸው አልፈው ለሀገራቸው የዲጂታል ልማት ስትራቴጂ ትግበራ አሻራቸውን እያኖሩ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ስልጠናውን የወሰዱ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና በመውሰዳችን ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት ከማግኘት ባለፈ በዘርፉ ብቁ ተወዳዳሪ መሆን አስችሎናል ብለዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡ ወጣቶች መካከል ወጣት አኸዛ ወልደጊወርጊስ፤ የኮደርስ ስልጠና በመውሰድ በዘርፉ የተሻለ ክህሎትና እውቀት ያገኘችበት መልካም እድል መሆኑን ገልፃለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ በመሆን ከራስ ተጠቃሚነት አልፎ በዲጂታል የአገልገሎት ዘርፍ ጥራትና ፍጥነት ያለው አገልግሎት ለመስጠትም ወሳኝ መሆኑን ተናግራለች። ስልጠናውን ከወሰዱ ወጣቶች መካከል ሰሎሞን ገብረመድህን እና ጸጋአብ ገብረእግዛብሄር፤ የኮደርስ ስልጠናው በተለይም ለወጣቶች መልካም እድል ይዞ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ስልጠናውን በመውሰዳቸው በዘርፉ ብቁ ተወዳዳሪ እና የስራ እድል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በተግባር አይተነዋል ያሉት ወጣቶቹ ሌሎችም ጊዜ ሳያባክኑ እድሉን እንዲጠቀሙበት መክረዋል። የኮደርስ ስልጠናው የዳታ ሳይንስ፣ ዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስና አንድሮይድ የማበልጸግ እና ሌሎች ተያያዥ ዕውቀቶችን ማግኘት የሚያስችል መሆኑ ይታወቃል።
ስፖርት
ቱርክዬ ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች
Mar 26, 2026 31
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቱርክዬ ሮማንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን ኢስታንቡል በሚገኘው ቱርፓስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርዲ ካዲኦግሉ በ53ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ቱርክዬ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች። ውጤቱን ተከትሎ ቱርክዬ ወደ ጥሎ ማለፉ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ አልፋለች። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከስሎቫኪያ እና ኮሶቮ አሸናፊ ጋር መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ትጫወታለች። የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ ጥሎ ማለፍ ቀሪ ጨዋታዎች ማምሻውን መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ። በጥሎ ማለፉ የሚያልፉ አራት ሀገራት አስቀድመው በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫ ያለፉ 12 የአውሮፓ ሀገራትን ይቀላቀላሉ።
23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ይካሄዳል
Mar 26, 2026 53
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ከመጋቢት 20 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሐረር ከተማ እንደሚካሄድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ ውድድሩንና ፌስቲቫሉን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት ለስፖርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት በአዲሱ የስፖርት ፖሊሲ አማካኝነት የባህል ስፖርቶችን ለማልማት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሁነቱ የኢትዮጵያን ህብረ ብሄራዊ አንድነት፣ ብዝሃነት እና አብሮነት የሚተዋወቅበት መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ህይወት መሐመድ በበኩላቸው ውድድሩና ፌስቲቫሉ ህብረተሰቡን በባህል ስፖርት ተሳታፊና ተጠቃሚ ከማድረግም ባሻገር የባህል ስፖርትን ማህበረሰብ አቀፍ የማድረግ አላማ እንዳለው ገልጸዋል። በውድድርና ፌስቲቫሉ ከአፍሪካ ባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን የተጋበዙ የክብር እንግዶች እንደሚታደሙበት ጠቁመዋል። በ11 የስፖርት አይነት በሚካሄደው ውድድርና ፌስቲቫል ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ1500 በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ። ሁነቱ የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። ውድድሩና ፌስቲቫሉ "የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል
Mar 26, 2026 65
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ነገ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ታደርጋለች። ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው በሚደረግበት ኤል አብዲ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ማምሻውን አከናውኗል። ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት ልምምዳቸውን ሰርተው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኤል ጀዲዳ ኤል አብዲ ስታዲየም ይከናወናል።
ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
Mar 26, 2026 46
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአርባምንጭ ከተማዋ መድሃኒት ዓለሙ በ79ኛው ደቂቃ በራሷ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች። የድሬዳዋ ከተማዋ መዓዛ አብደላ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች። ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉንም አስመዝግቧል። በውድድር ዓመቱ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 10ኛ ደረጃን ይዟል። አርባምንጭ ከተማ ባለፉት 14 የሊጉ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ይርጋጨፌ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 2፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፈዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ 21ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በቱርክዬ በሚከናወነው የዩኤፋ የወዳጅነት ዋንጫ ዝግጅት እና ተሳትፎ ያደርጋል። በብሔራዊ ቡድኑ ተሳትፎ ምክንያት የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
አካባቢ ጥበቃ
የበልግ ዝናብ ስርጭት ለግብርና ምርታማነትና ለእንስሳት መኖ አቅርቦት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው-የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Mar 26, 2026 69
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018(ኢዜአ)፦የዘንድሮው የበልግ ዝናብ ስርጭት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚከናወኑ የግብርና ስራዎች ስኬታማነትና ለእንስሳት መኖ አቅርቦት መሻሻል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ተቋሙ የአየር ጸባይ አዝማሚያዎችን፣አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን በወቅቱ ለማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው ተቋማት የማድረስ ስራውን በልዩ ትኩረት እየከወነ ይገኛል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ባለው የበልግ ወቅትም፣ በተለይም በሀገሪቱ ደቡባዊ አጋማሽ የዓመታዊ ዝናብ መጠኑ እስከ 55 በመቶ የሚሸፈንበት ዋነኛ ወቅት ነው ብለዋል። በ2018 ዓ.ም የበልግ ወቅት አብዛኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም በ55 የሚደርሱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ35 እስከ 148 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መመዝገቡን ገልጸዋል። ባለፉት ቀናት የታየው ተስፋ ሰጪ የዝናብ ስርጭት ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ጠቅሰው፥ ለበልግ እርሻ ዝግጅትና ለዘር ስራ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለሰውና ለእንስሳት የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማሻሻሉን እንዲሁም የእንስሳት መኖ ልማትን በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ ድርሻ መኖሩ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። በመጪዎቹ ሚያዝያና ግንቦት ወራትም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የበልግ ዝናብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በተለይም በደቡብና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ዝናቡ ዘግይቶ የሚወጣ በመሆኑ ለግብርናውና ለአካባቢ ጥበቃ ስራው ተጨማሪ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል። ይሁን እንጂ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ወደ ጎርፍ አደጋ ሊቀየር ስለሚችል ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
በጣና ሐይቅ ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት አዲስ የንቅናቄ ዘመቻ ተጀመረ
Mar 25, 2026 96
ባህር ዳር ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ በጣና ሐይቅ ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት አዲስ የንቅናቄ ዘመቻ ተጀመረ። የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሐይቁ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነውን የእምቦጭ አረም በተደመረ አቅም ለማስወገድ የትብብር ጥሪ አቅርቧል። ከጣና ሃይቅና አካባቢው የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ የሚያስችል የንቅናቄ መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ ሽንብጥ ቀበሌ የጣና ዳርቻ በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ፤ በጣና ሃይቅ ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የእምቦጭ አረም በተባበረ ክንድ በማስወገድ የሃይቁን ህልውና መጠበቅ ይገባናል ብለዋል። አረሙን ለማጥፋት በሰው ኃይል እና በማሽን እንዲሁም አጠቃላይ የሕዝቡን ጠንካራ ተሳትፎ ማእከል ያደረገ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል። የእምቦጭ አረም በቀላሉ የመስፋፋትና የማንሰራራት ባሕሪ ያለው በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ዘመቻ እና የክትትል ስራ የሚያስፈልግ ስለመሆኑም አፅኖት ሰጥተዋል። በመሆኑም በሐይቁ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነውን የእምቦጭ አረም በተደመረ አቅም ለማስወገድ እንዘጋጅ በማለት ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል። የመከላከል ሥራው በሰው ኃይልና በማሽነሪ በመታገዝ እንዲሁም ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በባዮሎጂካል ዘዴ እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ማሳካት በሚያስችል መልኩ ዝግጅት እየተደረገ ነው
Mar 25, 2026 102
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ማሳካት በሚያስችል መልኩ ውጤታማ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ(ዶ/ር) ገለጹ። አስተባባሪው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ዘንድሮ የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር፣ የመጀመርያው ምዕራፍ ማጠቃለያ ዓመት በመሆኑ ዝግጅቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዚህም በዘንድሮው መርሃ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ በላይ ለመትከል እቅድ ተይዞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋት የፍራፍሬ ችግኞችን የማስፋት፣ የሀገር በቀል ዝርያዎችን ቁጥር ከፍ የማድረግ ብሎም የእፅዋት አይነት ስብጥር በሰፊው እየተሰራበት መሆኑንም ገልፀዋል። በበጋው ወቅት የተከላ ቦታዎችን የመለየት፣ የተለዩ ቦታዎች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ የማከናወን፣ ከየአካባቢው አየር ንብረት ጋር የሚጣጣሙ ችግኞችን የማፍላትና የተለዩ ቦታዎች ላይ ካርታ የማዘጋጀት ስራ በስፋት መከናወኑን ነው ያስታወቁት። በዚህም በክልሎች እስካሁን 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለችግኝ ተከላ የሚውሉ ቦታዎችን መለየታቸውን ጠቅሰው እስካሁን ከ110 ሺህ በላይ ችግኝ ጣቢያዎች ወደ ስራ ገብተው ችግኞች እያፈሉ ይገኛሉ ብለዋል። በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል በእቅድ መያዙን ተናግረው እስካሁን 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ችግኝ ዝግጁ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ በቀሪው ጊዜ የእንክብካቤ ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቅሰው ጉድጓድ የማዘጋጀት ስራዎችን ጨምሮ ሌሎችም እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረውን የክረምት ዝናብ ብቻ የመጠበቅ ልምድ መቀየሩን ጠቁመው ይህም ችግኞች ረጅም የዝናብ ወቅት እንዲያገኙ በማድረግ የፅድቀት መጠናቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምረው አስረድተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አሁን ላይ የህዝቡ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው በቀጣይም የዜጎችን የባለቤትነት ስሜት የማሳደግ እና የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በክልሉ ከ458 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ተከናውኗል-ቢሮው
Mar 24, 2026 111
ባህርዳር ፤መጋቢት 15 /2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ወራት በአርሶ አደሩ ተሳትፎ በ458 ሺህ 794 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ መከናወኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ ። የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ በዘንድሮ የበጋ ወራት ከዘጠኝ ሺህ የሚበልጡ ተፋሰሶችን መሰረት ያደረገ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ተካሂዷል። በዚህም ከ458 ሺህ 794 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የማሳና የጋራ ላይ ዕርከን ስራዎችን መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ከ91 ሺህ ሄክታር በላይ የተራቆቱና የተጎዱ ተራራማ ቦታዎችን በመከለል ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ተጠብቀው መልሰው እንዲያገግሙ መደረጉንም አመልክተዋል ። በተጨማሪም ከ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚበልጡ የተለያዩ የውሃ ማስረጊያ ስትራክቸሮች መከናወናቸውን ጠቁመው የውሃ ማፋሰሻና መቀልበሻ ቦዮች ግንባታ ስራዎችም መካሄዳቸውን ተናግረዋል ። አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በየጊዜው እየተረዳ በመምጣቱ ከዕቅድ በላይ ስራውን መፈፀም እንደተቻለም አስታውቀዋል። በመጭው የክረምት ወቅት በበጋ ወራት የተከናወነውን የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በስነ-ህይወታዊ ዘዴ ለማጠናከር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዓለሙ ይግዛው እንዳሉት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ መስራት ከተጀመረ ወዲህ የተራቆቱ መሬቶች ደን መልበስ ጀምረዋል ። የእርሻ መሬቶችም የአፈር ለምነታቸው እንዲጨምርና የሰብል ምርታማነት እየተሻሻለ እንዲመጣ ማስቻሉንም ገልፀዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በየዓመቱ እየሰራን እንገኛለን ያሉት ደግሞ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓንጓ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ሙሉነህ ይግዛው ናቸው። ባለፉት ዓመታት በሰራነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተፋሰሶች በማገገማቸው ለእንስሳት ዋነኛ የመኖ ምንጭ ሆነዋል ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 123
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 239
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 245
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 224
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3266
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 348
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 403
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 381
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 21, 2026 721
ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ባሳለፍነው ሳምንት … ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል የነዳጅ ብክነትን ለመቀነስ ምን ዓይነት ብልኀት መጠቀም ይመከራል? ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም ጂ (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። #ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 21, 2026 193
በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ (በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት ስትወጥን የቀደመ ወረቷን፤ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን ይዛ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን ቀረጸች። ይህን ዕውን ለማድረግ ስትዘይድም የሕዝቧን የፋይናንስ፣ የዕውቀት እና የጉልበት ዐቅም በመደመር መጠቀምን ሻተች። በዚህም መሠረት በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶችን አስመዘገበች። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኢዜአ ዐይን …! ✍️ ገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የወንዞች ዳርቻዎችና መናፈሻዎችን ለማልማት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ገበታ ለሸገር ኢኒሼቲቭ፤ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን የሚሸፍን ነው። የሚሠራበትን ገንዘብ ለማሰባሰብም የገበታ ለሸገር የእራት ምሽት በዳግማዊ አጼ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ተዘጋጀ፤ ባለሀብቶች፣ የንግድ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ድርጅቶችም ተሳትፈዋል። ኢኒሼቲቩ አንድነት ፓርክን ጨምሮ የእንጦጦ መናፈሻንና ሌሎች የተለያዩ መዲናዋን ያስዋቡ በረከቶችን ችሯል። ይህም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በማልማት በርካታ ቱሪስቶችን ከመሳብ ባለፈ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ለምጣኔ ሃብት ዕድገት ጉልኅ አስተዋጽዖ አበርክቷል። ለዚህ ሁሉ ስኬት መነሻ የሆኑትን ጉዳዮች ያስጀመሩትም ያስፈጸሙትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገበታ ለሸገር የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ ገበታ ለሀገር የተሰኘውን ኢኒሼቲቭ አበሠሩ። ✍️ ገበታ ለሀገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻን ለማልማት ያለመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። ይህም በአዲስ አበባ ከተሠራው ገበታ ለሸገር ቀጥሎ የተከናወነ ነው። በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የገበታ ለሀገር ዓላማ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ የቱሪስት መስኅብ የሚሆኑና የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ አካባቢዎችን ማዘጋጀት መሆኑን አስገንዝበዋል። በገበታ ለሀገር መርሐ-ግብር ባለሀብቶችን ጨምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህን ለማሳካት የሀገሪቱን ባለሃብቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ መርሐ-ግብሮች የተሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ውጤታማ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገበታ ለሀገር ውጥን፤ እንደ ሀላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና የተፈጥሮ ሀብቶችን አጉልተው በማሳየት ይበል ያሰኘ ውጤት አስመዝግቧል። ✍️ ገበታ ለትውልድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም ገበታ ለትውልድ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ይህም ተጨማሪ መዳረሻዎች እንዲለሙ አስችሏል። በዚህ ኢኒሼቲቭ ሥር በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች የመዳረሻ ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕዳሴ ግድብ አካባቢና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎች እየለሙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የገበታ ለትውልድ አካል የሆነውን የሸበሌ ሪዞርት በይፋ መርቀዋል። እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት እንደሆነም ተገልጿል። ሎጎ ሐይቅ ሪዞርትም ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረቀ ሲሆን፤ ለጎብኚዎች የማይረሳ ትውስታን የሚሰጥ እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኖ ቀርቧል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቋሚ ምስክርም ነው ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት። የቱሪዝም ልማቱን ከተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ፣ ከዘላቂነትና ከአካታችነት ጋር በማቀናጀት፤ ሪዞርቱ የወሎ ሕዝብ ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ዕሴት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅበት ሰፊ ገበታ ሆኖ ያገለግላል። ታሪካዊ ቦታዎችና የሀገር መገለጫ መሠረተ-ልማቶች ብሔራዊ ትርክቶችንም የሚገነቡ ናቸው። በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመስጠት ብሎም በየአካባቢው የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። የቱሪዝም ዘርፉን ለማጎልበት፣ ብዙ ጎብኚዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው። እንዲሁም ነባር ቅርሶችን በማደስና በመጠገን ለትውልድ ለማሻገር ደማቅ ዐሻራ አሳርፈዋል። በሌላ በኩል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት የመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ ዐሳይተዋል። ባለሀብቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም ሀገራቸውን የመሥራት ሚና እንደሚጠበቅባቸው አሥተምረዋል። ቱሪዝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ብሎም በርካታ የሥራ ዕድሎች በመፍጠር በኢኮኖሚው ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግሥት ላስጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ነው። ከአምስቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎችም አንዱ የሆነው ለዚህ ነው። መሠረተ-ልማቶች ከሚገነቡባቸው ጡቦች ባለፈ የነገን ሀገራዊ ማንነት፣ ራዕይ እና መዳረሻን ይበይናሉ። ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ እንኳንም ታሰቡ፤ እንኳንም ተሳኩ። ይህ ባይሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መዳረሻ ባላገኘች ነበር።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 14, 2026 1400
ከየካቲት 29 - መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ኢትዮጵያ • ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተመልክተዋል። ማዕከሉ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል • በተመሳሳይ በድሬዳዋ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማኅበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። • የድሬዳዋ የኮሪደር ልማትንም የጎበኙ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬዳዋ ዕውን እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል። • ከድሬዳዋ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር መርሐ-ግብር ያከናወኑት ባለፈው ሳምንት ነው። • በድሬዳዋ የሚገኘውን እመርታ ቤተ-መጻሕፍትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል። ቤተ-መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ ለ1 ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። • በሳምንቱ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ሥራ ተመልክተዋል። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ፤ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ ዕቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል። • የቁንድዶ ተራሮችንም ጎብኝተዋል። • በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከልም ተመልክተዋል። ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር ዐቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል። • በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ናሲኦል ዋሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። • ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር አካሂደዋል። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሹመት መስጠታቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌ/ጄኔራል አሥራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድን እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች አድርገው የሾሙት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካቸው ጋር በጅቡቲ የቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጊሌ በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝታቸውን ቀጥለውም ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚሁ ወቅትም ከፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ✍️ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጋር መምከራቸው • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል። በዚሁ ወቅትም የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት የመደመር መንግሥት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል። • ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዳይሬክተር ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) ጋር በዲጂታል ልማት ያለ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ እና ትብብራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይም የታደሙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምኅሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ኅያው የሕይወት ስንቅ ነው ብለዋል። ✍️ የመሬት ናዳና ጎርፍ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ • ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ የዜጎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል። ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። • ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ያስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። እስካሁንም በአደጋው ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስና መልሶ ለማቋቋም ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገኑ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ✍ ምክር ቤቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማወጁ • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማስመልከት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ዐውጇል። በዚህም መሠረት ትናንት የጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ዐበይት_ጉዳዮች #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 437
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3741
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2515
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8306
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6791
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ተከፍሎ የማያልቅ የኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ውለታ አለብን - የመናዊያን ፍልሰተኞች
Mar 19, 2026 2334
በዮሐንስ ደርበው ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ ለተገፉ፣ ጥላ ከለላ ለሚሹ፣ ለተከዙና ለታረዙ የሀገራት ዜጎች መጠጊያ ናት። የኢትዮጵያን ቸርነትም ከተጠለሉባት እንግዶቿ በላይ ምሥክር የለም። የኢትዮጵያን ደጅ የረገጡ ሁሉ በቆይታቸው ለተደረገላቸው ሁሉ ‘ውለታችንን በምን እንክፈል’ ሲሉ ይደመጣሉ። ከአያሌ ሀገራት በመልከ ብዙ ቀውሶች ሳቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ የቆሰሉ ልባቸው ታክሞ፣ ዕንባቸው ታብሶና ሕይወታቸው ታድሶ ኑራቸውን አደላድለዋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በዚህም ከአፍሪካም ሆነ ከተቀረው ክፍላተ ዓለም የጦርነትና ግጭት ጥላ ያጠላባቸውና ሰላምን የተጠሙ የቀጣናው ሀገራት ዜጎች ኢትዮጵያን ሲሹ ማየት የተለመደ ነው። የየመን ዜጎች ለዚህ ማሳያ ናቸው። ኢብቲሳም ኻሊድ እና መሰል የመናዊያን ከየመን የእርስ በርስ ግጭት በኋላ የኢትዮጵያን ደጅ ረግጠው ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፍ የተድላ ኑሮ እየኖሩ ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረገችው ኢብቲሳም እንደምትለው፤ በየመን አለመረጋጋት በፈጠረው ጠባሳ እርሷና መሰሎቿ ለፍልሰት ተዳርገዋል። ለዚህ ደግሞ ምርጫቸው ኢትዮጵያ ሆነች። ወደ ኢትዮጵያም መጥተው የሀገሬው ፊት ሳይኮሰኩሳቸው በፍቅር እንደተቀበሏቸው ትናገራለች። በዚህም ዛሬ የመናዊያን ተስፋቸው ለምልሞ፣ ሕይወታቸው ሠምሮ ኢትዮጵያን እንደ እናት ቆጥረው እየኖሩ ስለመሆኑ ትናገራለች። ከ11 ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ኢብቲሳም፤ በወቅቱ ቀኑ እንደጨለመባት ታወሳለች። ሰው ከቤቱ፣ ከወገኑ…ከሀገሩ ወጥቶ ወዴት ይሄዳል? በወቅቱ የነበረውን ጭንቀት ማየልም ታስታውሳለች። አሁን ግን ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ በጎነት ዐውርታ አትጠግብም። “አሁን ፍልሰተኛ አይደለሁም፤ ያለሁት በሁለተኛዋ ሀገሬ ኢትዮጵያ ነውና” ትላለች። እንዲህ ባለው የረመዳን ወቅት ደግሞ የፍልሰተኞች ሁሉ ሰብሳቢ ናት። “ሁሉም ከእነ ቤተሰቡ ወደ ቤቷ እየመጣ ያፈጥራል። በዚህም በፍልሰት እንደመጡ ሳይሆን ቤተሰባዊነት ይሰማቸዋል። ከየመን፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ አፍጋኒስታን፣ ኮንጎሊዝ (DRC) ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሁሉ ሰብሰብ ብለው የኢፍጣር መርሐ-ግብርን እንደሚያከናውኑም ታነሳለች። በዚህ ላይ ኢትዮጵያውያን ብርታት ናቸው ትላለች፤ ሁሌም ‘አይዟችሁ፣ በርቱ፣ ነገ ጥሩ ይሆናል’ እያሉ ያበረቱናል፤ ክብርና ፍቅር ይሰጡናል ስትልም ታስረዳለች። የኢትዮጵያንና ሕዝቧን ውለታ እንዴት መክፈል ይቻላል? ኢትዮጵያን ሀገራችን ብለን ነው እየጠራን ያለነው። እንደ እንግዳ እንደ ፍልሰተኛ እራሳችንን አናስብም፤ እንደሀገሬው አንዱ እንጅ፤ የምትለው ኢብቲሳም፤ ኢትዮጵያን እንዴት ብዬ ነው የምገልጻት? እናትን መግለጽ ይቻላል? እናትን መግለጽ ከተቻለ ኢትዮጵያን በዚያ ልክ መግለጽ ይቻል ይሆናል፤ እኔ ግን አይቻለኝም በማለት ትናገራለች። “የዛሬ 11 ዓመት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት፤ የሰው ፊት አልገረፈኝም፤ ፊቱን ያዞረብኝም የለም። ኢትዮጵያውያን ደግ፣ ቅንና ደስ የምትሉ ሕዝቦች ናችሁ” ስትል ስሜቷን ትገልጻለች። ኢትዮጵያ እንደ ኒውዮርክ እያደገች ነው፤ እኛ ከመጣን በኋላ እንኳን በርካታ ለውጦች ዕያየን ነው ስትልም የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት አንስታለች። ለአብነትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በርካታ ነገሮች መስተካከላቸውን በመጠቆም፤ ለዚህም የኢትዮጵያን መንግሥት እናመሠግናለን ብላለች። ከፍልሰተኞች ጋር በተያያዘ በርካታ ሕጎች በመሻሻላቸው፤ ዛሬ በራሴ ስም ንግድ ፈቃድ አውጥቼ እየሠራሁ ነው፤ በጨረታዎችም እወዳደራለሁ፤ የበጎ አድራጎት ማኅበር መመሥረትና መምራት ችያለሁ። እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣቸው ለውጦች ናቸው ብላለች። በምድረ ኢትዮጵያ ያለን ሁሉ ለኢትዮጵያ ዕድገት እንተባበር ስትልም ጥሪ አቅርባለች። ህልማችን ከኢትዮጵያውያን ጎን ሆነን ኢትዮጵያን በማሳደግ ጥረት በንቃት መሳተፍ ነው፤ የኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ውለታ መመለስ አለብን ስትልም ትናገራለች። በኢብቲሳም ኻሊድ ቤት በተዘጋጀ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ የተሳተፈው አነስ አንዋር ለኢዜአ እንዳለው፤ ኢትዮጵያ በሯን ከፍታ አስጠልላዋለች። ከተለያዩ ሀገራት ብንመጣም ሰብሰብ ብለን ስናፈጥር፤ ማኅበራዊና ቤተሰባዊነታችን ይጠናክራል ብሏል። ብዙ ፈተናዎችን ዐይተናል፤ አልፈናቸው እዚህ ደርሰናል የሚለው አነስ፤ “ኢትዮጵያዊነት መልካምነት ነው” ሕዝቡ በክብር ነው የተቀበለን፤ ከምሥጋና ውጭ ምን ማለት እንችላለን? አመሥጋኞች ነን ሲል ገልጿል። እየተማርኩ ነው፤ ትምህርቴን አጠናቅቄ በሙያዬ በመሠማራት ኢትዮጵያን ማገዝ እፈልጋለሁ ብሏል። ራኪያ አሊ አብዱረዛቅ በበኩሏ በፈረንጆቹ 2011 ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷን ታወሳለች። ትምህርቷንም ተከታትላ መመረቋን ገልጻ፤ ቤተሰብ አፍርታ ሁለት ልጆችንም ወልዳ እየኖረች ነው። ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሀገሬ ናት፤ ሰላም አላት፤ ሕዝቡም ሰው አክባሪ ነው። ለኢትዮጵያ የተሻለ ልማት ደግሞ መተባበር ወሳኝ ስለሆነ ለዚሁ እንትጋ ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች። #ፍልሰተኞች #ኢዜአ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 658
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ። እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል። የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል። በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል። ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል። በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡