ቀጥታ፡

ብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን አድርጓል

ቀብሪ ደሃር፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እውን ማድረጉን በፓርቲው የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የዐቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አብዱራህማን አህመድ ገለጹ።

ፓርቲው በሶማሌ ክልል ቆረሃይ ዞን ቀብሪ ደሃር ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቅ የማጠቃለያ መርሐ-ግብር አካሂዷል።

አቶ አብዱራህማን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እንዲገነባ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ነው።




ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ በሀገር ጉዳይ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እውን ያደረገ መሆኑን አንስተው፤ ዜጎች ፍትሐዊና እኩል የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አቅዶ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ከዚህ በፊት በሀገሪቱ የተፈጠሩትን ችግሮች በማረምና ስብራቶችን በመጠገን ዕቅዶችን በመንደፍ የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በተለይም የክልሉ ሕዝብ ከሀገሪቱ ፖለቲካ የዳር ተመልካችነት ወጥቶ እኩል ተሳትፎ በማድረግ የልማት ተጠቃሚነቱ የተረጋገጠበት ወቅት መሆኑን አረጋግጠዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውንም ለአብነት አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም