ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ

ቦዲቲ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በካርዳችን የነገዋ ኢትዮጵያን ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የቦዲቲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ።




አስተያየታቸው ለኢዜአ ከሰጡት መካከል አቶ ተመስገን ጫማ እንዳሉት፤ በወሰዱት ካርድ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተስፋ ብሩህ ሊያደርግ ይችላል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዕለቱን እየጠበቁ ነው።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ መሳተፍ ሳይችሉ መቆየታቸውን የተናገሩት ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ዘነበች ጋንአሞ፤ አሁን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰዳቸው ዕድለኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል።




በወሰዱት ካርድ ለሀገር ሰላምና ልማት መጠናከር የተሻለ የሚሠራውን ፓርቲ ለመምረጥ እንደተዘጋጁም አስረድተዋል።

አቶ ባሩድ በርገነ እና መምህር ታምራት ዮናስ በበኩላቸው፤ ምርጫው ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በንቃት ለመሳተፍ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

 

በምርጫ ክርክሩ በተከታተልነው መሰረት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻለ ፖሊሲና ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ አማራጭ ያለውን ፓርቲ በመምረጥ ለነገይቱ ኢትዮጵያ መጽናት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።




ዜጎች ለምርጫው ሰላማዊነትና ፍትሐዊነት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸውም መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም