ቀጥታ፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቀሌ 70 እንደርታን በመለያ ምት አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ አምርቷል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመለያ ምት 7 ለ 6 በማሸነፍ ለፍጻሜ ያለፈ ሲሆን ዋንጫውን ለማንሳት ከሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ነገ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም