ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ 17 ዓመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን የቡሩንዲ አቻውን 2ለ1 አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ ያደረገውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ 2ለ1 አሸንፏል።

አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለቡድኑ የማሸነፊያ ሁለት ግቦችን ሊዲያ እያሱ ማስቆጠር ችላለች።

ኢትዮጵያ በ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ደቡብ ሱዳንን በድምር ውጤት 8 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወቃል።

ተጋጣሚዋ ብሩንዲ በመጀመሪያው ዙር ማላዊን በአጠቃላይ ውጤት 4 ለ 2 አሸፋለች።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታው ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቡጁምቡራ ላይ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች ለመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ትጫወታለች።

10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም