ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018(ኢዜአ)፦ ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተፈጥሮ እውነት ከታሪክ ክብር ጋር በተዋሃደባት፣ በጣና ሐይቅና በዓባይ ወንዝ በታጀበችው የውበት ማማዋ ባሕር ዳር ገብተናል ብለዋል።
በመልዕክታቸውም ባሕር ዳር ከተማ በልማት ጎዳና ላይ የምታሳየው መነቃቃት የነገ ተስፋችንን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ፣ ፍቅርና አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ለተደረገልን ደማቅ አቀባበል ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉና ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ በጸሎትና በምርቃታቸው ላልተለዩን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለመላው የባሕር ዳር ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።