ቀጥታ፡

ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ዲላን ፔጅ በሀረር የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን ይጎበኛል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ዲላን ፔጅ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን ለመጎብኘት ሀረር ከተማ ገብቷል።

ከዓለም ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ የሆነው እንግሊዛዊው ዲላን ፔጅ በሀረር በሚኖረው ጉብኝትም በሀረር ኢኮ ፓርክ የጅብ ትርዒት ከመታደም ባለፈ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ተዘዋውሮ ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል።


 

ከዲላን ፔጅ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መገኘታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም