ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል
May 6, 2026 29
ደብረ ብርሃን ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የመንግስት ሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ። የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጋር በመተባበር የሚያካሂዱት የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ስራ ዛሬ ተጀምሯል። የመምሪያ ኃላፊው ተወካይ አቶ ተሾመ ሸዋየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤የመንግስት ሰራተኛውን መረጃ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት እየተካሔደ ያለውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለማፋጠን የሚያስችል ነው። በተለይም የሰራተኛውን መረጃ በአግባቡ በመሰብሰብ፣ በመሰነድና ለአገልግሎት በማዋል ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። ዲጂታል የመረጃ አሰባሰብ ስራው የሰራተኛውን መበትና ጥቅሙን በማስከበር የስራ ተነሳሽነቱን ለማሳደግ የሚያስችል እንደሆነም አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት በዞኑ የሚገኙት 98 በመቶ የሚደርሱ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል መታወቂያ ያወጡ መሆኑ ለተጀመረው ምዝገባ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ነው የገለጹት። ከመንግስት ሰራተኞቹ መካከል አቶ አሰገደው ማሞ እንደገለጹት፤ የሰራተኛው መረጃ ዲጂታላይዝ መደረጉ የፋይል ጥራትንና የመረጃ ብክነትን ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል። በተጨማሪም ህገ-ወጥ የሰራተኛ ዝውውር፣ ቅጥርንና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። ሌላኛዋ የመንግስት ሰራተኛ ወይዘሮ መዓዛ ግርማ በበኩላቸው፤በዘመናዊ መንገድ እንዲሰነድ የተደረገው የሰራተኛው መረጃ በተገቢው መንገድ የስራ ገበታው ላይ ተገኝቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳል ነው ያሉት። ይህም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። ዛሬ በዞኑና በወረዳዎች የተጀመረው የመረጃ ማጣራትና የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የአካል ማረጋገጥ ስራ እስከ መጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል
May 6, 2026 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠንና የኢንቨስትመንት ስኬትን በማረጋገጥ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀደም ሲል ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ስኬታማ ተግባራት ተመዝግበዋል። በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱና ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉ የዘርፉ ዕድገት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች አማካኝነት ከ4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ እንዳሉትም፣ ኤክስፖው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የዘርፉን አስተዋጽኦ ዘላቂ ለማድረግ መሰረታዊ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በተለይም በኢንቨስትመንት ረገድ ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል። ይህም የሀገሪቱን የወደፊት ኢኮኖሚ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችሉ የፋይናንስና የፖሊሲ ድጋፎች ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተተገበሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል። ኤክስፖው የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን፣ የኢንዱስትሪውን ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል ብለዋል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬን በማዳንና ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት፣ በራስ አቅም የመቆም የኢኮኖሚ አርበኝነትን እያረጋገጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን በዕውቀትና ክህሎት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትም ከተለያዩ የትምህርትና የሥልጠና ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ፍጥነትን፣ ፈጠራንና የዝላይ መርህን በመጠቀም በትንሽ ወጪ ከፍተኛ ምርት በማምረት፣ የኢንዱስትሪውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኤክስፖው አማካኝነት በርካታ አምራቾች ከግልና ከመንግሥት ተቋማት ጋር ጠንካራ የገበያ ትስስርና የሥራ ስምምነቶችን በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
በዞኑ በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው
May 6, 2026 89
ነገሌ ቦረና ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸው ተገለጸ። ብልጽግና ፓርቲ በነገሌ ቦረና ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት የለውጡ መንግስት ህዝብን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለግብርና ልማት ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም በተለይም በዞኑ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተከናወነ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በሌማት ትሩፋትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መርሀ ግብር በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል። በለውጡ መንግስት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መሰረት በማድረግ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል አሰባሳቢ ትርክት ላይ መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ ናቸው። በዞኑ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዝርጋታዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቁመዋል። ፓርቲው በሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታች ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ ልማትን ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አንስተዋል።
ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አውጥተዋል
May 6, 2026 84
ኮምቦልቻ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውን የፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ገለፁ። በኮምቦልቻ ከተማ ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አፈጻጸም ያለበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ ተካሄዷል። ዳይሬክተሩ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። መታወቂያው ለአካታች ኢኮኖሚና የፋይናንስ እድገት፣ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት፣ ህገ-ወጥነትንና ወንጀልን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንኑ ጠቀሜታ በመገንዘብም እንደ ሀገር እስካሁን ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መታወቂያውን ማውጣታቸውን ነው የተናገሩት። በ2020 ዓ.ም መታወቂያውን 115 ሚሊዮን ለሚደርሱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ነው ያመለከቱት። በዛሬው እለት የተካሔደው መድረክ አላማም እስካሁን የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በክልሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አተገባበር ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል። መታወቂያው ሀገራዊ መለያ ከመሆኑ ባሻገር የተቀላጠፈ እና ፍትሀዊ አገልግሎትን ለመስጠት፣ ወንጀልን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። መታወቂያውን ከተቋማት ጋር በማስተሳሰርና በማቀናጀት አተገባበሩን ለማሳለጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የፋይዳ መታወቂያ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። በቀጣይም ተከታታይ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲያወጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አመራሩ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት። በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች መታወቂያውን ማውጣት ችለዋል ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም ናቸው። ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲወስዱ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ አመራሩም ህብረተሰቡን በማስተባበር ጭምር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በመድረኩም የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
የአፍሪካን ትክክለኛ ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ ነው
May 6, 2026 74
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ትክክለኛ ታሪክ ለዓለም ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን የሴኔጋል እና የቤኒን የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ጉባኤውም ከሚያዚያ 29 እስከ 30/2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎችና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት መድረክም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እየከተሙ ይገኛል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ሴኔጋላዊው የይዘት ፈጣሪ ጃው ኬቹን እና ቤኒናዊቷ የዲጂታል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሬጂ ቦይዘር፤ ጉባኤው ለግንኙነትና ለልምድ ልውውጥ ወሳኝ የጋራ መድረክ ነው ብለዋል። ሴኔጋላዊው የይዘት ፈጣሪ ጃው ኬቹን፤ ጉባኤው የአፍሪካዊያንን የቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች ለዓለም ለማስተዋወቅ ድንበር ተሻጋሪ ፋይዳ እንዳለው ገልጿል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኝበትን ዕድል በማመቻቸት የአፍሪካን የዲጂታል ድምፆች በማቀራረብ የልምድ ልውውጥን እንደሚያጠናክር ተናግሯል። በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣቱም የሀገሪቱን ባህልና ዕድሎች በማየት የአህጉሪቷን የይዘት ፈጣሪዎች የእርስ በዕርስ ትስስር እንደሚያጎለብት አንስቷል። በአዲስ አበባ ለተደረገለት ደማቅ አቀባበልም ምስጋናውን አቅርቧል። ቤኒናዊቷ የዲጂታል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሬጂ ቦይዘር በበኩሏ፤ ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ጉባኤ በአፍሪካ የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር ውስጥ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን የሚያገናኝ ወሳኝ አህጉራዊ ተነሳሽነት መሆኑን ገልፃለች። ጉባኤውም ከፍተኛ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን፣ የፖሊሲ አውጪዎችንና መገናኛ ብዙኅንን በጋራ የሚያገናኝ መሆኑን ተናግራለች። የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ማህበረሰብ ማስተዋወቅ የሚያስችል የግንኙነት ሥርዓት ለመፍጠርም ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስታለች። የአፍሪካ ብርቅዬ የዲጂታል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የጋራ መድረክም የአህጉሪቷን ትክክለኛ ትርክትና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ ለማስገንዘብ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። አዲስ አበባንም የአህጉሪቱ ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚቀርጹ ውይይቶች ማዕከል ያደርጋታል።
ፖለቲካ
በዞኑ በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው
May 6, 2026 89
ነገሌ ቦረና ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸው ተገለጸ። ብልጽግና ፓርቲ በነገሌ ቦረና ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት የለውጡ መንግስት ህዝብን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለግብርና ልማት ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም በተለይም በዞኑ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተከናወነ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በሌማት ትሩፋትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መርሀ ግብር በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል። በለውጡ መንግስት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መሰረት በማድረግ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል አሰባሳቢ ትርክት ላይ መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ ናቸው። በዞኑ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዝርጋታዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቁመዋል። ፓርቲው በሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታች ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ ልማትን ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር በስልክ ተወያዩ
May 6, 2026 88
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። በውይይታቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውንም ጠቁመዋል።
በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል
May 6, 2026 94
ቦንጋ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል ሲሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን ተከትሎ የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ ተጠናቅቆ፤ ፓርቲዎች በፖሊሲና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ክርክር እያደረጉ ይገኛሉ። በፓርቲዎቹ መካከል የሚደረገው ክርክር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህዝቡ በቀጥታ እየደረሱ ነው። ይህን አስመልክተው በቦንጋ ከተማ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል ብለዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ አየለ ሀይሌ ፓርቲዎቹ በተለያዩ ጉዳዮች ለይ የሚያደርጓቸውን ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እየተከታተሉ መሆናቸውንና ባገኙት ግንዛቤ ሀገር አሻጋሪ ሀሳብ የያዘውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። ወጣት መቅደስ ከበደና መንግስቱ አለማየሁ የተባሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ ምርጫ የሀገርና የሕዝቦችን መፃኢ እድል የሚወሰን ትልቅ ኩነት በመሆኑ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ይፈልጋል ብለዋል። በተለይም ወጣቱ የወሰደውን ካርድ በአግባቡ ተጠቅሞ ነገውን የተሻለ ለማድረግ ይበጀኛል፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻግራል ያለውን ፓርቲ መምረጥ እንደሚገባው መክረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የምርጫ ክርክር በሀገራችን የዲሞክራሲ ምህዳሩ እየሰፋ መምጣቱን ማሳያ ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌው አቶ በየነ በቀለ፣ ይህም ለመራጩ ህዝብ ብዙ አማራጮችን ይዞ መምጣቱን ገልፀዋል። በክርክሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመመረጥ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ መሬት ላይ የሚያወርዱትን ሀገር አሻጋሪ ሀሳብ ጨዋነት በተመላበት መልኩ ማቅረብ እንዳለባቸውም አመልክተዋል። እርሳቸውም በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እየቀረቡ ያሉትን የምርጫ ክርክሮች እየተከታተሉ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም በመታገዝ በዕውቀት ላይ የተመሰረት ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል
May 6, 2026 144
ሮቤ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክቱን በማስተዋወቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ -ግብር በሮቤ ከተማ አካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈትበ ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር)፤ ፓርቲው በሁሉም መስኮች ባከናወናቸው ስራዎች ውጤታማ በመሆን የህዝብን ተጠቃሚነት እውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በመደመር እሳቤ ሀገራዊ ልማትንና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት ለላቀ ልማትና ስኬት እየተጋ መሆኑን ገልጸው በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። በባሌ ዞን እና አካባቢው በለውጡ ዓመታት የአካባቢውን እምቅ ሃብቶች በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት መሰራቱን አስታውሰው ልማቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውንም አስታውሰው የሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ኡመር፣ የጎባ-በርበሬ-ደሎ መና-ብታታ፣ የሮቤ-አጋርፋ- አርሲ የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለአብነት ጠቅሰዋል። በመሆኑም በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሀኪም አልይ፤ በዞኑ በተለይም የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም የስንዴ ልማት እመርታዊ ማንሰራራት የታየበት መሆኑን አንስተው በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችና አዳዲስ ኢንሸቲቮችም ስኬታማ መሆን ተችሏል ብለዋል።
በለውጡ ዓመታት ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካ መስኮች ንቁ ተሳታፊ የሆኑበት ዕድል ተፈጥሯል
May 6, 2026 83
ጂንካ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በለውጡ ዓመታት ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካ መስኮች ንቁ ተሳታፊ የሆኑበት ዕድል መፈጠሩን የጂንካ ከተማ ሴቶች ተናገሩ። በለውጡ ዓመታት በብልጽግና ፓርቲና በመንግሥት በተለያዩ መስኮች ለተመዘገቡ አኩሪ ድሎች እውቅና የሰጠና የከተማው ሴቶች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል። በድጋፍ ሰልፉ የታደሙ ሴቶችም ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር ለመጡ ተጨባጭ ውጤቶች ዕውቅና የሰጡ መፈክሮችን አሰምተዋል። በድጋፍ ሰልፉ የታደሙት የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ አዳነች ሉሉ፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንና ለእዚህም ዕውቅና ለመስጠት በድጋፍ ሰልፉ ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካው መስክ ንቁ ተሳታፊ የየሆኑበት እድል ተፈጥሯል ያሉት ወይዘሮ አዳነች፣ ለዚህም ተጠቃሚነታችን በማደጉ ዕውቅና እንሰጣለን ብለዋል። ሌላዋ የሰልፉ ታዳሚ ወጣት ራሄል አበራ በበኩሏ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነትና በመንግሥት በተከናወኑ ሥራዎች በተለያዩ ዘርፎች አንፀባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል። በተለይ የሴቶች እኩልነት እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በየደረጃው መረጋገጡን ጠቅሳ፣ ሴቶች በየመስኩ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ሀገር የሚመሩበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል። ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ወሰንየለሽ ካሳ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ ናቸው። በእነዚህ ዓመታት ሴቶች በቁልፍ ቦታዎች ጭምር ተመድበው የመምራት አቅማቸውን ማሳየታቸውን ገልጸው፣ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነትም እያደገ መጥቷል ብለዋል። ከዚህ አኳያ የመጡ ተጨባጭ ለውጦች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለጹት ወይዘሮ ወሰንየለሽ፣ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች እውቅና ለመስጠትና ድጋፋቸውን ለመግለጽ በሰልፉ ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል። በጂንካ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳም አካሂደዋል።
የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር እድገት እንዲረጋገጥ ሠርቷል
May 5, 2026 293
ይርጋጨፌ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፡- የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሠ መሥተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ። በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ የብልጸግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ተካሂዷል። አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ብልጽግና የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል። የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን ገልጸው፤ ብልጽግናን በመምረጥ ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባ አመልክተዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግሥት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቁመዋል። በዞኑ የቡና ልማትን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት አማካይ ምርታማነትን በሔክታር 11 ነጥብ 9 ኩንታል እንዲሁም በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ 20 ኩንታል ማድረስ መቻሉንም አንስተዋል።
ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና የልማት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራች ነው
May 5, 2026 332
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና የልማት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራች መሆኑን በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ገለጹ። ኢትዮጵያና ፊንላንድ ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የዲፕሎማሲ እና የልማት አጋርነት እንዳላቸው የገለጹት አምባሳደሯ፣ በበርካታ መስኮች ውጤታማ ተግባራት ሲያከናወኑ መቆየታቸውንም ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል በተለይም በትምህርት፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት፣ በገጠር ልማትና በንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ላይ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ ትብብር መደረጉን በአብነት ጠቅሰዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፊንላንድ በመሬት አስተዳደርና በዲጂታል የመሬት ምዝገባ ስራዎች ውጤታማ ትብብር ስታደርግ መቆየቷን ጠቁመዋል። ፊንላንድ አሁን ካለው የልማት ትብብር ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ጠንካራ የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ግብ የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ፣ የፊንላንዱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኖኪያ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር እያከናወነ ያለው የጋራ ተግባር ለዚህ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። በትምህርትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። ፊንላንድ በሁሉም ረገድ የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችንና ስታርትአፖችን ለማበረታታት የያዘችው አቅጣጫ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አምባሳደሯ ጠቁመዋል። ፊንላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ የስታርትአፕ እንቅስቃሴ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንደምትመደብ በማንሳት፣ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ወጣቶችና የፈጠራ ባለቤቶች ለማገናኘት መታቀዱን ገልጸዋል። ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም ብክነትን መቀነስና የአካባቢ ጥበቃን ማረጋገጥ ላይ የተሰማሩ አዳዲስ ንግዶች በኢትዮጵያ ብቅ እያሉ መሆኑን አምባሳደሯ ገልጸው፤ ይህ ዘርፍ ለቀጣዩ የኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።
ፖለቲካ
በዞኑ በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው
May 6, 2026 89
ነገሌ ቦረና ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸው ተገለጸ። ብልጽግና ፓርቲ በነገሌ ቦረና ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት የለውጡ መንግስት ህዝብን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለግብርና ልማት ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም በተለይም በዞኑ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተከናወነ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል። በሌማት ትሩፋትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መርሀ ግብር በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል። በለውጡ መንግስት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መሰረት በማድረግ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል አሰባሳቢ ትርክት ላይ መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ ናቸው። በዞኑ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዝርጋታዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቁመዋል። ፓርቲው በሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታች ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ ልማትን ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር በስልክ ተወያዩ
May 6, 2026 88
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። በውይይታቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውንም ጠቁመዋል።
በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል
May 6, 2026 94
ቦንጋ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል ሲሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 24 ቀን እንዲካሄድ መወሰኑን ተከትሎ የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ ተጠናቅቆ፤ ፓርቲዎች በፖሊሲና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ክርክር እያደረጉ ይገኛሉ። በፓርቲዎቹ መካከል የሚደረገው ክርክር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህዝቡ በቀጥታ እየደረሱ ነው። ይህን አስመልክተው በቦንጋ ከተማ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተደረገ ያለው የምርጫ ክርክር በእውቀት ላይ ተመስርተን ደምፅ ለመስጠት ያግዘናል ብለዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ አየለ ሀይሌ ፓርቲዎቹ በተለያዩ ጉዳዮች ለይ የሚያደርጓቸውን ክርክሮች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እየተከታተሉ መሆናቸውንና ባገኙት ግንዛቤ ሀገር አሻጋሪ ሀሳብ የያዘውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። ወጣት መቅደስ ከበደና መንግስቱ አለማየሁ የተባሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ ምርጫ የሀገርና የሕዝቦችን መፃኢ እድል የሚወሰን ትልቅ ኩነት በመሆኑ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ይፈልጋል ብለዋል። በተለይም ወጣቱ የወሰደውን ካርድ በአግባቡ ተጠቅሞ ነገውን የተሻለ ለማድረግ ይበጀኛል፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻግራል ያለውን ፓርቲ መምረጥ እንደሚገባው መክረዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የምርጫ ክርክር በሀገራችን የዲሞክራሲ ምህዳሩ እየሰፋ መምጣቱን ማሳያ ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌው አቶ በየነ በቀለ፣ ይህም ለመራጩ ህዝብ ብዙ አማራጮችን ይዞ መምጣቱን ገልፀዋል። በክርክሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመመረጥ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ መሬት ላይ የሚያወርዱትን ሀገር አሻጋሪ ሀሳብ ጨዋነት በተመላበት መልኩ ማቅረብ እንዳለባቸውም አመልክተዋል። እርሳቸውም በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እየቀረቡ ያሉትን የምርጫ ክርክሮች እየተከታተሉ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም በመታገዝ በዕውቀት ላይ የተመሰረት ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል
May 6, 2026 144
ሮቤ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክቱን በማስተዋወቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ -ግብር በሮቤ ከተማ አካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈትበ ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር)፤ ፓርቲው በሁሉም መስኮች ባከናወናቸው ስራዎች ውጤታማ በመሆን የህዝብን ተጠቃሚነት እውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በመደመር እሳቤ ሀገራዊ ልማትንና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት ለላቀ ልማትና ስኬት እየተጋ መሆኑን ገልጸው በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። በባሌ ዞን እና አካባቢው በለውጡ ዓመታት የአካባቢውን እምቅ ሃብቶች በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት መሰራቱን አስታውሰው ልማቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውንም አስታውሰው የሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ኡመር፣ የጎባ-በርበሬ-ደሎ መና-ብታታ፣ የሮቤ-አጋርፋ- አርሲ የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለአብነት ጠቅሰዋል። በመሆኑም በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሀኪም አልይ፤ በዞኑ በተለይም የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም የስንዴ ልማት እመርታዊ ማንሰራራት የታየበት መሆኑን አንስተው በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችና አዳዲስ ኢንሸቲቮችም ስኬታማ መሆን ተችሏል ብለዋል።
በለውጡ ዓመታት ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካ መስኮች ንቁ ተሳታፊ የሆኑበት ዕድል ተፈጥሯል
May 6, 2026 83
ጂንካ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በለውጡ ዓመታት ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካ መስኮች ንቁ ተሳታፊ የሆኑበት ዕድል መፈጠሩን የጂንካ ከተማ ሴቶች ተናገሩ። በለውጡ ዓመታት በብልጽግና ፓርቲና በመንግሥት በተለያዩ መስኮች ለተመዘገቡ አኩሪ ድሎች እውቅና የሰጠና የከተማው ሴቶች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ ዛሬ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል። በድጋፍ ሰልፉ የታደሙ ሴቶችም ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር ለመጡ ተጨባጭ ውጤቶች ዕውቅና የሰጡ መፈክሮችን አሰምተዋል። በድጋፍ ሰልፉ የታደሙት የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ አዳነች ሉሉ፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንና ለእዚህም ዕውቅና ለመስጠት በድጋፍ ሰልፉ ላይ መሳተፋቸውን ገልጸዋል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሴቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካው መስክ ንቁ ተሳታፊ የየሆኑበት እድል ተፈጥሯል ያሉት ወይዘሮ አዳነች፣ ለዚህም ተጠቃሚነታችን በማደጉ ዕውቅና እንሰጣለን ብለዋል። ሌላዋ የሰልፉ ታዳሚ ወጣት ራሄል አበራ በበኩሏ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነትና በመንግሥት በተከናወኑ ሥራዎች በተለያዩ ዘርፎች አንፀባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል። በተለይ የሴቶች እኩልነት እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በየደረጃው መረጋገጡን ጠቅሳ፣ ሴቶች በየመስኩ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ሀገር የሚመሩበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል። ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ወሰንየለሽ ካሳ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ ናቸው። በእነዚህ ዓመታት ሴቶች በቁልፍ ቦታዎች ጭምር ተመድበው የመምራት አቅማቸውን ማሳየታቸውን ገልጸው፣ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነትም እያደገ መጥቷል ብለዋል። ከዚህ አኳያ የመጡ ተጨባጭ ለውጦች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የገለጹት ወይዘሮ ወሰንየለሽ፣ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች እውቅና ለመስጠትና ድጋፋቸውን ለመግለጽ በሰልፉ ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል። በጂንካ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳም አካሂደዋል።
የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር እድገት እንዲረጋገጥ ሠርቷል
May 5, 2026 293
ይርጋጨፌ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፡- የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሠ መሥተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ። በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ የብልጸግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ተካሂዷል። አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ብልጽግና የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል። የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን ገልጸው፤ ብልጽግናን በመምረጥ ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባ አመልክተዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግሥት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቁመዋል። በዞኑ የቡና ልማትን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት አማካይ ምርታማነትን በሔክታር 11 ነጥብ 9 ኩንታል እንዲሁም በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ 20 ኩንታል ማድረስ መቻሉንም አንስተዋል።
ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና የልማት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራች ነው
May 5, 2026 332
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና የልማት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራች መሆኑን በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ገለጹ። ኢትዮጵያና ፊንላንድ ለረጅም ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የዲፕሎማሲ እና የልማት አጋርነት እንዳላቸው የገለጹት አምባሳደሯ፣ በበርካታ መስኮች ውጤታማ ተግባራት ሲያከናወኑ መቆየታቸውንም ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል በተለይም በትምህርት፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት፣ በገጠር ልማትና በንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ላይ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ ትብብር መደረጉን በአብነት ጠቅሰዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፊንላንድ በመሬት አስተዳደርና በዲጂታል የመሬት ምዝገባ ስራዎች ውጤታማ ትብብር ስታደርግ መቆየቷን ጠቁመዋል። ፊንላንድ አሁን ካለው የልማት ትብብር ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ጠንካራ የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ለማሳደግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ግብ የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሯ፣ የፊንላንዱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኖኪያ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር እያከናወነ ያለው የጋራ ተግባር ለዚህ ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። በትምህርትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። ፊንላንድ በሁሉም ረገድ የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችንና ስታርትአፖችን ለማበረታታት የያዘችው አቅጣጫ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አምባሳደሯ ጠቁመዋል። ፊንላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠንካራ የስታርትአፕ እንቅስቃሴ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንደምትመደብ በማንሳት፣ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ወጣቶችና የፈጠራ ባለቤቶች ለማገናኘት መታቀዱን ገልጸዋል። ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም ብክነትን መቀነስና የአካባቢ ጥበቃን ማረጋገጥ ላይ የተሰማሩ አዳዲስ ንግዶች በኢትዮጵያ ብቅ እያሉ መሆኑን አምባሳደሯ ገልጸው፤ ይህ ዘርፍ ለቀጣዩ የኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።
ማህበራዊ
የሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል
May 6, 2026 29
ደብረ ብርሃን ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የመንግስት ሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥና ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ። የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጋር በመተባበር የሚያካሂዱት የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ስራ ዛሬ ተጀምሯል። የመምሪያ ኃላፊው ተወካይ አቶ ተሾመ ሸዋየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤የመንግስት ሰራተኛውን መረጃ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት እየተካሔደ ያለውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለማፋጠን የሚያስችል ነው። በተለይም የሰራተኛውን መረጃ በአግባቡ በመሰብሰብ፣ በመሰነድና ለአገልግሎት በማዋል ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል። ዲጂታል የመረጃ አሰባሰብ ስራው የሰራተኛውን መበትና ጥቅሙን በማስከበር የስራ ተነሳሽነቱን ለማሳደግ የሚያስችል እንደሆነም አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት በዞኑ የሚገኙት 98 በመቶ የሚደርሱ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል መታወቂያ ያወጡ መሆኑ ለተጀመረው ምዝገባ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩንም ነው የገለጹት። ከመንግስት ሰራተኞቹ መካከል አቶ አሰገደው ማሞ እንደገለጹት፤ የሰራተኛው መረጃ ዲጂታላይዝ መደረጉ የፋይል ጥራትንና የመረጃ ብክነትን ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል። በተጨማሪም ህገ-ወጥ የሰራተኛ ዝውውር፣ ቅጥርንና ሌሎች ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል። ሌላኛዋ የመንግስት ሰራተኛ ወይዘሮ መዓዛ ግርማ በበኩላቸው፤በዘመናዊ መንገድ እንዲሰነድ የተደረገው የሰራተኛው መረጃ በተገቢው መንገድ የስራ ገበታው ላይ ተገኝቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳል ነው ያሉት። ይህም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። ዛሬ በዞኑና በወረዳዎች የተጀመረው የመረጃ ማጣራትና የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የአካል ማረጋገጥ ስራ እስከ መጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
የአፍሪካን ትክክለኛ ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ ነው
May 6, 2026 74
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ትክክለኛ ታሪክ ለዓለም ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጠንካራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን የሴኔጋል እና የቤኒን የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ጉባኤውም ከሚያዚያ 29 እስከ 30/2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎችና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት መድረክም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እየከተሙ ይገኛል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ሴኔጋላዊው የይዘት ፈጣሪ ጃው ኬቹን እና ቤኒናዊቷ የዲጂታል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሬጂ ቦይዘር፤ ጉባኤው ለግንኙነትና ለልምድ ልውውጥ ወሳኝ የጋራ መድረክ ነው ብለዋል። ሴኔጋላዊው የይዘት ፈጣሪ ጃው ኬቹን፤ ጉባኤው የአፍሪካዊያንን የቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች ለዓለም ለማስተዋወቅ ድንበር ተሻጋሪ ፋይዳ እንዳለው ገልጿል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኝበትን ዕድል በማመቻቸት የአፍሪካን የዲጂታል ድምፆች በማቀራረብ የልምድ ልውውጥን እንደሚያጠናክር ተናግሯል። በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣቱም የሀገሪቱን ባህልና ዕድሎች በማየት የአህጉሪቷን የይዘት ፈጣሪዎች የእርስ በዕርስ ትስስር እንደሚያጎለብት አንስቷል። በአዲስ አበባ ለተደረገለት ደማቅ አቀባበልም ምስጋናውን አቅርቧል። ቤኒናዊቷ የዲጂታል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሬጂ ቦይዘር በበኩሏ፤ ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ጉባኤ በአፍሪካ የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር ውስጥ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን የሚያገናኝ ወሳኝ አህጉራዊ ተነሳሽነት መሆኑን ገልፃለች። ጉባኤውም ከፍተኛ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎችን፣ የፖሊሲ አውጪዎችንና መገናኛ ብዙኅንን በጋራ የሚያገናኝ መሆኑን ተናግራለች። የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ማህበረሰብ ማስተዋወቅ የሚያስችል የግንኙነት ሥርዓት ለመፍጠርም ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስታለች። የአፍሪካ ብርቅዬ የዲጂታል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የጋራ መድረክም የአህጉሪቷን ትክክለኛ ትርክትና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ ለማስገንዘብ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። አዲስ አበባንም የአህጉሪቱ ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚቀርጹ ውይይቶች ማዕከል ያደርጋታል።
ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን ሚና ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይጠናከራሉ
May 6, 2026 62
መልካ ቁንጡሬ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገሪቱ ያሉ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል። ዕለቱ በዋናነት የቅርሶች ጥበቃና ለትውልድ ማስተላለፍ ያለውን ፋይዳ በሚያጎሉ ሁነቶች እየታሰበ መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ ነው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት መካነ ቅርስ እየተከበረ የሚገኘው። በዓለም አቀፍ ደረጃ "የአፍሪካን ቅርሶች ማክበር፤ የነገ መሪዎችን ማብቃት" በሚል መሪ ቃል የተሰየመው ይህ ዕለት፤ በሀገራችን "የአፍሪካን ጥልቅ የሰው ልጅ ታሪክ ማክበር፤ የመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት የአርኪዮሎጂና ፓሌኦንቶሎጂ መካነ ቅርስን መጠበቅ" በሚል መሪ ቃል በድምቀት እየታሰበ ነው። በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ እንደገለጹት፤ ዕለቱን ማክበር በቅርስ ዙሪያ የወጡ ዓለም አቀፍ አዋጆችንና ደንቦችን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ አለው። ይህም በሀገራችን ያሉትን ባህላዊ እና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን ሚና ለማጎልበት የሚያግዙ ናቸው ብለዋል። በተጨማሪም የኅብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የቱሪዝም ፍሰት እንዲጨምርና ወጣቶች በቅርስ ጥበቃ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል። ዘንድሮ ቀኑ በመልካ ቁንጡሬ እንዲከበር የተመረጠው፣ መካነ ቅርሱ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 2ኛ ዓመት ለማክበርና በቅርሱ አጠባበቅና አስተዳደር ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ለመወያየት ታስቦ መሆኑም ገልጸዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፤ በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ መከበሩ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን ፋይዳ ለማስገንዘብ ይረዳል ብለዋል። በቅርሶች ላይ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች እንዲያድጉና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያለውን የቅርስ ጥበቃ ትብብር ለማጠናከር ዕድል እንደሚፈጥርም አክለዋል። የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደራራ ከተማ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በመልካ ቁንጡሬ የተገኙ የአርኪኦሎጂ እና የፓሊዮንቶሎጂ ውጤቶች ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛና የዓለም ሥልጣኔ ምንጭ መሆኗን በተጨባጭ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። ቦታው የእንስሳት ቅሪቶች፣ የጥንታዊ ሰው የእግር አሻራ እና ከድንጋይ ዘመን ጀምሮ ያለውን የሥልጣኔ ማስረጃ የያዘ በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው የገለጹት አቶ ደራራ፤ መንግሥት ለቅርሶች በሰጠው ልዩ ትኩረት መካነ ቅርሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊመዘገብ መቻሉን አስታውሰዋል። የሚመለከታቸው አካላትና መላው ማኅበረሰብ እነዚህን ቅርሶች በመጠበቅና በመንከባከብ፣ ለሀገራዊ ብልጽግናና ለትውልድ መሸጋገሪያ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ጤና ችግሮች ላይ መፍትሄ የሚያመጡ ምርምሮችን እያከናወነ ነው
May 6, 2026 104
አዳማ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ አርሲ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለአካባቢው ማህበረሰብ የጤና ችግሮች መፍትሄ የሚያመጡ ምርምሮችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በዩኒቨርሲቲው ስር የሚገኙ ሆስፒታሎችም ለአካባቢው ማህበረሰብ ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፍቃዱ ምትኩ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ የጤና ችግሮች መፍትሄ የሚያመጡ ምርምሮችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው በጤና፣ በግብርና፣ በኢንጂነሪንግና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ከንድፈ ሃሳብ ባለፈ ተግባር ተኮር ትምህርትን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በምርምር ስራዎቹ በተለይ በአካባቢው የጤና ችግሮች የሆኑትን ለይቶ የመፍትሄ አማራጮችን ከመጠቆም ባለፈ በአእምሮ ጤና፣ በጉሮሮ ካንሰር፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ጠለቅ ያሉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በስሩ ከሚገኘው የአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተጨማሪ አዲስ ያስገነባው የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል በዘንድሮ ዓመት አገልግሎት መጀመሩን አክለዋል። በአሁኑ ወቅም በስሩ የሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝድ ማድረግ መቻሉንም ነው የገለጹት። የዩኒቨርሲቲው የህክምና ዘርፍ ተማሪዎች ተግባር ተኮር ትምህርት ለመከታተልና የተለያዩ ምርምሮችን ለማከናወን በሆስፒታሎቹ ወስጥ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወቱም ነው የተናገሩት። የዩኒቨርሲቲው የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል ዳይሬክተርና የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ዶክተር ጀማል ረሻድ፤ ሆስፒታሉ የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎትን በተሟላ መልኩ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። በተለይ የማህፀን ህክምናና የወሊድ አገልግሎት እንዲሁም የህፃናት ክትባትና የጨቅላ ህፃናት ህክምና አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሆስፒታሉ 200 አልጋዎች እንዳሉት ጠቁመው ከዚህ ውስጥም 70 የሚሆኑት ለጨቅላ ህፃናት ህክምና አገልግሎት እየዋሉ መሆኑንም ተናግረዋል። ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ወዲህ በቀን በአማካይ ለ15 እናቶች የወሊድና ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ሆስፒታሎቹ ከእናቶችና ህፃናት ህክምና በተጨማሪ ሌሎች አገልግሎቶችን በዘመናዊ መልኩ እየሰጡ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል
May 6, 2026 31
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠንና የኢንቨስትመንት ስኬትን በማረጋገጥ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀደም ሲል ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ስኬታማ ተግባራት ተመዝግበዋል። በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱና ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉ የዘርፉ ዕድገት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች አማካኝነት ከ4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ እንዳሉትም፣ ኤክስፖው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የዘርፉን አስተዋጽኦ ዘላቂ ለማድረግ መሰረታዊ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በተለይም በኢንቨስትመንት ረገድ ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል። ይህም የሀገሪቱን የወደፊት ኢኮኖሚ በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችሉ የፋይናንስና የፖሊሲ ድጋፎች ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተተገበሩ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል። ኤክስፖው የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን፣ የኢንዱስትሪውን ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል ብለዋል። በተጨማሪም የውጭ ምንዛሬን በማዳንና ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት፣ በራስ አቅም የመቆም የኢኮኖሚ አርበኝነትን እያረጋገጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን በዕውቀትና ክህሎት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትም ከተለያዩ የትምህርትና የሥልጠና ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ ሰፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ፍጥነትን፣ ፈጠራንና የዝላይ መርህን በመጠቀም በትንሽ ወጪ ከፍተኛ ምርት በማምረት፣ የኢንዱስትሪውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በኤክስፖው አማካኝነት በርካታ አምራቾች ከግልና ከመንግሥት ተቋማት ጋር ጠንካራ የገበያ ትስስርና የሥራ ስምምነቶችን በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በማልማት ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማዋል ተግባራት ይጠናከራሉ
May 6, 2026 75
ደብረ ማርቆስ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የደብረ ማርቆስ ከተማን ባህል፣ ታሪክ ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላከተ። የደብረ ማርቆስ ከተማ ገጽታን የሚገነባ፣ ቅርሶቿን በማስተዋወቅ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል "ሚያዚያን በማርቆስ" የተሰኘ ፌስቲቫል ዛሬ ተካሄዷል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፤በከተማዋ የሚገኙ የመስህብ ሃብቶችና ፀጋዎች በማስተዋወቅ ህብረተሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው። የከተማዋን ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና ማህበራዊ እሴት በመጠበቅና በማልማት ለቱሪስት መስህብነት ለማዋል ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህም ቅርሶችና እሴቶች የቀድሞ ይዘታቸውን ጠብቀው ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፉ ከማድረግ ባሻገር ጎብኚዎችን ለመሳብ ያስችላል ብለዋል። ዛሬ የተካሄደው "ሚያዚያን በማርቆስ" የባህል ፌስቲቫል እና ፓናል ውይይት በከተማዋ የሚገኙ የመስህብ ሃብቶችን በመለየትና በማስተዋወቅ የሀብት ምንጭ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አእምሮ በበኩላቸው እንደገለጹት "ሚያዚያን በማርቆስ" የአካባቢውን ቱባ ባህል ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ነው። ባለፉት አራት ዓመታት ፌስቲቫሉን በማካሄድ የአካባቢውን ማህበረሰብ መስተጋብር በማጠናከርና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች ወደ አካባቢው እንዲመጡ በማድረግ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል ከቱሪዝም ልማቱ የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በፌስቲቫሉ የከተማዋና የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የባህል አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መሳተፋቸውም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የብድር አስተዳደር ላይ በተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች በዕዳ ዕፎይታ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል
May 6, 2026 130
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የብድር አስተዳደር ላይ በተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች በዕዳ ዕፎይታ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ገለጹ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያዘጋጀው ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ሉዓላዊ ፋይናንስ ፎረም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በፎረሙ መክፈቻ ላይ የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እንደተናገሩት፤ የብድር ዕዳ አስተዳደር ለማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ ለልማት ስትራቴጂና ለፖሊሲ ተዓማኒነት መሰረት ነው። በኢትዮጵያ ዕዳ አስተዳደር ላይ በተከናወኑ ወጤታማ ስራዎች የብድር ዕፎይታ ላይ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቡድን-20 የጋራ ማዕቀፍ ስር ትልቅ ምዕራፍ ላይ መድረሷን ገልጸው፤ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የብድር እፎይታ ጊዜ አግኝታለች ብለዋል። በኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠር ሁሉን አቀፍ ሪፎርም በማካሄድ ወደ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት መሸጋገር፣ የገንዘብ ፖሊሲን ማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ማሳደግ፣ በዕዳ አስተዳደር ግልጽነትን መፍጠር እንዳስቻለ ገልጸዋል፡፡ በዚህም የዋጋ ግሽበትን መቀነስ፣ የወጭ ንግድ ገቢን ማሳደግ እና የውጭ ምንዛሬ ክምችትን በማሳደግ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ተችሏል ብለዋል፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር እና የንግድ መስመሮች እንዲስተጓጎሉ ማድረጉን ጠቅሰው፤ በአፍሪካ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአፍሪካ ዘላቂነት ያለው ኢኮኖሚ ለመገንባት የብድር ወጪን መቀነስ፣ የሀገር ውስጥ እና ቀጣናዊ የፋይናንስ ገበያዎችን እና የዕዳ አስተዳደር አቅምን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡ የውጭ ፋይናንስ ጥገኝነትን ለመቀነስ የሀገር ውስጥ የምንዛሪ ቦንድ ገቢን ማሳደግ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ብድር የልማት እንቅፋት ሳይሆን የልማት መሣሪያ የሚሆኑበትን አሰራር ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በበኩላቸው፤ ዓለም አቀፋዊ የጅኦፖለቲካ ውጥረቶች የአፍሪካን የጸጥታና የንግድ ፍሰት በማስተጓጎል የሸቀጦችን ዋጋ አንሯል ብለዋል፡፡ ይሄውም የኢንቨስትመንት ፍላጎትን በመገደብና የካፒታል ዋጋን በመጨመር የአፍሪካን የኢንቨስትመንት ተመራጭነት ገድቧል ብለዋል፡፡ የዕዳ ስልቶችን ከአየር ንብረት እና ከልማት ግቦች ጋር ማጣጣም ፣ ተቋማዊና የመረጃ ምንጮችን ማጠናከር፣ የተቀናጀ የፋይናንስ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶችና የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ
May 6, 2026 68
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች እና የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየውን አራተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤክስፖ መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለጉብኝት የመጡትን እንግዶች በመቀበል፣ በኤክስፖው የቀረቡ የአምራች ኢንዱስትሪ ውጤቶችንና በንቅናቄው የተመዘገቡ ስኬቶችን አስጎብኝተዋል። በኤክስፖው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አውጥተዋል
May 6, 2026 84
ኮምቦልቻ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውን የፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ገለፁ። በኮምቦልቻ ከተማ ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ አፈጻጸም ያለበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ ተካሄዷል። ዳይሬክተሩ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለሁሉም ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። መታወቂያው ለአካታች ኢኮኖሚና የፋይናንስ እድገት፣ ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት፣ ህገ-ወጥነትንና ወንጀልን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንኑ ጠቀሜታ በመገንዘብም እንደ ሀገር እስካሁን ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መታወቂያውን ማውጣታቸውን ነው የተናገሩት። በ2020 ዓ.ም መታወቂያውን 115 ሚሊዮን ለሚደርሱ ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ነው ያመለከቱት። በዛሬው እለት የተካሔደው መድረክ አላማም እስካሁን የነበሩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በቀጣይ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለመ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በክልሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አተገባበር ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል። መታወቂያው ሀገራዊ መለያ ከመሆኑ ባሻገር የተቀላጠፈ እና ፍትሀዊ አገልግሎትን ለመስጠት፣ ወንጀልን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። መታወቂያውን ከተቋማት ጋር በማስተሳሰርና በማቀናጀት አተገባበሩን ለማሳለጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የፋይዳ መታወቂያ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያፋጥን ነው ብለዋል። በቀጣይም ተከታታይ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲያወጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አመራሩ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት። በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች መታወቂያውን ማውጣት ችለዋል ያሉት ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም ናቸው። ሁሉም ዜጎች ፋይዳ መታወቂያን እንዲወስዱ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ አመራሩም ህብረተሰቡን በማስተባበር ጭምር እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በመድረኩም የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላ ስራ ተጀመረ
May 6, 2026 72
ሐረር፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላ ስራ ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላ ስራውን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አስጀምረውታል። ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በዚሁ ጊዜ የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። በተለይም ትክክለኛ የመረጃ ግብዓት ከመስጠት አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል። የተከላ ስራው በአጭር ጊዜ እንዲከናወን የክልሉ መንግስት እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሪክተር በላቸው ፀሐይ፤ ቴክኖሎጂው መረጃን በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ተደራሽ ለማድረግ የላቀ ፋይዳ አለው ብለዋል። እንዲሁም 35 ኪሎ ሜትር ራድየስን በመሸፈን ትክክለኛ ልኬት የሚወስድና 24 ሰዓት የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ለሌሎችም መረጃን መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያመጣቸውን ውጤቶች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም ሳይንሳዊ መሠረት ያለው ትውልድ መፍጠር ይገባል
May 5, 2026 305
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ያመጣቸውን ውጤቶች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም ሳይንሳዊ መሠረት ያለው ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የበላይ ጠባቂ አቶ ደመቀ መኮንን ለኢዜአ እንዳሉት፤ መንግሥት ሳይንሳዊ ትውልድ መፍጠር የሚያስችል ሥርዓት ገቢራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለሳይንስ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ ተቋማት እንዲገነቡና በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ጉልህ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የስፔስ ሳይንስ ዘርፍ በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ አዳዲስ ሁነቶችን የሚመጥን ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ ገንቢ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን በመጥቀስ፤ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ጭምር አጀንዳ መሆን የቻለበትን አውድ ፈጥሯል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ መንግሥት ለስፔስ ሳይንስ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ የአቅም ግንባታና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ አቅሙን እያጠናከረ መሆኑን በመግለጽ፤ የእንጦጦ የጠፈር ምርምር ማዕከል (ኦብዘርቫቶሪ) ተደራጅቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንና የላሊበላን በቀጣይ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንዲሁም ተቋማትና ግለሰቦች በዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተወዳዳሪ ሆነው ለመውጣት ሳይንስ መሠረታዊ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ደመቀ፤ ህልምን ለማሳካት ሳይንስን የተመረኮዘ አገርና ማኅበረሰብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የሰው ሠራሽ አስተውሎት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መሆኑን ገልጸው፤ ሳይንስን መሠረት ባደረገው የዓለም እንቅስቃሴ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ያመጣውን ዕድል መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቶች በስታርት አፕ ቴክኖሎጂና በኢንተርፕረነርሽፕ በስፋት እየተሳተፉ መሆኑን በማንሳት፤ ለዚህ የሚሆን ዝግጁ ወጣትና ማኅበረሰብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስን ለማሳደግ ጥሩ መሠረት እንዳለ በመጥቀስ፤ የተጀመሩ መልካም ጅምሮችን የበለጠ ማላቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኤ አይ ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው
May 4, 2026 246
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና ከእሑድ ኤ አይ ስቱዲዮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኤ አይ ሙዚቃ ውድድር ተካሂዷል፡፡ ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደሉት ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) ዘርፍ ያላትን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አሁን ላይ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ችግሮች የሚፈቱበት ቁልፍ መሳሪያ እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ ኤ አይ የሰው ልጅን የማሰብ፣ የመገንዘብ፣ የማመዛዘን፣ የማቀድ፣ የመማርና ቋንቋን የመረዳት አቅምን በማሳደግ የተለያዩ ተግባራትን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን ያስችላል ብለዋል፡፡ ቴክኖሎጂው በጥበብና መዝናኛው ዘርፍ ያለውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አዲስ መሳሪያ ብቻ ሳይሆን ለችግሮች አዲስ የመፍትሄ ሃሳብ ማመላከቻ መንገድ በመሆን በዘርፉ ይዘቶችን በፍጥነት ለማዘጋጀት አማራጭ ሃሳብ ይዞ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡ ተቋማቸው ኤ አይ ቴክኖሎጂን በሚገባ የተረዳ እና ለበጎ አላማ የሚጠቀም የሰው ሃይል ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ የኤ አይ ሙዚቃ ውድድሩ የዚሁ ሥራ አካል መሆኑን ጠቁመው ይህም ቴክኖሎጂው በጥበብ ዘርፍ ያለውን አቅም ከማሳየት ባለፈ በኢትዮጵያ ታሪክ የቴክኖሎጂና ጥበብን ጥምረት መግለጽ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡ ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የኤ አይ ሙዚቃ ውድድር በጎ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራ ትግበራን በማበረታታት ወጣቶች ቴክኖሎጂውን በሃላፊነትና በሥነ ምግባር እንዲጠቀሙ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ውድድሩ በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በዘርፉ ሥራ ፈጣሪዎች መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የይዘት ፈጠራ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች መኖራቸውን መረዳት እንደተቻለ ጠቁመው በሒደቱ የተገኘው ውጤት አበረታች እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ስፖርት
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርጉት ተጠባቂ ፍልሚያ
May 6, 2026 89
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ዛሬ በሚደረጉ ሶስት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል። በዕለቱ ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ግጥሚያውም በአዲስ አበባ ስታዲየም ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል። ሲዳማ ቡና በ55 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ መድን በ35 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሊጉን እየመራ የሚገኘው ሲዳማ ቡና በ29ኛ ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል። የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ መድን ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ሲዳማ ቡና መሪነቱን ለማጠናከር፣ ኢትዮጵያ መድን ደግሞ ከወራጅ ቀጠናው ርቆ ደረጃውን ለማሻሻል የሚያደርጉት ይህ ጨዋታ ለሁለቱም ክለቦች ወሳኝ የሚባል ነው። ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ የመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው። በሌላኛው መርሐ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከነገሌ አርሲ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ35 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ነገሌ አርሲ በ45 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ድል የቀናው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስፍራ ለመራቅ የሚያስችለውን ሶስት ነጥብ ያስገኝለታል። አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል። ማሸነፍ ወደ ድል መንገድ ይመልሰዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከባህር ዳር ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ፋሲል ከነማ በ43 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባህር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት ያልቻለው ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ባህር ዳር ከተማ በዘንድሮው ውድድር ካደረጋቸው ጨዋታዎች መካከል 16 ጊዜ በአቻ ውጤት በመጨረስ በሊጉ ቀዳሚው ነው። ባለፉት ሶስት ጨዋታዎችም ድል አልቀናውም። ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ ይፋለማሉ።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ድግስ፦ ባየር ሙኒክ ከ ፒኤስጂ
May 6, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ባየር ሙኒክ ከፒኤስጂ ዛሬ የሚያደርጉት የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ የአውሮፓ ኃያላን ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ፒኤስጂ 5 ለ 4 አሸንፏል። ማራኪ፣ አዝናኛ እና በማጥቃት ላይ የተመሰረተው የመጀመሪያው ጨዋታ በእግር ኳስ ቤተሰቡ አድናቆት ተችሮታል። ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምንጊዜም ምርጥ ጨዋታዎች አንዱ እና ከፍጻሜው በፊት የፍጻሜ ጨዋታ የሚል ስያሜም በብዙዎች ዘንድ ተሰጥቶታል። ሁለቱም ክለቦች ለዛሬው ጨዋታ ማጥቃትን ቀዳሚ መመሪያቸው አድርገው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ከቡድኖቹ ካምፕ ተሰምቷል። የቡድኖቹ የማጥቃት ጠንካራ ፍላጎት ለእግር ኳስ አፍቃሪያን መልካም ዜና ነው። የስድስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ባየር ሙኒክ ለፍጻሜው ለማለፍ ይጫወታል። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ክብሩን በማስጠበቅ ጉዞው ለመቀጠል ጠንካራ ፈተና ከጀርመኑ ክለብ ይጠብቀዋል። እግር ኳስ አፍቃሪያን እንደ መጀመሪያው ዙር ሁሉ በዛሬውም ጨዋታ በቴሌቪዥን መስኮታቸው ማራኪ ፉክክርን ለመመልከት በጉጉት ይጠብቃሉ። የ38 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ጆአኦ ፒንሄሮ ተጠባቂውን ፍልሚያ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በፍጻሜው ከአርሰናል ጋር ይገናኛል። ትናንት በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል።
አርሰናል ከ20 ዓመታት በኋላ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፈ
May 5, 2026 201
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ በ44ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ግልጽ የግብ እድሎች ውስን በነበሩበት ጨዋታ አርሰናል በመጀመሪያ አጋማሽ ያገኘውን መሪነት አስጠብቆ ወጥቷል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አልፏል። መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ ለፍጻሜ ያለፉት እ.አ.አ በ2006 ነበር። ለፍጻሜ ሲያልፉ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። አርሰናል በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል። 14 ጨዋታዎቹን አድርጎ 11ዱን ሲያሸንፍ በሶስቱ አቻ ወጥቷል። አርሰናል በፍጻሜው ከባየር ሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በቡዳፔስት ይጫወታል። አትሌቲኮ ማድሪድ ከ10 ዓመታት በኋላ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ የማለፍ ህልሙ አልተሳካም። የባየር ሙኒክ እና ፒኤስጂ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ነገ ይደረጋል።
ምድረ ገነት ሽሬ እና ድል ዳግም ተገናኝተዋል
May 5, 2026 166
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ምድረ ገነት ሽሬ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንተነህ ተስፋዬ በ21ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ምድረ ገነት ሽሬ በ33 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በሊጉ ለመቆየት በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል። በውድድር ዓመቱም ሰባተኛ ድሉን አግኝቷል። በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ42 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ በተደረጉ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን፣ አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል። ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው
May 6, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ ገለጸ። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ያካሄደችው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር፣ በአካባቢ ጥበቃ በኩል ዓለምአቀፍ ትኩረትን የሳበ ለውጥ ማስመዝገብ ችላለች። እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ልዩ ልዩ የችግኝ ዓይነቶችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች። ይህም የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ያመጣ ሲሆን፤ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና የውኃ ሀብትን በመጠበቅ ለግብርናው ዘርፍ ዕድገት ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። መርኃ ግብሩ የፍራፍሬ ተከላን በማካተቱ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለዜጎች ሥርዓተ ምግብ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተም ይገኛል። የኢትዮጵያ ደን ልማት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምርትና ምርታማነትን በተጨባጭ እንዲጨምር ማድረጉን ጠቅሰው ቀደም ሲል በዓመት በሄክታር ይታጠብ የነበረን 130 ቶን አፈር፣ አሁን ወደ 54 ቶን ዝቅ ማለቱንም ገልጸዋል። በተለይም በበጋ ወቅት በሚከናወኑ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች የአፈር መሸርሸርን መከላከልና የውኃ ሀብቶችን መጠበቅ ተችሏል ነው ያሉት። በጥናት እንደተረጋገጠው የምርት እና ምርታማነት ማደጉን፣ የደን ሽፋን መጨመሩንና የአፈር መሸርሸር መቀነሱን የገለጹት አስተባባሪው፤ አረንጓዴ አካባቢዎችን በማስፋፋት ለኑሮ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በዓለም የምግብ ድርጅት እጅግ ውስን ፍራፍሬ ከሚያመርቱ ሀገራት መካከል ትመደብ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የችግኝ ጣቢያዎችን በማብዛትና ክትትልን በማጠናከር በመርኃ ግብሩ የሚተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች መጠንና ጥራት ላይ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል። በተለይም በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ዝግጅት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል። አምና 600 ሚየዮን የሚሆኑ የፍራፍሬ ችግኞች መተከላቸውን አውስተው ዘንድሮ ከዚህ በላይ እንደሚሆን አመልክተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ፋይዳዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበቱ መምጣታቸውን ጠቁመው፤ የፍራፍሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና ለገበያ ማዕከላት ማቅረብ የጀመሩ አርሶ አደሮች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች ይበልጥ ለማስፋት የክትትልና ድጋፍ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የፍራፍሬ ምርቶች ማኅበረሰቡ አማራጭ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ በማድረግ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ሚና እያበረከቱ እንደሚገኙም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘምን ያከናወነቻቸው ተግባራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው
May 6, 2026 130
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘመን ያከናወነቻቸው ውጤታማ ስራዎች የአፍሪካን አቅም የሚያሳድጉ መሆናቸውን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ ሜቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን ሳይንቲፊክ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በኮንፍረንሱ የተሳተፉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ በሚቲዎሮሎጂ እንዲሁም በሃይድሮሎጂ ምልከታዎች ዙሪያ በጋራ መሥራታቸው ወሳኝ ነው። ይህም የተፈጥሮ አደጋዎች ሳይከሰቱ አስቀድሞ ጥንቃቄ ማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስልቶችን ለማጎልበት እንደሚረዳ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በዘርፉ ላከናወነቻቸው የቴክኖሎጂና የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች አድናቆታቸውን ገልጸው፤ እነዚህ ኢንቨስትመንቶች ከኢትዮጵያ አልፈው ለአህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስርና የመቋቋም አቅምን ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ፣ የታዳሽ ኃይልን ከማስፋፋት እና በሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ ያሳየችው ውጤት የመንግስትን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚምባቡዌ የመጡት ፍሪዶ ሙካንጋ በሰጡት አስተያየት፤ በኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘመንና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እጅግ የሚያስደንቁና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በመረጃ አያያዝና በከፍተኛ አቅም በሚሰሩ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂዎች ላይ ያደረገው ኢንቨስትመንት መንግሥት ለዜጎቹ ሕይወት መታደግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሥነ-ምሕዳርን ከመጠበቅ ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎች ላይ ትኩረት ማድረጉ፣ ለዜጎች የገቢ ምንጭ እንዲሆንና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል። በሃይድሮሎጂ ዘርፍ የሚደረጉ ምልከታዎችና ጥናቶችም ለኃይል ማመንጫ፣ ለመስኖ ልማትና ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የጀርባ አጥንት ለሆኑ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑን መረዳታቸው ጠቅሰዋል፡፡ የታንዛንያው ተወካይ ዶክተር ፍሬድበሪት ኦዱንጋ በበኩላቸው፤ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም አቅሟን ለማጎልበት ሀገራት በጋራ መሥራት፣ ግብዓቶችን መጋራት እና የተቀናጁ ስልቶችን መቅረጽ እንዳለባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በውኃ አስተዳደር እና በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ግንባታ ላይ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለአህጉራዊ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ሰፊ ጥረት ለመላው አፍሪካ የመቋቋም አቅም መጎልበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኬንያዊቷ ማሪያ ሎኪ ቻሬም በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በበለጠ ፍጥነትና ውጤታማነት ለመፍታት የአፍሪካ ሀገራት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለሌሎች ሀገራት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከኢትዮጵያ ልምድ በመነሳት የአፍሪካ ሀገራት ለአህጉሪቱ ስኬት መሥራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
በዞኑ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ39 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል
May 6, 2026 72
ደሴ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ39 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ቡድን መሪ መገርሳ ተሾመ ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ በተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ የደን ሽፋንን በማሳደግ፣ በተፋሰሶች በእንሰሳት መኖ፣ በንብ ማነብ፣ በፍራፍሬ ልማትና በሌሎችም ለወጣቱ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል በዘንድሮ ክረምት በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርህ ግብር ከ39 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉንና ለዚህም የችግኝ ዝግጅት መከናወኑን ተናግረዋል። የደሴ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አደም ከድር በሰጡት አስተያየት በየአመቱ ችግኞችን በማፍላት በራሳቸው መሬት በመትከልና የተረፈውን በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በቃሉ ወረዳ ነዋሪ ወጣት አህመድ መሀመድ በበኩሉ በያዝነው በጋ ከ100 ሺህ በላይ የማንጎ፣ ቡና፣ አቡካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች ማዘጋጀቱንና በመጭው ክረምት በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አመላክቷል። በደቡብ ወሎ ዞን ባለፈው ክረምት ከተተከለው 210 ሚሊየን ችግኝ መካከል ከ75 በመቶ በላይ መጽደቁን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በጅማ ዞን ለዘንድሮው የአረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጁ ሆነዋል
May 6, 2026 79
ጅማ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በጅማ ዞን ለዘንድሮው የአረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጁ መደረጋቸውን የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት አስታወቀ። የጅማ ዞን ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ቲጃኒ ተማም፤ ለደን ልማት፣ ለፍራፍሬ፣ ለውበትና የእንስሳት መኖን ጨምሮ ሌሎችንም ባካተተ መልኩ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ለዚህም 91 ሺህ ሄክታር መሬት ለችግኝ መትከያ የተዘጋጀ መሆኑንና ለስኬታማነቱ ከወዲሁ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ለልማቱ የችግኝ ዝግጅት ከማድረግ በተጓዳኝ ከዚህ ቀደም የተተከሉትን የመንከባከብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ዘንደሮም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ ቀርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሙላቱ ደበሌ እና አርሶ አደር ቲጃኒ አባ ጎጀም፤ የሚተከሉ ችግኞች ለምግብ ዋስትና መሰረት እየሆኑ በተግባር እየተጠቀምንባቸው እንገኛለን ብለዋል። ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለእንስሳት መኖ እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የሚተከሉ ችግኞች ትልቅ ትርጉም እንዳላቸውም አንስተዋል። በመሆኑም የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብና የተራቆቱ አካባቢዎችን በዛፍ በመሸፈን የበኩላችንን እንወጣለን ነው ያሉት። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውንም አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት ትልቅ አቅም የሆነ ኢንሼቲቭ ነው። በተመሳሳይ በጉጂ ዞን ድርቅና የአካባቢ መራቆትን ለመቋቋም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ መጀመሩን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ቡድን መሪ ወንዶ ሸርቦቴ እንዳሉት በዞኑ ለደን፣ ለጥላ ዛፍ፣ ለፍራፍሬ ልማት፣ ለውበትና ለእንስሳት መኖ የሚውሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ የበልጉን ዝናብ በመጠቀም በ6 ሺህ 726 ሄክታር መሬት ላይ መተከላቸውን ገልጸዋል። ቀደም ብለው የተተከሉ ችግኞች የእንስሳት መኖና የከርሰና ገጸ ምድር ውሀ አቅርቦትን በማሻሻል የህብረተሰቡን ኢኮሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቅሰዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት ይገባል
Apr 28, 2026 790
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት እንደሚገባ የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃጸም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 ጎን ለጎን የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድን ሀገር በቀል በማድረግ አካታች ዕድገትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራትም ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን ከአጀንዳው ጋር በማጣጣም የበጀት ድልድልና የፖሊሲ እርምጃዎችን ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦች የበለጸገች አህጉርን እውን ለማድረግም የአባል ሀገራት ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። የአጀንዳ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት የተሳለጠ የለውጥ ሽግግርን ለመፍጠርም ጠንካራና የተሰናሰለ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ የፖሊሲ ፍሰት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በወሳኝ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚኖራቸውን ትብብርና ቅንጅት የሚያበረታታ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትርና ተሰናባቿ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ ቢሮ ሊቀ-መንበር ሮቢናህ ናባንጃ በበኩላቸው፤ የአፍሪካውያን ድምፅ በወሳኝ የዓለም መድረኮች ላይ መንፀባረቅ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በከፍተኛ ደረጃ ከሚደረግ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ባለፈ በወሳኝ ስትራቴጂክ ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካትም ሎጂስቲክስ፣ ትራንስፖርትና መሰል የትኩረት ዘርፎች ላይ በስፋት በመሰማራት ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ነው
Apr 28, 2026 431
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 በትይዩ የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። በአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድ ሀገር በቀል እንዲሆን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራት ብሔራዊ የልማት ዕቅዶቻቸው ከአጀንዳው ጋር እየተጣጣመ መምጣቱን በማንሳት፤ የበጀት ድልድልና ፖሊሲዎቻቸው ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ የሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን በማሳካት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በሀገራት መካከል ያለው ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸውን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አለባቸው
Apr 27, 2026 454
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸው ላይ እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታንዛኒያ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናትን ለአረንጓዴ የኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ማዋል" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁት የ12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ቅድመ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ እንደ ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ግራናይት እና ሌሎች የከርሰ ምድር ሀብቶችን ጨምሮ የዓለምን 30 በመቶ ማዕድናትን ይዛለች፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻዋን የዓለምን ከፍተኛ የኮባልት ማዕድን የያዘች መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም አፍሪካን የዓለም አቀፍ የኃይል ሽግግር /Energy Transition/ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ዩራኒዬምና ሌሎች የከርሰ ምድር የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ፤ ለዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል አቅርቦት አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ኃይል ልማት እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት ብትሆንም አብዛኛው በጥሬ እቃ መልክ ወደ ውጭ የሚላክ በመሆኑ የአህጉሪቱ የእርስ በእርስ ግብይት ከሁለት በመቶ እንዳማይዘል ተናግረዋል፡፡ በአህጉሪቱ የማዕድናት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን መገንባት ቢቻል በየዓመቱ ከ24 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና ለ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማዕድን ፖሊሲ ለእሴት መጨመር፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ሁሉን አቀፍ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአህጉሪቱ የተቀናጀ ቀጣናዊ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለውን ፍላጎት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አህጉራዊ የማዕድን ሀብቶችን ወደ ዘላቂ ብልጽግና መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጣናዊ እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር የማዕድን ጸጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካዳሪ ሲንጎ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና አካታች ዕድገት ለማስመዝገብ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የሚኖረን ትብብርና ተሳትፎ ስትራቴጂያዊና መዳረሻ ግብ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮት ሽግግርን ለመፈጠር በአቅም ግንባታ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 838
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 310
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 189
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 26, 2026 570
ክልሎች፤ሚያዝያ 18 /2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር የምንቃኝበት ነው። በዚህ ሳምንትም አንኳር የክልሎች ክንውኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ቀርበዋል። የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተም! ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማት ስራ መደባኛ ስራዋ ካደረገች ወዲህ አያሌ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእቅድ እና በቁርጠኝነት በመከናወኑ ከውጪ የሚገባ ስንዴ ቀርቷል፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቱም ቀጥሏል። ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ሽግግርም ዓመቱን ሙሉ በማልማት እየታጀበ ሲሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ነው። በዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በተያዘው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊማ፣ በጂዳ ወረዳ ሲባ ሲርቲ እና ቂምቢቢት ወረዳ ሰገሌና ደርማሙሳ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ እና በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ አስቃኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፎቶ ጋር ያያዙት መልዕክትም ''ይህ የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተማችን ነው'' ይላል። ብሪክስ -- ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች። መድረኩም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የተካሄደበት፤ በብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የተሰጠበትም መሆኑ ተመላክቷል። ማረም እና ማነጽ የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል እንዲሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነው። የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ “የማረሚያ ተቋማት ለሀገር ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት፣ ከማረሚያ ቤት የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም ከማረም የማነጽ ተሃድሶ ልማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉባኤው በልዩ ሁኔታ የመከረበት ነው። ኢትዮጵያ ማምረቷን ቀጥላለች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክሲፖ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ ነው ብለዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት። ዘንድሮ ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል በኢትዮጵያ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ውኃ የህልውና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ለፍጡራን ሁሉ ውኃ ህይወት ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ግን ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል። በሳምነቱም በአፋር ክልል ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር እና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተከናወነው ልማት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱ በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ መንግስት የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል፤ በተለይም የለውጡ መንግስት ለቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሰራው ስራ የውኃ ተደራሽነት በእጅጉ ማደጉን አንስተዋል። ልምድ ልውውጥ እና ተሞክሮ -ለምክር ቤቶች ሌላው ቅኝታችን በዚህ በተጠናቀቀው ሳምንት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱን የዳሰሰ ነው። የጋራ የምክክር መድረኩ ዓለማ የልምድ ልውውጥና የልማት ሥራዎችን በመመልከት ተሞክሮ መለዋወጫ ነው።የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ መንግስት ሕዝቡ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት ማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ይገባል ብለዋል።የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶች ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል። የጤና ልማት ስራ እስከ አክሞ ማዳን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት የአጋር ድርጅቶች አስተዋጾ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም የተመለከተው በዚህ ሳምንት ነው። ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ መሰል የጤና ዘርፍ የልማት ስራዎች መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ከማሳካት አንጻር እገዛቸው ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።ማዕከሉ ማህበረሰቡ በቅርበት ሕክምና እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ሲታከም ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ ያስቀራል። ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ማሽኖች፣ የመድሃኒት ቤት፣ መኝታ አልጋዎችና የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሟልቶ የተገነባ መሆኑም ታውቋል። የከተሞች ኮሪደር- ከቱሪዝም እስክ ኮንፍረንስ ማዕከልነት በኮሪደር ልማት እጅግ ከተዋቡ እና ከደመቁ የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ ናት። በሳምንቱ የከተማዋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ የምስጋናና ዕውቅና እንዲሁም የአራተኛ ዙር የኮሪደር ልማትና የሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርቡ ቀጥሏል ብለዋል። በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሪደር እና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች እንደሚቀጥሉ አንስተው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ምርጫ -የዴሞክራሲ መሰረት ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹበትም ነበር። ኢትዮጵያዊያን መጪውን ጊዜ የተሻለ የሚያደርግላቸውን መንግስት ለመመረጥ ዝግጅታቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 577
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል። ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል። በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል። በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ትንታኔዎች
የ471 ሚሊዮን ተከታዮች ባለቤት የሆኑ የ30 ሀገራት ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሳተፉበት ታሪካዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ
May 6, 2026 76
በመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) ላይ ለመሳተፍ፣ ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡና በአጠቃላይ 321 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 61 ታዋቂ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። እነዚህንም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 120 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ የይዘት ፈጣሪዎች ይቀላቀሏቸዋል። ታሪካዊው ጉባኤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ጉባኤው በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና በኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ የጋራ ትብብር የተዘጋጀም ነው። በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል አዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ የአፍሪካን ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደገና ለመቅረጽ ያለመ ነው። ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበር እና የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅበት ስም ነው) ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ሴራሊዮናዊው ቦይዜ ክሪሽ፣ ቤኒናዊው ሬጌ ቦይዘር፣ ሴኔጋላዊው ጃው ኬቹፕ እና ስዊዛላንዳዊው ጎጎ እስዋቲኒ ኤምኤም ሌሎች ለጉባኤው የገቡ የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖፐ ፈጣሪዎች ናቸው። የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል። ጉባኤው በአፍሪካ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሰባሰቡበት፣ ስለራሳቸውና ስለ አፍሪካ የሚናገሩበት፣ እንዲሁም ስለ ይዘት ፈጠራና ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች የሚወያዩበት መድረክ ነው። ይህም ተጽእኖ ፈጣሪዎቹን በአንድ መድረክ የማገናኘት ትልቅ አጋጣሚን ፈጥሯል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመጠቀም የይዘት ፈጣሪነት የወደፊት ሁኔታ፣ የአፍሪካ አዎንታዊ ገጽታን መገንባት እና የዲጂታል ተጽዕኖን ከአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ጋር ማጣጣም በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሶስት የከፍተኛ ደረጃ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ። ጉባኤው "በችግር ላይ የተመሰረተ" ዘገባን በእውነተኛ የአፍሪካ የዕድገት ታሪኮች ለመተካት የታለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑም ተመልክቷል። የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ የማስተዋወቅ እድሉ ሰፊ ነው። እነዚህ የይዘት ውጤቶች የአፍሪካን መልካም ገጽታ ለዓለም፣ የኢትዮጵያንም መልካም ገጽታ ለአፍሪካውያን ማሳየት የሚችሉ ናቸው። ጉባኤው ሐሙስ ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚጀመር ሲሆን፣ ከ470 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ተከታዮች አይኖች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ላይ አርፈዋል። ይህም አፍሪካ የራሷን ታሪክ ራሷ መተረክ የጀመረችበት አዲስ ዘመን ማሳያ ሆኗል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 523
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 25, 2026 622
ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥን ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም ገልፀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር መምከራቸው ነው። በዚሁ ወቅትም፤ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር መክረናል ብለዋል። በተመሳሳይም ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት ይዘው ከመጡት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እንዲሁም የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች ሲሉም አስታውቀዋል። • በኢትዮጵያ የበቆሎ መስኖ ውጤታማነት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ፤ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዕርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን ዕውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። • መሶብ የሞባይል አገልግሎት መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሶብ አገልግሎት የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የስራውን ውጤታማነት ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰራሩን ይበልጥ መስፋፋት አስፈላጊነትም ገልጸዋል።ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን ገልጿል። አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ሥርዓት እንዳለውና የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ማካተቱንም አመላክቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል። በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደኅንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል፤ መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ፣ ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ፣ የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን፣ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል። • የ100 ቀናትና የ9 ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት የሥራ ዘመኑ 3ኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የዕድገት ሂደትን አስመዝግቧል ብለዋል። ጥረቶቻችን የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ስለ 3ኛው 100 ቀን አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው የ100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ተገምግሟል። በዚሁ ወቅትም አቶ ተመስገን፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ የሚገባትም ትልቅ ሥፍራ ነው፤ እኛ ደግሞ የዚህ ታሪክ ሠሪዎች የመሆን ዕድል በእጃችን ላይ ነው ሲሉ አዝገንዝበዋል። በኮሪደር ልማት፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችና በዲጂታል ኢትዮጵያ ዘርፍ የተካሄደው የመሠረተ-ልማት አብዮት የሀገራችንን እንዲሁም የከተሞቻችንን ገጽታና አገልግሎት ቀይሯል ብለዋል። በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት አማካኝነት የተረጅነትን ቀንበር ሰብረን ወደ ምግብ ሉዓላዊነት እየተጓዝን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዲፕሎማሲው መስክም ኢትዮጵያ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት በመሸጋገር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነቷን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሳድጋለች ብለዋል። • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ፤ በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች፣ በሀገራችን የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የሚመለከት የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ ስምምነት፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ፣ በሥድስት ዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ መክሮ በማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል። • ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች ብሎ ባጋራው መረጃ፤ በመሠረተ-ልማት (የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት)፣ በዲጂታል መሳሪያዎች (ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም)፣ በዲጂታል መንግሥት (በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትሕ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ) የሚሉትን አንስቷል። በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት (5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በዕውቀትና በፈጠራ ማብቃት፣ በተቋማት ግንባታ (ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር)፣ በሕግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት (በፋይዳ መታወቂያ ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት) የሚሉት ጉዳዮችን ጠቅሷል። • የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ሀገራዊ የስንዴ ልማትን በተመለከተም ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል ብሏል። ከሌማት ትሩፋት አንጻርም፤ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው፤ የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። ዲጂታል ኢትዮጵያን አስመልክቶም፤ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው ብሏል። የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትም፤ የከተሞች መሠረተ-ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት አኳያም፤ የማምረት ዐቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው ብሏል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ስለመሆኑም አመላክቷል። እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ሲልም በአጽንዖት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 571
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል። በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 4449
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2974
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8767
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7252
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 751
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 872
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።