ምድረ ገነት ሽሬ እና ድል ዳግም ተገናኝተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ምድረ ገነት ሽሬ እና ድል ዳግም ተገናኝተዋል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ምድረ ገነት ሽሬ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንተነህ ተስፋዬ በ21ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ምድረ ገነት ሽሬ በ33 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በሊጉ ለመቆየት በሚያደርገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል።
በውድድር ዓመቱም ሰባተኛ ድሉን አግኝቷል።
በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ42 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ዛሬ በተደረጉ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን፣ አርባምንጭ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።