ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በውይይታቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም