ቀጥታ፡

የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር እድገት እንዲረጋገጥ ሠርቷል

ይርጋጨፌ፤ ሚያዝያ 27/2018 (ኢዜአ)፡- የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሠ መሥተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ።

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ሐሳብ የብልጸግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ተካሂዷል። 



 
አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ብልጽግና የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል። 

የለውጡ መንግሥት ኅብረ-ብሔራዊነትን በማጠናከር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ አበክሮ መሥራቱን ገልጸው፤ ብልጽግናን በመምረጥ ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባ አመልክተዋል። 


 

የጌዴኦ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግሥት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቁመዋል። 

በዞኑ የቡና ልማትን ለማሻሻል በተደረገ ጥረት አማካይ ምርታማነትን በሔክታር 11 ነጥብ 9 ኩንታል እንዲሁም በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ 20 ኩንታል ማድረስ መቻሉንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም