ቀጥታ፡

በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል

ሮቤ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ።

ብልፅግና ፓርቲ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክቱን በማስተዋወቅ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ -ግብር በሮቤ ከተማ አካሄዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈትበ ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር)፤ ፓርቲው በሁሉም መስኮች ባከናወናቸው ስራዎች ውጤታማ በመሆን የህዝብን ተጠቃሚነት እውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በመደመር እሳቤ ሀገራዊ ልማትንና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት ለላቀ ልማትና ስኬት እየተጋ መሆኑን ገልጸው በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

በባሌ ዞን እና አካባቢው በለውጡ ዓመታት የአካባቢውን እምቅ ሃብቶች በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት መሰራቱን አስታውሰው ልማቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

በዞኑ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውንም አስታውሰው የሮቤ-ጎሮ-ሶፍ ኡመር፣ የጎባ-በርበሬ-ደሎ መና-ብታታ፣ የሮቤ-አጋርፋ- አርሲ የአስፋልት መንገድ ግንባታን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በመደመር እሳቤ በህብረ ብሄራዊ አንድነት ለላቀ ልማትና ስኬት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
 

የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሀኪም አልይ፤ በዞኑ በተለይም የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የስንዴ ልማት እመርታዊ ማንሰራራት የታየበት መሆኑን አንስተው በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችና አዳዲስ ኢንሸቲቮችም ስኬታማ መሆን ተችሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም