ቀጥታ፡

በዞኑ በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው 

ነገሌ ቦረና ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ቦረና ዞን በለውጡ አመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸው ተገለጸ።

ብልጽግና ፓርቲ  በነገሌ ቦረና ከተማ  ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት የለውጡ መንግስት ህዝብን  በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለግብርና ልማት  ትኩረት ሰጥቷል።


 

በዚህም በተለይም በዞኑ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በተከናወነ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

በሌማት ትሩፋትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መርሀ ግብር በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል።

በለውጡ መንግስት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን መሰረት በማድረግ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል አሰባሳቢ ትርክት ላይ መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ ናቸው።


 

በዞኑ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዝርጋታዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቁመዋል።

ፓርቲው በሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አካታች ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ  ልማትን ለማስቀጠል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን  አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም