ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በተፈጠረልን የሥራ ዕድል የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ተግተን እየሰራን ነው-የኮምቦልቻ ከተማ ወጣቶች
Apr 15, 2026 27
ደሴ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ከቤተሰብ ጥገኝነት በመላቀቅ ኑሯቸውን ለመቀየርና የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ተግተው እየሰሩ መሆኑን በኮምቦልቻ ከተማ ወደሥራ የገቡ ወጣቶች ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ ሥራና ክህሎት መምሪያ በበኩሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ12 ሺህ 876 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል። የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው መካከል ወጣት መሀመድ ጌታቸው ለኢዜአ እንደገለጸው፣ ቀደም ሲል ሥራ በማጣቱ ምክንያት የቤተሰብ ጥገኛ ሆኖ ቆይቷል። ዘንድሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገለት የመስሪያ ቦታ ድጋፍ የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ከፍቶ የራሱን ሥራ መጀመሩን ገልጾ፣ በዚህም ከቤተሰብ ጥገኝነት በመላቀቅ ኑሮውን ለማሻሻል ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት ካሱ ታረቀኝ በበኩሏ በተመቻቸላት የመስሪያ ቦታ በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርታ በምታገኘው ገቢ ከቤተሰብ ጠባቂነት ተላቃ ተጠቃሚ መሆን እንደጀመረች ተናግራለች። "ያለሥራ ብዙ የከፋ ጊዜ አሳልፊያለው" የምትለው ወጣቷ ዘንድሮ ባገኘችው የሥራ ዕድል ጠንክራ በመስራት የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስና ሀብት ለማፍራት ግብ ማስቀመጧን ተናግራለች። ለዚህም በሥራዋ ውጤታማ ለመሆን ተግታ እየሰራች መሆኑን ጠቅሳ፣ ከተማ አስተዳደሩ በመስሪያ ቦታ ያደረገላት ድጋፍ በሥራዋ ውጤታማ እንድትሆን ጠቀሜታ አለው ብላለች። የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይትባረክ ጌታሁን በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሮ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግና ዘርፉን ለማነቃቃት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በየደረጃው ያለው አመራር ከዘርፉ ባለሙያ ጋር ተግባብቶ ወደሥራ በመግባቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ12 ሺህ 876 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ወጣቶች ወደሥራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸው፣ ከተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች መካከል ግብርና፣ አገልግሎት፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ንግድ፣ ኮንስትራክሽንና ማዕድን እንደሚገኙበት አመልክተዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ ሥራ ለመጀመር የገንዘብ እጥረት ላለባቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚዎች ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር የተመቻቸ ሲሆን፣ በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑም የገበያ ትስስር እየተፈጠረላቸው ተናግረዋል። ግንባታቸው በተጠናቀቁ 12 ሼዶች የተደራጁ ወጣቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸው፣ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራትም በሌሎች ዘርፎች የተሻለ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት የአገልግሎት አሰጣጥን ያሻሻሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል
Apr 15, 2026 38
ቢሾፍቱ ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሳደጉ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ያሻሻሉ ስኬቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። የክልሉ የፓርቲና የመንግሥት የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የሀርሰዴ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ስኬታማ የልማትና የብልጽግና ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ የከተማ እና የገጠር የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። ከዚህም ባለፈ የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማቀላጠፍ የሚያግዙ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቶች መተግበራቸውንም ተናግረዋል። በቀጣይም የተመዘገቡ በጎ ሥራዎችን የበለጠ ከማጠናከር ባለፈ፣ ዕቅዶችን በአግባቡ ካለመተግበር ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም ይገባል ብለዋል። በተለይም ሁሉንም የልማት ኃይሎች በማቀናጀት የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ውጤታማ ማድረግ ከክልሉ አመራር የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል። በግምገማው ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና በሥራ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ዝርዝር አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡበትም ገልጸዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የልማት ተግባራት መከናወናቸውንና የማኅበረሰቡም ተሳትፎ ጠንካራ እንደነበር ገልጸዋል። በዘጠኝ ወራቱ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ትልቅ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ኃላፊው፤ በቀረው አጭር የበጀት ዓመቱ ወራት ውስጥ ያልተከናወኑ ሥራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በማከናወን የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የመንግስት የማስፈጸም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት የሚያሳዩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ወሎ የብዝኃነት እና የአብሮነት ተምሳሌት ናት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Apr 15, 2026 67
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ወሎ የብዝኃ ሃይማኖትና ባህል መገኛ፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት እንዲሁም የታሪክ ማህደር ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ወሎ ኮምቦልቻ መግባታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ እንደ ቦርከና ወንዝ የማይነጥፈው የህዝቡ ገራገርነትና የማይጠገበው ትኅትና፣ እንዲሁም እንደ ጦሳ ተራራ የገዘፈው መስተንግዶና ደማቅ አቀባበል ልባቸውን በሐሴት እንደሞላው ገልጸዋል። በወሎ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸውና አርሂቡ ብለው ለተቀበሏቸው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለመላው የወሎ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። Ethiopian News Agency #ኢዜአ
በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አመርቂ ውጤት ተገኝቶበታል
Apr 15, 2026 31
ወላይታ ሶዶ ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች አመርቂ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ። በክልሉ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የበልግ ወቅት ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር "አረንጓዴ አሻራ ለተምሳሌት ሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ሼላ ቦርኮሼ ቀበሌ ተካሂዷል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ባለፉት የለውጥ አመታት ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አመርቂ ዉጤት ተገኝቶበታል፡፡ መርሃ ግብሩ የተራቆቱና ከጥቅም ውጭ የነበሩ መሬቶች ለምተው እንደገና ጥቅም እንዲሰጡ ከማድረጉ ባሻገር 18 ነጥብ 95 ከመቶ የነበረውን የክልሉን የደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 86 ከመቶ በላይ ለማሳደግ ማስቻሉን ገልጸዋል። የችግኝ ተከላው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ በመሆኑም ለተያዘው የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላም በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል። በዘርፉ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠልም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ ወጥቶ ችግኝ መትከልና መንከባከብ እንደሚገባውም አሳስበዋል። በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊና የዲላ ክላስተር አስባባሪ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸዉ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ በበጋው ወራትም 1 ሺህ 384 የማህበረሰብ ተፋሰስ ውስጥ 159 ሺህ ሄክታር መሬት በዋና ዋና የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች መሸፈናቸውም ገልጸዋል። በበልግ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የጥምር ደን ፣ የፍራፍሬ ፣ የሀገር በቀል እጽዋት፣ የቡና ፣ የእንሰት ፣የጥላና የጌጥ ዛፍ ችግኞች ተከላ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጎድቶ የነበረውን የተፈጥሮ ሀብት መመለስ ተችሏል ያሉት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዞኑ 16 ተራራዎችን ለማልማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮ የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሆንም አብራርተዋል።
የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል
Apr 15, 2026 106
አሶሳ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናገሩ። 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት እና የወንድማማችነት ድልድይን ለመገንባት የሃይማኖቶች እኩልነትና አብሮነትን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ይገኛል። ሃይማኖቶች ለሰላም እና ለህዝቦች አብሮነት ያላቸውን አስተምህሮ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባልም ብለዋል። የሃይማኖት ካባ ደርበው በህዝቦች መካከል ግጭት ለማስነሳት የሚሞክሩ ግለሰቦችን በማውገዝ የሃይማኖቶችን መቻቻል እና አብሮነትን በሚሰብኩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ነው ያሉት። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በየአካባቢው በመንቀሳቀስ በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት ለማስቀጠልና የሰላምን አስፈላጊነት ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ሃይማኖቶች የሰላም እሴት ባለቤት መሆናቸውን የገለፁት አቶ ጌታሁን፤ በሰላም ግንባታ እና በልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክም ሰላምን ይበልጥ ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እና ሲምፖዚየም እንደሚካሄድ ይጠበቃል። በመድረኩ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ፖለቲካ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል
Apr 15, 2026 137
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተለወጠ ካለው ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር ራሱን እንዲያራምድ፣ ዲፕሎማቶቹም በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም ይፋ ማድረጊያ መርኃ ግብር አካሂዷል። ፕሮግራሙ ዲፕሎማቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን በቂ እውቀትና ክህሎት ታጥቀው አገራዊ ጥቅምን ለማስከበር እንዲችሉ ለማድረግ የታለመ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በመርኃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ ተቋሙን በላቀ ደረጃ ለማዘመን የሚያስችል የሦስት ዓመት አጠቃላይ የተቋም ግንባታ ፍኖተ ካርታ ተነድፎ ወደ ሥራ ተገብቷል። የፍኖተ ካርታው አካል የሆኑ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በተለይም ተቋሙን የማዘመን እና ምቹ የሥራ አካባቢን የመፍጠር ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በተቋም ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችን አቅም ማላቅ ለውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ዲፕሎማቶች ውስብስብ በሆነው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ ኢትዮጵያን በብቃት እንዲወክሉ ክህሎት፣ እውቀትና ግንዛቤያቸው አሁን ካለበት በላይ ከፍ እንዲል እንደሚደረግ ተናግረዋል። የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራሙ ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል። ሚኒስቴሩ ተቋማዊ አቅምን፣ በውስጣዊ አሠራሩ ዘመናዊ እና ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ ቀዳሚ ዓላማው እንደሆነ ገልፀዋል። ዲፕሎማቶች እና የሥራ ኃላፊዎች በሙያዊ ክህሎት፣ በትንታኔ እና በተግባራዊ ዕውቀት እንዲበለጽጉ ማድረግም እንዲሁ። ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የዲፕሎማሲ ልምዶችን በተቋሙ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ገልፀዋል። የፕሮግራሙ ተግባራዊ መሆን ኢትዮጵያ በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እንደሚያሳድገው አመልክተው፤ ለሀገሪቷ የዲፕሎማሲ ስኬት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተናግረዋል። ይህ ሁለገብ የሪፎርም አጀንዳ ለዲፕሎማቶች እና ለሚኒስቴሩ ሠራተኞች የሙያ ሥልጠና መስጠት፣ የውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት (IFA) ሥርዓተ-ትምህርትን መከለስ፣ አዲስ የሥነ-ምግባር ደንብ ማዘጋጀት እና ከፍተኛ የድህረ-ምረቃ ትምህርቶችን ማመቻቸት የሚሉት ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
Apr 14, 2026 1340
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ከሁለትዮሽ ስብሰባቸው ቀጥሎ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ተገኝተዋል። እነዚህ ስምምነቶች በትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለወደፊት ትብብራችን እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ-ካርታ እንደሚያገለግሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል። የትብብር ማዕቀፉ፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያን በመደመር መርህ በማጣመር ለአኅጉራዊ ትስስር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ከመሆኑም ባለፈ፣ የአፍሪካ ሀገራት በእውነተኛ ትብብር ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል።
በፈተናዎች ሁሉ የጸናው የኢትዮጵያና የላይቤሪያ ወዳጅነት
Apr 14, 2026 716
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት አላቸው። ይሄ ወዳጅነት በፈተናዎች ጊዜ ሁሉ ጸንቶ የዘለቀም ነው። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ውስጥ ብቸኛ ነፃ ሀገራት በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች (ለምሳሌ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የአፍሪካውያን ድምፅ ሆነው በጋራ ይቆሙም ነበር። የሀገራቱ የወዳጅነት እና የትብብር ስምምነትም እ.አ.አ በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ የጀመረ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለው ዘላቂ ወዳጅነት እና በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) በጋራ ለመቆም ቃል የተገባበት ሰነድም ተደርጎ ይወሰዳል። የዘመናዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት የጣሉትም ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ቱብማን ናቸው። እ.ኤ.አ. በ1954 ፕሬዝዳንት ቱብማን ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ይፋዊ ግንኙነት እንዲጀመር በር ከፍቷል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እ.አ.አ. 1958 ጉብኝት ወደ ሞንሮቪያ በማድረግ፣ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ የነፃነት ንቅናቄዎችን በጋራ ለመደገፍ ተወያይተዋል። እነዚህ ጉብኝቶች የሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆኑ አህጉራዊ ፋይዳም ነበራቸው። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ሲመሰረት፣ ሁለቱ ሀገራት "የሞንሮቪያ" እና "የካዛብላንካ" ቡድኖችን ልዩነት በውይይት በመፍታት ለአህጉሪቱ አንድነት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አስመስክረዋል። በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በ”ሞንሮቪያ ቡድን” እና "የካዛብላንካ ቡድን" መካከል የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በጋራ በመስራታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊመሰረት ችሏል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በችግር ውስጥ የተፈተነ ወዳጅነት ነው የሚል ሀሳብ በብዙዎች ይነሳል። የዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ነው። ላይቤሪያ ለ14 ዓመታት በዘለቀው አውዳሚ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት መንግሥታዊ መዋቅሯ ፈርሶ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2003 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰላም እንዲያስከብሩ ከጠራቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ነበረች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ በርካታ ሰራዊቷን በማሰማራት ለሀገሪቷ ሰላም ዋጋ ከፍላለች። ሰራዊቱ አማፂያንን ትጥቅ በማስፈታት፣ ተዋጊዎች ከማህበረሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ በማድረግ እና የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል። ዋና ከተማዋ ሞንሮቪያ እና በገጠራማ አካባቢዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዳይጣስ ጥብቅ ቁጥጥር አድርጓል። የኢትዮጵያ ሰራዊት የጤና ቡድን በየሰፈሩ በመዘዋወር ለላይቤሪያውያን ነፃ የህክምና እርዳታ እና መድሃኒትም ይሰጥ ነበር። ሰራዊቱ የራሱን ስንቅ ለተቸሩ ዜጎች በማካፈል ወንድማማችነትን በተግባር አሳይቷል። እ.ኤ.አ በ2014 የኢቦላ ወረርሽኝ በላይቤሪያ በከፋ ሁኔታ በተከሰተበት ወቅትም፣ ሌሎች ሀገራት ሰራዊታቸውን ሲያስወጡ ኢትዮጵያ ግን የህክምና ቡድኖችን እና ሰራዊቷን በማቆየት ከላይቤሪያ ህዝብ ጎን ቆማች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሶስት ተከታታይ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች እንዲካሄዱ በሰላም ማስከበሩ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የላይቤሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የላቀ አገልግሎት ሜዳሊያ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ከወታደራዊ ተልዕኮ ባለፈ የደም እና የአጥንት መስዋዕትነት ከፍላለች። ይህ የሰራዊቱ ተሳትፎ ዛሬም ድረስ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ላለው ጥብቅ ወዳጅነት ዋነኛው ምክንያት ተደርጎ ይወሳል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራቱ መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች ለሁለትዮሽ ትብብሩ መጠናከር አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እ.አ.አ በ2006 ስልጣን በያዙ ማግስት አዲስ አበባን ጎብኝተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሰላም ለማስፈን ላደረገችው ድጋፍ እውቅና የሰጡበት ነበር። ሰርሊፍ በላይቤሪያ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ሲያበቃ እ.አ.አ ጁላይ 2015 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ለተደረገላቸው የህክምና ቡድን ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት እ.አ.አ በ2017 ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳላኝ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቷ በወቅቱ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ላይቤሪያ ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ልማት ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ በወቅቱ ገልጸው ነበር። የላይቤሪያ የእግር ኳስ ኮከብ እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ እ.አ.አ በ2018 ስልጣን ከያዙ በኋላ በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተሳተፉ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል። የቀድሞው የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ከማያህ እ.አ.አ በ2022 በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን (Joint Ministerial Commission) እንዲቋቋም ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በላይቤሪያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMIL) ላይ በነበረበት ወቅት፣ የተለያዩ የመከላከያ ሚኒስትሮች እና የጦር አዛዦች የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ኃይል ለመጎብኘት እና ከላይቤሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት በተደጋጋሚ ወደ ሞንሮቪያ ተጉዘዋል። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ውይይቶች በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶችም ተፈራርመዋል። ሰላም ፣ ደህንነት፣ ጤና፣ የአየር አገልግሎት፣ የቪዛ ነፃ መብት ፣ የንግድ ትብብር ማዕቀፍ፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ባህል እና ስፖርት ስምምነት ከተደረገባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ። የአየር አገልግሎት ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ ያለምንም ገደብ እንዲበር እና ላይቤሪያን ከቀሪው ዓለም ጋር ማገናኘት የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ነው። የሰላም ማስከበር ስምምነቱ በተባበሩት መንግሥታት ማዕቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንድትልክ የተደረገው ስምምነት በላይቤሪያ መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ድርሻ ነበረው። በኪነ-ጥበብ እና በስፖርት ዘርፍ (በተለይም በእግር ኳስ) የሁለቱ ሀገራት ወጣቶች ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአከይ እ.አ.አ 2023 ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡበት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ለማደስ እና በንግድ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም ከተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ጋር ውይይት አድርገዋል። የሁለትዮሽ ውይይቱ በቴክኖሎጂ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኢትዮጵያ ለመገንባት ባቀደችው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይቶቹ ላይ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ ቆይታ እጅግ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖራቸውም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክርም ታምኖበታል። የኢትዮጵያ እና የላይቤሪያ መጻኢ ግንኙነት ከታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ አጋርነት የማሳደግ ፍላጎት በሁለቱም ወገን በኩል አለ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የአቪዬሽን ትስስር፣ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና በአህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ማዕቀፍ የሚደረግ ትብብር ለጋራ ብልጽግና መሰረት ይጥላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር ተወያዩ
Apr 14, 2026 769
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ አቻቸው ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ከላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጋር የነበራቸው ውይይት ፍሬያማ እንደነበር አመልክተዋል። በውይይታቸው በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍ መከፈቱን ገልጸዋል። ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠል፣ በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች መፈረሙን ጠቁመዋል። እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ብለዋል። በተጨማሪም ስምምነቶቹ ከአጋሮች የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሰረት እንደሚያገለግሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው
Apr 14, 2026 721
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡትን የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል በማድረጌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ግዛት ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት፣ አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት ሲሉም አስፍረዋል። በዚህ መንፈስ ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር፤ የጋራ ህልሞቻችንን በማይናወጥ መሠረት እና የመፈጸም ቁርጠኝነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን ጽኑ እምነት አለኝ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ተወያዩ
Apr 14, 2026 547
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣይ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ቁልፍ መስኮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ወታደራዊ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ
Apr 14, 2026 746
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ወታደራዊ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማምተዋል። የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ከላይቤሪያ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ብርጋዲየር ጄኔራል ጄራልዲን ጃኔት ጆርጅ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ሚኒስትር አይሻ (ኢ/ር) ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት መሆናቸውን አስታውሰው፤ ይህ የታሪክ ትስስር አሁን ላለው ወታደራዊ ትብብር ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በወታደራዊ ኢንዱስትሪና በዐቅም ግንባታ ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡ ብርጋዲየር ጄኔራል ጄራልዲን ጃኔት ጆርጅ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የሰላም ማስከበር ስምሪትን ጨምሮ በወታደራዊ ሳይንስ እና በዘመናዊ መከላከያ ግንባታ ያካበተችው ተሞክሮ ለላይቤሪያ ትልቅ ትምህርት የሚገኝበት መሆኑን ገልፀዋል። ላይቤሪያ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰፊ ልምድ የመቅሰም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላትም አስታውቀዋል። በተለይም በስልጠና እና በቴክኒክ ዘርፎች የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሠሩ መናገራቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ የላከው መረጃ ያመላክታል።

ማህበራዊ
የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል
Apr 15, 2026 106
አሶሳ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናገሩ። 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት እና የወንድማማችነት ድልድይን ለመገንባት የሃይማኖቶች እኩልነትና አብሮነትን የማጠናከር ስራ እየተሰራ ይገኛል። ሃይማኖቶች ለሰላም እና ለህዝቦች አብሮነት ያላቸውን አስተምህሮ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሃይማኖቶችን አስተምህሮ ለሰላም እሴት ግንባታ እና ለህዝቦች አብሮነት መጠናከር ልንጠቀምበት ይገባልም ብለዋል። የሃይማኖት ካባ ደርበው በህዝቦች መካከል ግጭት ለማስነሳት የሚሞክሩ ግለሰቦችን በማውገዝ የሃይማኖቶችን መቻቻል እና አብሮነትን በሚሰብኩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን ነው ያሉት። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በየአካባቢው በመንቀሳቀስ በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት ለማስቀጠልና የሰላምን አስፈላጊነት ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ሃይማኖቶች የሰላም እሴት ባለቤት መሆናቸውን የገለፁት አቶ ጌታሁን፤ በሰላም ግንባታ እና በልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክም ሰላምን ይበልጥ ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እና ሲምፖዚየም እንደሚካሄድ ይጠበቃል። በመድረኩ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማምጣት ዝግጅት እያደረጉ ነው
Apr 15, 2026 59
ደብረ ብርሃን ፤ ሚያዚያ 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማምጣት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች ገለጹ። በሸዋ ሮቢት አጠቃላይ 2ኛ እና ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜሮን ሙላቱ ለኢዜአ እንደገለጸችው፤ጊዜዋን በአግባቡ ተጠቅማ በማጥናት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት የሚያስችላትን ውጤት ለማምጣት ጥረት እያደረገች ነው። መምህራንም ከመደበኛው የትምህርት ጊዜ ውጭ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶችን እንድታደርግ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ነው የምትናገረው። ትምህርት ቤቱም እንዲሁ አጋዥ መጻህፍትን በማሟላት፣ ቤተ መጻህፍቱን በማደራጀት ፣ የቤተሙከራ ግብአቶችን በማሟላት ድጋፍ እያደረገ ነው ብላለች። በመምህራንና በቤተሰብ የሚደረግላት እገዛ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ለመቀጠል እየረዳት መሆኑንም ነው ያመለከተችው። ተማሪ ኑሩ ኢብራሂም በበኩሉ፤ ለሀገር አቀፍ ፈተናው በቡድንና በተናጠል በማጥናት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ነው ያመለከተው። የትምህርት ቤቱ መምህራን ተማሪዎች ሊኖራቸው ስለሚገባ የአጠናን ስልት፣ በፈተና ጊዜ ሊኖር ስለሚገባ መረጋጋት እና የማናውቀውን ጠይቀን እንድንረዳ የሚያደርጉት ጥረት ዝግጅታችን የተሟላ እንዲሆን እያደረገ ነው ብሏል። በሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ቡድን መሪ አቶ መለሰ ደርብ በበኩላቸው፤ በዞኑ በ54 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 6 ሺህ 219 ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንዲችሉም አስቀድሞ ከመምህራንና ከወላጅ ህብረት ጋር ውይይት በማድረግ ወደ ስራ መገባቱን ነው ያመለከቱት፡፡ በተለይ ትምህርት ቤቶቹ አጋዥ መጻህፍትን በማሟላት፣ የጥናትና የትርፍ ጊዜ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ሞዴል ፈተናዎችን በመስጠት ተማሪዎቹ ቀድመው እንዲዘጋጁ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በሐረሪ ክልል 250 አባወራዎችን ያካተተ ሞዴል መንደር ሊገነባ ነው
Apr 13, 2026 369
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በገጠር ኮሪደር ልማት በቀጣይ ሁለት ወራት 250 አባዎራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሞዴል መንደር እንደሚገነባ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ። በክልሉ የገጠር ኮሪደር ዐቢይ ኮሚቴ ዕቅድ እና አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ርዕሰ መሥተዳድሩ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከፅዱና ውብ አካባቢ ባለፈ ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ እንዲፈጠር እያስቻለ ነው። በዚህም መሠረት በሐረር ከተማ በኮሪደር ልማት ዘርፍ የተመዘገበውን ውጤት በገጠሩ ክፍል ለማስፋት እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በገጠር አካባቢ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችም፤ የአርሶ አደሩን የአኗኗር ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው ያመላከቱት። ለአብነትም አርሶ አደሩ ያለውን ሀብትና ፀጋ በአግባቡ ተጠቅሞ ኢኮኖሚውን በማሳደግ በዚያው ልክ የተመቸ ኑሮ እንዲመራ የሚያግዝ መሆኑን ነው ያስረዱት። በክልሉ የሞዴል ገጠር መንደር መፈጠሩን የገለጹት ርዕሰ መሥተዳድሩ፤ ሞዴል መንደሩም ውኃና የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች እንዲሟሉ ተደርጓል ብለዋል። በቀጣይ ሁለት ወራትም 250 አባዎራዎችንና እማወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት ይሠራል ነው ያሉት። የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ በላቀ ቁርጠኝነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠው፤ ለዚህም አርሶ አደሩ እያከናወነው የሚገኘውን የላቀ ተሳትፎና ድጋፍ እንዲያጠናክር አሳስበዋል። በየደረጃው የሚገኘው አመራርም ሥራዎችን በቅንጅት እና በትብብር እንዲሠራ ነው ያሳሰቡት። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የገጠር_ኮሪደር
ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማብሰር የሚያስችሉ ተጨባጭ ተግባራትን እያከናወነች ነው
Apr 13, 2026 715
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማብሰር የሚያስችሉ ተጨባጭ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ እልፍ ጸጋዎች፣ እምቅ አቅሞች፣ ብሩህ ተስፋዎች፣ ተዝቀው የማያልቁ እሴቶችና ባለታሪክ ህዝቦች ያሏት ሀገር ናት፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ አቅሞቿና አንጡራ ሀብቶቿ ዜጎቿን ከድህነት ኢትዮጵያን ከተረጂ ሀገራት መደብ ሳያወጧት ዓመታት ነጉደዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች የተጀመሩ ኢኒሼቲቮች ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያመጡ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም እሳቤ እየተተገበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ምንም ያልጎደላት ምንም ያላነሳት ሆና እያለ ለምን ተረጂ፣ ለማኝ ትሆናለች ከሚል ዕሳቤ የመነጨ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢኒሼቲቩ ተረጅነትና ጠባቂነት ወዴት እየወሰደን ነው ከሚል ቁጭት በመነሳት መጀመሩን ገልጸው፤ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ከመቻል ባለፈ የክብር የነጻነትና የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ መንግሥት ተረጂነትን ለማስቀረትና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በግብርናው መስክ ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማብሰር የሚያስችል የሚጨበጥ ተግባር እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአደጋ ምላሽ ፈንድ በማቋቋም፣ የሎጂስቲክ ስርዓቱን በማሳለጥና ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በማስቀረት ክልሎች የመጠባበቂያ ክምችታቸውን እያሳደጉ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ለረጅም ዘመን እሴት ሆኖ የቀጠለውን የቤተሰብ ኃላፊነትና የማህበረሰብ አጋርነት ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ 10 ክልሎች ሰብዓዊ ድጋፍን በራሳቸው አቅም መሸፈን መቻላቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ፥ አሁን ላይ ከውጭ የምናስገባው ስንዴ የለም ብለዋል። ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የጀመረችው ጉዞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር ሰጪነት በከፍተኛ ተነሳሽነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ በስኬታማ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
ኢኮኖሚ
በተፈጠረልን የሥራ ዕድል የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ተግተን እየሰራን ነው-የኮምቦልቻ ከተማ ወጣቶች
Apr 15, 2026 27
ደሴ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ከቤተሰብ ጥገኝነት በመላቀቅ ኑሯቸውን ለመቀየርና የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ተግተው እየሰሩ መሆኑን በኮምቦልቻ ከተማ ወደሥራ የገቡ ወጣቶች ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ ሥራና ክህሎት መምሪያ በበኩሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ12 ሺህ 876 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል። የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው መካከል ወጣት መሀመድ ጌታቸው ለኢዜአ እንደገለጸው፣ ቀደም ሲል ሥራ በማጣቱ ምክንያት የቤተሰብ ጥገኛ ሆኖ ቆይቷል። ዘንድሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገለት የመስሪያ ቦታ ድጋፍ የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ከፍቶ የራሱን ሥራ መጀመሩን ገልጾ፣ በዚህም ከቤተሰብ ጥገኝነት በመላቀቅ ኑሮውን ለማሻሻል ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት ካሱ ታረቀኝ በበኩሏ በተመቻቸላት የመስሪያ ቦታ በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርታ በምታገኘው ገቢ ከቤተሰብ ጠባቂነት ተላቃ ተጠቃሚ መሆን እንደጀመረች ተናግራለች። "ያለሥራ ብዙ የከፋ ጊዜ አሳልፊያለው" የምትለው ወጣቷ ዘንድሮ ባገኘችው የሥራ ዕድል ጠንክራ በመስራት የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስና ሀብት ለማፍራት ግብ ማስቀመጧን ተናግራለች። ለዚህም በሥራዋ ውጤታማ ለመሆን ተግታ እየሰራች መሆኑን ጠቅሳ፣ ከተማ አስተዳደሩ በመስሪያ ቦታ ያደረገላት ድጋፍ በሥራዋ ውጤታማ እንድትሆን ጠቀሜታ አለው ብላለች። የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይትባረክ ጌታሁን በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሮ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግና ዘርፉን ለማነቃቃት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በየደረጃው ያለው አመራር ከዘርፉ ባለሙያ ጋር ተግባብቶ ወደሥራ በመግባቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ12 ሺህ 876 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ወጣቶች ወደሥራ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸው፣ ከተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች መካከል ግብርና፣ አገልግሎት፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ንግድ፣ ኮንስትራክሽንና ማዕድን እንደሚገኙበት አመልክተዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ ሥራ ለመጀመር የገንዘብ እጥረት ላለባቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚዎች ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር የተመቻቸ ሲሆን፣ በሥራቸው ስኬታማ እንዲሆኑም የገበያ ትስስር እየተፈጠረላቸው ተናግረዋል። ግንባታቸው በተጠናቀቁ 12 ሼዶች የተደራጁ ወጣቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸው፣ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራትም በሌሎች ዘርፎች የተሻለ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ለ20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት የአገልግሎት አሰጣጥን ያሻሻሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል
Apr 15, 2026 38
ቢሾፍቱ ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ ተግባራት የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሳደጉ እና የአገልግሎት አሰጣጥን ያሻሻሉ ስኬቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። የክልሉ የፓርቲና የመንግሥት የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የሀርሰዴ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ስኬታማ የልማትና የብልጽግና ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ የከተማ እና የገጠር የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። ከዚህም ባለፈ የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማቀላጠፍ የሚያግዙ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቶች መተግበራቸውንም ተናግረዋል። በቀጣይም የተመዘገቡ በጎ ሥራዎችን የበለጠ ከማጠናከር ባለፈ፣ ዕቅዶችን በአግባቡ ካለመተግበር ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ማረም ይገባል ብለዋል። በተለይም ሁሉንም የልማት ኃይሎች በማቀናጀት የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ውጤታማ ማድረግ ከክልሉ አመራር የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል። በግምገማው ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና በሥራ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ዝርዝር አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡበትም ገልጸዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ የልማት ተግባራት መከናወናቸውንና የማኅበረሰቡም ተሳትፎ ጠንካራ እንደነበር ገልጸዋል። በዘጠኝ ወራቱ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ትልቅ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ኃላፊው፤ በቀረው አጭር የበጀት ዓመቱ ወራት ውስጥ ያልተከናወኑ ሥራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በማከናወን የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። የመንግስት የማስፈጸም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት የሚያሳዩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ11ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል
Apr 15, 2026 45
አዳማ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እስካሁን ድረስ ከ11 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በ2018 የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 250 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 301 ሺህ 160 ሄክታር በማልማት ከዕቅድ በላይ ለማሳካት ተችሏል። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ የከርሰ ምድር ውሃ እና የአዋሽ ወንዝን በመጥለፍ የተካሄደ መሆኑንም ጠቁመዋል። የውሃ አማራጮቹን በመጠቀም በዞኑ 11 ወረዳዎች ከለማው መሬት ውስጥ እስካሁን ከ50ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የደረሰ የስንዴ ሰብል በሰው ጉልበት ታጭዶ መሰብሰቡን ጠቁመዋል። ከ208 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የለማው የበጋ መስኖ ስንዴም በኮምባይነር ታግዞ መሰብሰቡን ነው የገለጹት። የምርት አሰባሰቡን ለማቀላጠፍና የምርት ብክነትን ለመከላከል እንዲቻል 125 ኮምባይነሮች በዞኑ እንዲሰማሩ መደረጉንም አመላክተዋል። በእጅና በኮምባይነር ታግዞ በተደረገ የምርት አሰባሰብ ሂደት እስካሁን ድረስ ከ11 ሚሊዮን 104 ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መሰብሰቡን አቶ አብነት ተናግረዋል። እንደ እሳቸው ገለፃ በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከተሸፈነው አጠቃላይ መሬት ከ13 ሚሊዮን 100 ሺህ ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ በቅድመ ምርት ትንበያ ወቅት ተገምቷል። አብዛኛው መሬት በኩታ ገጠም እና በሜካናይዜሽን እርሻ የለማ ሲሆን ይህም ምርትን በፍጥነት ለመሰብሰብና ምርታማነትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አውስተዋል። የመስኖ ልማት ሥራው በዞኑ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የአርሶ አደሩን ገቢ በማሳደግ ምጣኔ ሀብታዊ ተጠቃሚቱን እያሳደገውም ብለዋል። በዞኑ እስካሁን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ285 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በመሳተፍ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አብራርተዋል። በመስኖ ልማት ዘንድሮ በምርታማነት ብልጫ እንዳለ የገለጹት አቶ አብነት፣ ለዚህም ወደ ልማት ያልገቡ ቀበሌዎች በነፍስ ወከፍ የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ጭምር ወደ ልማት መግባታቸውን በምክንያትነት ጠቅስዋል።
የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በሀገር በቀል እውቀት የተቃኘ እና በራስ ባለቤትነት የሚመራ ነው- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
Apr 15, 2026 99
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም በሀገር በቀል እውቀት የተቃኘ እና በራስ ባለቤትነት የሚመራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ። የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ የፀደይ ወቅት ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ከስብሰባው ጎን ለጎን በተዘጋጀ የልማት አቅም ግንባታ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል። እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን አጠቃላይ የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያ አጀንዳ ለከፍተኛ የዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች አብራርተዋል። በስብሰባው ላይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ፣ ከዓለም ባንክ እና ከአውሮፓ ኮሚሽን የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። የባንኩ ገዥ "ገበያዎችን፣ተቋማትን እና መረጋጋትን በፈታኝ ወቅቶች ውስጥ መገንባት" በሚል መሪ ርዕስ በሰጡት ገለጻ፤ በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አማካኝነት በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ እየተከናወነ ያለውን መዋቅራዊ ሽግግር በዝርዝር አቅርበዋል። በዚህም ዘርፉን ለማዘመን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ለተሳታፊዎች አስረድተዋል። የባንኩ ገዥ ኢትዮጵያ ወደ ወለድ ተመን ተኮር የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ እያደረገች ያለውን ሽግግር እና በገበያ የሚወሰን የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት ትግበራን በዋናነት አንስተዋል። በተጨማሪም በአዲሱ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ እና በዘመናዊ የባንክ ሥራ ሕግጋት የታገዘው የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እየለወጠው እንደሚገኝ ገልጸዋል። የገዢው መልዕክት ዋነኛ ማጠንጠኛም የሪፎርም ባለቤትነት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሀገር በቀል እውቀት የተቃኙ እና በስትራቴጂያዊ ቅደም ተከተል የሚመሩ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ከተለያዩ አካላት የሚገኘው ማንኛውም የቴክኒክ ድጋፍም ቢሆን በሀገሪቱ ፍላጎት ላይ የተመሠረተና ከልማት የቅድሚያ ትኩረቶች ጋር የተጣጣመ እንጂ ከውጭ ተጽዕኖ የሚመነጭ አለመሆኑን አስገንዝበዋል። ወደፊት ስለሚከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ የሰጡት የባንክ ገዥው፤ በቀጣዩ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የፋይናንስ ገበያን ይበልጥ ማሳደግ እና ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ የሪፎርሙ ቀዳሚ አጀንዳዎች መሆናቸውን አመልክተዋል። ለዚህም ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ተከታታይነት ያለው የተቋማት አቅም ግንባታ፣ የፖሊሲ ቀጣይነት እና የግል ዘርፉን የሚመራውን ኢኮኖሚ መሸከም የሚችል ጠንካራ የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት ወሳኝ መሆኑን መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውነው ግብርና ተኮር የምርምር ሥራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Apr 15, 2026 30
ጅማ ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦የሚያከናውናቸው ግብርና ተኮር የምርምር ሥራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን ዘርፈ ብዙ የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ ግብርና ተኮር የምርምር ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በጅማ ዞን እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግም የተፈጥሮ ማዳበሪያን አምርቶ ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል። የተፈጥሮ ማዳበሪያው በባዮቻር (Biochar) ላይ ተመስርቶ የተመረተ ሲሆን፣ የአፈር ጤንነትን በማሻሻል ምርታማነትን ከማሳደግ በተጨማሪ አካባቢን ከኬሚካል ተፅዕኖ ለመጠበቅ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። 'ባዮቻር' የእርሻ ተረፈ ምርቶችና የቅጠላ ቅጠል ውጤቶችን በከፍተኛ ሙቀት በማቃጠል የሚገኝ የከሰል ዓይነት ሲሆን ይህም የከሰል ዓይነት የሚዘጋጅበት ዋነኛ ዓላማ ለማገዶነት ሳይሆን የአፈርን ለምነት ጠብቆ ለማቆየት ነው። በተጨማሪም የአፈር ለምነትን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም መረጃዎች ያሳያሉ ። በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ ምክትል ዲን ፍቅረማርያም ገዳ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምር ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከሚያደርጉ የምርምር ስራዎች አንዱ በባዮቻር ላይ የተመሠረተ ማዳበሪያን ተደራሽ ማድረግ መሆኑን ገልጸው በእስካሁኑ ሂደትም ከ500 በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያውን በአርሲ እና በባቱ ከሚገኙ የምርምር ማዕከላት ጋር በመሆን ለአርሶ አደሩ የማስፋፋት ሥራ እየተሠራ ሲሆን ፤ በተጨማሪም በሲዳማ ክልልም ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በጅማ ብቻ ከ300 በላይ አርሶ አደሮች የተፈጥሮ ማዳበሪያውን ከመጠቀም ባሻገር ሥልጠና ወስደው እራሳቸው በማምረት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። ቡኖ በደሌ ዞንን ጨምሮ በአጎራባች ዞኖች ለባለሙያዎች እና ለአርሶ አደሮችም ሰፊ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርና እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ሚልኪያስ አህመድ (ዶ/ር) ለማዳበሪያው ዝግጅት አስፈላጊ የሆነው ባዮቻር አገልግሎት ላይ ካልዋሉ ተረፈ ምርቶች የሚዘጋጅ መሆኑን አመልክተዋል። የምርምር ሥራው ላለፉት 12 ዓመታት ሲሞከር እንደነበር የገለጹት ተመራማሪው ከ3 ዓመታት ወዲህ ግን ተጨባጭ ለውጥ በማምጣቱ እንዲስፋፋ እየተደረገ ነው ብለዋል። በጅማ ዞን የዴዶ ወረዳ ነዋሪው አርሶ አደር ቢያ ሀጂ፤ በምርምር ውጤቱ የተገኘውን ማዳበሪያ ተጠቅመው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በተሰጣቸው ሥልጠና መሠረትም ወደ ማምረት ሥራ ገብተው 10 ኩንታል የባዮቻር የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረታቸውን ገልጸዋል። ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ራያ አባፊጣ ፤ተመራማሪዎቹ ባቀረቡት የተፈጥሮ ማዳበሪያን ተጠራጥረው እንደነበር ገልጸው፤ ሆኖም ውጤታማ መሆኑን ካወቅኩ በኋላ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ወደ ማምረት ስራ ገብቻለሁ ብለዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም የጅማ ዞን ወረዳዎች ለማዳረስ እንዲሁም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋፋት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቷል
Apr 14, 2026 482
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፦የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የትምህርትና ክህሎት ለሥራ (ኢዝ) ፕሮጀክት አስተባባሪ ገለጹ። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የትምህርትና ክህሎት ለሥራ (ኢዝ) ፕሮጀክት ለ12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የሥራና ክህሎት ቢሮዎች የአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማት ድጋፎች አድርጓል። ሚኒስቴሩ ድጋፍ ካደረጋቸው መካከል ኮምፒውተሮች፣ የኔትወርክ መሰረተ ልማት ቁሳቁሶች፣ ለቪዲዮ ኮንፍረንስ የሚያገለግሉ ቴሌቪዥኖች፣ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ጄኔሬተሮችና የሶላር ፓኔሎች ይገኙበታል። በሚኒስቴሩ የኢዝ ፕሮጀክት አስተባባሪና የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ሀፍቶም ገብረእግዚአብሄር እንዳሉት፤ የሥልጠና ማዕከላትን በዘመናዊ መንገድ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ማሟላት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። ለአብነትም ሚኒስቴሩ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 70 ኮሌጆች አስፈላጊው መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው መደረጉን ጠቁመው፤ በዚህም የሥልጠና አቅምን ከፍ ያደረጉ ውጤቶች እየተገኘበት ነው ብለዋል። ዛሬ ፕሮጀክቱ ለ12ቱ ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ያደረገው የአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማቶች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ዓይነተኛ ሚና እንዳለውም አክለዋል። ድጋፉ እንደ ሀገር ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብርን ስኬታማ ከማድረግ አኳያ ፋይዳ እንዳለውም አብራርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዳግማዊት ግርማ፤ ወጣቱ የዲጂታል ክህሎት አዳብሮ የርቀት ሥራዎች (ሪሞት ጆብስን) ጨምሮ አዳዲስ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች መገኘታቸው ለሥራው መቃናት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ነስረዲን ቃዲ በበኩላቸው፤ በክልሉ ከመደበኛ ስልጠና ባሻገር የነዋሪዎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ያለመ ሕዝባዊ ስልጠና መርሃ ግብር ተጀምሯል ብለዋል። ዛሬ የተገኘው ድጋፍ ሥራውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዓለሙ ገብሬ እንደገለጹት፤ ድጋፉ በክልሉ የሚገኙ የሥልጠና ማዕከላት ሥልጠናዎችን በጥራትና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ እንዲያደርጉ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች ለመላው አፍሪካ ኩራት ናቸው
Apr 14, 2026 280
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች ለመላው አፍሪካ ኩራት ናቸው ሲሉ የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ ገለፁ። ኢትዮጵያ በውጭ አገልግሎት አሰጣጥ (outsourcing) እና በፈጠራ ዘርፍ በአህጉሪቱ ተወዳዳሪና የማይበገር አቅም እየገነባች መሆኑንም ገልጸዋል። የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክን ጎብኝቷል። ሚኒስትሯ ሳራ ቤይሶሎው ኒያ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የታዩ ለውጦች ለመላው አፍሪካ ኩራት ናቸው። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያላቸውን ፍላጎትም ገልጸዋል። በተለይም በቴክኖሎጂ፣ በግብርና እና በትምህርት ዘርፎች ላይ በትብብር በመሥራት የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል። አፍሪካ ያላትን ሰፊ የሰው ሀይል በተለይም የወጣቶችን ኃይል በአግባቡ ለጠቀም በ"ደቡብ-ደቡብ" አገራት መካከል ያለው ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። በአፍሪካ ደረጃ በጋራና በቅንጅት ከተሰራ አህጉሪቷን በልማት ማሳደግ እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተዋል። በአይ ሲቲ ፓርክ የተመለከቷቸውን የዳታ ማዕከላት አስመልክተው ኢትዮጵያ በውጭ አገልግሎት አሰጣጥ (outsourcing) እና በፈጠራ ረገድ በአህጉሪቱ ተወዳዳሪና የማይበገር አቅም እየገነባች መምጣቷን ገልፀዋል። በተለይም ወጣቶች አዳዲስ ግኝቶችን እንዲያመነጩ በፓርኩ ውስጥ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ለሌሎች አገራት ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል። በተለይም የዳታ ማዕከሉ አፍሪካ የራሷን መረጃ በራሷ አቅም የመያዝ ብቃት እንዳላት ማሳያ መሆኑንም ገልጸው፤ ላይቤሪያ ከኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተሞክሮ በመቀመር የራሷን የዳታ ማከማቻ ማዕከል ለመገንባት ያላትን ፍላጎት አረጋግጠዋል። ጉብኝቱ በሁለቱ ጥንታዊ አፍሪካዊ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ አጋርነት የሚያሸጋግር መሆኑ ተመላክቷል። በላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የተመራ ልዑክ ለስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል
Apr 14, 2026 222
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን ገለጹ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ የሆነው የ 5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በጅማ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች ዘንድ ትልቅ መነቃቃትን እየፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል። ስልጠናው የሠራተኞችን የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑም ተገልጿል። ሰራተኞቹ እንደሚናገሩት፤ የስልጠናው መርሃ ግብር በሥራቸው ላይ ተጨማሪ ዕውቀትና ክህሎት ጨምሮላቸዋል። በኢፌዲሪ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጅማ ዲስትሪክት ሠራተኞች የሆኑት ምህረት ካሳ እና ቁምነገር ወርቅዬ፣ ተቋሙ የኮምፒውተርና የኢንተርኔት አገልግሎትን ምቹ በማድረጉ የተለያዩ ኮርሶች መውሰዳቸውን ይናገራሉ። ከስልጠናው በኋላም በተቋሙ ውስጥ ለሚሰሩት ሥራ ትልቅ እገዛ ማድረጉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሥልጠና ሰርተፊኬት ማግኘት መቻላቸውን ጠቅሰው፣ ሌሎች ሠራተኞችም ዕድሉን እንዲጠቀሙበት መክረዋል። የዲስትሪክቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን መሸሻ በበኩላቸው፣ ከተቋሙ 140 ሠራተኞች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ስልጠናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ቀሪዎቹም ስልጠናውን እንዲያገኙ የግንዛቤ ማስጨበጥና የቴክኖሎጂ አቅርቦትን የማመቻቸት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በጅማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ውስጥ የሚሰሩት ሙስሊማ አወል እና መሐመድ ኃይደር፣ አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ባለበት በዚህ ወቅት ስልጠናው እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። "ከመደበኛ ሥራችን ጎን ለጎን ስልጠናውን መውሰዳችን ሥራችንን ይበልጥ ለማቀላጠፍና ለማስፋት እያገዘን ነው" ብለዋል። የማዕከሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አብዲ ሰለሞን እንደገለጹት፣ ከተቋሙ 104 ሠራተኞች መካከል 80 ያህሉ ስልጠናውን አጠናቅቀው ሰርተፊኬት ወስደዋል። ስልጠናው ሠራተኞች ለማኅበረሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት በእውቀት ላይ የተመሠረተና ፈጣን እንዲሆን እያስቻለ መሆኑንም አክለዋል።
ስፖርት
ሃዋሳ ከተማ ከምድረ ገነት ሽሬ መቻል ከድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ዛሬ ይጠበቃሉ
Apr 15, 2026 74
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል። ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ሃዋሳ ከተማ ከምድረ ገነት ሽሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ሃዋሳ ከተማ በውድድር ዓመቱ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ በ11ዱ ሲያሸንፍ በሰባቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል። 30 ግቦችን በ26ቱ ጨዋታዎች ላይ ሲያስቆጥር 21 ጎሎችን አስተናግዷል። ሃዋሳ ከተማ በ41 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ ካከናወናቸው 26 ጨዋታዎች መካከል ስድስቱን ያሸነፈው ምድረ ገነት ሽሬ በበኩሉ 10 ጊዜ ተሸንፏል። 10 ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። 17 ግቦችን ሲያገባ 21 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ምድረ ገነት ሽሬ በ28 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሃዋሳ ከተማ ማሸነፍ በዋንጫ ፉክክሩ ለመቆየት የሚያስችለውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያገኛል። ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደርጋል። ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች አንዱንም ማሸነፍ ያልቻለው ምድረ ገነት ሽሬ ሶስት ነጥብ ማግኘት ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ጥረት ወሳኝ የሚባል ነው። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ከሚያዚያ 5 ወደ ዛሬ የተሸጋገረ ነው። በሌላኛው መርሐ ግብር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከመቻል በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ካደረጋቸው 26 ጨዋታዎች መካከል ሰባቱን ሲያሸንፍ ስምንት ጊዜ ተሸንፏል። 11 ጊዜ አቻ ተለያይቷል። 18 ግቦችን በጨዋታዎቹ ላይ ሲያስቆጥር 25 ጎሎችን አስተናግዷል። ቡድኑ በ32 ነጥብ 14ተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው መቻል በበኩሉ በውድድር ዓመቱ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ በ10ሩ ድል ሲቀናው ስድስት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ 10 ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል። 33 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 21 ግቦች ተቆጥረውበታል። መቻል በ40 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ26ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ምድረ ገነት ሽሬን 1 ለ 0፣ መቻል የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፈዋል። ሁለቱም ቡድኖች በድል ጉዟቸው ለመቀጠል ይፋለማሉ። በሌላኛው መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ባካሄዳቸው 26 ጨዋታዎች ስድስት ጊዜ ሲያሸንፍ ዘጠኝ ጊዜ ተሸንፏል። በ11 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል። 20 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ በተመሳሳይ 20 ጎሎች ተቆጥረውበታል። መድን በ29 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ ከ26 የሊጉ ጨዋታዎች መካከል ሰባቱን ሲያሸንፍ በአምስቱ ሽንፈት አጋጥሞታል። በ14 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 19 ግቦች ሲያስቆጥር 18 ግቦችን አስተናግዷል። ባህር ዳር ከተማ በ35 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል ያልቀናው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስጋት በመጠኑ እንዲርቅ ያስችለዋል። በ26ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን 2 ለ 1 የረታው ባህር ዳር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በርካታ ጊዜ (በ14 ጨዋታዎች ) አቻ የወጣ ቡድን ነው።
የባየር ሙኒክ እና የሪያል ማድሪድ ተጠባቂ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ
Apr 15, 2026 172
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቀሪ ሁለት የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ይካሄዳሉ። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ባየር ሙኒክ ከሪያል ማድሪድ 75 ሺህ 24 ተመልካቾችን በሚያስተናግደው አሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በበርናባው ባካሄዱት ጨዋታ ባየር ሙኒክ 2 ለ 1 አሸንፏል። ሉዊስ ዲያዝ እና ሃሪ ኬን የማሸነፊያ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። ኪሊያን ምባፔ ለማድሪድ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱ ባየር ሙኒክ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ያለውን እድል የተሻለ አድርጓል። የ15 ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሪያል ማድሪድ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የመግባት እድሉ ያበቃለት አይደለም። በሻምፒዮንስ ሊጉ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ማድሪድ ውጤቱን ለመቀልበስ ጠንካራውን ባየር ሙኒክ ማሸነፍ ይጠበቅበታል። የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ባየር ሙኒክ፣ ወደ ግማሽ ፍፃሜው (አራት ውስጥ) የመግባት ዕድሉ በራሱ እጅ ላይ ይገኛል። በሌላኛው መርሐ ግብር አርሰናል ስፖርቲንግ ሊዝበንን ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ያስተናግዳል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አርሰናል ከሜዳው ውጪ በካይ ሃቫርትዝ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል። አርሰናል ወደ ግማሽ ፍጻሜ የመግባት ሰፊ ግምት አግኝቷል። የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በውድድሩ ጠንካራ ቡድን የሆነውን አርሰናልን ከሜዳው ውጪ የማሸነፍ ከባድ የቤት ስራ ይጠብቀዋል። ትናንት በተደረጉ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ፒኤስጂ ሊቨርፑልን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ባርሴሎናን በድምር ውጤት በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
ፒኤስጂ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለግማሽ ፍጻሜ አለፉ
Apr 15, 2026 125
አዲስን አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል። በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፒኤስጂ ሊቨርፑልን 2 ለ 0 አሸንፏል። ኡስማን ዴምቤሌ በ72ኛው እና 91ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎሎቹን አስቆጥሯል። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ በድምር ውጤት 4 ለ 0 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ፒኤስጂ በግማሽ ፍጻሜው ከባየር ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ አሸናፊ ጋር ይጫወታል። በሌላኛው መርሐ ግብር ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል። በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ላሚን ያማል እና ፌራን ቶሬስ ለባርሴሎና ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አዴሞላ ሉክማን ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። የባርሴሎናው ኤሪክ ጋርሺያ በ80ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። በመጀመሪያው ጨዋታም የባርሴሎናው ፓው ኩባርሲ በቀይ ካርድ መውጣቱ የሚታወስ ነው። በጨዋታው ባርሴሎና ብልጫ ቢወስድም ጨዋታውን ለመቀልበስ የሚያስችሉ ተጨማሪ ጎሎችን ማስቆጠር አልቻለም። ውጤቱን ተከትሎ አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር ውጤት 3 ለ 2 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። የማድሪዱ ክለብ በግማሽ ፍጻሜው ከአርሰናል እና ስፖርቲንግ ሊዝበን አሸናፊ ጋር ይጫወታል። የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ነገም ሲቀጥል ባየር ሙኒክ ከሪያል ማድሪድ እና አርሰናል ከስፖርቲንግ ሊዝበን ይጫወታሉ።
ፋሲል ከነማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
Apr 14, 2026 260
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ20ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ታምራት በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ዘጠኝ አድርሷል። ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ፋሲል ከነማ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በ31 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል። ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አመርቂ ውጤት ተገኝቶበታል
Apr 15, 2026 31
ወላይታ ሶዶ ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች አመርቂ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ። በክልሉ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የበልግ ወቅት ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር "አረንጓዴ አሻራ ለተምሳሌት ሀገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ሼላ ቦርኮሼ ቀበሌ ተካሂዷል። የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ባለፉት የለውጥ አመታት ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አመርቂ ዉጤት ተገኝቶበታል፡፡ መርሃ ግብሩ የተራቆቱና ከጥቅም ውጭ የነበሩ መሬቶች ለምተው እንደገና ጥቅም እንዲሰጡ ከማድረጉ ባሻገር 18 ነጥብ 95 ከመቶ የነበረውን የክልሉን የደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 86 ከመቶ በላይ ለማሳደግ ማስቻሉን ገልጸዋል። የችግኝ ተከላው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ በመሆኑም ለተያዘው የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላም በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል። በዘርፉ የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠልም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ ወጥቶ ችግኝ መትከልና መንከባከብ እንደሚገባውም አሳስበዋል። በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊና የዲላ ክላስተር አስባባሪ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸዉ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ በበጋው ወራትም 1 ሺህ 384 የማህበረሰብ ተፋሰስ ውስጥ 159 ሺህ ሄክታር መሬት በዋና ዋና የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ስራዎች መሸፈናቸውም ገልጸዋል። በበልግ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የጥምር ደን ፣ የፍራፍሬ ፣ የሀገር በቀል እጽዋት፣ የቡና ፣ የእንሰት ፣የጥላና የጌጥ ዛፍ ችግኞች ተከላ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጎድቶ የነበረውን የተፈጥሮ ሀብት መመለስ ተችሏል ያሉት ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዞኑ 16 ተራራዎችን ለማልማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮ የበልግ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሆንም አብራርተዋል።
በሐረሪ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተጠናከረ ዝግጅት እየተደረገ ነው
Apr 15, 2026 53
ሐረር ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆኑን የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት አጠቃቀም እና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አራርሶ አደም፤ ለኢዜአ እንደገለጹት ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ላላቸው የችግኝ ዓይነቶች ትኩረት ተሰጥቷል። የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ ከወዲሁ የችግኝ ማፍላትና የተከላ ቦታ መለየትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል። በመጪው ክረምት በክልሉ የተራቆቱ አካባቢዎችን ስነ-ምህዳር ለመመለስ የሚያስችሉና የደንነት ጠቀሜታ ካላቸው ችግኞች በተጓዳኝ ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየፈሉ መሆኑን ተናግረዋል። ችግኞቹም በመንግስት የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችና በግለሰቦች እየተዘጋጁ መሆኑን አንስተው ከእነዚህ ችግኞች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውን አብራርተዋል። ቀሪዎቹ ችግኞች ደግሞ ሀገር በቀል ዛፎችና፣ ለእንስሳት መኖና ለደን አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን አቶ አራርሶ አክለዋል። ጥምር ጥቅም የሚሰጡት የአፕል፣ የማንጎና የአቮካዶ ችግኞችም በክላስተር እንደሚተከሉ ጠቁመዋል። በክረምቱ ወራት በክልሉ የሚተከሉት ችግኞች 1ሺህ ሄክታር የሚሆን መሬት በስነ ህይወት ለማልበስና መልሶ ለማልማት ግብ መቀመጡን ጠቁመው ለዚህም ከወዲሁ የቦታ መረጣ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። ችግኞቹ በተራቆቱ አካባቢዎችንና በማህበረሰቡ ተሳትፎ በ600 ሄክታር መሬት የተፋሰስ ልማት በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ቦታ ላይ እንደሚተከሉም አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ክረምት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር በተራቆቱ አካባቢዎች የተተከሉት ችግኞች በሚደረግላቸው እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አቶ አራርሶ አክለዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
Apr 15, 2026 148
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፡- በድሬዳዋ አስተዳደር ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የፍራፍሬ እና ለደንነት የሚውሉ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የአስተዳደሩ የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ባለስልጣን አስታወቀ። ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዓመታት በአስተዳደሩ የተተከሉ ችግኞች የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የገጠሩን ማህበረሰብ ከተረጂነት ወደ አምራችነት እያሸጋገሩ መሆናቸውም ተመላክቷል። በድሬደዋ አስተዳደር የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ባለስልጣን የደን ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በአስተዳደሩ በሚገኙ ከ20 በላይ የችግኝ ጣቢያዎች የተለያዩ ችግኞች በጥራት እየተዘጋጁ ነው። ከአስተዳደሩ ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የፍራፍሬ፣ የደንና የውበት ችግኞች በማፍላት ለተከላ ዝግጁ እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። በዘንድሮ ክረምት ከሚተከሉት ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ከድሬደዋ ስነምህዳርና አየር ንብረት ጋር ስምሙ የሆኑ የተለያዩ ፍራፍሬዎች መሆናቸውን አንስተዋል። የሚተከሉት ፍራፍሬዎች በተለይም የገጠሩን ማህበረሰብ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገርና የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እያገዙ መሆናቸውን በማስገንዘብ። አቶ ማስረሻ አክለውም ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በአስተዳደሩ የተተከሉት ችግኞች ከ80 በመቶ በላይ ፀድቀው የግብርናን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ምቹ መደላድል ከመፍጠር በዘለለ የሌማት ትሩፋት መርሃግብርን ውጤታማ እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል። በባለስልጣኑ የደን ልማት ቡድን መሪ አቶ ማሙሽ ዘውዴ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሰባት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የተተከሉት ችግኞች የድሬዳዋን በረሃማ ስነምህዳር በመቀየር የከተማዋን የጎርፍ ተጋላጭነት እያስቀሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በተለይም በገጠር ቀበሌዎች የተተከሉት የሎሚ፣ የፓፓያ፣ የብርትኳን እና ሌሎች ምርጥ የፍራፍሬ ችግኞች የአርሶአደሩን ገቢ በመጨመር እና ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ተጨባጭ ውጤቶች እያስገኙ ናቸው ብለዋል። እነዚህን ፍሬያማ ውጤቶች ለማስቀጠል በአሁን ሰዓት እየጣለ የሚገኘውን የበልግ ዝናብ ጥቅም ላይ በማዋል 75 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞች በገጠር ቀበሌዎች መተከላቸውን ለአብነት አንስተዋል። እንደ አቶ ማሙሽ ገለፃ ባለፈው ጥር ወር የተካሄደው የተፋሰስ ልማት በአስተዳደሩ ለሚተከሉት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የጉድጓድ ቁፋሮ እና ሌሎች ዝግጅቶች በከፊል እንዲጠናቀቁ አስችሏል። እነዚህ የቅድመ ተከላ ዝግጅቶች የመጪውን ክረምት የችግኝ ተከላ በላቀ እና በተናበበ መንገድ ዳር ለማድረስ እንደሚያስችሉም አንስተዋል። በአስተዳደሩ ባለፉት ሰባት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎች ህብረተሰቡንና ባለድርሻዎችን በማስተባበር የተለያዩ የደን፣ የውበት እና የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለው የድሬደዋን የደንና ስነምህዳር በከፍተኛ ደረጃ እየለወጡ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ ተጠቃሚ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ
Apr 14, 2026 90
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፡-በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ ተጠቃሚ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ለበልግ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እንደሚጠናከር አስታውቋል። በዚህም በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸዉ በሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች፣ ስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖራቸው ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንዲሁ። የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ ሰሜን ምዕራብና የምዕራብ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል። በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጿል። በሚያዚያ የመጀመሪያዉ አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ3 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆንም ተመላክቷል። በመደበኛ ሁኔታ የበልግ ዝናብ በአብዛኛዎቹ በልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ እስከ ሚያዚያ የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት ቀጣይነት የሚኖረው ሲሆን በተጨማሪም ከሚጠናከሩት ሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ጋር ተያይዞ ወቅታዊው ዝናብ ቀስ በቀስ ወደ ምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እንደሚስፋፋ ተገልጿል። በሚያዚያ የመጪዎቹ አሥር ቀናት በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ዝናብ ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ ገጽታ እንደሚኖራቸው ትንበያው አመላክቷል። በመሆኑም በልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል። በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተመላክቷል። ዋነኛ እና ሁለተኛ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚና የበልግ ሰብል አብቃይ በሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ፤ የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች የስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎችና የመካከለኛው የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች የተስፋፋ እርጥበት እንደሚያገኙ ተመላክቷል። እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ሰሜን ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተስፋፋ እርጥበት ያገኛሉ ተብሏል። በመሆኑም አርሶ አደሮች አርብቶ አደሮች እና የሚመለከታቸው አካላት የሚጠበቁ መልካም ሁኔታዎችን በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳስቧል። እንዲሁም ሊኖር የሚችሉ ተያያዥ ስጋቶችን ለመቀነስ የተቀመጡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ኢንስቲትዩት አስገንዝቧል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 419
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ሊቀ መንበርነትን ተረከበች
Apr 3, 2026 330
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የእ.አ.አ አፕሪል 2026 የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት (AU PSC) ተዘዋዋሪ ሊቀመንበርነትን በይፋ መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ ሊቀ መንበርነቱን የተረከበችው ከኮትዲቯር ነው። ኢትዮጵያ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በሊቀመንበርነት መምራት እንደምትጀምር ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2025 በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል ሆና ከተመረጠች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊቀ መንበር መሆን ችላለች። በሊቀመንበርነት ቆይታዋ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ በሚገኙ አገራዊ እና ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን እንደምትመራ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያን ሊቀ መንበርነት በይፋ ለማብሰር እና አዲስ የተመረጡ የምክር ቤቱን አባላት ለመቀበል መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሰብሳቢነት የሰንደቅ ዓላማ የማውለብለብ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2004 ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ጀምሮ በአባልነት ስታገለግል የቆየች መሆኑን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ እ.አ.አ በ2025 በድጋሚ ለሦስት ዓመታት አባል ሆና መመረጧን አውስቷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም አራት ጊዜ የምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣ በንቃት ስትሳተፍ መቆየቷ ተወስቷል።
ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል
Mar 28, 2026 622
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አስገነዘቡ። 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው እየተሳተፋ የሚገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ተለዋዋጭ በሆነው የአለም የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ውስጥ የአባል ሀገራቱን ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ ድርጅት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም በአፅንኦት ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በንግግራቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ ይበጃሉ ያላቸውን ሀሳቦችም አካፍለዋል። በዚህም ድርጅቱ የብዙኃነት አቅም ያለው በመሆኑ ይህን አቅም ወደ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ማምጣት ያስፈልጋል ነው ያሉት። ለዚህም የደቡብ - ደቡብ ግንኙነትን ማጠናከር ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ያሉ ሲሆን መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚን ከገነቡ ሀገራትና ድርጅቶች ጋር ያለን ግንኙነት ከቀደመው የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ ግንኙነት ወደ የጋራ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር እንዳለባቸውም ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባትና ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን መስራት የአባል ሀገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት አባል ሀገራት ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸው ሚና ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት(አምራችነት) መሸጋገር እንዳለበትም ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዳይ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ባስመዘገበቻቸው ውጤቶች ቀጣዩን የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ መመርጧን አስታውሰዋል። ይህም የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ልማት በመገንባት ሂደት ያላቸውን ተሞክሮ የሚያቀርቡበት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በበኩላቸው ሶስቱም ቀጣናዎች የጎላ አስተዋጽኦ ባላደረጉበት የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገዱ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ፍትህ እንዲረጋገጥ የተባበረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በጉባኤው አፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ክልሎችን የወከሉ መሪዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን አፍሪካን በመወከል የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ መልእከት አስተላልፈዋል። የድርጅቱን የፋይናንስ ምንጭ ቀጣይነት ማረጋገጥ፣ የድርጅቱን መዋቅራዊ አሰራር ማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ አቋም መያዝ በጉባኤው ጎልተው የተሰሙ ድምፆች መሆናቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል። በማላቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ እየተካሄደ የሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ፣ ካርቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ እስከ ነገ መጋቢት 20/2018 ዓም ድረስ ይቆያል። በጉባኤው ከሶስቱም ክልሎች የሚገኙ የሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የዓለም የውሃ ቀን እየተከበረ ነው
Mar 22, 2026 312
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ 34ኛው የዓለም የውሃ ቀን ዛሬ በዓለም ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። “ውሃ እና ስርዓተ ጾታ” የዘንድሮ መሪ ቃል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሃ ቀን ቁልፍ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል። ተመድ የዓለም የውሃ ቀውስ ለሁሉም ሰው የሚተርፍ ቢሆንም ተፅዕኖው ግን እኩል እንዳልሆነ አመልክቷል። ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እና የንጽሕና መጠበቂያ አገልግሎቶችን የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው በማይከበርባቸው ቦታዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነት ጎልቶ እንደሚታይ ገልጿል። በዚህም ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋነኛ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቅሶ ሴቶችና ልጃገረዶች የውሃ መፍትሔዎች ማዕከል የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል። ሴቶች የውሃን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መቅረጽ አለባቸው ያለው ተመድ ለዚህም የሴቶች ድምፅ፣ አመራር እና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያስታወቀው። በዘንድሮው የዓለም ውሃ ቀን ከሚተላለፉ መልዕክቶች አንዱ ውሃ ባለበት እኩልነት ያብባል የሚለው እሳቤ ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች በውሃ ውሳኔዎች ላይ እኩል ድምፅ ሲኖራቸው፣ አገልግሎቶቹ ይበልጥ አካታች፣ ቀጣይነት ያላቸው እና ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመድ አመልክቷል። ለሁሉም የሚተርፍ ጤናማ፣ የበለጸገ እና እኩልነት የሰፈነበት መጻኢ ጊዜን ለመገንባት፤ የሴቶች የውሃ ዘርፍ አመራር ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስራን ማከናወን እንደሚገባም አስታውቋል። የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። እ.አ.አ 1992 በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ አየር እና ልማት ኮንፍረንስ (ሪዮ ኮንፍረንስ) የዓለም መሪዎች የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል። ከኮንፈረንሱ ውጤቶች መካከል አንዱ ውሃን አስመልክቶ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ያተኮረ ቀን የመሰየም ምክረ ሀሳብ ነው። በዚሁ መሰረት ተመድ እ.አ.አ 1992 ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማርች 22 እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ተከትሎ የዓለም የውሃ ቀን ከእ.አ.አ 1993 ጀምሮ እየተከበረ ይገኛል። በዓለም በላይ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ። የአየር ንብረት ለውጥ እና ፈጣን የህዝብ እድገት ለውሃ እጥረት ዋንኛ መንስኤዎች ናቸው።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 13, 2026 179
በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ አንዱ ምሰሶ - የስንዴ ልማት በሙሴ መለሰ ስንዴ በኢትዮጵያ በከፍትኛ ደረጀ ከሚመረቱና ለግብይት ከሚውሉ የሰብል ምርቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ከሆኑ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች። ከ2011/2012 የምርት ዘመን በፊት ኢትዮጵያ በመኸር የምታለማው ስንዴ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሔክታር ያልበለጠ ነበር። የበጋ መስኖ ስንዴ ሲጀመርም 3 ሺህ ሔክታር ብቻ እንደነበር መረጃዎች ያመላክታሉ። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመኸር፣ በበጋ መስኖ እና በበልግ ወቅት 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ስንዴ እያለማች እንደምትገኝ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያስረዳል። ሚኒስቴሩ የ2018 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፤ 4 ነጥብ 29 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ስንዴ በማልማት ከበጋ መስኖ ስንዴ 175 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን መግለጹ ይታወሳል። በኢትዮጵያ በአብዛኛው የስንዴ ምርት የሚመረተው በአነስተኛ አርሶ አደሮች ነው። ባለፉት ዓመታት ግን የሜካናይዝድ እርሻ የስንዴ ምርቱን በእጥፍ እንደጨመረው ይገለጻል። መንግሥት መስኖን በመጠቀም ስንዴን በዓመት አንድ ጊዜ ከማምረት ወደ ሦስት ጊዜ ማምረት የሚቻልበትን አሰራር በመፍጠር የሀገሪቱን ምርታማነት ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ107 ሚሊየን ኩንታል በላይ ነው። ይህንን ፍላጎቷን ለመሙላት ለዓመታት ከ700 ሚሊየን ዶላር እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ለስንዴ ግዥ ወጪ ታደርግ ነበር። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከዓመታዊ የስንዴ ፍላጎቷ ከ25 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ትሸፍን የነበረውም ከውጭ በምትገዛው ስንዴ ነበር። መንግሥት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በማስፋፋትና በየዓመቱ የሚመረትበትን ዙር በመጨመር ኢትዮጵያ የስንዴ ፍጆታዋን ሙሉ በሙሉ እንድትሸፍን በትኩረት ሲሠራ ቆይቷል። በዚሁ በ2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገር ስንዴ ማስገባት አቆመች። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያገኘችው ውጤት ከውጭ ማስገባትን ማስቆም ብቻ አልነበረም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራስን ብቻ ሳይሆን ኤክስፖርት የማድረግ ዐቅም እንዳላት በመግለጽ፤ ስንዴ ወደ ውጪ መላክ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት ሀገራዊ ግብ መሰረት ኢትዮጵያ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ውጭ የመላክ ተግባርን በይፋ አስጀምራለች። የስንዴ ኤክስፖርቱ ኢትዮጵያ ገጽታዋን የሚለውጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ መግባቷን የሚያመላክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ገልጸው ነበር። ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ ዐቅም እንዳላት ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ አረጋግጧል። ኮሚቴው የሀገራዊ የነፍስ ወከፍ ፍጆታና የሀገሪቱን አጠቃላይ የምርት ሚዛን በማጥናት ከፍጆታ የሚተርፍ 32 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ወደ ውጭ መላክ እንደሚቻልም ተገልጿል። 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ባሳለፍነው የካቲት ወር በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄዱ የሚታወስ ነው። በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ከጉባዔው ጎን ለጎን በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ ተምሳሌታዊ የሆነ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ የስንዴ ምርታማነቷን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሸፈን ባለፈ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሏን ሕብረቱ መመልከት መቻሉንም ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት በዓመት ውስጥ ለምግብ ምርቶች ከሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ ስንዴ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ስንዴ መተካት እንደሚቻል በተግባር ያሳየችበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል። ኮሚሽነሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን ተሞክሮ ወስደው ወደ ተግባር እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ሥራ ላይ እያሳየች ያለውን ሥራ አስፍታ ከቀጠለች በምግብ ራሷን የመቻል ሕልሟን የማሳካት እድሏ ሰፊ መሆኑንም ማመላከታቸው ይታወሳል።
የጤና ነገር ...
Apr 3, 2026 2136
በዮሐንስ ደርበው የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። የኒውትሬሽን ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የሰው ልጅ የሰውነት ክፍል 60 በመቶው ውኃ እንደመሆኑ ለተስተካከለ ጤና ሚዛን መጠበቅ በቂ ውኃ መጠጣት ይገባል። ውኃን በትክክለኛው መጠንና ጊዜ መውሰድ ከተቻለ የኩላሊት ህመም ተጋላጭነትን 50 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ይጠቁማሉ። ነገር ግን ሰውነት የሚፈልገውን የውኃ መጠን በአግባቡ ካላገኘ ለዕለታዊ እና በጊዜ ሂደት ሥር ለሚሰድዱ ህመሞች የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምርም ያነሳሉ። ለመሆኑ ሰውነት የሚፈልገውና በቂ የውኃ መጠን የሚባለው መጠኑ ስንት ነው? በቂ ውኃ አለመጠጣትስ የሚያስከትለው ችግር ምንድን ነው? በሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ የኒውትሬሽን መምህር፣ ተመራማሪ እና ደራሲ ይሁኔ አየለ ምላሽ አላቸው። አንድ ሰው የሚያስፈልገው የውኃ መጠን በዕድሜ፣ ጾታ፣ በሥራ ባሕርይ፣ በመኖርያ አካባቢ፣ እንደ ጤና ሁኔታው እና እንደ ሰውነት ክብደቱ እንደሚወሰንም በምላሻቸው አስገንዝበዋል። ለምሳሌ የስኳር ታማሚዎች፣ የምታጠባ እናት፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች፣ ብዙ አድካሚና ላብ የሚያወጡ፣ በሞቃታማ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቀን 3 ሊትር ውኃ መጠጣት አለባቸው ይላሉ። በአማካይ ግን በቀን አንድ ሰው ከ2 እስከ 3 ሊትር ውኃ መጠጣት እንደሚጠበቅበት ይገልጻሉ። ጤናማ ሕይወት የሚመሠረተው ከውኃ ነው፤ ለምሳሌ ውኃማውን 60 በመቶ የሰውነት ክፍል ሚዛን ለማስጠበቅ የግድ አስፈላጊውን መጠን ውኃ መጠጣት እንደሚገባ ይመክራሉ። በሰውነት ውስጥ የሚካሄደው ሕይወታዊ ሂደት (ባዮሎጂካል ፕሮሰስ) ውኃን መሠረት ያደረገ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለምሳሌ ለተስተካከለ የሥርዓተ-ምግብ ሂደት፣ ቆሻሻን ከሰውነት አጣርቶ ለማስወጣት፣ የአጥንት መገጣጠሚያ ሥራን ለማስተካከል እና ለሌሎችም በርካታ የሰውነት ክፍሎች የተሳለጠ ተግባር ውኃ ቁልፍ መሆኑን አንስተዋል። ይህን ተከትሎም ውኃ ካሎሪ አልባው መድኃኒት (ተፈጥሯዊው መድኃኒት) እስከመባል መድረሱን ነው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያስረዱት። ሰውነት የሚያስፈልገውን ያህል ውኃ አለመጠጣት ግን ድካም ያስከትላል፤ ለማየት፣ ለመንቀሳቀስ፣ ለመሥራት፣ ለማሰብ፣ ለመረጋጋት . . . አያስችልምና ሲሉ ያብራራሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ ሰው ውኃ የመጠማት መጠኑ ከአራት በመቶ በላይ ከሆነ ለሞት ሊጋለጥ እንደሚችልም ጠቅሰዋል። ውኃ አለመጠጣት፤ የጨጓራ ህመምን በማባባስ ማስገሳት፣ የቆዳ ድርቀትና ግርጣት፣ የኩላሊት ህመም ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ያደርጋል ነው ያሉት። ከምግብ በፊት 30 ደቂቃ ቀድሞ ውኃ መጠጣት ውፍረትን ለመቀነስ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። በቂ ውኃ ከመጠጣት በተጨማሪ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ማዘውተር እንደሚመከርም ገልጸዋል። የፈላ ውኃ እና የዝናብ ውኃን በብዛት መጠጣት በሰውነት ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድና በኩላሊት ላይም ጫና እንደሚፈጥር አመላክተዋል። ለተስተካከለ ጤናማ ሕይወት የግድ ውኃ መጠጣትን ልማድ ማድረግ እንደሚገባም ይመክራሉ። #ውኃ_መጠጣት #ጤና #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency
ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች
Apr 3, 2026 2246
በዮሐንስ ደርበው የለውጡ መንግሥት ኢትዮጵያን ማሥተዳደር ከጀመረ እነሆ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ 8 ዓመት ሞላው። በእነዚህ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማኅበራዊ ዘርፉ በዲፕሎማሲውና በሌሎችም መስኮች የተለያዩ ስኬቶች ተከናውነዋል። በእነዚህ ጥቂት ዓመታትም ለማሳካት ቀርቶ ለማሳብ የማይደፈሩ ብዙ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። የተገኙት ስኬቶች ከጊዜያቸው የፈጠኑ ናቸው። ለዚህም ሕዝቡ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በነቂስ እየወጣ አድናቆቱን ገልጿል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሰጡት የሰላ አመራርነትና ቁርጠኝነትም አክብሮቱንና ምሥጋናውን ገልጿል። የለውጡ መንግሥት አካሄድ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የልማት ፕሮጀክቶችም በይበልጥ ተስፋፍተውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆሙም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ባስተጋቧቸው መልዕክቶቻቸው አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በለውጡ መንግሥት ለማሳካት ቀርቶ ለማሰብ የማይደፈሩ ተግባራት ተከናውነዋል። ከእነዚህ ከፍተኛ ጥቅም ከተገኘባቸው የታሪክ እጥፋትን ካሠረጹ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹን ቀጥለን በወፍ በረር እንዳሥሣለን። ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች ሥልጣኔ - በምርጫ ካርድ መምረጥ የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል። • የኮሪደር ልማት እንደምናውቀው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነትና ልዩ ትኩረት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ከሁሉም አስቀድሞ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። አሁን ላይ ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የበርካታ ከተሞችን ገጽታ የቀየሩ አስደማሚ ሥራዎች ተከናውነውበታል። ይህም በገጠር ጭምር ተጠናክሮ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ለዘመናት አሮጌ ገጽታዋን ይዛ ያሸለበችውን አዲስ አበባ እንደ አዲስ የፈጠራትም ይኸው ፕሮጀክት ነው። አሁን ላይ መዲናይቱ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባን ለውጥ ዐይተው ዝም ማለት አልቻሉም። ከመደመማቸው አንጻር የዘወትር አጀንዳቸውም እያደረጓት ይገኛሉ። ይህንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ ኮሪደር ልማት ማለት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት ነው ማለታቸው ይታወሳል። ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑንንም አስረድተዋል። ከለውጡ መንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፉን እንቅስቃሴ ለማሳደግም ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ድርብርብ ፕሮጀክት ነው የኮሪደር ልማት። • የበጋ መስኖ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የለውጡ መንግሥት ዋነኛ ትኩረቱ ነው። ለዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን አንዱ ማሳኪያ ሥልት አድርጎ እየተጋ ይገኛል። የበጋ መስኖ ስንዴ ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ ማስገባት አቁማ መላክ እንድትጀምር ያስቻለ ኢኒሼቲቭ ነው። በዘመናዊ የግብርና ዘዴዎችና በሜካናይዜሽን ታግዞ በስፋት እየተሠራበትም ይገኛል። ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በምርታማነት ማደግና የሥራ ዕድል በመፍጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል። የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብም ከፍተኛ ውጤት ተገኝቶበታል። ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ላይ ባሳየችው ትጋት፤ ፍጆታዋን በራሷ ዐቅም የሸፈነችው፣ ስንዴን ከውጭ ማስገባትን ያቆመችው፤ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችው በለውጡ መንግሥት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ በመሸለም ለጥረታቸው ዕውቅና መስጠቱም ይታወሳል። • መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል አንድ ጉዳይን ለማስፈጸም እዚያም እዚህም መንከራተት የግድ ነበር። በዚህ አያበቃምና ወረፋውም ሌላ ችግር ነው። መንግሥት በተለያዩ መድረኮች ባካሄዳቸው ሕዝባዊ ውይይቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉልን የሚሉ እሮሮዎች በረከቱ። መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል ሥራ ወደ ተግባር አሥገባ። በዚህም መሠረት ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ ጀመረ። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነውም አሉ። ለዚህ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ የሆነውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስጀመራቸውንም ገለጹ። እንግዲህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በመሰብሰብ በቴክኖሎጂ ታግዘው በተሳለጠ ሂደት እንዲሰጡ በማድረግ የተገልጋይን እንግልት፣ ገንዘብ እና ጊዜ መቀነስ ያስቻለ አሠራር ነው። እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት ተደርጎም ይወሰዳል። በየከተሞቹም እየተስፋፋ ነው። • አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ አይ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ ጉጉት እንዳላቸው በቁጭት በተለያዩ መድረኮች ያነሳሉ። ለዚህም መፍትሔ ዘይደው ተቋማትን ከማቋቋም ጀምሮ ለዘርፉ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ተግተዋል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ ለመጓዝ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን አቋቋመች። የኤ አይ ዩኒቨርሲቲ በመክፈት በግብርናው፣ በጤናው እና በሌሎችም ዘርፎች የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠርም በሂደት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት ቀይሮ ወደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ሕንፃ በተዛወረበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአምስት ዓመት ውስጥ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ መድረሱ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ በከፍተኛ ደረጃ የሚታይ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ የሮቦቶችን ሶፍትዌር ብቻ ሳይሆን ውጫዊ የአካል ክፍልን (ሃርድዌር) መሥራት ጀምሯል ብለዋል። ድሮን ማምረት ብቻ ሳይሆን የማነጋገር ዐቅም እየፈጠረ ያለ ተቋም መሆኑንም አንስተዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደር አሠራርን የሚከተል መሆኑን ጠቁመው፤ በርካታ ምርቶችን አውጥቷል ማለታቸው ይታወቃል። ብንፈልግም ባንፈልግም ራሳችንን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሂደት ውስጥ ማስገባት ካልቻልን ደረጃው የትም ቦታ ይሁን እንደ ሀገር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከትላልቅ ሪቮሉሽኖች ወደ ኋላ እንቀራለን ሲሉ ማስገንዘባቸውም ይታወሳል። • የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው። በዚህ ሂደት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊታአውራሪነት ይጠቀሳል። በተደራጀና ተቋማዊ ሆኖ ባልተቆራረጠ አካሄድ እየተከናወነ ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተተከሉ ችግኞችም በየዘርፉ ተጠቃሚነት አድጓል፤ ተጠናክሮም ይቀጥላል። • የሌማት ትሩፋት ከመጋቢት ሥጦታዎች አንዱ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ነው። የምርት አቅርቦትን በማስፋት ለተረጋጋ ግብይት እና ለተመጣጠነ ሥርዓተ-ምግብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይም ይገኛል። ኢኒሼቲቩ ለግብርና ኢንቨስትመንትና ለሀገራዊ የሥርዓተ-ምግብ መሻሻል ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ነው። የዋጋ ንረትን በማረጋጋት፣ የምርት ስብጥርን በማሳደግና በዘላቂነት በማቅረብ ረገድም የጎላ ሚና አለው። የግድ ሰፋፊ መሬት መፈለግ ሳያሻ በትንሽ ቦታ ብዙ በማምረት ፍጆታን ከመሸፈን አልፎ ኢኮኖሚን በመደጎም እና የሥራ ዕድል በመፍጠርም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። • የቱሪስት መዳረሻ ልማት ቅርሶች እንዲጠገኑ፣ አዳዲስ ሎጂዎች እንዲገነቡ፣ በመዳረሻ ስፍራዎች መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ያስቻሉ ተግባራት በለውጡ መንግሥት ተከናውነዋል፤ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ እና ስኬታማ ኢኒሼቲቭ ነው። በዚህ ሂደት ከሐሳብ አመንጭነት ባሻገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የጻፉትን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ጭምር ለቅርስ ጥገናና ለቤተ-መጻሕፍት ግንባታ እንዲውል አድርገዋል። በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት፤ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ትላልቅ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ ወደ ተግባር አስገብተዋል። በእነዚህ ኢኒሼቲቮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ትሩፋታቸውም ሰፊ አበርክቷቸውም በርካታ ሆኖ ብቅ ብሏል። አማራጭ የቱሪስት መዳረሻም ሆነዋል። • የተቋማት ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪል ሐሳብ በተካሄደው የዐበይት ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ኮንፈረንስ ላይ፤ የተቋማት ግንባታና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው ብለዋል። በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው ሲሉም አስገንዝበዋል በወቅቱ። ዘመን የማይለውጣቸው ዘላቂ ጠንካራ ሃገራዊ ተቋማትን በመገንባት ረገድ ብዙ ርቀት መጓዝም ተችሏል። በመሆኑም የመንግሥት ተቋማት ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲሆኑ በማድረግ እና ሥርዓት በተለዋወጠ ቁጥር የማይፈርሱ ወይም የሚሻገሩ ተቋማት መገንባት ተችሏል። ይህ ትጋት ተጠናክሮም ቀጥሏል።
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 3752
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … በኢዜአ ዐይን …! የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ትንታኔዎች
በፈተናዎች ሁሉ የጸናው የኢትዮጵያና የላይቤሪያ ወዳጅነት
Apr 14, 2026 716
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት አላቸው። ይሄ ወዳጅነት በፈተናዎች ጊዜ ሁሉ ጸንቶ የዘለቀም ነው። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ውስጥ ብቸኛ ነፃ ሀገራት በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች (ለምሳሌ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የአፍሪካውያን ድምፅ ሆነው በጋራ ይቆሙም ነበር። የሀገራቱ የወዳጅነት እና የትብብር ስምምነትም እ.አ.አ በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ የጀመረ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለው ዘላቂ ወዳጅነት እና በዓለም አቀፍ መድረኮች (እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) በጋራ ለመቆም ቃል የተገባበት ሰነድም ተደርጎ ይወሰዳል። የዘመናዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት የጣሉትም ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና ፕሬዝዳንት ዊሊያም ቱብማን ናቸው። እ.ኤ.አ. በ1954 ፕሬዝዳንት ቱብማን ወደ አዲስ አበባ ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ይፋዊ ግንኙነት እንዲጀመር በር ከፍቷል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እ.አ.አ. 1958 ጉብኝት ወደ ሞንሮቪያ በማድረግ፣ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ የነፃነት ንቅናቄዎችን በጋራ ለመደገፍ ተወያይተዋል። እነዚህ ጉብኝቶች የሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆኑ አህጉራዊ ፋይዳም ነበራቸው። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ሲመሰረት፣ ሁለቱ ሀገራት "የሞንሮቪያ" እና "የካዛብላንካ" ቡድኖችን ልዩነት በውይይት በመፍታት ለአህጉሪቱ አንድነት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አስመስክረዋል። በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ በ”ሞንሮቪያ ቡድን” እና "የካዛብላንካ ቡድን" መካከል የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በጋራ በመስራታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊመሰረት ችሏል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በችግር ውስጥ የተፈተነ ወዳጅነት ነው የሚል ሀሳብ በብዙዎች ይነሳል። የዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ነው። ላይቤሪያ ለ14 ዓመታት በዘለቀው አውዳሚ የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት መንግሥታዊ መዋቅሯ ፈርሶ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2003 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰላም እንዲያስከብሩ ከጠራቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ነበረች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ በርካታ ሰራዊቷን በማሰማራት ለሀገሪቷ ሰላም ዋጋ ከፍላለች። ሰራዊቱ አማፂያንን ትጥቅ በማስፈታት፣ ተዋጊዎች ከማህበረሰብ ጋር እንዲቀላቀሉ በማድረግ እና የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል። ዋና ከተማዋ ሞንሮቪያ እና በገጠራማ አካባቢዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዳይጣስ ጥብቅ ቁጥጥር አድርጓል። የኢትዮጵያ ሰራዊት የጤና ቡድን በየሰፈሩ በመዘዋወር ለላይቤሪያውያን ነፃ የህክምና እርዳታ እና መድሃኒትም ይሰጥ ነበር። ሰራዊቱ የራሱን ስንቅ ለተቸሩ ዜጎች በማካፈል ወንድማማችነትን በተግባር አሳይቷል። እ.ኤ.አ በ2014 የኢቦላ ወረርሽኝ በላይቤሪያ በከፋ ሁኔታ በተከሰተበት ወቅትም፣ ሌሎች ሀገራት ሰራዊታቸውን ሲያስወጡ ኢትዮጵያ ግን የህክምና ቡድኖችን እና ሰራዊቷን በማቆየት ከላይቤሪያ ህዝብ ጎን ቆማች። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሶስት ተከታታይ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች እንዲካሄዱ በሰላም ማስከበሩ ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የላይቤሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች የላቀ አገልግሎት ሜዳሊያ እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በላይቤሪያ የነበራት የሰላም ማስከበር ሚና ከወታደራዊ ተልዕኮ ባለፈ የደም እና የአጥንት መስዋዕትነት ከፍላለች። ይህ የሰራዊቱ ተሳትፎ ዛሬም ድረስ በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ላለው ጥብቅ ወዳጅነት ዋነኛው ምክንያት ተደርጎ ይወሳል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራቱ መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች ለሁለትዮሽ ትብብሩ መጠናከር አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እ.አ.አ በ2006 ስልጣን በያዙ ማግስት አዲስ አበባን ጎብኝተዋል። ይህም ኢትዮጵያ በላይቤሪያ ሰላም ለማስፈን ላደረገችው ድጋፍ እውቅና የሰጡበት ነበር። ሰርሊፍ በላይቤሪያ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ሲያበቃ እ.አ.አ ጁላይ 2015 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ለተደረገላቸው የህክምና ቡድን ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት እ.አ.አ በ2017 ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳላኝ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ፕሬዝዳንቷ በወቅቱ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን ላይቤሪያ ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ልማት ዘርፍ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ በወቅቱ ገልጸው ነበር። የላይቤሪያ የእግር ኳስ ኮከብ እና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ እ.አ.አ በ2018 ስልጣን ከያዙ በኋላ በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተሳተፉ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል። የቀድሞው የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ከማያህ እ.አ.አ በ2022 በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን (Joint Ministerial Commission) እንዲቋቋም ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በላይቤሪያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMIL) ላይ በነበረበት ወቅት፣ የተለያዩ የመከላከያ ሚኒስትሮች እና የጦር አዛዦች የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ኃይል ለመጎብኘት እና ከላይቤሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት በተደጋጋሚ ወደ ሞንሮቪያ ተጉዘዋል። ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ውይይቶች በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶችም ተፈራርመዋል። ሰላም ፣ ደህንነት፣ ጤና፣ የአየር አገልግሎት፣ የቪዛ ነፃ መብት ፣ የንግድ ትብብር ማዕቀፍ፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ባህል እና ስፖርት ስምምነት ከተደረገባቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ። የአየር አገልግሎት ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ ያለምንም ገደብ እንዲበር እና ላይቤሪያን ከቀሪው ዓለም ጋር ማገናኘት የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ ነው። የሰላም ማስከበር ስምምነቱ በተባበሩት መንግሥታት ማዕቀፍ ውስጥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንድትልክ የተደረገው ስምምነት በላይቤሪያ መረጋጋት እንዲመጣ ትልቅ ድርሻ ነበረው። በኪነ-ጥበብ እና በስፖርት ዘርፍ (በተለይም በእግር ኳስ) የሁለቱ ሀገራት ወጣቶች ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችሉ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአከይ እ.አ.አ 2023 ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡበት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ለማደስ እና በንግድ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም ከተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ጋር ውይይት አድርገዋል። የሁለትዮሽ ውይይቱ በቴክኖሎጂ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኢትዮጵያ ለመገንባት ባቀደችው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይቶቹ ላይ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል። በፕሬዝዳንቱ ቆይታ እጅግ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖራቸውም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የፕሬዝዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክርም ታምኖበታል። የኢትዮጵያ እና የላይቤሪያ መጻኢ ግንኙነት ከታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ አጋርነት የማሳደግ ፍላጎት በሁለቱም ወገን በኩል አለ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የአቪዬሽን ትስስር፣ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እና በአህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ማዕቀፍ የሚደረግ ትብብር ለጋራ ብልጽግና መሰረት ይጥላል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 11, 2026 158
ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዝያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል ፦ • ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው፤ ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው ብለዋል። የትንሣኤ በዓል ከሞት ባሻገር ሕይወት ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት መሆኑንም ገልፀው፤ ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው ብለዋል በመልዕክታቸው። የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን ሲሉ ገልፀዋል። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ በጥልቁ ጨለማ ጠፍተን እንድንቀር አሥረው ለመያዝ የሚሞክሩ ወጥመዶች ብዙ ናቸው፤ ወደ ተስፋ ምድር እንዳንሻገር የሚጎትቱ ሰበቦች ሞልተዋል፤ ዳሩ ግን ከሕማማቱ ወዲያ ትንሣኤ ከዕንቅፋቱ ባሻገር ስኬት እንደሚጠብቀን አምነን እንታገላለን ሲሉም አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ወደ ትንሣኤ መቃረቧን ገልፀው፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሚበሰርባቸው ምዕራፎች አንዱ ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ መሆኑንም አመላክተዋል። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም ብለዋል። • የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት ካደረጉት የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ አከናውነናል ሲሉም አስታውቀዋል። ስምምነቶቹ ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ የቆዩ ግንኙነቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ብለዋል። ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ሸኝተዋቸዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኢሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል ብለዋል። • የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ዓመታዊ አፈጻጸም ግምገማ ባሳላፍነው ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ፕሬዚዳንት ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት አድርገዋል። • የሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሹመት መራዘም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9) እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አሥተዳደርን በርዕሰ መሥተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አሥተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን ሹመት ለአንድ ዓመት አራዝመዋል። • ማዕድ ማጋራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ሕጻናት ማዕድ አጋርተዋል። • የአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ኅልፈተ ሕይወት አምባሳደር ቆንጅት፤ በዲፕሎማሲው መስክ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ላበረከቱት ጉልኅ አስተዋጽዖ፣ ለሰጡት አስተምኅሮና ለነበራቸው ብልኅ አመራር ምንጊዜም ሲታወሱ እንደሚኖሩ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባስተላለፉት የኀዘን መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል። ትጉኅና ከብረት የጠነከሩ ዲፕሎማት ነበሩ በማለት ለሙያቸው የነበራቸውን ጽኑ አቋምና የሀገር ፍቅር ስሜትም አንስተዋል። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት በማረፋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል። አምባሳደሯ ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል ብለዋል። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት የኀዘን መግለጫ መልዕክት፤ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ እና ታላቅ ዐሻራን ማሳረፍ የቻሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል። አምባሳደር ቆንጂት እስከ ከፍተኛ ዲፕሎማትነት በደረሰ ረጅም የሥራ ዘመናቸው ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ያስመዘገቡት ድል እና ያበረከቱት አስተዋጽዖ ሁልጊዜም በክብር የሚታወስ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ባሳለፍነው ሳምንት “ፖሊሳዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ 20ኛው የፖሊስ ኮሚሽነሮች መክፈቻ ጉባዔ ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት፤ የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ ፖሊስ በሚሰጠው አገልግሎት ታማኝም አሳማኝም መሆን አለበት ብሎ ያምናል ብለዋል። የፖሊስ ኃይላችን የጥፋት ኃይሎች በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት በአንድነት በመቆምና መስዋዕትነት በመክፈል ቀልብሷል፤ ይህም ለሁላችንም ኩራት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የፖሊስ አመራሮችና የሠራዊቱ አባላት በዕውቀት፣ በታማኝነትና በሕዝብ አገልጋይነት ሥነ-ልቦና ለላቀ ተልዕኮ እንድትዘጋጁ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
ከፓን አፍሪካኒዝም እስከ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት - የኢትዮጵያ እና ብሩንዲ የስድስት አስርት ዓመታት የዲፕሎማሲ ጉዞ
Apr 9, 2026 467
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያና የብሩንዲ ግንኙነት የሚጀምረው አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ለመውጣት በምትታገልበት ወሳኝ ወቅት እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት እንደመሆኗ፣ ብሩንዲ እ.ኤ.አ በ1962 ከቤልጂየም ቅኝ አገዛዝ ወጥታ ነፃነቷን ስታገኝ ግንኙነታቸውን በይፋ ከጀመሩ የመጀመሪያዎቹ አገራት ተርታ ትመደባለች። ይህ ግንኙነት በወቅቱ በነበረው የፓን-አፍሪካዊነት መንፈስ እና አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካዊ ችግሮች በሚለው መርህ ላይ የቆመ ነበር። ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ምስረታ ላይ የነበራቸው የጋራ ተሳትፎ ለዘመናት ለዘለቀው ወንድማማችነት ጠንካራ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አዳዲስ ከቅኝ ግዛት ነፃ የሚወጡ የአፍሪካ ሀገራትን ወደ አህጉራዊው መድረክ ለማምጣት በነበራቸው ራዕይ መሰረት፣ ከብሩንዲ የመጀመሪያው ንጉሥ ምዋሚ ምዋቡትሳ አራተኛ ጋር የጠበቀ ግንኙነት መስርተዋል። ግንኙነቱ በይፋ ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በኋላም (እ.አ.አ 1963) ብሩንዲ በአዲስ አበባ በተመሰረተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) ላይ በመስራች አባልነት እንድትሳተፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጋለች። በወቅቱ የነበረው የሀገራቱ ግንኙነት በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል እና በቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነበር። በወቅቱ ይደረጉ በነበሩ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብስባዎች ላይ ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ አህጉራዊ አጀንዳዎችን በጋራ አንጸባርቀዋል። ኢትዮጵያ በብሩንዲ የሰላም ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውታለች። በተለይም በብሩንዲ የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ጥረት እና በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (AMIB) ውስጥ የኢትዮጵያ ሰራዊት ቀዳሚ ተሳትፎ ነበረው። ልዑኩ በአፍሪካ ህብረት ታሪክ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ በአህጉሪቱ የተመራና የተደራጀ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንደሆነ ይወሳል። ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሞዛምቢክ ጋር በመሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ልካለች። ሰራዊቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲከበር ማድረግ፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ (DDR) ላይ ትልቅ ስራ ሰርቷል። ኢትዮጵያ በወታደራዊ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲው ረገድም ንቁ ተሳትፎ አድርጋለች። የአሩሻ የሰላም ስምምነት እንዲሳካ እና በብሩንዲ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በወቅቱ የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች በኢጋድ (IGAD) እና በአፍሪካ ህብረት በኩል ጫና ሲያደርጉና ሲያሸማግሉ ቆይተዋል። በብሩንዲ በተለያዩ ቡድኖች መካከል እምነት እንዲገነባ ኢትዮጵያ እንደ ገለልተኛ እና ታማኝ አደራዳሪ ትታይ ነበር። ተልዕኮው ስራውን አጠናቆ ወደ ተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (ONUB) ሲቀየርም የኢትዮጵያ ሰራዊት እዛው በመቆየት ለሰላሙ ዘላቂነት አስተዋፅኦ ማድረጉን ቀጥሏል። ይህም ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ይህም በሁለቱ ሀገራት ትብብር ውስጥ በትልቁ የሚነሳ እና የሚወሳ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም እና በፖለቲካዊ ወዳጅነት ላይ መሰረት አድርጎ የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት ወደ ተለያዩ መስኮች እየሰፋ መጥቷል። እ.አ.አ በ1970ዎቹ መጀመሪያ በሀገራቱ መካከል የተፈረሙ የንግድ እና የባህልን ትብብር የማጠናከር የጋራ መግባቢያ ሰነዶች የዚሁ ማሳያ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በሀገራቱ መካከል የተደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና የጋራ ስብሰባዎች ግንኙነቱን ከማጠናከር ባለፈ የትብብር አድማሱን ማስፋትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን ማየት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2023 በብሩንዲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ብሩንዲ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ አቪዬሽን እና ቀጣናዊ ሰላም ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው። በጉብኝቱ ወቅት ብሩንዲ የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት እና የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ በስፋት ለመተግበር ያላትን ፍላጎት አሳይታለች። የሁለትዮሽ ውይይቱ የተለያዩ ውጤቶች የተገኙበት ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን የሚያቀላጥፉ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ውሳኔ ተላልፏል። ኢትዮጵያ ለብሩንዲ በቴክኒክ እና በሙያ ስልጠና (TVET) ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች። የሀገራቱ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን (JMC) በየጊዜው እየተገናኘ ስምምነቶችን እንዲከታተል መመሪያ ተሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውይይቱ በተጨማሪ ግብርና እና ኢንዱስትሪን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2023ቱ የብሩንዲ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ በዋና ማሳያነት የሚጠቀስ ነው። የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ እ.አ.አ በ2021 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለብሩንዲ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ችግኞችን በስጦታ አበርክተው ነበር። ይህም ሀገራቱ በግብርና እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያላችውን ፍላጎት የሚያሳይ ነበር። በፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ወቅት የመጀመሪያ የኢትዮ-ብሩንዲ የመጀመሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባ ተደርጓል። በወቅቱ በግብርና፣ በቱሪዝም እና በትምህርት ዘርፍ አዳዲስ የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። እ.አ.አ በ2023 የብሩንዲ ፓርላማ የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) በህግ አፀደቀ (Ratified)፤ ይህም ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ተደርጎ ተቆጠረ። ኢትዮጵያ ብሩንዲ ስምምነቱን እንድታጸድቅ ድጋፍ አድርጋለች። ይህም የሀገራቱን የውሃ ትብብር የበለጠ ያጸና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። የቀድሞው የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል። ይህም በሀገራቱ የከፍተኛ አመራሮች የጉብኝት ልውውጦች ውስጥ የሚጠቀስ ነው። ከንኩሩንዚዛ ጉብኝት ሁለት ዓመታት በኋላ እ.አ.አ በ2014 ብሩንዲ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ከፍታለች። ይህም የሀገራቱን ትብብር ለማጠናከር የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ ከብሩንዲ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ስራ የሚሸፍነው በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ በተለያዩ ጊዜያት ተደራራቢ ታክስን ማስቀረት፣ በኢንቨስትመንት፣ አየር ትራንስፖርት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመከላከያ እና ፀጥታ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲሁም ባህልና ስፖርት ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈራርመዋል። ጉብኝቶችና ስምምነቶች ኢትዮጵያና ብሩንዲ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር በማሳለጥ እና የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው ሚና ወሳኝ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያና የብሩንዲ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን (Joint Ministerial Commission - JMC) መጋቢት 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሄዷል። ስብስባውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ፣ የቀጣናዊ ትስስርና የልማት ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና በጋራ መርተውታል። በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የዘርፍ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በስብስባው ማብቂያ የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶች ተፈርመዋል። ስምምነቶቹም በዋናነት በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር (በተለይም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ)፣ በግብርና ምርታማነት፣ በአቪዬሽን እና በቀጣናዊ ደህንነት ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ስብስባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) መርህ መሰረት በማድረግ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር፣ የመሰረተ ልማት ግንኙነቶችን ማስፋፋት እና በአባይ ተፋሰስ የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈረም በስኬት ተጠናቋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ እና የብሩንዲን ትብብር የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል ነው። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሁለቱን ሀገራት ትብብር ከማጠናከር ባለፈ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትስስር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። የኢትዮጵያ እና የብሩንዲ መጻኢ የሁለትዮሽ ትብብር በሁለገብ ዘርፎች ላይ ያተኮረና ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚሸጋገርበት ወቅት እንደሚሆን ይጠበቃል። የፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጉብኝት እና የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽኑ ውሳኔዎች፣ ለቀጣዮቹ ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚኖረው ጠንካራ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትስስር መጠናከር ጉልህ ሚና ይኖረዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 4, 2026 1156
በዮሐንስ ደርበው ከመጋቢት 20 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ አዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ መሆኗን ገልጸው፤ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፣ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ፣ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ብለዋል። ፈጣን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሔዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሠራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ ዐቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው ከፍተዋል። በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው ብለዋል በወቅቱ። የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከል ማከተቱን አብራርተዋል። ምርምርን ወደ ፖሊሲ፣ ፈጠራን ደግሞ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ በመቀየር፤ ይህ ማዕከል በመድኃኒት ምርት ራሳችንን ለመቻል፣ ዘላቂ የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ እስካሁን ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። • የአዲስ ስፖርት ፓርክ መመረቅ ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የከተማችንን እድሳት ለማፋጠን እና የዜጎቻችንን ክብር ለመመለስ የገባነውን ቃል አንዱ ማረጋገጫ የሆነውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን በይፋ መርቀን ከፍተናል ብለዋል። በ5 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፕሮጀክት፤ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ 15 አትሌቶችን የሚዘክሩ የክብር ሐውልቶችን በፓርኩ መሃል በማቆም፣ የጀግኖቻችን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ ስፖርተኞች ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋልም ነው ያሉት። የኦሎምፒክ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የ800 ሜትር የሩጫ ትራክን ጨምሮ፤ እያንዳንዱ የዚህ ማዕከል ክፍል የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንዲያሟላ ተደርጎ ተገንብቷል ሲሉም ገልፀዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በአፋር ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል። በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት፤ ለሌሎች በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሠነድ እንደሚሆን አመላክተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው "የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ቅንጅት ለሀገራዊ ሰላም እና ደኅንነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ብሔራዊ የደኅንነት ኮንፈረንስ ላይ የተሳተፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የጸጥታና ደኅንነት ተቋሞቻችን ችግርን ወደ ዕድል እንዲቀየሩ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ጉዟችን ተጀመረ እንጂ አልተቋጨምና ከትናንት ዕዳዎች ተላቀን፣ የዛሬ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን ለነገው ትውልድ የምትመጥን ሀገር ለመገንባት በዓላማ ጽናት እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል። • ስለ መጋቢት 24 መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የመጣውን የለውጡን መንግሥት የሚደግፉ ሕዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ሰልፎች ላይም መንግሥት ባለፉት ሥምንት ዓመታት ያመጣቸውን ለውጦች እና የተገኙ ስኬቶችን የሚያወሱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም (ዶ/ር) ለሰጡት ስኬታማ አመራርነት የሚያሞግሱና የሚያመሠግኑ መልዕክቶች ተስተጋብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ቀኑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝባዊ ግፊትና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው ብለዋል። ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሠራለን ሲሉም ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በኃይልና በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አስደማሚ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብሏል። የለውጡን መሠረት ከማስፋትና ከማጽናት ወደ ማላቅ የተሸጋገረችው ኢትዮጵያ፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌትነቷን በተግባር ታውጃለች ሲልም ገልጿል። ይህን ለውጥ ዕውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፤ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በድል እንደሚያሳርጉት ጥርጥር የለውም ነው ያለው። • የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በInvest in Ethiopia 2026 ፎረም፤ ከቻይና፣ ፖላንድ፣ ሕንድ፣ ሲንጋፖር እና ኬንያ ከመጡ አጋሮች ጋር የ13 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት አስታውቋል። በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድንና በአረንጓዴ አሞኒያ ዘርፎች ላይ ያተኮሩት እነዚህ ስምምነቶች፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ጉልህ ማሳያ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ጽሕፈት ቤቱ ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል ብሏል። የ1954 የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ሲልም አስገንዝቧል ጽሕፈት ቤቱ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3877
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2635
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8429
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6917
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 451
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ
Apr 12, 2026 952
በኅብረትና ጽናት የሚቀረጽ ብርሃን፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቀበኔሳ ገቢሳ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ተስፋን፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን እና ከኃጢአት ነፃ መውጣትን የሚያበስር ኃይማኖታዊ በዓል ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ የሰው ልጅ የዘለዓለም የሕይወት አክሊልን ተስፋ ያደረገበት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት እንዲሁም የሰው ልጅ ከዘለዓለም ሞትና ከኃጢአት ባርነት ነፃ የወጣበት የድኅነት፣ የፍቅር፣ የጽናትና የተስፋ ብርሃን ብስራት ነው፡፡ የትንሣኤ በዓል ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የመነሳቱ ታላቅ ምሥጢር የሚታሰብበት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ የሰው ልጅ ከውርደት ወደ ክብር፣ ከኃጢያት ባርነት ወደ ድኅነት እንዲሁም ከጉስቁልና ወደ ብሩህ ተስፋ የተሸጋገረበት የድል አዋጅ ነው። በዕለቱም በሞት ላይ ሕይወት፣ በሐዘን ላይ ደስታ፣ በቂም ላይ ይቅርታ ተበስሮበታል። ከበዓላት ሁሉ የላቀ የነጻነት ተምሳሌት ነው ትንሣኤ። 👉የትንሣኤ ሕያው አስተምሮ በዕለት ተዕለት ሕይወት ትንሣኤ ሲከበር ከሥርዓተ አምልኮ ባለፈ፣ በዓሉ የሚሰጠውን ታላቅ አስተምሮ ማጤን ይገባል። ትንሣኤ በየቀኑ ካለንበት ድካምና ውድቀት በአዲስ መንፈስ የመነሳት አቅም ነው። በዓሉ የሚያስተምረንን የጽናት፣ የተስፋና የአብሮነት ዕሴት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መኖር ያስፈልጋል። ለዚህም የተቸገሩን መርዳት፣ የታመሙትን መጠየቅና የተጣሉትን ማስታረቅ የበዓሉን ትርጉም እውነተኛ ያደርገዋል። 👉የኢትዮጵያ ትንሣኤ፤ በፈተና የጸና ብርሃን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓሉን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፤ "የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈታኝ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ሆና እያለች ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችንም እሾህ የበዛበት ሊሆን ይችላል። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጨለማ ወጥመድ ሊያሥሩን የሚሞክሩ መሰናክሎች ቢበዙም፣ እምነታችን ግን ከሕማማት በኋላ ትንሣኤ እንደሚመጣ ነው" ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ዛሬም ትንሳኤዋን እያየች ነው። መቃብሯ ተከፍቷል፤ ማኅተሙም ተሰብሯል። የትንሣኤውን ዜና ሊያደበዝዙ የሚሞክሩ የውሸት ወሬዎችና ተስፋ አስቆራጭ ትረካዎች የሀገራችንን የብርሃን ጉዞ ሊገቱት አይችሉም። ትንሳኤው እውነት ነው፤ ብርሃኑም የማይቀለበስ ሀቅ ሆኗል" ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡ 👉ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ ምክክር፤ የተስፋ ምዕራፎች የኢትዮጵያ ትንሣኤ አንዱ መገለጫ ዴሞክራሲን የመገንባት ጽናት ነው። ትንሣኤ ያለ ሕማማት እንደማይገኝ ሁሉ ዴሞክራሲ ያለ ፈተና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ዴሞክራሲ የሚገነባው በጽናት እንጂ በፍርሃት አይደለም። ዴሞክራሲን እየገነባን በትዕግሥትና በቆራጥነት ወደ ተስፋዋ ምድር እንደርሳለን። አሁን ያለው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ቀውስና ማህበራዊ አለመረጋጋት የትንሳኤን ትምህርት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡ ችግሮችን በብቸኝነት የምንወጣበት ጊዜ አብቅቷል። ዛሬ እንደህዝብ የሚያስፈልገን ከ"እኔ" ወደ "እኛ" መሸጋገር፣ የግል ፍላጎትን ለጋራ ስኬት መስዋዕት ማድረግ ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን። የአንድነት ጉዟችንን በማጠናከር ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ጫናዎችን ለመቋቋም በጋራ መቆም ይገባናል። የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና የተጣሉትን በማስታረቅ የተግባር አብሮነትን በማሳየት የበዓሉን እውነተኛ ትርጉም መግለጥ ይገባል፡፡ 👉ምርጫ፤ ከኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበትና ተስፋ የታደሰበት ዕለት ነው። እኛም በምርጫ ካርዳችን የሃሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ አንድነት ድል በማድረግ የኢትዮጵያን የብልፅግና ትንሳኤ እናረጋግጣለን። በትንሣኤ በዓል የምንማረው ይቅርታና ጽናትም ለምርጫችን ስኬት አቅም ይሆናል። በኅብረት የምንሰጠው ድምፅም የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ የመቅረጽ ኃይል በእጃችን መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው "ምርጫ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማብሰሪያዎች አንዱ ምዕራፍ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልፅግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድኅነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!!" ብለዋል። 👉የወደፊት እጣ ፈንታችን በእጃችን ከፊታችን የሚጠብቁን ሀገራዊ ምክክርና የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የወደፊት መጻኢ ዕድል የሚወስኑ ታላላቅ ሁነቶች ናቸው። እነዚህ ሂደቶች ስኬታማ የሚሆኑት እያንዳንዱ ዜጋ የድርሻውን ሲወጣ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በልባችን ውስጥ ይቅርታና አብሮነት ሲነግስ ብቻ ግቡን ይመታል። ትንሣኤ ሞት ድል የተነሳበት እንደሆነው ሁሉ፣ በምክክሩም ጥልን፣ ጥርጣሬን፣ ያለመግባባት መንፈስን ድል መንሳት ይገባል፤ ቅንነት፣ ተስፋና መተሳሰብ ለምክክሩ ስኬት የመተማመኛ ቁልፎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ 2018 ዓ.ም ደግሞ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማሳያ አንጓ ነው፤ የዜጎች ነፃ ተሳትፎ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ፍላጎታቸውን የሚያረጋግጡበት ማረጋገጫ ማህተም ጭምር፡፡ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን የሚያስከብሩበት፤ የሌላውን ሃሳብ አክብረው የራሳቸውን የሚያስከብሩበት ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በጋራ የሚቆሙበት መድረክ ነው፡፡ ትንሣኤ የድልና የነጻነት በዓል ነው። ይህንን ታላቅ ዕለት ስናከብር ያለፈውን ቁስል ሽረን፣ ለነገ ተስፋ ሰንቀን መሆን አለበት። እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ችግሮችን በንግግር በመፍታት ለሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ስኬታማነት የድርሻችንን መወጣት ይገባናል። የተሻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በጋራ እንቁም! መልካም የትንሳኤ በዓል!!