ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 26
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018(ኢዜአ)፦ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር "የሕግ የበላይነትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች - ለዘላቂ ሰላም እና ዕድገት" በሚል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ ጉባኤን አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት፥ ኢትዮጵያ መደበኛ የፍርድ ተቋማቷን ብታዘምንም አብዛኛው ሕዝባችን ችግሩን የሚፈታበት ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓት ግን ተገቢው ቦታ ሳይሰጠው ቆይቷል ብለዋል፡፡ አሁን ግን በሀገራችንም ሆነ በክልላችን ተደራሽ፣ ቅቡልነት ያለው እና በመርሕ ላይ የቆመ ፍትሕን ለማስፈን እንዲቻል መደበኛና ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ተጣጥመውና ተናብበው የሚጓዙበትን ዐውድ መፍጠር የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶቻችንን ከዘመናዊ ዕሳቤዎች ጋር ማስተሣሠር፣ በሕግ መደገፍ እና አሠራሮቻቸውን ማዘመን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከምንተገብራቸው ሪፎርሞች ጋር አሠናስሎ ማዋወቀር ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የጎደላቸውን ሞልተን በትክክል ከተጠቀምንባቸው፣ በጉዳዮች ብዛት በከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙ መደበኛ የፍትሕ ተቋሞቻችንን ትርጉም ባለው ደረጃ ያግዛሉ፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እና የባለቤትነት ስሜት የሚንጸባረቅባቸውን መፍትሔዎች ያቀርባሉ። ይህ ኮንፈረንስ ይሄንን አዎንታዊ ጥምረት ለመፍጠር የተሻለውን መንገድ እንደሚጠቁም እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ይጠናቀቃል
Jan 24, 2026 27
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018(ኢዜአ)፦ የኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ማጠናቀቅ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ-ጁቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ገለጸ፡፡ የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን አቅም መከናወኑ በቀጣይ በዘርፉ ለሚከናወኑ ሥራዎች የተሻለ ልምድና አቅም መፍጠር የሚያስችል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ ኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘው የሶስት ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ግንባታ በመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል፡፡ የባቡር መስመሩ መገንባት የባቡር መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የተለያዩ የወጭና ገቢ ምርቶችን ለማጓጓዝ የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል፡፡ በኢትዮ-ጁቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ባለሙያዎች አቅም የሚገነባው ይሄው የባቡር መስመር ግንባታ በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለታል፡፡ የፕሮጀክቱ ማናጀር ኢንጅነር ንግስት ሀይሉ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የባቡር መስመሩን ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ማጠናቀቅ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት የባቡሩን ሀዲድ ለማንጠፍ የሚያስችሉ የጉድጓድ ሙሌት፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት እንዲሁም የማፋሰሻ ግንባታዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የባቡር መስመር ግንባታው 70 በመቶ መድረሱን ገልጸው፤ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ የባቡር መስመር ግንባታው በኢትዮጵያውያን አቅም የሚሰራ መሆኑን ገልጸው፤ አስፈላጊውን የሰው ሀይልና የግንባታ ግብዓቶች በማሟላት በትጋት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ግንባታው በኢትዮጵያውያን አቅም መሰራቱ በቀጣይ በዘርፉ ለሚከናወኑ ሥራዎች የተሻለ የሥራ ልምድና አቅም መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 28
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል ዛሬ ጎብኝተዋል። በዚህም፥ ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ለተሳፋሪዎች ተመቻችቶ፤ ለዕይታ ተስማምቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብራቸውን ለማጠናከር ያለመ ምክክር አደረጉ
Jan 24, 2026 33
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብር በይበልጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አግባብ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከፎረሙ ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንድ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የተካሄደው በዳቮስ ከተካሄደው የ2026 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጎን ለጎን ነው። በውይይቱ ወቅትም ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በዓለም አቀፍ ልማት፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ እንድትመክር ፎረሙ ላበረከተው መልካም አጋጣሚም አመሥግነዋል። በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በልማት አጋርነት ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ያደረገችው ተሳትፎ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።
ኢኒስቲትዩቱ ይፋ ያደረገው የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ የሥራ ጫናን ከማቅለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል
Jan 24, 2026 29
ሀዋሳ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፦የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በመቀናጀት ይፋ ያደረገው የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ የሥራ ጫናን ከማቃለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። የቋሚ ኮሚቴው አባላት በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ በኢንስቲትዩቱ የተሰራ ዘመናዊ የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራን ተመልክተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺ ሀሰን በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፣ኢንስቲትዩቱ የህብረተሰቡን ኑሮ የሚያቃልሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያፈለቀ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የስራ ጫና የሚያቃልል የእንሰት መፋቂያ፣ መጭመቂያና መቁረጫ መሳሪያ አንዱ ነው ብለዋል። በርካታ ሴቶች በእንሰት ሥራ እንደሚሰማሩ ገልጸው፣ እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂዎች መምጣታቸው የሥራ ጫናውን ከማቃለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ፖለቲካ
ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 26
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018(ኢዜአ)፦ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር "የሕግ የበላይነትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች - ለዘላቂ ሰላም እና ዕድገት" በሚል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ ጉባኤን አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት፥ ኢትዮጵያ መደበኛ የፍርድ ተቋማቷን ብታዘምንም አብዛኛው ሕዝባችን ችግሩን የሚፈታበት ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓት ግን ተገቢው ቦታ ሳይሰጠው ቆይቷል ብለዋል፡፡ አሁን ግን በሀገራችንም ሆነ በክልላችን ተደራሽ፣ ቅቡልነት ያለው እና በመርሕ ላይ የቆመ ፍትሕን ለማስፈን እንዲቻል መደበኛና ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ተጣጥመውና ተናብበው የሚጓዙበትን ዐውድ መፍጠር የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶቻችንን ከዘመናዊ ዕሳቤዎች ጋር ማስተሣሠር፣ በሕግ መደገፍ እና አሠራሮቻቸውን ማዘመን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከምንተገብራቸው ሪፎርሞች ጋር አሠናስሎ ማዋወቀር ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የጎደላቸውን ሞልተን በትክክል ከተጠቀምንባቸው፣ በጉዳዮች ብዛት በከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙ መደበኛ የፍትሕ ተቋሞቻችንን ትርጉም ባለው ደረጃ ያግዛሉ፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እና የባለቤትነት ስሜት የሚንጸባረቅባቸውን መፍትሔዎች ያቀርባሉ። ይህ ኮንፈረንስ ይሄንን አዎንታዊ ጥምረት ለመፍጠር የተሻለውን መንገድ እንደሚጠቁም እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 28
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል ዛሬ ጎብኝተዋል። በዚህም፥ ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ለተሳፋሪዎች ተመቻችቶ፤ ለዕይታ ተስማምቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብራቸውን ለማጠናከር ያለመ ምክክር አደረጉ
Jan 24, 2026 33
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብር በይበልጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አግባብ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከፎረሙ ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንድ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የተካሄደው በዳቮስ ከተካሄደው የ2026 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጎን ለጎን ነው። በውይይቱ ወቅትም ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በዓለም አቀፍ ልማት፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ እንድትመክር ፎረሙ ላበረከተው መልካም አጋጣሚም አመሥግነዋል። በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በልማት አጋርነት ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ያደረገችው ተሳትፎ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።
በክልሉ የፍትሕ ተቋማትን ተምሳሌትና የልምድ ተሞክሮ መቅሰሚያ የሚያደርጉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Jan 24, 2026 39
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የፍትሕ ተቋማትን ተምሳሌትና የልምድ ተሞክሮ መቅሰሚያ የሚያደርጉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀው “የሕግ የበላይነትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች -ለዘላቂ ሰላም እና ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በክልሉ ግጭቶች የሚፈቱበት የዳበረ ባህላዊ እሴት መኖሩን ጠቅሰል፡፡ ይህንን ሀብት ተቋማዊ ለማድረግ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የክልሉን የዳኝነትና የፍትሕ ተቋማት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ነጻ፣ገለልተኛ፣ጠንካራና ተጠያቂነት ያለው የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት የክልሉ መንግሥት ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለዚህም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የፍርድ ቤቶችን ተቋማዊ ነጻነት የሚያጠናክሩ የሕግ ማሻሻያዎች ተደርገው በክልሉ ምክር ቤት ጸድቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል። የፍትሕ ሥርዓቱን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለምአንተ አግደው በበኩላቸው፤ የዳኝነት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን አብራርተዋል። ፍርድ ቤቱ የጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም ተከትሎም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው መዝገብ ማስከፈትና አቤቱታ ማቅረብ የሚችሉበት ኢ-ፋይሊንግ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በአካል ሳይገኙ በቴክኖሎጂ ታግዘው ክርክር የሚያደርጉበት የርቀት ክርክር (Remote Litigation) አሠራር መተግበሩን ጠቅሰው፥ በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ደረጃ የተደራጁ ዘመናዊ ችሎቶች በስፋት ተግባራዊ መደረጋቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ የአፍሪካ ሕብረትን ወክለው የተገኙት አምባሳደር ሳሌህ መሐመድ፤ መድረኩ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የመልካም አስተዳደርና የመረጋጋት አጀንዳ ለማራመድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። የአፍሪካ ኅብረት በመድረኩ ያለው ተሳትፎ ሂደቱን ለመደገፍ ብቻ ሳይሆን ከክልሉ የፍትሕ ሪፎርም ተሞክሮ ለመቅሰም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በፓርቲው መዋቅሮች ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Jan 24, 2026 40
ሐዋሳ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ )፡- በብልጽግና ፓርቲ መዋቅሮች ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት ስትራቴጂክ ሥራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ስትራቴጂክ ሥራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዘጋጅነት ለዋና ጽሕፈት ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አመራርና ባለሙያዎች በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የተቀናጀ የተቋም ሀብት አሥተዳደር አውቶሜሽን ትግበራ ሥልጠና ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር እንዳሉት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት ስትራቴጂክ ግብ ተጥሎ እየተሠራ ይገኛል። ሥልጠናው በፓርቲው መዋቅሮች በንብረት፣ በሰው ኃይልና በፋይናንስ አሥተዳደር ላይ ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዝ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከዋናው ጽሕፈት ቤት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ላይ ባሉ ጽሕፈት ቤቶች ላይ ተግባራዊ በማድረግ የፓርቲውን አሠራር ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ፤ ሥልጠናው በፓርቲው ሀብትን በአግባቡ ለማሥተዳደር ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በክልሉ የፓርቲ ጽሕፈት ቤቶች ዘመናዊ አሠራርን ለመዘርጋት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችም አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል። ከሥልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የግዥና ንብረት አሥተዳደር ዳይሬክተር ተመስገን ከተማ፤ ሥልጠናው አሠራሮችን ወጥ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል። በክልሉ በፓርቲው ጽሕፈት ቤቶች የግዥና ንብረት አሥተዳደርን ለማዘመን ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጠቅው ሥልጠናው የጀመሩትን ሥራ ለማፋጠን እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፋይናንስና በጀት ቡድን መሪ አብዮት ታደለ በበኩላቸው፤ የወሰዱትን ሥልጠና በክልላቸው ባሉ የፓርቲው መዋቅሮች በማውረድም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያና የብሔራዊ ኩራት መገለጫ ነው
Jan 24, 2026 45
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያና የብሔራዊ ኩራት መገለጫ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶም "ጥቁር አንበሳ" የተሰኘው አስደማሚ የአየር ላይ ትርዒት በመከናወን ላይ ነው። የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ መርሃ ግብሩ የ90 ዓመት ክብረ በዓል ብቻ ሳይሆን፣ የዘጠኝ አስርት ዓመታት የጠንካራ ብሔራዊ አገልግሎትና ያልተቋረጠ የልህቀት ማሳያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ላለፉት 90 ዓመታት የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ጽኑ ምሽግ ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ኃይል መስራች መሆኗን፣ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን መደገፏንና የብሔራዊ ጥቅሟን የሚገዳደሩ ኃይሎችን አቅም ያከሸፈች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ይህ የ90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት የኢትዮጵያን የኩራት መገለጫነትና የበረራ ልህቀት በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በአከባበሩ ላይ የአፍሪካና የሌሎች ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች በመገኘታቸው ኩራት እንደሚሰማቸው የገለጹት ሌተናል ጀነራል ይልማ ለዚህ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የአየር ትርኢቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገነባ መሆኑን ጠቅሰው፤ ካዴቶች ለህልማቸው እንዲተጉ፣ ዜጎችም በሀገራቸው የቴክኖሎጂ መጻኢ ዕድል እንዲተማመኑ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያ፣ የብሔራዊ ኩራትና ዓለም አቀፋዊ ተፈላጊነትን ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል። "ባለፈው እንኮራለን፤ በአሁኑ እንመራለን፤ የቀጣዩን እንቀርፃለን" ያሉት ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ መርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሽግግርና የጋራ ትብብር ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዓሉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስኬትን እንዲሁም የአራተኛውና አምስተኛው ትውልድ የአየር ኃይል አቅም መገለጫ መሆኑን ጠቁመዋል። የአየር ኃይል አባላት እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን በማሳለፍ የኢትዮጵያን አቅም በተግባር ስላሳዩ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ የዓለም አቀፍ አጋሮች በዚህ መርሃ ግብር መሳተፋቸው ግንኙነታችንን በማጠናከር የጋራ ትብብራችንን ለማሳደግና አስተማማኝ የአየር ኃይል አቅም ለመገንባት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኢትዮጵያን ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Jan 24, 2026 60
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኢትዮጵያን ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የጥቁር አንበሳ የአየር ላይ ትርኢት እየተካሄደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ አየር ኃይሉ ባለፉት 90 ዓመታት በብዙ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ አልፏል። አየር ኃይሉ ኢትዮጵያን በየትኛውም አቅጣጫ ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም መሆኑን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ባለፈ በቅኝ ግዛት ማብቂያ ዘመን የታንዛኒያን አየር ክልል የጠበቀ የአፍሪካዊያን ኩራት መሆኑንም አንስተዋል። አየር ኃይሉ አሁን ላይ በዘመናዊ ትጥቅ እየታገዘ በላቀ ብቃት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል። እኛ ያለ ኢትዮጵያ እናት የለንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ እናታችን መተኪያ የሌላት መሆኗን በመገንዘብ ለሀገር ልዕልና በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። የኢፌዴሪ አየር ኃይልን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ካለው አቅም በእጥፍ ለማሳደግም ከወዲሁ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት የ10 ነጥብ 3 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ማመለከቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ይህ ዕድገት ሙሉ የሚሆነው ጠንካራ ወታደራዊና ጸጥታ ተቋማትን በመገንባት ጭምር መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትናንት ላይ የቆመች ሀገር አይደለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አየር ኃይሏ ነገን የዋጀ እንዲሁም ዘመኑ የደረሰበትን አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ እኛ የሰው አንፈልግም፣የራሳችንንም አንሰጥም፤የተሰጠብን ካለም ማወራረዳችን አይቀርም ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ ነው
Jan 24, 2026 52
ደብረ ብርሃን፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል መንግሥትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰው የዘላቂ ሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች የማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሂዷል። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደጀኔ ልመንህ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤በክልሉ መንግሥትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰው የዘላቂ ሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በመፍታት በየቀኑ እየገቡ መሆኑን ጠቁመው፥መንግሥትም የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት በዘላቂነት የማቋቋም ሥራ መቀጠሉን ተናግረዋል። አሁን ላይ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት መኖሩን ጠቅሰው፤ ይህም ለልማትና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ቀጣይነት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል። መንግሥት ለዘላቂ ሰላምና ልማት በትጋትና በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የሥልጠና ዳይሬክተር ብርሃኑ ተስፋዬ ናቸው። የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት የማቋቋም ሥራም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውቀዋል። የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው የተመረቁ የቀድሞ ታጣቂዎች በሚሰማሩበት የልማት መስክ ሁሉ ለሀገር ሰላምና ልማት የላቀ አበርክቶ እንደሚኖራቸውም አመላክተዋል። ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ በመቆም መሥራት የዜጎች ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። የቀድሞ ታጣቂዎችም የበደሉትን ሕዝብ በልማት ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን ባወጡት ባለስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል።
ፖለቲካ
ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 26
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018(ኢዜአ)፦ከትናንት በጎ ዕሴቶችን መውሰድ፤ዛሬ ጠቃሚ አዳዲስ ዕሴቶችን መገንባት፤ ነገ ኢትዮጵያ እንድትበለጽግ የሚያደርጓት ቁልፍ ተግባራት ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር "የሕግ የበላይነትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች - ለዘላቂ ሰላም እና ዕድገት" በሚል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ ጉባኤን አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት፥ ኢትዮጵያ መደበኛ የፍርድ ተቋማቷን ብታዘምንም አብዛኛው ሕዝባችን ችግሩን የሚፈታበት ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓት ግን ተገቢው ቦታ ሳይሰጠው ቆይቷል ብለዋል፡፡ አሁን ግን በሀገራችንም ሆነ በክልላችን ተደራሽ፣ ቅቡልነት ያለው እና በመርሕ ላይ የቆመ ፍትሕን ለማስፈን እንዲቻል መደበኛና ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ተጣጥመውና ተናብበው የሚጓዙበትን ዐውድ መፍጠር የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡ ለዚህ ደግሞ ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶቻችንን ከዘመናዊ ዕሳቤዎች ጋር ማስተሣሠር፣ በሕግ መደገፍ እና አሠራሮቻቸውን ማዘመን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከምንተገብራቸው ሪፎርሞች ጋር አሠናስሎ ማዋወቀር ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የጎደላቸውን ሞልተን በትክክል ከተጠቀምንባቸው፣ በጉዳዮች ብዛት በከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙ መደበኛ የፍትሕ ተቋሞቻችንን ትርጉም ባለው ደረጃ ያግዛሉ፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እና የባለቤትነት ስሜት የሚንጸባረቅባቸውን መፍትሔዎች ያቀርባሉ። ይህ ኮንፈረንስ ይሄንን አዎንታዊ ጥምረት ለመፍጠር የተሻለውን መንገድ እንደሚጠቁም እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 24, 2026 28
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ እየተጠናቀቀ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባሕርዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል ዛሬ ጎብኝተዋል። በዚህም፥ ተርሚናሉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ፣ለተሳፋሪዎች ተመቻችቶ፤ ለዕይታ ተስማምቶ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።በቅርብ ወራት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆንም ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብራቸውን ለማጠናከር ያለመ ምክክር አደረጉ
Jan 24, 2026 33
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እና የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ትብብር በይበልጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አግባብ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከፎረሙ ፕሬዚዳንት ቦርጌ ብሬንድ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የተካሄደው በዳቮስ ከተካሄደው የ2026 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጎን ለጎን ነው። በውይይቱ ወቅትም ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፤ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ ለፕሬዚዳንቱ ገለጻ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከተለያዩ አጋሮች ጋር በዓለም አቀፍ ልማት፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ እንድትመክር ፎረሙ ላበረከተው መልካም አጋጣሚም አመሥግነዋል። በቀጣይም ሁለቱ ወገኖች ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በልማት አጋርነት ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በ2026 የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ያደረገችው ተሳትፎ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።
በክልሉ የፍትሕ ተቋማትን ተምሳሌትና የልምድ ተሞክሮ መቅሰሚያ የሚያደርጉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Jan 24, 2026 39
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የፍትሕ ተቋማትን ተምሳሌትና የልምድ ተሞክሮ መቅሰሚያ የሚያደርጉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀው “የሕግ የበላይነትና አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች -ለዘላቂ ሰላም እና ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እንደገለጹት፤ በክልሉ ግጭቶች የሚፈቱበት የዳበረ ባህላዊ እሴት መኖሩን ጠቅሰል፡፡ ይህንን ሀብት ተቋማዊ ለማድረግ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የክልሉን የዳኝነትና የፍትሕ ተቋማት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ነጻ፣ገለልተኛ፣ጠንካራና ተጠያቂነት ያለው የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት የክልሉ መንግሥት ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለዚህም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የፍርድ ቤቶችን ተቋማዊ ነጻነት የሚያጠናክሩ የሕግ ማሻሻያዎች ተደርገው በክልሉ ምክር ቤት ጸድቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል። የፍትሕ ሥርዓቱን ለማዘመንና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለምአንተ አግደው በበኩላቸው፤ የዳኝነት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን አብራርተዋል። ፍርድ ቤቱ የጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም ተከትሎም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው መዝገብ ማስከፈትና አቤቱታ ማቅረብ የሚችሉበት ኢ-ፋይሊንግ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በአካል ሳይገኙ በቴክኖሎጂ ታግዘው ክርክር የሚያደርጉበት የርቀት ክርክር (Remote Litigation) አሠራር መተግበሩን ጠቅሰው፥ በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ደረጃ የተደራጁ ዘመናዊ ችሎቶች በስፋት ተግባራዊ መደረጋቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ የአፍሪካ ሕብረትን ወክለው የተገኙት አምባሳደር ሳሌህ መሐመድ፤ መድረኩ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን የመልካም አስተዳደርና የመረጋጋት አጀንዳ ለማራመድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። የአፍሪካ ኅብረት በመድረኩ ያለው ተሳትፎ ሂደቱን ለመደገፍ ብቻ ሳይሆን ከክልሉ የፍትሕ ሪፎርም ተሞክሮ ለመቅሰም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በፓርቲው መዋቅሮች ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Jan 24, 2026 40
ሐዋሳ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ )፡- በብልጽግና ፓርቲ መዋቅሮች ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በፓርቲው ዋና ጽሕፈት ቤት ስትራቴጂክ ሥራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ገለጹ። በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ስትራቴጂክ ሥራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አዘጋጅነት ለዋና ጽሕፈት ቤትና ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አመራርና ባለሙያዎች በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የተቀናጀ የተቋም ሀብት አሥተዳደር አውቶሜሽን ትግበራ ሥልጠና ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር እንዳሉት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት ስትራቴጂክ ግብ ተጥሎ እየተሠራ ይገኛል። ሥልጠናው በፓርቲው መዋቅሮች በንብረት፣ በሰው ኃይልና በፋይናንስ አሥተዳደር ላይ ወጥነት ያለው ዘመናዊ አሠራር ለመዘርጋት የሚያግዝ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከዋናው ጽሕፈት ቤት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ላይ ባሉ ጽሕፈት ቤቶች ላይ ተግባራዊ በማድረግ የፓርቲውን አሠራር ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ፤ ሥልጠናው በፓርቲው ሀብትን በአግባቡ ለማሥተዳደር ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በክልሉ የፓርቲ ጽሕፈት ቤቶች ዘመናዊ አሠራርን ለመዘርጋት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችም አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል። ከሥልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የግዥና ንብረት አሥተዳደር ዳይሬክተር ተመስገን ከተማ፤ ሥልጠናው አሠራሮችን ወጥ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል። በክልሉ በፓርቲው ጽሕፈት ቤቶች የግዥና ንብረት አሥተዳደርን ለማዘመን ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጠቅው ሥልጠናው የጀመሩትን ሥራ ለማፋጠን እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፋይናንስና በጀት ቡድን መሪ አብዮት ታደለ በበኩላቸው፤ የወሰዱትን ሥልጠና በክልላቸው ባሉ የፓርቲው መዋቅሮች በማውረድም የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያና የብሔራዊ ኩራት መገለጫ ነው
Jan 24, 2026 45
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያና የብሔራዊ ኩራት መገለጫ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶም "ጥቁር አንበሳ" የተሰኘው አስደማሚ የአየር ላይ ትርዒት በመከናወን ላይ ነው። የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ መርሃ ግብሩ የ90 ዓመት ክብረ በዓል ብቻ ሳይሆን፣ የዘጠኝ አስርት ዓመታት የጠንካራ ብሔራዊ አገልግሎትና ያልተቋረጠ የልህቀት ማሳያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ላለፉት 90 ዓመታት የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ጽኑ ምሽግ ሆኖ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ኃይል መስራች መሆኗን፣ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን መደገፏንና የብሔራዊ ጥቅሟን የሚገዳደሩ ኃይሎችን አቅም ያከሸፈች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ይህ የ90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት የኢትዮጵያን የኩራት መገለጫነትና የበረራ ልህቀት በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በአከባበሩ ላይ የአፍሪካና የሌሎች ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች በመገኘታቸው ኩራት እንደሚሰማቸው የገለጹት ሌተናል ጀነራል ይልማ ለዚህ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የአየር ትርኢቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ገጽታ የሚገነባ መሆኑን ጠቅሰው፤ ካዴቶች ለህልማቸው እንዲተጉ፣ ዜጎችም በሀገራቸው የቴክኖሎጂ መጻኢ ዕድል እንዲተማመኑ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገራዊ አቅም ማሳያ፣ የብሔራዊ ኩራትና ዓለም አቀፋዊ ተፈላጊነትን ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ መሣሪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል። "ባለፈው እንኮራለን፤ በአሁኑ እንመራለን፤ የቀጣዩን እንቀርፃለን" ያሉት ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፤ መርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪ ሽግግርና የጋራ ትብብር ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዓሉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስኬትን እንዲሁም የአራተኛውና አምስተኛው ትውልድ የአየር ኃይል አቅም መገለጫ መሆኑን ጠቁመዋል። የአየር ኃይል አባላት እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን በማሳለፍ የኢትዮጵያን አቅም በተግባር ስላሳዩ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ የዓለም አቀፍ አጋሮች በዚህ መርሃ ግብር መሳተፋቸው ግንኙነታችንን በማጠናከር የጋራ ትብብራችንን ለማሳደግና አስተማማኝ የአየር ኃይል አቅም ለመገንባት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኢትዮጵያን ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Jan 24, 2026 60
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኢትዮጵያን ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ የጥቁር አንበሳ የአየር ላይ ትርኢት እየተካሄደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ አየር ኃይሉ ባለፉት 90 ዓመታት በብዙ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ አልፏል። አየር ኃይሉ ኢትዮጵያን በየትኛውም አቅጣጫ ለመድፈር ለሞከሩ ኃይሎች ሁነኛ መድሃኒት ሆኖ ሀገር ያጸና ተቋም መሆኑን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ባለፈ በቅኝ ግዛት ማብቂያ ዘመን የታንዛኒያን አየር ክልል የጠበቀ የአፍሪካዊያን ኩራት መሆኑንም አንስተዋል። አየር ኃይሉ አሁን ላይ በዘመናዊ ትጥቅ እየታገዘ በላቀ ብቃት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል። እኛ ያለ ኢትዮጵያ እናት የለንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ እናታችን መተኪያ የሌላት መሆኗን በመገንዘብ ለሀገር ልዕልና በጋራ መስራት አለብን ብለዋል። የኢፌዴሪ አየር ኃይልን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ካለው አቅም በእጥፍ ለማሳደግም ከወዲሁ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት የ10 ነጥብ 3 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ማመለከቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ይህ ዕድገት ሙሉ የሚሆነው ጠንካራ ወታደራዊና ጸጥታ ተቋማትን በመገንባት ጭምር መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትናንት ላይ የቆመች ሀገር አይደለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አየር ኃይሏ ነገን የዋጀ እንዲሁም ዘመኑ የደረሰበትን አቅም የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ እኛ የሰው አንፈልግም፣የራሳችንንም አንሰጥም፤የተሰጠብን ካለም ማወራረዳችን አይቀርም ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተደረሰው የሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ ነው
Jan 24, 2026 52
ደብረ ብርሃን፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል መንግሥትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰው የዘላቂ ሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። የተሃድሶ ሥልጠና የወሰዱ የቀድሞ ታጣቂዎች የማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሂዷል። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደጀኔ ልመንህ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤በክልሉ መንግሥትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የተደረሰው የዘላቂ ሰላም ስምምነት የተሳካ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የቀድሞ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በመፍታት በየቀኑ እየገቡ መሆኑን ጠቁመው፥መንግሥትም የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት በዘላቂነት የማቋቋም ሥራ መቀጠሉን ተናግረዋል። አሁን ላይ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት መኖሩን ጠቅሰው፤ ይህም ለልማትና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ቀጣይነት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል። መንግሥት ለዘላቂ ሰላምና ልማት በትጋትና በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የሥልጠና ዳይሬክተር ብርሃኑ ተስፋዬ ናቸው። የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት የማቋቋም ሥራም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውቀዋል። የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው የተመረቁ የቀድሞ ታጣቂዎች በሚሰማሩበት የልማት መስክ ሁሉ ለሀገር ሰላምና ልማት የላቀ አበርክቶ እንደሚኖራቸውም አመላክተዋል። ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ በመቆም መሥራት የዜጎች ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። የቀድሞ ታጣቂዎችም የበደሉትን ሕዝብ በልማት ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን ባወጡት ባለስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ አረጋግጠዋል።
ማህበራዊ
ባህላዊ ሥርዓቶች ውስጥ ያሉ የአብሮነት ዕሴቶችን ለሰላም ግንባታና ልማት መጠቀም ይገባል
Jan 24, 2026 43
ሸኮ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፦ ባህላዊ ሥርዓቶች ውስጥ ያሉ የአብሮነት እሴቶችን ለሰላም ግንባታና ልማት መጠቀም እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ተናገሩ። የሸኮ ዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል "ቲካሻ ቤንጊ" በሸኮ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶች ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ ውስጥ ያሉ ብሔረሰቦች የራሳቸውን ባህል፣ ታሪክና ሥርዓት በማልማት የመጠቀም ልምድ እየተጠናከረ መጥቷል። የሸኮ ዘመን መለወጫ "ቲካሻ ቤንጊ" የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና የእርቅ ዕሴቶች እንዳለው ጠቅሰው እነዚህን እና ሌሎች ባህላዊ ሥርዓቶችን ጠብቆ ለሰላም ግንባታና ልማት መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። አዝመራ ተሰብስቦ በጎተራ ከተከማቸ በኋላ የጥጋብና የደስታ ዘመን ማሳያ ተደርጎ የሚከበረው "ቲካሻ ቤንጊ" ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መጠናከር ትርጉም ያለው እንዲሆንም መስራት ይገባል ነው ያሉት። ሸኮዎች ተፈጥሮን የሚንከባከቡበትና የባህላዊ ግጭት መፍቻ እውቀቶች ሳይበረዙ ለትውልድ በመሸጋገር ጥቅም እንዲሰጡ መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። በክልሉ ባህላዊ ሥርዓቶች ያሏቸውን መልካም እሴቶች ለማጎልበት የክልሉ መንግሥት እኩል የመልማት ዕድል እንደሚያመቻችም ርዕሰ መስተዳደሩ ጠቁመዋል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን "ቲካሻ ቤንጊ" አዲስ እህል በጋራ በመቅመስ የሚከበር የቀደምት አባቶች ሥርዓት ሲሆን ከምርትና ምርታማነት ጋር የተሳሰረ መሆኑንም ገልጸዋል። ተስማምቶ በሰላምና በፍቅር የመኖር ትርክት የሚነገርበት "ቲካሻ ቤንጊ" መከበሩ ጠቃሚ ዕሴቶች ለትውልድ እንዲተላለፉ አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራልም ብለዋል። ሸኮዎች ከማኅበራዊ ሥርዓት ባሻገር ከተፈጥሮ ጋር ባላቸው ቁርኝት ጠብቀው ካቆዩት ደን ውስጥ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና እና ማር ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል። የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉሩሙ በበኩላቸው "ቲካሻ ቤንጊ" በዓል ስላለፈው አዝመራ እና የምርት ሁኔታ ምስጋና፥ ለቀጣይ ልማትም ልመና ለፈጣሪ የሚቀርበበት እንደሆነ ገልጸዋል። በበዓሉ ከጎረቤት ጋር ተሰባስቦ በመብላትና በመጠጣት ከማክበር ባሻገር ስለ አካባቢው መመካከርና ስለ ቀጣይ እርሻ ሥራ መመሪያና ምረቃ ከአባቶች የመቀበል ትውፊታዊ ሥርዓት እንዳለ ጠቅሰዋል። መንግሥት ለባህል ልማት በሰጠው ትኩረት እየተከበረ ባለው "የቲከሻ ቤንጊ" በዓልን በማልማት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ ገዛኸኝ ኡፐም እና ታታሪ ዘካሪያስ ከሩቅም ከቅርብም በአንድ አደባባይ ተሰባስበን ማክበራችን አብሮነታችን ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል። ተደብቀው የቆዩ ቱባ የባህል ሃብቶችን መጠቀም ከተቻለ የልማትና የተረጋጋ የሰላም ሁኔታን በጋራ መፍጠር እንደሚቻል ተናግረዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት እያሳደገ ነው
Jan 24, 2026 135
አሶሳ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ችግር በማቃለል የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሩ ማስቻሉን የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ተናገሩ። የኢትዮጵያ ደን ልማት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቡራሞ ወረዳ ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለዐቅመ ደካሞች አስረክቧል። በዚሁ ወቅት አቶ ከበደ፤ ለዐቅመ ደካሞች የሚደረገው ድጋፍ መንግሥት ለወገን ደራሽ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ብሎም እያከናወነ ያለው ሰው ተኮር ተግባር አካል ነው ብለዋል። ከቤት ግንባታ በጨተማሪ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። የቤቱ ባለቤቶች ፈዳይል ደኑ እና ኪፈያ አሲመድ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት የነበረው የመኖሪያ ቤታቸው ለመኖሪያ ምቹ እንዳልነበረ አውስተዋል። አሁን የኢትዮጵያ ደን ልማት ምቹ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ስለሰጣቸው መደሰታቸውን እና ቤቶቹ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ሙሉ የቤት ዕቃ የተሟላላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። መንግሥት እያከናወነ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
አምስተኛው ሀገር አቀፍ የሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ለኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ስኬትና ለፖሊሲ ግቦች መሳካት ቁልፍ ሚና የጫወታል-ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)
Jan 24, 2026 50
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡-አምስተኛው ሀገር አቀፍ የሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ለኢትዮጵያ የልማት ዕቅዶች ስኬትና ለፖሊሲ ግቦች መሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። አምስተኛው ዙር የኢትዮጵያ የሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት ይፋ ማድረጊያ አውደ ጥናት እየተካሔደ ነው። ጥናቱ በእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ በቤተሰብ ዕቅድ አጠቃቀም፣ በወሊድ መጠን፣ በጤና ተቋም የመውለድ ተሞክሮ፣ በሕፃናት ክትባት እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳየች ላይ ያተኮረ ሲሆን የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸው ተመላክቷል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፥ ጥናቱ ከመደበኛ ስታቲስቲካዊ መረጃነት ባለፈ ለሀገራዊ ብልጽግና ጉዞ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ያለው የፖሊሲ መሣሪያ ነው ብለዋል። ጥናቱ መንግሥት ለልማት ዕቅዶች ስኬታማነት በመረጃ ላይ የተመሠረተ አሠራርን ለመከተል ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም አክለዋል። ጥናቱ ከጤና ዘርፍ በዘለለ ሰፊ የማክሮ-ኢኮኖሚ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሯ የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ለመገምገም እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሰው ኃይል ልማት፣ በእናቶችና ሕፃናት ጤና እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች የታዩ ለውጦችን በትክክል ለመለካት እንደሚያስችል ጠቅሰው፥ ጥናቱ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የተከተለ መሆኑ ለመረጃው ተዓማኒነትና ለዓለም አቀፍ አጋርነት ወሳኝ መሠረት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፥እውነተኛና ጥራት ያለው መረጃ የወደፊቱን የጤና ሥርዓት ውጤታማ ለማድረግ ዋነኛው መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ ሲተገበሩ የነበሩ መረጃዎች በአብዛኛው በግምትና በትንበያ ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ አዲሱ ጥናት ግን ያለንበትን እውነታ በሐቀኝነት ለመገምገም እንደሚረዳና ለቀጣዩ የጤና ዘርፍ የኢንቨስትመንት ዕቅድ እንደ መነሻ እንደሚያገለግል አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት እንደ ኮቪድ-19 እና የአየር ንብረት ለውጥ ያሉ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ቢገጥሟትም፣ ጥናቱ ሳይስተጓጎል እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጌጎ ተስፋዬ (ዶ/ር)፤ የጥናቱ ውጤት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘላቂ የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓት ለመዘርጋትና የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚረዳ ትልቅ መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ውጤቱ የበርካታ ወገኖች የተቀናጀ ርብርብ ግኝት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ተዓማኒ መረጃን የማመንጨትና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ የመቅረጽ አቅሟን በተግባር ያረጋገጠችበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ዴስክ ኃላፊና የጥናቱ አቅራቢ አቶ ወርቅነህ ወልደጊዮርጊስ እንደገለጹት፤ ጥናቱ በእናቶችና ሕፃናት ጤና እና በቤተሰብ ዕቅድ አጠቃቀምና በወሊድ መጠን ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በጤና ተቋም የመውለድ ተሞክሮ፣ በሕፃናት መቀንጨር እና የሕፃናት ክትባትን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችም የጥናቱ ትኩረት እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሠረትም መሻሻሎች እየታዩ መሆኑን ጠቅሰው፥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትም ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን አመላካች መሆኑን ገልጸዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ምሁራን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሚናቸውን በይበልጥ ማጎልበት ይጠበቅባቸዋል
Jan 24, 2026 43
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- ምሁራን የጋራ ትርክትን በማስረጽ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሚናቸውን ማጎልበት እንደሚጠበቅባቸው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) አስገነዘቡ። ለልጆቻችን የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ ምሁራን የወል ትርክትን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ኃላፊነት አለብን ሲሉም ገልጸዋል። ምሁራን የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጹ ስትራቴጂካዊ መሐንዲሶች መሆናቸውን ገልጸው፤ ትውልድን በመቅረጽና የጋራ መግባባትን በመፍጠር ረገድ ቀዳሚውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ቀደም ሲል የጋራ ማንነትን የሚገነቡ የወል ትርክቶች መዳከማቸው ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አውስተዋል። ምሁራን በዝምታ ውስጥ በመሆን የታሪክ ተወቃሽ መሆን የለባቸውም፤ በመማር ማስተማር ሂደት ያሉ መምህራንም የተማሪዎችን ስብዕና እና ሀገራዊ ፍቅር በመገንባት ላይ ሊሠሩ ይገባል ብለዋል። የወል ትርክቶች ከታችኛው እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካተው ትውልዱ እንዲማርባቸው ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ምሁራን በትውልድ መካከል ድልድይ በመሆን የጋራ መግባቢያ ነጥቦችን ማፍለቅ እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመው፤ ልዩነቶችን ወደ ውበት የሚቀይሩ ጥናታዊ ጽሑፎችንና ውይይቶችን ማበረታታት ይገባቸዋል ብለዋል። የወል ትርክትን ማጎልበት የኅልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ምሁራን በያሉበት መስክ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢኮኖሚ
የኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ይጠናቀቃል
Jan 24, 2026 27
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018(ኢዜአ)፦ የኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር የሚያገናኘው የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ማጠናቀቅ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ-ጁቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ገለጸ፡፡ የባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን አቅም መከናወኑ በቀጣይ በዘርፉ ለሚከናወኑ ሥራዎች የተሻለ ልምድና አቅም መፍጠር የሚያስችል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ ኤ ኤም ጂ ኢንዱስትሪ ፓርክን ከዋናው ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ጋር የሚያገናኘው የሶስት ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ግንባታ በመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል፡፡ የባቡር መስመሩ መገንባት የባቡር መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የተለያዩ የወጭና ገቢ ምርቶችን ለማጓጓዝ የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል፡፡ በኢትዮ-ጁቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ባለሙያዎች አቅም የሚገነባው ይሄው የባቡር መስመር ግንባታ በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለታል፡፡ የፕሮጀክቱ ማናጀር ኢንጅነር ንግስት ሀይሉ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የባቡር መስመሩን ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ ቀድሞ ማጠናቀቅ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት የባቡሩን ሀዲድ ለማንጠፍ የሚያስችሉ የጉድጓድ ሙሌት፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት እንዲሁም የማፋሰሻ ግንባታዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የባቡር መስመር ግንባታው 70 በመቶ መድረሱን ገልጸው፤ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚያስችል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ የባቡር መስመር ግንባታው በኢትዮጵያውያን አቅም የሚሰራ መሆኑን ገልጸው፤ አስፈላጊውን የሰው ሀይልና የግንባታ ግብዓቶች በማሟላት በትጋት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ግንባታው በኢትዮጵያውያን አቅም መሰራቱ በቀጣይ በዘርፉ ለሚከናወኑ ሥራዎች የተሻለ የሥራ ልምድና አቅም መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶችን በብዛት የማምራት ሥራ እየተከናወነ ነው
Jan 24, 2026 59
አዳማ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የግብርና ምርቶችን በጥራት እና በብዛት የማምራት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ተናገሩ። በክልሉ የግብርና ሽግግር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የሁለተኛ ምዕራፍ የትግበራ ፕሮግራም ለባለድርሻ አካላት የማስተዋወቂያ መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። አቶ አወሉ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን የተቀናጀ ቴክኖሎጂና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለአርሶአደሩ በአግባቡ ተደራሽ እየተደረገ ነው። ሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ፕሮግራም በተለይም አርሶአደሩ የቴክኖሎጂና የግብዓት አቅርቦት በሚፈልገው መልኩ እንዲያገኝ የሚያግዝ ነው ብለዋል። የአፈር ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ የእርሻ ትራክተርና ኮምባይነር በአግባቡ ማቅረብ እንዲቻል ሥራውን የሚያሳልጥ ኩባንያ እንደሚቋቋምም አመላክተዋል። በብዛት ከማምረትና በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች በማምረት ለውጪ ገበያ የማቅረብ ሥራው እንደሚጠናከር አስገንዝበዋል። አርሶ አደሩን ጨምሮ የግብርና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በጥራት፣ በብዛትና በአይነት ማምረት ላይ ማተኮር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ደሳለኝ ዱጉማ በበኩላቸው፤ በክልሉ በ25 የግብርና የምርት አይነቶች ምርታማነት ለመጨመር ኢንሼቲቭ ተቀርጾ እየተሠራ ነው ብለዋል። ምርትና ምርታማነት እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው፤ በክልሉ ከ7 ሚሊየን በላይ አርሶአደሮች በኩታ ገጠም ተደራጅተው ወጥነት ባለው መልኩ ቴክኖሎጂና የኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በተለይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ኢንዱስትሪ መር የግብርና አሰራርና አመራረት ሂደት ለመከተል እንዲሁም የአርሶአደሩን ተጠቃሚነትና የግብርና ሽግግር ለማፋጠን በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወነ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም የሰብል እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ማሳደግ እንደተቻለም ጠቁመዋል። በዋና ዋና ሰብሎች በተለይ ስንዴ፣ የቢራ ገብስ፣ በቆሎና ሌሎች ሰብሎች ምርት ከመጨመር ባለፈ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የስንዴና ቢራ ገብስ ምርት በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉንም አስታውሰዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ትግበራም ገበያ ተኮር የሰብል እና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በጥራት፣ በብዛትና በአይነት በማምረት በእሴት ሰንሰለት አልፈው ለገበያ እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል። በተጨማሪም የምርት ማቀነባበሪያዎች በማስፋፋት ረገድ አርሶ አደሩ ባለቤት እንዲሆንና ለምርቱ ተገቢውን ገበያ እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑንም አመላክተዋል።
የሴፍትኔት ፕሮግራሙ ከራስ አልፎ ለሌሎች መትረፍ የሚቻልበትን ዕድል ፈጥሯል
Jan 24, 2026 41
አዳማ፣ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት ሶስት ዓመታት ሲተገበር የቆየው የምግብ ዋስትናና የሴፍትኔት ፕሮግራም ዜጎች ከራስ አልፈው ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማስቻሉን የአዳማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በአስተዳደሩ በምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመሳተፍ ሽግግር ያደረጉ 646 አባወራና እማወራዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ንጋቱ ሞቱማ በዚሁ ወቅት፤ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ድህነትን በመቀነስና የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት በከተማ ጽዳትና ውበት፣ በአረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ላይ በመሳተፍ የራሳቸውን ገቢ በመፍጠር ኑሯቸውን አሻሽለዋል ሲሉም ገልጸዋል። ፕሮግራሙ በከተማዋ በድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ኑሮ በመቀየር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው፤ አስተዳደሩ ተጠቃሚዎቹን ወደ ዘላቂ ልማት በማሸጋገር ረገድ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። አስተዳደሩ ለሥራ እድል ፈጠራ የገነባቸውን ሼዶች የፕሮግራሙ ተሳታፊዎችን በማደራጀት አንደሚያስተላልፍና የባንክ ብድር የሚያገኙበትን ዕድል አንደሚፈጥርምአመልክተዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ግዛው በበኩላቸው፤ በከተማዋ በተመረጡ አካባቢዎች የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሙ መተግበሩን አውስተዋል። የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ከጊዜያዊ ድጋፍ ባለፈ ከተረጅነት ራሳቸውን በማላቀቅ ቋሚ ጥሪት ማፍራት እንዲችሉ የመቋቋሚያ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም አረጋግጠዋል። ከተጠቃሚዎች መካከል የመልካ-አዳማ ወረዳ ነዋሪ ዓባይነሽ ደርቤ፣ በፕሮግራሙ ከመታቀፋቸው በፊት ከአራት ልጆቻቸው ጋር በችግር ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ተናግረዋል። በከተማ ጽዳትና ውበት ስራ በመሳተፍ ከሚያገኙት ገቢ ቆጥበው የወተት ላም በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሪት ማፍራትና ኑሯቸውን ማሻሻል መቻላቸውንም ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት ተመረተ
Jan 24, 2026 81
አርባ ምንጭ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት መመረቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ አፈጻጸም ተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተገመገመ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚሁወቅት፤ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገሪቱ ራሷን የምትችልበት የሉዓላዊነት ማጠንጠኛ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ባለፉት ስድስት ወራት 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት መመረቱን ገልጸው፤ 204 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርትም ወደ ውጭ ተልኳል ብለዋል። በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ161 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፤ በዘርፉ በርካታ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ መቻሉን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነቃቃ በማድረጉ የማምረት ዐቅም ባለፈው ዓመት ከነበረው ከ46 በመቶ ዘንድሮ ወደ 66 በመቶ አድጓል ነው ያሉት። በሌሎች ሀገራት የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ መኖር አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱን በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማበልጸግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በተኪ ምርት ላይ ትኩረት በማድረጋችን ፈጣን ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል፤ ይህም የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን የሚያጠናክር ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ሥራ የመገባቱ ውጤት ነው ብለዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጌትነት በጋሻው (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክልሉ ከ2 ሺህ በላይ አነስተኛ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች እንዳሉ ጠቅሰው ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። መንግሥት ለኢንዱስትሪ ልማት በሰጠው ትኩረት የዜጎች ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መምጣቱን የተናገሩት ደግም በብልጽግና ፓርቲ የአርባ ምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አይሶጸ ሂሎታ ናቸው። በአካባቢው የሚገኙ የሞሪንጋ፣ ሙዝና የሸማ ምርቶች ላይ ዕሴት በመጨመር ተጠቃሚነትን ማሳደግ መቻሉንም አስታውቀዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢኒስቲትዩቱ ይፋ ያደረገው የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ የሥራ ጫናን ከማቅለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል
Jan 24, 2026 29
ሀዋሳ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፦የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በመቀናጀት ይፋ ያደረገው የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ የሥራ ጫናን ከማቃለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። የቋሚ ኮሚቴው አባላት በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ በኢንስቲትዩቱ የተሰራ ዘመናዊ የእንሰት መፋቂያ ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራን ተመልክተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺ ሀሰን በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፣ኢንስቲትዩቱ የህብረተሰቡን ኑሮ የሚያቃልሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያፈለቀ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የስራ ጫና የሚያቃልል የእንሰት መፋቂያ፣ መጭመቂያና መቁረጫ መሳሪያ አንዱ ነው ብለዋል። በርካታ ሴቶች በእንሰት ሥራ እንደሚሰማሩ ገልጸው፣ እንዲህ አይነት ቴክኖሎጂዎች መምጣታቸው የሥራ ጫናውን ከማቃለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ፈጣን እድገት ለአፍሪካ ሀገራት አብነት ይሆናል - የአፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች
Jan 23, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር ኃይል ፈጣን እድገት ለአፍሪካ ሀገራት አብነት ይሆናል ሲሉ የአፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀው የአቪዬሽን ኤክስፖ ተከፍቷል። ኤክስፖው የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ኤክስፖውን የጎበኙ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች፤ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ በሚሆን አግባብ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ስለመሆኑ መታዘባቸውን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የቦትስዋና ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ሞታሲ ቼሌኒያኔ፤ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በአቪዬሽን፣ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አስደማሚ ለውጥ ውስጥ መሆኑን ከኤክስፖው መመልከታቸውን ገልጸዋል። በተለይ አየር ኃይሉን ጥገናን ጨምሮ በሌሎች ቁልፍ የዘርፉ ምህንድስና ስራዎች ራሱን ለመቻል እያከናወነ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን አንስተው፤ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከዚህ ልምድ መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የናሚቢያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ማካንዚ ቺቤራ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ባለፉት ጊዜያትም ሆነ አሁን ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የራሱን እና የአፍሪካን አቅም ለማሳደግ ጥረት እያደረገ ነው። የአፍሪካ ሀገራት በጋራ እና በትብብር ከሰሩ ብዙ ርቀት መሄድ እንደሚችሉ ጠቁመው፤ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የወሰደውን ተነሳሽነት አድንቀዋል። በኢትዮጵያ የጋቦን ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል አርሲዴ አንጉሌ፤ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሀገር የሚወክል ተቋም እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ጥሩ ምሳሌ ነው ብለዋል።
የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ሥራችንን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ አግዞናል -ሰልጣኞች
Jan 23, 2026 142
ወልቂጤ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮ-ኮደርስ ያገኙት ስልጠና የዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ ሥራቸውን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ እንዳገዛቸው በወልቂጤ ከተማ የኮደርስ ሰልጣኞች ገለጹ። መንግስት ለዜጎች ያመቻቸው የአምስት ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ዜጎች ከዲጂታል ዓለሙ ጋር ለመራመድ የሚያስችላቸውን የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት እያስጨበጣቸው ነው። በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞችም ስልጠናውን እንዲወስዱ በአስተዳደሩ የተመቻቸላቸውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የዲጂታል እውቀታቸውን እያሳደጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ስልጠናውን የወሰዱት ሠራተኞች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኢትዮ-ኮደርስ በተለያዩ ዘርፎች ያገኙት ስልጠና የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማሳደግ ሥራቸውን እንዲያዘምኑና ውጤታማ እንዲሆኑ እያገዛቸው ነው። በወልቂጤ ከተማ የኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ባለሙያ ወጣት ሰለሞን ደርብ በኢትዮ ኮደርስ በዳታ ፕሮግራሚንግ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በአንድሮይድ ዘርፎች ስልጠና ወስዶ ክህሎቱን ማሳደጉን ተናግሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በሌሎች ዘርፎች ተጨማሪ ስልጠና እየወሰደ መሆኑን ጠቁሞ፣ በኮደርስ ስልጠና ባገኘው እውቀት በትርፍ ሰአቱ ተጨማሪ ሥራ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግሯል። የከተማው ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ባለሙያ ወጣት ጅብሪል መጀል በበኩሉ፤ የዲጂታል እውቀቱን ለማሳደግ የሚያግዘውን የኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ከራሱ ባለፈ ሌሎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል። ያገኘው ስልጠና በኮምፒውተር ሳይንስ በዲግሪ ለመማር መነሳሳት እንደፈጠረለት ገልጾ፣ በቀጣይም በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጠውን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል። በማይክሮ ሶፍት መተግበሪያዎች በወሰደው ስልጠና ያገኘውን እውቀትና ክህሎት በተቋም ሥራ በመተግበር ሥራውን ለማቀላጠፍና ለችግር መፍቻነት እየተጠቀመበት መሆኑን ተናግሯል። በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ያለንን እውቀትና ክህሎት በማሳደግ ከዲጂታል ዓለም ፈጣን እድገት ጋር ለመጓዝ የሚያስችል ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ ሰልጣኝ ወይዘሮ አቻምየለሽ ዘርጋ ናቸው። ስልጠናው ከኋላቀር የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማላቀቅ የግልና የመስሪያ ቤት መረጃዎችን ለማዘመን የሚያስችል እውቀት እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡ በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በአራት የተለያዩ ዘርፎች የቀሰሙት እውቀት በቴክኖሎጂ ብቁና ተወዳዳሪ ባለሙያ እንዳደረጋቸው የተናገሩት ደግሞ የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ባለሙያ አቶ ጅላሉ ሙዘይን ናቸው ። ስልጠናው የተለያዩ አገልግሎት የሚሠጡ ሶፍትዌሮችን አበልጽገው እንዲጠቀሙ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሃምዱ ካሚል፤ በከተማው እስካሁን ድረስ 20ሺህ የሚጠጉ ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደው የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በቀጣይ ስልጠናውን በሁሉም የመንግስት መዋቅር ተደራሽ በማድረግ ዜጎች የቴክኖሎጂ ክህሎትና ዕውቀታቸውን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ኮሌጆች ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት የማይተካ ድርሻ አላቸው
Jan 23, 2026 69
ቦንጋ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ብቃት ያለው የሰው ሀይል በማፍራት የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናና ፋይዳ መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የቢሮ ምክትል ሀላፊና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስፋው እንደገለጹት፤ ኮሌጆች ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ብቃት ያለው የሰው ሀይል በማፍራት የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ ለዚህም ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ግብአቶች በማደራጀት ለሰው ሀይል ልማት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አክለዋል። ለዲጂታል ኢትዮጵያ መሳካት ድርሻ ላላቸው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እና ለፋይዳ መታወቂያ ኢንሼቲቮች ትኩረት መስጠት ሌላው ተግባራቸው መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። በክልሉ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዓመት ከ110 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እስካሁን ድረስ 28 ሺህ 90 ሰዎች እንደወሰዱና 8 ሺህ የሚጠጉትም ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ዜጎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በዓመቱ ለማሳካት ከታቀደው ውስጥ እስካሁን ድረስ 246 ሺህ 436 ዜጎችን የመታወቂያው ባለቤት ለማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል። ሥራውን ለማሳካትም የአሁኑ የንቅናቄ መድረክ ተደማሪ አቅም ይሆናል ብለዋል። በመድረኩ የተገኙት የካፋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ በበኩላቸው፤ በዞኑ በኮደርስ ስልጠና በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሥራዎች እንደተጀመሩና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ኢንሼቲቮቹን ለማሳካት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሁለተኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መደረጉንም ጠቁመዋል።
ስፖርት
ዌስትሃም ዩናይትድ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል
Jan 24, 2026 38
አዲስ አበባ፤ ጥር 16 /2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ሰንደርላንድን 3 ለ 1 አሸንፏል። በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሪሴንሲዮ ሳመርቪል እና ማቲውስ ፈርናንዴዝ በጨዋታ ጃሮድ ቦወን በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ብሪያን ብሮቤይ ለሰንደርላንድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ዌስትሃም ዩናይትድ በ20 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን አስመዝግቧል። ዌስትሃም ዩናይትድ ከዋርጅ ቀጣና ለመውጣት እያደረገ ባለው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። 17ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስት ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሰንደርላንድ በ33 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል
Jan 24, 2026 49
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ እጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል። በዚሁ መሠረት ነገሌ አርሲ ከሲዳማ ቡና፣ ቤንች ማጂ ቡና ከኢትዮጵያ መድን፣ መቻል ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ቦዲቲ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ። የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር መጋቢት 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል። በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 81 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ውድድር ነው።
ማንችስተር ሲቲ ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል
Jan 24, 2026 80
አዲስ አበባ፤ጥር 16/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል። በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ምሽት 12 ሰዓት ላይ ማንችስተር ሲቲ በኢትሃድ ስታዲየም ዎልቭስን ያስተናግዳል። ማንችስተር ሲቲ በ43 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ዎልቭስ በስምንት ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ውሃ ሰማያዊዎቹ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፉም። ከ12 ነጥብ ማግኘት የቻሉት ሶስት ብቻ ነው። በአንጻሩ በሊጉ 16 ሽንፈት ያስተናገደው ዎልቭስ በበኩሉ በውድድር ዓመቱ አንድ ጨዋታ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው። ማንችስተር ሲቲ በዋንጫ ፉክክሩ ለመቆየት ከዛሬው ጨዋታ ሶስት ነጥብ መውሰድ ይኖርበታል። ዎልቭስ ማሸነፍ ከከረመበት ወራጅ ቀጠና ለመውጣት በሚያደርገው ትግል አጋዥ አቅም ይሆነዋል። በሌሎች መርሃ ግብሮች ቦርንማውዝ ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ በቫይታሊቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። ቦርንማውዝ በ26 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ባለሜዳው ቦርንማውዝ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ፣ ሊቨርፑል ከአራት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ። ዌስትሃም ዩናይትድ ከሰንደርላንድ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30፣ ፉልሃም ከብራይተን እና በርንሌይ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው
Jan 23, 2026 105
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የስፖርት ቱሪዝም ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። የስፖርት ቱሪዝም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣ የቱሪዝም ዘርፍ ነው። በኢትዮጵያም በአትሌቲክስ፣ በጎዳና ላይ ሩጫ፣ ባሕላዊ እና ሌሎች የጉብኝት ቦታዎች የእግር ጉዞ የስፖርት አይነቶች ለስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚነት ምቹ አቅሞች ናቸው። የኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም አቅሞችም በሀገር ገጽታ ግንባታ፣ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማሳደግና በስፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው። የአዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማትም በስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየም ግንባታ፣ በብስክሌትና በእግር መንገድ የስፖርት ዘርፎች ለስፖርት ቱሪዝም ዕድገት ወሳኝ ምዕራፍ ከፍተዋል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በጥቂት ዓመታት ውስጥ በአዲስ አበባ የተገነቡ መሠረተ ልማቶች ለስፖርት ቱሪዝም እንቅስቃሴ ምቹ ምኅዳር መፍጠር አስችለዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሐመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን ለስፖርት ቱሪዝም ምቹ ለማድረግ የተሰሩ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት እያስገኙ ነው ብለዋል። በተለይም የመዲናዋ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት እያደገ መምጣት ለስፖርት ቱሪዝም እንቅስቃሴ ወሳኝ ምዕራፍ መክፈቱን ገልጸዋል። በዚህም ባለፉት ሁለት ዓመታት 16 ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ሁነቶችን በስኬት በማስተናገድ ኢትዮጵያ ለስፖርት ቱሪዝም አቅም እንዳላት በተግባር ማሳየት እንደተቻለ ተናግረዋል። ለአብነትም በየዓመቱ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎች የሚሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት መስተናገዳቸውን አንስተዋል። በኢትዮጵያ በስፖርት ቱሪዝም የሚስተናገዱ ሁነቶችም በሀገር ገጽታ ግንባታና በውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲሁም የስፖርት መሠረተ ልማትን በማስፋፋት አዎንታዊ ሚና እንዳላቸው አብራርተዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያ 32 ብሔራዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ዓለም አቀፍ የስፖርት ሁነቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያመጡ በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን 5ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክና የአፍሪካ የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያን የስፖርት ዲፕሎማሲ እና ስፖርታዊ ኩነቶች የማስተናገድ አቅም በማሳደግ ቀዳሚ የአፍሪካ የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የተፋሰስ ልማት ሥራ የመሬት ለምነትን በመጨመር ምርታማነትን አሳድጓል
Jan 23, 2026 130
ሃዋሳ፤ ጥር 15/2018 (ኢዜአ):-የተፋሰስ ልማት ሥራ የአፈር መሸርሸርን በማስቀረትና የመሬት ለምነትን በመጨመር ምርታማነታቸውን በማሳደጉ ልማቱን አጠናክረው መቀጠላቸውን የሲዳማ ክልል አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ አርሶ አደሮቹ ለኢዜአ እንዳሉት ቀደም ሲል በተፋሰስ ልማት ያከናወኗቸው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የአፈር መሸርሸርን በማስቅረትና የመሬት ለምነትን በመጨመር ምርትና ምርታማነታቸውን እያሳደገው ነው። ተጠቃሚነታቸውን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በአሁኑ ወቅትም የተፋሰስ ልማት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ከአርሶ አደሮቹ መካከል አቶ ቶማስ መራሳ እንደገለጹት በየዓመቱ በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ በመሳተፍ የአካባቢያቸውን ለምነት እየጠበቁ ነው፡፡ ተፋሰስ ልማቱ ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚ እያደረጋቸው በመምጣቱ በአሁኑ ወቅትም በቡድን ተደራጅተው ልማቱን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተከናውኖ ባገገሙ መሬቶችም ቡናና ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሌላው አርሶ አደር ጴጥሮስ ሶቾሳ በበኩላቸው በተፋሰስ ልማት ሥራው አርሶ አደሩ በንቃት እየተሳተፈና ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በአካባቢያቸው ከዚህ ቀደም ገላጣ የነበሩና የተጎዱ መሬቶች ማገገማቸውን ጠቅሰው፣ በእርሻ ማሳቸው የነበረውን ባህር ዛፍም በመንቀል የመሬታቸውን ለምነት እየጠበቁና ምርታማነት እያሳደጉ መምጣታቸውን ተናግረዋል። የተፋሰስ ልማት ሥራው ምርት የማይሰጡ መሬቶች ወደ ምርት እንዲገቡና የሥራ እድል እንዲፈጠር ማድረጉን የገለጹት ደግሞ ሌላው አርሶ አደር ሳሙኤል ጢሞቲዮስ ናቸው። ቀበሌያቸው ተዳፋታማ በመሆኑ ጎርፍ መሬታቸውን በመሸርሸር ለምነቱን እያጣ በመምጣቱ ከልማቱ ተጠቃሚ ሳይሆኑ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ የተፋሰስ ልማት ሥራ ከተጀመረ ወዲህ በየዓመቱ ምርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው በክልሉ በየዓመቱ የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች የተጎዳ መሬት እንዲያገግም ጉልህ አስተዋጾ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የውሃ አማራጮችን በመጨመር የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና በመጫወታቸው ልማቱ በየዓመቱ እየተጠናከረ መምጣቱንም ገልጸዋል። በዚህም በክልሉ በየጊዜው በሚካሄዱ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ የሚሳተፉ አርሶ አደሮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ በዘንድሮ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ ከ147 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚለማ ሲሆን በተለዩ 678 ንኡስ ተፋሰሶች ለ30 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚከናወን ታውቋል።
ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በተፋሰስ ልማት ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው
Jan 22, 2026 98
ነቀምቴ ፤ ጥር 14 /2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደርና በተፋሰስ ልማት ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የውኃ ሀብትን በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው። ኢትዮጵያ የምትከተለው ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውኃ ሀብት አጠቃቀምና አስተዳደርም የልማት እንቅስቃሴን ለማፋጠን ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደርና በተፋሰስ ልማት ስራዎች እየከናወነች ያለው ሥራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን በመግለጽ። በሌላ በኩል ሚኒስቴሩ በተፋሰስ ልማትና በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል። ከውሃ ሀብት በተጨማሪ የኢነርጂ ሀብትን በአግባቡ መለየትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም አንስተዋል። በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፌዴራልና የክልሎች እንዲሁም ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።
የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ጥቅምን በተግባር ስላየነው አጠናክረን እንቀጥላለን - አርሶአደሮች
Jan 22, 2026 167
አሶሳ፤ ጥር 14/2018 (ኢዜአ)፦ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ጥቅምን በተግባር በማየታቸው ተግባሩን አጠናክረው መቀጠላቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቡልድግሉ ወረዳ አርሶአደሮች ተናገሩ። በምዕራብ ወለጋ ዞን በ 487 ተፋሰሶች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተከናወነ ነው የተፋሰስ ልማት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት ሆኗል- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አርሶአደ ሂድር ኡስማን እንዳሉት፤ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ዘላቂ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም እንዲኖር ከማድረግ በተጨማሪ የአካባቢውን የአየር ንብረት በማስተካከል ሚናው የጎላ ነው። ወይዘሮ ማርታ ዋቅቶላ በበኩላቸው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ መሠራት ከጀመረ ወዲህ በጎርፍ የሚወሰደው ለም አፈር በመቀነሱ ምርታማነታቸው እንዲጨምርና የአካባቢው ሥነ-ምኅዳርም መጠበቁን ተናግረዋል። የተፈጥሮ ፀጋን የማልማትና የመጠበቅ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከዚህ በፊት የተከናወነው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግ በደን እንዲሸፈኑ ማስቻሉን ያስረዱት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጭ ቢራቱ ፉፋ ናቸው። ቀደም ሲል ከተሠራው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ተጠቃሚነታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም አካባቢን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ ተግባር ስለሆነ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አርሶ አደሮቹ ለኢዜአ ገልጸዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አብዱልከሪም ሙሳ፤ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ሥነ-ምኅዳር ይጠብቃል፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በደለል እንዳይሞላ ይረዳል ብለዋል። ስለዚህ አርሶአደሩ ተሳትፎውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። ዘንድሮው በክልሉ ከ57 ሺህ ሔክታር በላይ ማሳ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን መታቀዱን አውስተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን በ 487 ተፋሰሶች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተከናወነ ነው
Jan 22, 2026 115
ጊምቢ፤ ጥር 14 /2018(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን በ487 ተፋሰሶች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና በጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ እንዳሉት፣ በዞኑ በ487 ተፋሰሶች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ ባለፉት አመታት በዞኑ በተከናወኑ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች በመጡ ተጨባጭ ለውጦች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረጋቸው ለዘንድሮ ተፋሰስ ልማት ስራዎች በነቂስ ወጥተው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ በዞኑ ከ273 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መካሄድ ጀምሯል በተለይም እየተከናወኑ ባሉ የተፋሰስ ልማት ስራዎች የእርከን ስራና ቀደም ብለው የለሙ ተፋሰሶች ከእንስሳትና ከሰው ንክኪ ነጻ እንዲሆኑ ጥበቃ ይደረግለታል ብለዋል። በዞኑ በላሎሳቢ፣ በመነስቡ፣ በጊምቢና ሆማ ወረዳዎች በእስካሁኑ እንቅስቃሴ በእርከን ስራ የተሻለ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በተፋሰስ ልማት መርሃ ግብር በተከናወኑት ስራዎች የተራቆቱ አካባቢዎች ወደ ልምላሜ መመለሳቸውን እና በዘንድሮው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ምክንያት እንደሆናቸው የሚናገሩት ደግሞ አርሶ አደር አምቢሳ ጉዲና ናቸው፡፡ ልማቱ ቀደም ሲል በአፈር መሸርሸር ምክንያት ምርታማነት ቀንሶ የነበረው የእርሻ መሬታቸው አሁን ላይ ማገገሙን ጠቅሰዋል። አርሶ አደር ከኔሳ አሙማ በበኩላቸው፤ ባለፉት አመታት በተከናወኑት የእርከንና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች በአካባቢያቸው ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በዘንድሮ የበጋ ወራት የእርከን ልማት ስራዎች ላይ ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ፤ ከድርቅ አደጋ ምላሽ ሰጪነት እስከ ቀጣናዊ ትስስር ተዋናይነት
Jan 21, 2026 192
በሙሴ መለሰ ምስራቅ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር በየጊዜው ከፍተኛ ለውጥ የሚያስተናግድ እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ቀጣና ነው። ከ300 ሚሊየን በላይ ህዝብ የሚኖርበት ይህ ቀጣና ከፍተኛ የሰው ሀብት ያለው ሲሆን ፈጣን የወጣት ህዝብ እድገት እና የገበያ ተደራሽነት መስፋት እየታየበት ይገኛል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የምስራቅ አፍሪካ አጠቃላይ ዓመታዊ ጥቅል ምርት(ጂዲፒ) እ.አ.አ በ2025 598 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ገልጿል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ያሉ ሀገራት የሚገኙበት ቀጣና ነው ምስራቅ አፍሪካ። ምስራቅ አፍሪካ ግብርና፣ ቁም እንስሳት፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮች እና በፍጥነት እያደገ የመጣው ዲጂታል ኢኮኖሚ እምቅ የኢኮኖሚ አቅሞቿ ናቸው። ከመልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻርም የኢትዮጵያ ከፍታማ ስፍራዎች፣ የታላላቅ ሀይቆች ተፋሰስ እና የአፍሪካ ቀንድ ዝቅተኛ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። ከቀይ ባህር እስከ ህንድ ውቅያኖስ ምስራቅ አፍሪካን የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የዓለም የማሪታይም ንግድ መተላለፊያ መስመሮች ይገናኙባታል። ይህ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ምስራቅ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና ጂኦ ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ሚና አሳድጓል። ቀጣናው ለመረጋገት እና ለትብብር ያለው ጠቀሜታም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለብዙ ክፍለ ዘመናት በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች በንግድ፣ በፍልሰት እና የባህል ትስስር ተጋምደዋል። በዘመናዊው ዓለም ይህ ታሪካዊ ትስስር ለቀጣናዊ ትስስር ጠንካራ አስተዋጽኦ ያለው ነው። በሀገራት በጋራ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች፣ የተሳናሰኑ ፖሊሲዎች እና የሰዎችና እቃዎች ነጻ ዝውውር የኢኮኖሚ እድገት እና አጠቃላይ ልማትን የሚያሳልጥ ነው። ቀጣናዊ ትስስር የተበታተነ ገበያ ወደ አንድ ማዕቀፍ ለማምጣት፣ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች በተለይም ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ አስተዋጽኦወ ቁልፍ ነው። ምስራቅ አፍሪካ እንደ እድሎቹ ሁሉ በርካታ ፈተናዎች ያሉበት ቀጣና ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚፈጠረው ድርቅ እና ጎርፍ፣ ግጭት፣ መፈናቀል እና የልማት ተደራሽነት ፍትሃዊ አለመሆን በዋናነት የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው። እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ፈተናዎች ከተናጠል ይልቅ የጋራ የተግባር ምላሽ ይፈልጋሉ። ፈተናዎችን ከግምት በማስገባት በቀጣናው በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ድርቅ እና የከባቢ አየር ችግር የተቀናጀ ምላሽ መስጠት የሚያስችለው ተቋማዊ ማዕቀፍ ከ40 ዓመታት በፊት ወደ ስራ ገባ። ይህ ተቋም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ነው። የኢጋድ መቋቋም እርሾ በወቅቱ በቀጣናው ያጋጥሙ የነበሩ ቀውሶች ናቸው። እ.አ.አ በ1980ዎቹ መጀመሪያ በቀጣናው የነበረው ድርቅ እና ረሃብ የብዙ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ይህም ቀጣናው ለአየር ንብረት ለውጥ ያለውን ተጋላጭነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። አደጋዎቹ ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው የተቀናጀ የጋራ ምላሽ የሚፈልጉ ናቸው። ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ዩጋንዳ ለአንገብጋቢው ቀጣናዊ ጉዳይ ምላሽ በመስጠት ኢጋድን እ.አ.አ በ1986 አቋቋሙ። ኢጋድ በወቅቱ ሲቋቋም ዋነኛ የስራ ድርሻው የነበረው ድርቅ፣ በረሃማነት እና ሁለቱ የሚያደርሷቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎችን ለመከላከል የሚደረጉ ቀጣናዊ ጥረቶችን ማስተባበር ነው። ይሁንና የከባቢ አየር ፈተናዎቹ ከፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ግጭት እና ካለመልማት ጋር ጥልቅ ቁርኝት ያላቸው መሆኑ አድማሱ የሰፋ ግብ ያለው ቀጣናዊ ተቋምን መፍጠር እንደሚያስፈልግ በወቅቱ ይነሳ ነበር። በዚሁ መሰረት ኢጋድ እ.አ.አ በ1996 በድጋሚ አደረጃጀቱ ተስተካክሎና የስራ ድርሻው ሰፍቶ እንደገና ተቋቋመ። ከድርቅ እና ከባቢ አየር ጉዳዮች በመሻገር ኢጋድ ሰላም እና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና ትስስር እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን ማጎልበት የተቋሙ ቁልፍ የትኩረት መስኮች ሆነዋል። የኢጋድ ዋና መቀመጫ ጅቡቲ ነው። የሰፋው የስራ ድርሻ ኢጋድን በአፍሪካ ቀንድ የምክክር፣ የውይይት እና የተቀናጀ ልማት የጋራ ማዕቀፍ እንዲሆን አድርጎታል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እ.አ.አ በ2026 የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት እንደሚያከብር ከሰሞኑ አስታውቋል። ኢጋድ በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ በስኬት ደረጃ ሊነሱ የሚችሉ ተግባራትን አከናውኗል። ከሰላም እና ደህንነት አንጻር ኢጋድ በቀጣናው ውስብስብ የሚባሉ ግጭቶች በእርቅ እና በውይይት እንዲፈቱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ለዓመታት በሱዳን ሲካሄድ የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲያበቃ እ.አ.አ በ2005 ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት እንዲፈረም በሰላም ሂደት ውስጥ የድርሻውን ተወጥቷል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ደቡብ ሱዳን በህዝበ ውሳኔ ራሷን የቻለች ሀገር ሆናለች። ኢጋድ በሶማሊያ የሰላም ጥረቶች ቁልፍ ተዋናይ ነበር። በሶማሊያ የፖለቲካ እርቅ እና መረጋጋት እንዲፈጠር ሲከናወኑ በነበሩ ስራዎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል። ቀጣናዊ ተቋሙ ባለው የእርቅ የስራ ክፍል ግጭቶች እንዳይከሰቱና ከተከሰቱም እንዲፈቱ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣም ይገኛል። ከተቋቋመበት የስራ ድርሻ አኳያ ኢጋድ በምግብ ደህንነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አደጋ ስጋት አስተዳደር ላይ ሰፋፊ ተግባራትን አከናውኗል። ለአብነትም የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያና ትግበራ ማዕከል (ICPAC) የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን በማጠናከር፣ በአየር ትንበያዎች እና የፖሊሲ ድጋፎች አማካኝነት አባል ሀገራት ለድርቅ እና ጎርፍ አደጋዎች ምላሽ እንዲሰጡ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል። ይህም ቀጣናዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን ለማጠናከርና የመንግስታትን አቅም ከመገንባት አኳያ ትልቅ ድርሻ እንደተወጣ ማዕከሉ ይገልጻል። ከኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ ትስስር አኳያም ኢጋድ ድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንዲያድግ፣ መሰረተ ልማት እንዲስፋፋና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲጠናከሩ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በትራንስፖርት ኮሪደሮች፣ በአርብቶ አደሮች እንቅስቃሴዎችና ቀጣናዊ ገበያዎች ላይ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ በአባል ሀገራት እንዲተገበር ከማድረግ ባለፈ ድጋፉን እየሰጠ ነው። ኢጋድ በቀጣናው ለንግድ እና ለእንቅስቃሴ የሆኑ መሰናክሎች እንዲቀንሱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ኢጋድ ከፍልሰተኞች ና ተፈናቃዮች ጋር ያሉ ችግሮች እንዲፈቱና ጉዳዩ ከፈተና ባለፈ የልማት እድል እንደሆነ በማንሳት ሁሉን አቀፍ እይታ እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል። በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢጋድ ተቋማዊ አቅሙን በማጠናከርና አጋርነቱን በማስፋት ረገድ የተለያዩ ስራዎችን አከናውኗል። ኢጋድ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰራ ነው። ተቋሙ በቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ ደረጃዎች ለአባል ሀገራት ቋሚ የምክክር ማዕቀፍ ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ይህም በሀገራት መካከል የጋራ መተማመንና የጋራ መግባባት እንዲኖር ያለው አስተዋጽኦ ወሳኝ የሚባል ነው። የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ በስኬቶች ብቻ የታጀበ አይደለም። ቀጣናዊ ተቋሙ ከፍተኛ ፈተናዎችም አጋጥመውታል። የመጀመሪያው በተደጋጋሚ ጊዜ የሚቀሰቀሱ እና ዘላቂ መቋጫ ያላገኙ ግጭቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ናቸው። ጉዳዮቹ የኢጋድን የእርቀ ሰላም ጥረቶች ፈተና ውስጥ ከተውታል። አንዳንድ ጊዜ በአባል ሀገራት መካከል ያሉ መከፋፈሎች ኢጋድ ቆራጥ ውሳኔ እንዳይወስን ሲገድበው ታይቷል። የፋይናንስና ተቋማዊ አቅም ውስነነቶች የኢጋድ የተለያዩ ማዕቀፎች ትግበራ ላይ መስተጓጎሎችን ፈጥረዋል። ኢጋድ ከውጭ አጋሮች የሚያገኘው ፈንድ ከራስ ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦት ጋር ማመጣጠን አለመቻል የተቋሙን የዘላቂነት እና የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ተጽእኖ አሳድረዋል። የፖለቲካ ተንታኞች ተቋሙ ከአባል ሀገራቱ የሚያገኝውን ጨምሮ ገቢ እና የፋይናንስ ቅሙን የሚያጠናክርባቸውን መንገዶች በሚገባ ማየት እንዳለበት ይመክራሉ። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ሌላኛው የኢጋድ ፈተና ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ደጋግመው የሚከሰቱ ድርቆች እና የጎርፍ አደጋዎች በተቋማዊ ምላሽና አቅም ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል። ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የከተሜነት መስፋፋትና መፈናቀል ጫናዎቹ ይበልጥ እንዲበረቱ አድርገዋል። ቀጣናዊ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎችን ወደ ተጨባጭ የሀገራት ትግበራ የማሸጋገር ጉዳይም ትኩረት እንደሚያሻውም ይነሳል። የሀገራት የሚለያዩ የትኩረት መስኮች እና አቅሞች በቀጣናዊ ማዕቀፎች ሂደትና ትግበራ ላይ የራሳቸውን ተጽእኖ ያሳድራሉ። 40 ዓመታትን ያስቆጠረው ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ትብብር ያለውን ወሳኝ ጠቀሜታ የሚያሳይ ህያው ተቋማዊ ምስክር ነው። ለድርቅ እና ረሃብ ምላሽ ከመስጠት በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት፣ አንድነት እና ልማት ቁልፍ ተዋናይነት ተሸጋግሯል። አንድነት እና የፖለቲካ ቁርጠኝነትን በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል ማጠናከር ለቀጣናዊ የተግባር ምላሽና ለተቋሙ ዘላቂ ውጤታማነት ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች ናቸው። የአባል ሀገራት የጋራ አንድነት የተረጋገጠበት ኢጋድ ለቀውሶች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ለጋራ ፍላጎቶች መሳካት ያለው ሚናም ያድጋል። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አቅም ግንባታና ዘላቂ ልማት ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ የኢጋድ የትኩረት አጀንዳ ሊሆን ይገባል። የኢጋድ የሰላም እና መረጋጋት ጥረቶች በሁሉን አቀፍ አስተዳደር፣ በወጣቶችና ሴቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲሁም በዘላቂ የሀገር ግንባታ አካሄዶች ሊደገፍ እንደሚገባ የፖለቲካ ባለሙያዎች ምክረ ሀሳባችውን ያስቀምጣሉ። የልማት ፍላጎት አለመሟላት እና የኑሮ ውድነትን ለግጭቶች አበይት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን ከስር መሰረቱ መፍታት ለዘላቂ መረጋጋት ወሳኝ ነው። ኢጋድ የተጣለበትን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር እውን የማድረግ ኃላፊነቱን የበለጠ ለመወጣት የመሰረተ ልማት ትስስሮች ማጠናከር፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ማድረግና በቀጣናው በፍጥነት እያደገ ለመጣው ዜጋ የስራ ፈጠራና እድሎችን የሚያሰፉ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን የማስፋት ስራ ላይ አበክሮ መስራት ይኖርበታል። ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ የሚያሳየው አንድ ግልጽ ሀቅ አለ። ይህም እውነታ የምስራቅ አፍሪካ መጻኢ ጊዜ እርስ በእርስ መተሳሰርና በትብብር መቆም እንደሆነ ነው። የተቋቋመበትን አላማ ዳግም ቃል ኪዳኑን በማደስ በቁርጠኝነት መስራት ከቻለ፣ ተቋማዊ አቅሙን በሚገባ ካጎለበተ፣ በሀገራት መካከል አጋርነትና ትብብርን ካጠናከረና የዲጂታል ዘመን በሚገባ በመዋጀት ከሰራ ኢጋድ ቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊ፣ አይበገሬናና የበለጸገ ቀጣና እንዲረከብ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወቱን መቀጠል ይችላል።
የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ትብብራቸውን ለማጽናት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Jan 14, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ትብብር እንዳላቸው አውስተው በጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) ማዕቀፍ ያላቸውን ግንኙነት አንስተዋል። በዮካሃማ በነሃሔ ወር 2017 ዓ.ም የተካሄደው ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም(ቲካድ) በሁለቱ ወገኖች አጋርነት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አመልክተዋል። ውይይቱ የሁለትዮሽ ትብብሩን የበለጠ ማጠናከርን ያለመ ነው። ጃፓን ለአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (African CDC) እያደረገች ያለው ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ዘላቂ እድገት እና ትስስር ለሚደግፉ የመሰረተ ልማት ስራዎች እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) በስኬት መካሄዱን አድንቀዋል። 10ኛው ቲካድ በአፍሪካ እንዲካሄድ ጃፓን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል። ሀገራቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ፒዳ) ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁልፍ ኢኒሼቲቮች መደገፏን እንደምትቀጥል ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ በዓለም አስተዳደር ውስጥ እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ሚና በማንሳት የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 ቋሚ አባል መሆኗ ትልቅ ሽግግር መሆኑን ተነግረዋል። ባለስልጣናቱ በአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን የከፍተኛ ደረጃ የምክክር መድረክ እና ቲካድ አማካኝነት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና የባለብዙወገን ዲፕሎማሲ እንዲጸና በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን እ.አ.አ በ1993 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰላም እና ደህንነት፣ ኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ንግድ፣ ጤና ፣ ግብርና፣ ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ከሁለቱ ወገኖች የትብብር መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውኃ ለአፍሪካ የኅልውና ጉዳይ ነው - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Jan 12, 2026 279
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ ውኃ ሁሉንም ዘርፍ የሚነካ አህጉራዊ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የሕብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው"ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሐሳብ የሚደረግ ነው። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ትኩረቱን ያደረገው በውኃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ውኃ በሁሉም አይነት እጅጉን ወሳኝ የሆነ ሀብት እና የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል። በብራዚል ቤለም የተካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ውኃ አንዱ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማዘጋጀት በመመረጧ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ያሉ ሲሆን፤ ለጉባኤው ስኬታማነት ሕብረቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ሰላም እና ደኅንነት የአፍሪካ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን የገለጹት ሊቀ መንበሩ ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሊቢያን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ኢ-ሕገመንግሥታዊ ለውጦች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቅሰው፤ ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንዲያከብሩ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርን ጨምሮ ለአህጉራዊ አጀንዳዎች እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። አህጉራችን ፈተናዎች ቢኖሩባትም በጋራ ከቆምን እናልፋቸዋለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የዛሬው ስብስባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል ሀገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ መሆኑ ይታወቃል።
51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይጀመራል
Jan 12, 2026 302
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። ስብሰባው "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሃሳብ የሚደረግ ነው። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ ጭብጥ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣የሕብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንደሚሳተፉበት ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ስብስባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን የአፈጻጸም እንዲሁም ሕብረቱ እ.አ.አ በ2025 ያካሄዳቸውን ስብሰባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል። ሰላም እና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትስስር፣ የተቋማዊ ሪፎርሞች እና የበጀት እቅዶችን የተመለከቱ የቴክኒክ ሰነዶችንም ያዘጋጃል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል አገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ ነው።
ሐተታዎች
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 621
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 562
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 781
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 922
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል። ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ። ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 604
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 554
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1186
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3504
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3152
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2013
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7828
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6316
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት
Jan 14, 2026 253
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል። ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል። የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።
ከማላጋ እስከ አፍሪካ ዋንጫ፤ የሞሮኮው አዲስ እንቁ ብራሂም ዲያዝ
Jan 13, 2026 273
የግል ክህሎት፣ ፈጣን አስተሳሰቡ እና በጠባብ ክፍተቶች ውስጥ ሰብሮ የመግባት አቅሙ ሙገሳ እንዲጎርፍለት አድርጓል። አንድ ለአንድ ሲገናኝ ተከላካዮችን በፈጣን አካላዊ ቅልጥፍና እና በድንገት አቅጣጫ በመቀየር የሚያልፍበት መንገድ እንዲሁም የመፍጠር አቅሙ የተመልካቾችን ቀልብ የሚይዝ ነው። የአማካይ እና የአጥቂ መስመርን በማገናኘት እና በአስገራሚ ሁኔታ አጭር ኳሶችን በማቀበልም የተዋጣለት ተጫዋች ነው ማለት ይቻላል። በቦታ አያያዙ የእግር ኳስ ልኅቀቱ ከፍተኛ ነው የሚል አድናቆት ከእግር ኳስ ባለሙያዎች አግኝቷል። ኳስን ሲያንከባልልም ለዐይን ይስባል። ከክህሎቱ እና ከማራኪ እንቅስቃሴው ባለፈ ወደ ኋላ እየመለሰ ተከላካዮችን ያግዛል፣ ኳስ ይነጥቃል። ይህ ተጫዋች የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተት የሆነው የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ ነው። የ26 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዲያዝ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። አዘጋጇ ሞሮኮ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ኮሞሮስን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል። ብራሂም አብዱልቃድር ዲያዝ የተወለደው እ.አ.አ ኦገስት 3 ቀን 1999 በስፔን ማላጋ ግዛት ነው። እናቱ ስፔናዊ አባቱ ሞሮኳዊ ናቸው። ዲያዝ ያደገው በማላጋ ነው። እግር ኳስንም በአንዳሉሺያዊቷ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል። በ16 ዓመቱ ካደገበት ማላጋ በመውጣት እ.አ.አ በ2015 ወደ ማንችስተር ሲቲ ወጣት አካዳሚ በ200 ሺህ ፓውንድ ወጪ ተዘዋወረ። ዲያዝ እ.አ.አ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2016 በካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ ሊግ ካፕ) ማንችስተር ሲቲ ከስዋንሲ ሲቲ ባደረገው ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ በኬሌቺ ኢናቺዩ ተቀይሮ በመግባት ለውኃ ሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያውን ጨዋታ ካደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ተፈራርሟል። እ.አ.አ ኖቬምበር 21 ቀን 2017 ማንችስተር ሲቲ ከፌይኖርድ ሮተርዳም ጋር ባደረገው የሻምፒዮናስ ሊግ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል። በወቅቱ ብራሂም ስተርሊን መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት ላይ ነበር ተቀይሮ የገባው። ዲያዝ በውኃ ሰማያዊዎቹ ማልያ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ የተጫወተው እ.አ.አ ዲሴምበር 19 ቀን 2017 ነው። ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ ለ88 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል። እ.አ.አ ጃንዋሪ 20 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። በወቅቱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን፤ በውድድር ዓመቱ አራት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሳትፎ ያደረገው ብራሂም ዲይዝ የሜዳሊያ ሽልማት አግኝቷል። እ.አ.አ ኦገስት 5 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 2 ለ 0 ባሸነፈበት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ ላይ በፊል ፎደን ተቀይሮ በመግባት ለ15 ደቂቃዎች ተጫውቷል። ዲያዝ እ.አ.አ 2018/19 ማብቂያ ላይ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያ ግቦቹን ለሲቲ አስቆጥሯል። በማንችስተር ሲቲ ያለው ውል እ.አ.አ 2019 ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት ይነሳ ነበር። ዲያዝ እ.አ.አ ጥር 2019 በ17 ሚሊዮን ዩሮ ከማንችስተር ሲቲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዘዋወረ። ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ውልም ፈርሟል። የክንፍ ተጫዋቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን በነጮቹ ማልያ ያደረገው እ.አ.አ ጥር 9 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ ሌጋኔን በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ወቅት ነው። ከአራት ቀናት በኋላ በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ሪያል ቤቲስን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠር ሶስት ወራትን ጠብቋል። እ.አ.አ ግንቦት 12 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ በላሊጋው በሪያል ሶሲዬዳድ 3 ለ 1 ሲሸነፍ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በወቅቱ ዲያዝ ስድስት ጨዋታዎች ላይ በላሊጋው የተጫወተ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዓመቱ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ሪያል ማድሪድ እ.አ.አ በ2021/21 የውድድር ዓመት ብራሂም ዲያዝ ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት ማምራቱን ይፋ አደረገ። ዲያዝ ሚላን እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2020 ክሮቶኔን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ ግንቦት 2021 ኤሲ ሚላን ጁቬንቱስን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ያስቆጠረው ግብም ተጠቃሽ ነው። ዲያዝ በኤሲ ሚላን የውሰት ውሉ ሲያበቃ በድጋሚ ለሁለት ዓመታት በውሰት የሚቆይበት ስምምነት ሪያል ማድሪድ ከጣልያኑ ክለብ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፤ ውሉ ሚላን ተጫዋቹን የማቆየት መብት ሰጥቶታል። እ.አ.አ መስከረም 15 ቀን 2021 ኤሲ ሚላን በሻምፒዮንስ ሊጉ የ3 ለ 2 ሽንፈት ሲያስተናግድ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ግቡን አስቆጥሯል። በ2023 ኤሲ ሚላን ቶተንሃም ሆትስፐርስን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ 1 ለ 0 ሲያሽንፍ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ በ2023 ሰኔ ወር ላይ ሪያል ማድሪድ ዲያዝ ከኤሲ ሚላን የሶስት ዓመታት የውሰት ቆይታ በኋላ ወደ ክለቡ መመለሱን አሳውቋል። ተጫዋቹ በኤሲ ሚላን ቆይታው 91 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ግቦችን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ዲያዝ ወደ ሪያል ማድሪድ ከተመለሰ በኋላ ኮንትራቱን እስከ 2027 አራዝሟል። እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2023 ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ሪያል ማድሪድ ላስ ፓልማስን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረክ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ዲያዝ እስከ አሁን ለሪያል ማድሪድ ባደረጋቸው 129 ጨዋታዎች 20 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከነዚህም ውስጥ 13ቱ በላሊጋው ያስቆጠራቸው ናቸው። ከክለብ ወጣ ስንል የተጫዋቹን የብሔራዊ ቡድን ቆይታ እናገኛለን። ዲያዝ በታዳጊነቱ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ለስፔን ወጣት ቡድኖች ተጫውቷል። እ.አ.አ በ2016/17 የውድድር ዘመን ለስፔን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ16 ዓመቱ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። በተለይም አዘርባጃን እ.አ.አ በ2017 ባዘጋጀችው 15ኛው የአውሮፓ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት አድናቆት አስችሮታል። በዚያ ቀጥለው በነበሩ ዓመታትም ለስፔን ከ19 እና ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ተጫውቷል። ብራሂም ዲያዝ በስፔን ታዳጊና ወጣት ቡድኖች ላይ በአጠቃላይ 28 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል። የስፔን ታዋቂ የስፖርት ጋዜጣ ማርካ እ.አ.አ ጥር 23 ቀን 2023 ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቀዱን የሚመለከት ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ከዜግነቱ ጋር በተያያዘ ያሉ አንዳንድ የአስተደዳር ጉዳዮች በወቅቱ መፍትሄ አግኝተዋል። ይሁንና ኮትዲቯር እ.አ.አ በ2023 ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሞሮኮው አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከተጫዋቹ ጋር በተደረገ የቅድሚያ ስምምነት ለተጫዋቹ ጥሪ አልተደረገለትም። ዲያዝ እ.አ.አ መጋቢት 10 ቀን 2024 ለሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሀገሪቷ ብሔራዊ መጫወት እንደሚፈልግ በይፋ ማሳወቁን ማርካ በወቅቱ ዘግቧል። ጥያቄውም ተቀባይነት አገኘ። በወቅቱ የሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንጎላ እና ሞሪታኒያ ጋር ለነበረበት የወዳጅነት ጨዋታ ለዲያዝ ጥሪ አድርገውለታል። እ.አ.አ መጋቢት 22 ቀን 2024 ሞሮኮ አንጎላን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። እ.አ.አ ጥቅምት 6 ቀን 2024 ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከጋቦን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 4 ለ 1 ስታሸንፍ የመጀመሪያ ግቡን ለሞሮኮ ማስቆጠር ቻለ። እ.አ.አ ሕዳር 15 ቀን 2024 ሞሮኮ በማጣሪያው ጋቦንን 5 ለ 1 ስትረታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ከሶስት ቀናት በኋላ ሞሮኮ ከሌሴቶ ጋር ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ 7 ለ 0 ስታሸንፍ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር በሀገሩ ማልያ የመጀመሪያ ሀትሪኩን ሰርቷል። እ.አ.አ ጥቅምት 2025 ሞሮኮ ራባት ላይ ኮንጎ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 በማሸነፍ በስፔን ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተይዞ የነበረውን 15 ተከታታይ ጨዋታዎችን የማሸነፍ ክብረ ወሰን በመስበር ወደ 16 ማድረስ ችላለች። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ ዲያዝ ተሰልፎ ተጫውቷል። የሞሮኮ ተከታታይ የማሸነፍ ጉዞ 19 ጨዋታዎች ደርሶ የነበረ ሲሆን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከማሊ ጋር አንድ አቻ ስትለያይ አብቅቷል። ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማጣሪያ ብታልፍም አስቀድማ ውድድሩን እንድታዘጋጅ እድል አግኝታ የነበረው ጊኒ በዝግጅት ማነስ ምክንያት በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለሞሮኮ ተሰጥቷል። ሞሮኮ የዘንድሮውን ውድድር በደማቅ ሁኔታ እያካሄደች ትገኛለች። በውድድሩ ላይ ጎልተው ከታዩ ተጫዋቾች መካከል ብራሂም ዲያዝ ተጠቃሽ ነው። በአፍሪካ ዋንጫው እስከ አሁን ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። በተሰለፈባቸው በእያንዳዱ ጨዋታዎች ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በአምስት የአፍሪካ ዋንጫ ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። ሞሮኮ በሩብ ፍጻሜው ማሊን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል። ሀገሩ ወደ ግማሽ ፍጻሜ እንድታልፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱንም እየመራ ይገኛል። ሞሮኮ በዚሁ ግስጋሴዋ ከቀጠለች ዲያዝ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ሞሮኮ በግማሽ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ታደርጋለች። ዲያዝ በዚህ ጨዋታ ላይ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ የእግር ኳስ ተንታኞች ብራሂም ዲያዝ እ.አ.አ በ2026 ወጥነት ያለው ብቃት ማሳየት ከቻለ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማቱን የሚወስድበት የለም እያሉ ይገኛሉ። ሞሮኳውያን በተጫዋቹ ፍቅር ልባቸው ከንፏል። በየጨዋታው ዲያዝ ዲያዝ እያሉ ከፍተኛ ድጋፍ እና ሙገሳ እየሰጡት ይገኛሉ። እሱም በድንቅ ብቃቱ ምላሽ እየሰጣቸው ነው። በተወለደበት ማላጋ ከተማ የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወት በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የበለጠ አብቧል። የሞሮኮው አዲሱ ኮከብ ብራሂም ዲያዝ ቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወት በስኬት እና በድል የደመቀ እንደሚሆን ከአሁኑ ድንቅ ብቃቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።