ቀጥታ፡

ኮሎምቢያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ 11 ጨዋታ ኮሎምቢያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ በተጠናቀቀው እና በጓድላሃራ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳንኤል ሙኞዝ በ76ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ኮሎምቢያ በተጋጣሚዋ ላይ ፍጹም የጨዋታ ብልጫ ወስዳለች።

ውጤቱን ተከትሎ ኮሎምቢያ በስድስት ነጥብ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።

አንድ ነጥብ ያላት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተካሄደው ጨዋታ ፖርቹጋል ኡዝቤኪስታንን 5 ለ 0 አሸንፋለች።

ፖርቹጋል በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ኡዝቤኪስታን ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኡዝቤኪስታን፣ ኮሎምቢያ ከፖርቹጋል የምድብ 11 የመጨረሻ ጨዋታዎች ናቸው።

ኮንጎ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ኡዝቤኪስታንን ማሸነፍ ይጠበቅባታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም