የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሕዝባዊ ውይይቶች አጀንዳዎችን ያሰባሰበበት የእስካሁኑ የምክክር ሂደት ቁልፍ ባሕርያት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሕዝባዊ ውይይቶች አጀንዳዎችን ያሰባሰበበት የእስካሁኑ የምክክር ሂደት ቁልፍ ባሕርያት
ባለድርሻ አካላት እንደሀገር ያልተግባባንባቸውን እጅግ መሠረታዊ የሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች በውይይት በማዳበር ለኮሚሽኑ ማስረከባቸው፤
የብዙ ባለድርሻ አካላት ሕመሞች፣ ሥጋቶች፣ ምኞቶች እና ተስፋዎች በአጀንዳ መልክ መቅረባቸው፤
በሂደቱ ኮሚሽኑ ለምክክሩ ሂደት የሚጠቅሙ እጅግ በርካታ ግብዓቶችን መሰብሰቡ፤
በአንፃራዊነት የተሳታፊዎችን ምቾት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለተሳታፊዎች ቅርብ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ ቦታዎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት መከናወኑ፤
በሕዝባዊ ውይይት አጀንዳን የመሰብሰብ ሥራ ሁለት ዓመታትን ፈጅቷል፤
በአጠቃላይ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ለሀገራዊ ምክክር ጉባዔው መካሄድ እንደ ቅድመ ሁኔታ በማገልገል የራሱን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።