ጋና ከእንግሊዝ ጋር አቻ ተለያየች - ኢዜአ አማርኛ
ጋና ከእንግሊዝ ጋር አቻ ተለያየች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ 12 መርሐ ግብር እንግሊዝ እና ጋና ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በቦስተን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እንግሊዝ የኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድሎችን የመፍጠር ብልጫ ወደ ጎል መቀየር አልቻለችም።
የተደራጀ የመከላከል ስልት ይዛ የገባችው ጋና ወሳኝ ነጥብ አግኝታለች።
ውጤቱን ተከትሎ እንግሊዝ እና ጋና በተመሳሳይ አራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ጋና ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት እድሏን አለምልማለች።
በዚሁ ምድብ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ፓናማ ከክሮሺያ በቶሮንቶ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሁለቱም ሀገራት በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።