ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ትሻለች-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ትሻለች-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደምትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሞዲ ያገኙትን ታሪካዊ የሕዝብ ውክልና የአለማችን ትልቁ ዲሞክራሲ የሆነችው ሕንድ ያላትን ዘላቂ የዲሞክራሲ ጥንካሬ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሕንዱን አቻቸውን የታመኑ ወዳጅ እና ታላቅ ወንድሜ ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነትም በታሪክ፣በአጋርነት እና ለሕዝቦቻቸው ባላቸው የጋራ ምኞት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትስስር መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ እና ሕንድ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እና የጀመሩትን የጋራ ጉዞ አብሮ ለመቀጠል ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።