የኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ):-የኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኳታሩ ኤሚር የብልጽግና ፓርቲ በጠቅላላ ምርጫው ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አላችሁ የደስታ መግለጫ መልዕክት ልከዋል።
ኤሚሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬትን የተመኙ ሲሆን፣በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንዲያድግና እንዲጠናከር ያላቸውን ፅኑ ፍላጎትም ገልጸዋል።