ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት ኢትዮጵያና ብሩንዲ በጋራ ይቆማሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት ኢትዮጵያና ብሩንዲ በጋራ ይቆማሉ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያና ብሩንዲ ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ዙሪያ አብረው እንደሚቆሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በሀገራቸው እና በአፍሪካ ህብረት ስም ያስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ትልቅ ብርታትን የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ብሩንዲ በጥልቅ የወንድማማችነት ትስስር፣እንዲሁም ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ዙሪያ አብረው ይቆማሉ ብለዋል።
ለሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሕዝቦቻችንና የአፍሪካን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን ይህንን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን አመልክተዋል።