ቀጥታ፡

የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት

በዮሐንስ ደርበው

👉 ከሰብል ልማት አኳያ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም ጅማሮውን ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ አሁን ዘርፈ-ብዙ ጥቅሙ በተጨባጭ እየተገለጠ ነው።

ከበርካታ ትሩፋቶቹ መካከልም የምርታማነት ማደግ ተጠቃሽ ነው።ይህን ተከትሎም የሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አድጓል።

ይህን ሐሳብ በአኃዝ አስደግፎ ለማየት ያህል፤ ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፊት (በ2010 ዓ.ም) በሔክታር የሚመረተው ስንዴ 22 ኩንታል፣በቆሎ 30 ኩንታል፣ ጤፍ 17 ኩንታል እንዲሁም ገብስ 23 ኩንታል ነበር።

ከኢንሼቲቩ ትግበራ በኋላ ደግሞ (በ2017 ዓ.ም) ስንዴ በሔክታር 36 ኩንታል፣ በቆሎ 46 ኩንታል፣ ጤፍ 20 ኩንታል፣ ገብስ 30 ኩንታል ማምረት ተችሏል።

በዚህም መሠረት በ2017 ዓ.ም 7 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 280 ሚሊየን ኩንታል ማምረት ተችሏል።

ስንዴን በትጋት በማምረትም ከውጭ ለማስገባት ይወጣ የነበረን 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት ተችሏል።

በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት

አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት

ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ

👉 ከፍራፍሬ አኳያ

የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በፍራፍሬው ዘርፍ ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል። በዚህም ገበያውን ከማረጋጋት ባለፈ ሕብረተሰቡ (አምራቹ) ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ በዚያው ልክ እንዲያድግ አስችሏል።


 

ኢትዮጵያም በአፍሪካ አቮካዶን በቀዳሚነት ወደ ውጭ የምትልክ ሁለተኛዋ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል።

👉 ከቡና ልማት መስፋፋት አኳያ

ሌላኛው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በረከት የቡና ልማት መስፋፋትና የውጭ ምንዛሬ ማደግ ነው።

ይህን በአሥረጂ አስደግፈን ብንመለከት፤ በ2011 ዓ.ም በ600 ሺህ ሔክታር ላይ ቡና ተተክሏል። 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ተሰብስቧል።738 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

እንዲሁም በ2017 ዓ.ም 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ ቡና ተተክሏል። 1 ነጥብ 58 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ተሰብስቧል። 2 ነጥብ 65 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል።

👉 ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ

ከአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

ከላይ የተጠቀሱ ማሳያዎችን (ናሙናዎችን) ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በቀጥታ ለሕዝቡ ጥቅም የቆመ መርሐ-ግብር መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም።

ስለዚህ በቀጣይ ሕብረተሰቡ በዚህ ኢኒሼቲቭ ላይ ያለጠባቂነት በንቃት በመሳተፍ እና ባሕሉ በማድረግ ተጠቃሚነቱንም በዚያው ልክ ለማሳደግ መትጋት ይጠበቅበታል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

ባለፉት ዓመታት 48 ቢሊየን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፤ በዘንድሮው መርሐ-ግብር ደግሞ 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምጧል።

#አረንጓዴ_ዐሻራ #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #ተስፋን_እንትከል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም