ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክሮችና የምረጡኝ ቅስቀሳዎች በመፍትሄ አማራጮች ላይ ያተኮሩ ሊሆኑ ይገባል
Feb 24, 2026 33
ወላይታ/አዳማ/ድሬዳዋ/ሆሳዕና፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረኮችና የምረጡኝ ቅስቀሳዎች ቅራኔና ግጭት ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ንግግሮች በመራቅ የመፍትሄ አማራጮች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ በተለያዩ ከተሞች ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ይፋ ባደረገበት መድረክ ፓርቲዎቹ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ መፈረማቸው ይታወቃል። ጠቅላላ ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግን አክብረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም ቦርዱ አስገንዝቧል። በምርጫ ቅስቀሳም ሆነ በክርክር መድረኮች የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በፈረሙት የስነ-ምግባር ደንብ መሰረት ፕሮግራማቸውን ሊያስተዋውቁ እንደሚገባና የህዝብ መገናኛ ብዙሃንም ለሁሉም እኩል ዕድል ሊሰጡ እንደሚገባ አመልክቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አከራካሪ የሆኑ ምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ውሣኔ አስተላለፈ በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን በማስመዝገብ በምርጫው ብቁ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ በተለያዩ ሚዲያዎች የምርጫ ክርክሮችን ማድረግ ጀምረዋል። በክርክሮቹ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማሉ የተባሉ ሃሳቦች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱንና የእስካሁኑን የፓርቲዎች እንቅስቃሴ በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተሮች የወላይታ ሶዶ፣ የአዳማ፣ የድሬዳዋ እና የሆሳዕና ከተሞች ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። አስተያየት ሰጪዎቹም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እራሳቸውን በማስተዋወቅ የፖሊሲና የሃሳብ ክርክሮች መጀመራቸው ለመራጩ ውሳኔ ወሳኝ ግብአት መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የፓርቲዎች የክርክር መድረኮችና የምረጡኝ ቅስቀሳዎች ቅራኔና ግጭት ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ንግግሮች በመራቅ የመፍትሄ አማራጮች ላይ እንዲያተኩሩ ገልጸዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪው ሺመልስ ተፈራ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ሲያስተዋውቁና የምርጫ ክርክር ሲያደርጉ እየተከታተልን እንገኛለን ብለዋል። በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ፕሮግራማቸውን ሲያስተዋውቁ ቢመረጡ በቀጣይ ምን ሊተገብሩ እንዳሰቡ ለማወቅ እያስቻለ ስለመሆኑ አንስተው፤ በክርክሩ የፖለቲካ ባህል እያደገ መምጣቱን ያየንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በመጠቀም ለሀገርና ህዝብ የፖለቲካ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት የሚያኖር ተግባር ፈፅመው የማለፍ አደራ አለባቸው ብለዋል። የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ዋቅጋሪ ቢራቱ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጠቅላላ ምርጫው በሃሳብ የበላይነት፤ ለሀገርና ህዝብ የሚጠቅሙ ጉዳዮችን በመያዝ በአጀንዳዎች ላይ ክርክር ማድረጋቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። በዚህም ሀገረ መንግስትን ማስቀጠል የሚያስችሉ ጠቃሚና ገንቢ ሃሳቦች እንደሚገኙበት አምናለሁ ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑት ደረጄ ጉተማ በበኩላቸው በምርጫ ክርክር ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገርን ትልቅ የሚያደርጉ ሀሳቦች ላይ አተኩረው መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል። ሀገርን የሚገነባ ሀሳብ የሚያራምድ ፓርቲ ለህዝብ የሚጠቅምና ለሀገር ግንባታ ሁነኛ መሰረት የሚያኖር መሆኑንም አንስተዋል። በጠቅላላው ምርጫው በሀሳብ የበላይነት ለመወዳደር ወደ ሜዳ የሚገቡ ፓርቲዎች ሀገርን ሊያሻግር የሚችል ሃሳብ ይዘው ሊመጡ ይገባል ያሉት ደግሞ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው ከበደ ኦሴቦ ናቸው። የክርክር መድረኩ ለፖለቲካ ፓርቲዎች አንዲት የጋራ ሀገር ለመምራት የሚያደርጉት ጥረት በመሆኑ ለሀገር የሚበጁ ሃሳቦችን በመሰነቅ መንቀሳቀስ እንዳሚገባቸው ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችል አውድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል
Feb 24, 2026 36
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችል አውድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡ አቶ አደም ፋራህ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተገኝተው የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴና ያከናወናቸውን የማሻሻያ ተግባራት ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠርና ተወዳዳሪነትን ከማላቅ አንጻር በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ መመልከታቸውንና ይህም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ይበልጥ ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ተቋም መሆኑን አንስተው በአሁኑ ወቅት ለዘመኑ የመገናኛ ብዙሃን ውድድር የሚያግዙ ስራዎች መሰራታቸውን መጥቀሳቸውንም እንዲሁ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊነትን ከህዝብ አመኔታ ጋር ያቀናጀ በመሆኑ ተልዕኮውን በተሳለጠ መንገድ እንዲወጣ የሚያስችለው ቁመና ላይ እንዲገኝ አግዞታል ነው ያሉት፡፡ ከለውጡ ወዲህ መገናኛ ብዙሃንን በተለያዩ ተቋማት የተከናወኑ የማሻሻያ ተግባራት አካል በማድረግ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ነው አቶ አደም ፋራህ የገለጹት፡፡ ከዚህ ቀደም መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዳይሰሩ የሚገድቡ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን አውድ ለመፍጠር ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንም ከለውጡ ወዲህ የተገኙ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በአግባቡ እየተጠቀመ ይገኛል ሲሉ መናገራቸውንም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዘገባው አስነብቧል፡፡
ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የተቀናጀ አሰራርን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል
Feb 24, 2026 47
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው 4ኛው አገር አቀፍ የፀረ ህገ-ወጥ ንግድ ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ ንግድ በነጋዴው፣ በህብረተሰቡና በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት ያደርሳል፡፡ መንግሥት አገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመግታት አሠራርን የማሻሻል፣ ቴክኖሎጂን የመጠቀምና ሌሎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አንስተዋል። በዚህም ህገ-ወጥነትን የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንና አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አመልክተዋል። ሆኖም የህገ-ወጥ ንግድ ባህሪ ተለዋዋጭ በመሆኑ አሁንም በመከላከል ረገድ ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በተለይም እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ የጋራ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ንግድ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊቁ በየነ በበኩላቸው፤ ህገ-ወጥነት በሸማቹና በነጋዴው መካከል ያለውን ፍትሀዊ ውድድር የሚያናጋ ትልቅ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን ለመቅረፍ አሠራሩን በዘመናዊ መንገድ እያደራጀ መሆኑን ጠቅሰው በንግድ ሥርዓቱ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አይናለም አባይነህ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ የንግዱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ትስስርና በመሠረተ ልማት አስደናቂ ሥራ እያከናወነች ነው
Feb 24, 2026 47
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በዲጂታል ትስስርና በመሠረተ ልማት አስደናቂ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ገለጹ። አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያና ፊንላንድ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል። ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የትምህርት ዘርፉን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ጠንካራ የልማት ትብብር እንዳላት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በዲጂታል ትስስር ረገድ ስኬታማ ሥራዎች እየሠራች መሆኑንም አንስተዋል። እንዲሁም በመሠረተ ልማት ግንባታ እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ፊንላንድ በአካታች ትምህርት እና በማህበረሰብ አቀፍ የገጠር ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የገጠር መሬት ምዝገባን ዲጂታላይዝ የማድረግ ፕሮጀክት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እየሠራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። አምባሳደሯ አክለውም ከልማት ትብብር ባለፈ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የቢዝነስ አጋርነት በመፍጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ነን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በአፍሪካ የነጻነት ትግል ታሪክና ለዓለም ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚና አለው
Feb 24, 2026 45
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በአፍሪካ የነጻነት ትግል ታሪክና ለዓለም ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚና እንዳለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንትና የጸረ አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በሰለጠኑበት ኮልፌ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ የተሰየመው የመታሰቢያ ሙዚየም ተመርቋል። በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ፖሊስ ምስረታ 117 ዓመታትን ያስቆጠረ ከአፍሪካ ቀዳሚው ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ የነፃነት ትግል የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸው፤ የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አባት የሆኑትን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ አሰልጥኗል ብለዋል። ኔልሰን ማንዴላ የፀረ አፓርታይድ ትግልን ለመቀላቀል እ.ኤ.አ በ1962 በኢትዮጵያ ለወራት ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ ለመሰልጠን የመረጡት ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችና የዓለም ጥቁር ህዝቦች ምልክት በመሆኗ ነው ብለዋል። ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያውያን የፖሊስ አባላትና መኮንኖች መሰልጠናቸውን ጠቅሰው፤ ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ብሩ፣ ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ፣ መቶ አለቃ ፈቃዱ ወንድም ከአሰልጣኞች መካከል መሆናቸውን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ፖሊስ እውቀትና ልምዱን በማካፈል ለደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ገንቢ ሚና ተወጥቷል ብለዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ነጻነት ታሪክ ቀረጻ ላይ ተሳትፎ እንዳላት ያነሱት ኮሚሽነር ጀነራሉ፤ ይሄውም የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋም የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባሩንና ሀገራዊ ሀላፊነቱን የተወጣበትን መንገድ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም በኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት የምታበረክተው አስተዋፅኦ ለዓለም ሰላም መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖለቲካ

በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር ለማድረግ ተዘጋጅተናል - ተፎካካሪ ፓርቲዎች
Feb 24, 2026 63
ባህር ዳር፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ፉክክር ለማድረግ መዘጋጀታቸውን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ። ፓርቲዎቹ ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሰሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪ ኃይለማርያም ብርሃኑ፤ ምርጫው የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት ሁሉን አቀፍና አካታች እንዲሆን ፓርቲያቸው ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ገልጸዋል። ፓርቲያቸው ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ በምርጫ ሥነ-ምግባር ላይ ግንዛቤ እየፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው፣ በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በሕግ አግባብና በሀሳብ የበላይነት ብቻ ለመፍታት በአጽንኦት እየሰራን ነው ብለዋል። ስልጣን በህዝብ ድምጽ በምርጫ ብቻ የሚመጣ በመሆኑ በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ፓርቲያቸው በጽኑ እንደሚያወግዝም አመልክተዋል። በብሔራዊ ጥቅም ላይ አንደራደርም- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፓርቲዎች በጋራ ባፀደቁት የምርጫ ሕግና ደንብ በመገዛት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆን የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) የአማራ ክልል የሥራ አስፈፃሚ አመራር አብደላ ስመኘው(ዶ/ር) ናቸው። ፓርቲያቸው የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንቡን ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ እየስተዋወቀ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ በሐሳብ የበላይነት ለማሸነፍና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካን ለማራመድ በትጋት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ለተሻለ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሁሉም የተሻለ ሀሳብ ማዋጣት እንዳለበት ገልጸው፣ጠቅላላ ምርጫው ሀገርን ያስቀደመና የሀሳብ የበላይነት የሚያሸንፍበት እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የምዕራብ ጎጃም ዞን የፋይናንስ ክፍል ሃላፊ ይርጋ ሞገስ በበኩላቸው፣ ሀገርና ህዝብን ማሻገር የሚያስችል ስልጣን የሚገኘው በምርጫ ብቻ በመሆኑ ፓርቲያቸው በሀሳብ የበላይነት ለመፎካከር መዘጋጀቱን አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
ክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት የፀጥታ ኃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየሰሩ ይገኛሉ
Feb 24, 2026 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሚገኙ ተገለጸ። የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ክልላዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል ። በክልሉ ወንጀልን ከመከላከል አንጻር በተከናወኑ ተግባራት በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ሲሳተፉ የነበሩ አካላትን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ማድረግ መቻሉ ተገልጿል። ከትራፊክ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በተወሰደው እርምጃ ሕግ ከማስከበር አንፃር አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን ምክር ቤቱ ገምግሟል። ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከል፣ አደገኛ እፅን ከመቆጣጠር፣ ኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ ንግድን በመከላከልና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመቆጣጠር አንፃርም በተከናወነው ኦፕሬሽኖች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አንስቷል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የኢኮኖሚ አሻጥር በሚፈጥሩ ስግብግብ ነጋዴዎች እና በመልካም አስተዳደር ችግር ህዝብን የሚያማርሩ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባሮ ተጠናክሮ መቀጠሉም ተመላክቷል። የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን የሕዝብን ደኅንነት ማስከበር ቀዳሚ ተግባር በመሆኑ በክልሉ ያለው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የፀጥታ ምክር ቤቱ አበክሮ የሚሰራ መሆኑም እንዲሁ። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የምርጫ ህግ እና ስርዓት እንዲከበር በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አመላክቷል። በቀጣይም የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በማስፈን የህግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የክልሉ ህዝብም ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት እና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ዛሬም እንደ ትላንቱ ለሰላም ዘብ እንዲቆም ምክር ቤቱ ጥሪውን አቅርቧል።
ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የምርጫ ምልክቱንና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ
Feb 24, 2026 90
ሮቤ፣ ነጌሌ ቦረና፣ መቱ፣ ጊምቢ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በባሌ፣ በምስራቅ ቦረና፣ በኢሉባቦር እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት/የስንዴ ነዶ/ እና ማኒፌስቶ ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ አስተዋውቋል። በመድረኮቹ ላይ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተመዘገቡ የልማት ድሎችና ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ፓርቲው የያዘውን የቀጣይ አምስት ዓመታት ራዕይ ላይ ውይይት ተደርጓል። የየዞኖቹ የፓርቲ አመራሮች ፤ ይህ ምልክት የተመረጠው በፓርቲው መሪነት የተመዘገበውን የስንዴ ልማትና የምግብ ዋስትና ስኬት ለመወከል መሆኑን አንስተዋል። በሮቤ ከተማ በተካሄደው መድረክ ላይ የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሐኪም አልይ እንዳሉት፤ በዞኑ በለውጡ ዓመታት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎችም መስኮች የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይ በዞኑ በግብርና ልማት፣ በአስፋልት መንገድ ተደራሽነት እና በጤናው መስክ የተሰሩ የልማት ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል። የለውጡ መንግስት ውስብስብ ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ መስኮች ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ብልፅግና ፓርቲ በጥቂት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገትና ስኬት ያስመዘገበ ፓርቲ ነው -ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) በዞኑ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የተተገበሩ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የአጋርፋ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አባ ገዳ መሐመድ ቡዴ ናቸው፡፡ በብልጽግና ፓርቲ የምስራቅ ቦረና ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብዲ በበኩላቸው ፣ በፓርቲው መሪነት ከተከናወኑት የልማት ድሎችና ስኬቶች መካከል የመስኖ ስንዴ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡ የተጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ለማስቀጠል የዞኑ ህዝብ በምርጫው ለፓርቲያቸው ድምጽ ለመስጠት ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡት ድሎችና ስኬቶች የሚያኮሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የበጋ መስኖ፣ የኮሪደር ልማት፣ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ የመንገድ፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት ግንባታዎች ከብዙ በጥቂቱ እንደሆኑም ጠቅሰዋል፡፡ የተጀመሩትን የልማት፣ የለውጥና ዕድገት ጉዞዎችን ለማስቀጠል ፓርቲውን እንዲመርጡም ጠይቀዋል፡፡ በዞኑ ሊበን ወረዳ የሜኤሳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ መሀመድ ከድር ለሰላማዊና ፍትሃዊ ምርጫ መካሄድ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡ በተመሳሳይም በኢሉአባቦር ዞንና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በተካሄደ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክትና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ፓርቲው ኢትዮጵያን ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን በማሸጋገር ረገድ ስኬታማ ጥረቶች ማድረጉ ተነስቷል። በቀጣይም ፓርቲው ሀገሪቱን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እንደሚሰራም ተመልክቷል።
የሴቶችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት እና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው
Feb 24, 2026 101
አሶሳ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦የሴቶችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት እና የውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል አስቴር ዳዊት ተናገሩ። በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ የሴቶች ንቅናቄ ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል። ለውጡ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ማረጋገጥ ችሏል በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር እና የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል አስቴር ዳዊት እንዳሉት፤ የሴቶችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት እና የውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው። በሀገር አቀፍ ደረጃ ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከመሆናቸው ባለፈ የፖለቲካ ተሳተፏቸው በእጅጉ እያደገ መምጣቱን ነው የገለጹት። በአሁኑ ወቅትም ሴቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ የሚገኙ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ በማድረግም ተወዳዳሪ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው፤ የሴቶችን ተሳትፎና አጋርነት በማጠናከር ለሀገረ መንግስት ግንባታ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት። በዘንድሮው ዓመት የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሴቶች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ ጠንካራ የሴቶች አደረጃጀቶችን በመፍጠር በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች በመሰማራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሰራቱን የተናገሩት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሴቶች ክንፍ አስተባባሪ አለምነሽ ይባስ ናቸው። በመድረኩ ላይ ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ የሴት አደረጃጀቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ብልፅግና ፓርቲ በጥቂት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገትና ስኬት ያስመዘገበ ፓርቲ ነው -ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)
Feb 24, 2026 87
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የኢትዮጵያን ዕድገት የሚያስቀጥል አስደማሚ ስኬት ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውንና የስንዴ ነዶ የምርጫ ምልክቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በሸገር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤትም በከተማ ደረጃ የማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መርኃ ግብር አካሂዷል። የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ብልፅግና ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ የኢትዮጵያን ዕድገት የሚያስቀጥል አስደማሚ ስኬት ያስመዘገበ ፓርቲ ነው። ፓርቲው በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የትግበራ ሂደት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስክ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ የሚያስችሉ ጠንካራ ስኬቶችን እያስገኘ መሆኑንም ገልጸዋል። ሕብረብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሰጠው ትኩረትም በዜጎች መካከል አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት አብሮነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል። በሸገር ከተማ በሁሉም የልማት መስኮች የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተወዳዳሪና ዘመናዊ ከተማን መገንባት የሚያስችሉ ስኬቶች በፓርቲው መሪነት መመዝገባቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የሸገር ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አለማየሁ ቱሉ በበኩላቸው፤ የመደመር ፍልስፍና የወለደው የብልፅግና ፓርቲ አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት አትዮጵያን መገንባት የሚያስችል ስኬት አስመዝግቧል ብለዋል። ፓርቲው በሸገር ከተማና በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለህዝብ ቃል የተገቡ የልማት ሥራዎችን በውጤታማነት መፈጸሙን ጠቅሰዋል።
በብሔራዊ ጥቅም ላይ አንደራደርም- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች
Feb 24, 2026 115
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ እንደራደርም ሲሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ አጀንዳ ነው። በተለይ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር ሊሂቃንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ሲሆን ሀላፊነቱ እጥፍ ድርብ ነው። በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምንም እንኳን የርዮተዓለም ልዩነትና የተለየ የፖሊሲ አተያይ ቢኖራቸው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ግን ሁሉም እንደማይደራደሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህያው ማሳያ መሆኑን ይጠቅሳሉ። የተለያዩ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርግ ይገባል። የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ነቢሃ መሀመድ እንደሚሉት፤ፓርቲው የጋራ በሆኑና ኢትዮጵያን አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር መጨመር እና እያደገ የመጣው ኢኮኖሚ ተከትሎ የባህር በር አስፈላጊ መሆኑን ፓርቲው ያምናል ያሉት ኃላፊዋ መንግሥት ያቀረበው የባህር በር ጥያቄን እንደግፋለን ብለዋል። ኢትዮጵያ መርህን ተከትላ በዲፕሎማሲው የባህር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ያቀረበችው ጥያቄ ውጤት እንዲያመጣ ነጻናትና እኩልነት ፓርቲ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያን ሊወር የመጣን ኃይል ኢትዮጵያዊያን ብሄር፣ ኃይማኖት እና ፆታ ሳይገድባቸው አንድ ሆነው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብረዋል ያሉት ወይዘሮ ነቢሃ፤ በባህር በር ጉዳይም ይሄ አንድነት ሊደገም ይገባል ብለዋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሊቀ መንበር ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው፤ የትኛውም የፖለቲካ ልዩነት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም በላይ ሊሆን አይችልም ሲሉ ተናግረዋል። ያለን የፖለቲካ አተያይ አልያም ርዮተዓለም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል መሆን የለበትም፤ ፓርቲያችን በዚህ ላይ የጸና አቋም አለው ብለዋል። የብሄራዊ ጥቅም የሕልውና ጉዳይ ነው፤ ህልውና ደግሞ ለድርድር አይቀርብም ያሉት ሊቀ መንበሩ፤ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ፓርቲያችን ዝግጁ ነው ብለዋል። የወለኔ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ፈይሰል አብዲላዚዝ፤ የባህር በር ጥያቄ ተገቢና የሕዝብ ጥያቄ መሆኑን ፓርቲው እንደሚገነዘብ ይገልጻሉ። ፓርቲው ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቶ የኢትዮጵያ መሻት እንዲሳካ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆምም ነው ያረጋገጡት። በብሄራዊ ጥቅም አጀንዳ ዙሪያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሆኖ በንቃት ሊሳተፍበት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ በበኩላቸው፤ በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሀገር ለምታቀርብልን ጥሪ ሁሌም ዝግጁ ነን ብለዋል። ፓርቲው ለልማት፣ ለሠላም እና ሀገራዊ ጉዳዮች ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመው፤ በዚህ ዙሪያም ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት የትኛውንም አይነት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን- የመከላከያ ሰራዊት አባላት
Feb 24, 2026 67
ጎዴ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፡- ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት የትኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን የምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ገለጹ። በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ በኢትዮ-ሶማሊያ ድንበር በሀገራዊ ግዳጅና ተልእኮ ላይ በመሆን የሀገርን ዳር ድንበር ሌት ከቀን በማስከበር ላይ ይገኛሉ። በድንበር አካባቢ በመገኘት ኢዜአ ያነጋገራቸው የእዙ የሰራዊት አባላት ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት መከበር በላቀ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን አንስተው የሀገር መከታ በመሆናቸው ክብርና ደስታ የሚሰማቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከእዙ አባላት መካከል መቶ አለቃ ጌታሰው የኔነህ እና አስር አለቃ ፋኖሴ ፈይሳ፤ ሰራዊቱ በሁሉም ረገድ በተደራጀና በተሟላ ቁመና ላይ ስለመሆኑ ተናግረዋል። በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ በስልጠና እና በስነ ልቦና ተዘጋጅቶ ለሀገሩ ክብርና ዳር ድንበር በጀግንነት ቆመናል ሲሉ አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ክብሯና ሉአላዊነቷ ሳይደፈር የኖረች ታላቅ ሀገር ስለመሆኗ አንስተው የዚህ አደራ ተረካቢ ሆነው በመቆማቸው ታላቅ ክብር የሚሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት መከበር በጀግንነት በመቆም የትኛውንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል። ምክትል አስርአለቃ ይመዲ ባንጃው እና አስርአለቃ መልካሙ ሸለመው በበኩላቸው፤ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት ሀገራችንንና ህዝባችንን በላቀ ወታደራዊ ብቃት፣ በጀግንነትና ቁርጠኝነት ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነን ብለዋል። በተለይም ለአገራችን ሠላምና እድገት ፀር የሆኑ እና የተላላኪ ባንዳዎችን እኩይ አላማ በማክሸፍ በሁሉም አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ የሚጠበቅብንን ሃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል። ከእዙ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ሌተናል ኮለኔል ስለሺ ብሩ፤ የሀገራችንን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ባእዳንንና ተላላኪዎችን እኩይ አላማ ከርቀት ማክሸፍ የሚችል ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱን ገልጸዋል። ከቀናት በፊት በተከበረው የመከላከያ ሠሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ አመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የሀገሩን ክብርና ዳር ድንበር ለማስከበር ለየትኛውም ግዳጅ ዝግጁ የሆነ ጀግና፣ ብቁና ጠንካራ ሰራዊት ገንብተናል ማለታቸው ይታወቃል።

ማህበራዊ
መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችል አውድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል
Feb 24, 2026 36
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችል አውድ ለመፍጠር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡ አቶ አደም ፋራህ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተገኝተው የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴና ያከናወናቸውን የማሻሻያ ተግባራት ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠርና ተወዳዳሪነትን ከማላቅ አንጻር በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ መመልከታቸውንና ይህም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ይበልጥ ጠንካራና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ተቋም መሆኑን አንስተው በአሁኑ ወቅት ለዘመኑ የመገናኛ ብዙሃን ውድድር የሚያግዙ ስራዎች መሰራታቸውን መጥቀሳቸውንም እንዲሁ፡፡ ተቋሙ ዘመናዊነትን ከህዝብ አመኔታ ጋር ያቀናጀ በመሆኑ ተልዕኮውን በተሳለጠ መንገድ እንዲወጣ የሚያስችለው ቁመና ላይ እንዲገኝ አግዞታል ነው ያሉት፡፡ ከለውጡ ወዲህ መገናኛ ብዙሃንን በተለያዩ ተቋማት የተከናወኑ የማሻሻያ ተግባራት አካል በማድረግ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ነው አቶ አደም ፋራህ የገለጹት፡፡ ከዚህ ቀደም መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዳይሰሩ የሚገድቡ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል በነፃነት እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን አውድ ለመፍጠር ሲሰራ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንም ከለውጡ ወዲህ የተገኙ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በአግባቡ እየተጠቀመ ይገኛል ሲሉ መናገራቸውንም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በዘገባው አስነብቧል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በአፍሪካ የነጻነት ትግል ታሪክና ለዓለም ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚና አለው
Feb 24, 2026 45
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በአፍሪካ የነጻነት ትግል ታሪክና ለዓለም ሰላም ዘብ በመቆም ግንባር ቀደም ሚና እንዳለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንትና የጸረ አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በሰለጠኑበት ኮልፌ ፌዴራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ የተሰየመው የመታሰቢያ ሙዚየም ተመርቋል። በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኖንሴባ ሎሲ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ፖሊስ ምስረታ 117 ዓመታትን ያስቆጠረ ከአፍሪካ ቀዳሚው ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ የነፃነት ትግል የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸው፤ የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አባት የሆኑትን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ አሰልጥኗል ብለዋል። ኔልሰን ማንዴላ የፀረ አፓርታይድ ትግልን ለመቀላቀል እ.ኤ.አ በ1962 በኢትዮጵያ ለወራት ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያ ለመሰልጠን የመረጡት ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችና የዓለም ጥቁር ህዝቦች ምልክት በመሆኗ ነው ብለዋል። ኔልሰን ማንዴላ በኢትዮጵያውያን የፖሊስ አባላትና መኮንኖች መሰልጠናቸውን ጠቅሰው፤ ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ብሩ፣ ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ፣ መቶ አለቃ ፈቃዱ ወንድም ከአሰልጣኞች መካከል መሆናቸውን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ፖሊስ እውቀትና ልምዱን በማካፈል ለደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ገንቢ ሚና ተወጥቷል ብለዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ነጻነት ታሪክ ቀረጻ ላይ ተሳትፎ እንዳላት ያነሱት ኮሚሽነር ጀነራሉ፤ ይሄውም የኢትዮጵያ ፖሊስ ተቋም የላቀ ሙያዊ ስነ-ምግባሩንና ሀገራዊ ሀላፊነቱን የተወጣበትን መንገድ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም በኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን ወዳጅነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት የምታበረክተው አስተዋፅኦ ለዓለም ሰላም መረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን ለማዘጋጀት ተመረጠች
Feb 24, 2026 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን ለማዘጋጀት መመረጧን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ መመረጧን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኅን መግለጫ ሰጥቷል። የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር በአህጉሪቱ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትን የማስተባበር፣ አቅም የመገንባትና እርስ በርስ በማቀናጀት የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚሰራ ነው። ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር 16ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ውሳኔ የተላለፈው በየካቲት ወር 2026 በካሜሩን ያውንዴ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው። ኢትዮጵያ 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን ለማዘጋጀት መመረጧ በሀገሪቷ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ለተከናወኑ ተግባራት እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል። ጉባዔውም ኮሚሽኑ ቀጣይ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ከአቻ ተቋማት ጋር ልምድና ተሞክሮ የሚጋራበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑም ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ጉባዔውን ለማስተናገድ የሚያስችል እቅድ አውጥቶ ወደስራ መግባቱን የገለፁት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ለጉባዔው መሳካት የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በታራሚዎች አያያዝ፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የአካል ጉዳተኞች የተጠቃለለ ሕግ ማውጣት የሚያስችል ፖሊሲ ዝግጅትና በማህበረሰብ ድርጅቶች ምኅዳር ላይ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። በማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መሻሻል እንደሚታይባቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የማሻሻያ ሥራዎች ማከናወኑንም አስረድተዋል። ጉባዔው በ2019 ዓ.ም እንደሚካሄድም ነው ዋና ኮሚሽነሩ የገለጹት።
ጥራቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የጤና ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል ቁልፍ ተግባር ነው
Feb 24, 2026 37
ኩታበር ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ጥራቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የጤና ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል ቁልፍ ተግባር መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገለፁ። በአውሮፓ ሕብረትና ዩኒሴፍ ድጋፍ ደረጃቸው የተሻሻሉ በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበርና ሱሉላ ጤና ጣቢያዎች ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ በበሽታዎች ቅድመ መከላከልና አክሞ በማዳን ትኩረት አድርጓል። ሚኒስቴሩ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት በማስፋት፣ደረጃቸውን በማሻሻልና የህክምና ግብዓት በማሟላት ለዜጎች የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ በማደራጀትና ደረጃቸውን በማሻሻል አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል። በዚህም እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ እንዲወልዱ በማድረግ በወሊድ ወቅት የሚያጋጥም የሞት ምጣኔን መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ሕብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ለጤና ተቋማት ደረጃ ማሻሻል ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በክልሉ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት ውጤታማ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ ናቸው። በአውሮፓ ሕብረትና በዩኒሴፍ ድጋፍ በክልሉ በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች 35 ብሎክ ህንጻዎች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል። ይህም የጤና ተቋማትን ደረጃ ከማሻሻሉ ባለፈ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል አንስተዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ መኮንን፡ የዞኑን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ማሕበራዊ አገልግሎቶችን ለማዳረስ በተደረገ ጥረት የጤና አገልግሎት ላይ መሻሻል መምጣቱን አመልክተዋል። የጤና ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻልና ግብዓቶችን ለማሟላት የተሰራው ስራ የተገልጋዩን ፍላጎት ማሟላት ያስችላል ብለዋል። የኩታበር ከተማ ነዋሪዋ ነኢማ መሀመድ፤ በአካባቢያቸው የሚገኘው ጤና ጣቢያ አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶለት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ኢኮኖሚ
ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የተቀናጀ አሰራርን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል
Feb 24, 2026 47
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው 4ኛው አገር አቀፍ የፀረ ህገ-ወጥ ንግድ ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ ንግድ በነጋዴው፣ በህብረተሰቡና በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት ያደርሳል፡፡ መንግሥት አገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመግታት አሠራርን የማሻሻል፣ ቴክኖሎጂን የመጠቀምና ሌሎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አንስተዋል። በዚህም ህገ-ወጥነትን የመከላከልና የመቆጣጠር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንና አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አመልክተዋል። ሆኖም የህገ-ወጥ ንግድ ባህሪ ተለዋዋጭ በመሆኑ አሁንም በመከላከል ረገድ ቅንጅታዊ አሰራር ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በተለይም እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት ረገድ የጋራ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ንግድ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊቁ በየነ በበኩላቸው፤ ህገ-ወጥነት በሸማቹና በነጋዴው መካከል ያለውን ፍትሀዊ ውድድር የሚያናጋ ትልቅ ፈተና መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን ለመቅረፍ አሠራሩን በዘመናዊ መንገድ እያደራጀ መሆኑን ጠቅሰው በንግድ ሥርዓቱ ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አይናለም አባይነህ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ የንግዱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የአርብቶ አደሩን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ ለእንስሳት ኢንሹራንስ ትኩረት ተሰጥቷል
Feb 24, 2026 56
አዳማ ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦የአርብቶ አደሩን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ ለእንስሳት ኢንሹራንስ ተደራሽነት ትኩረት መሰጠቱን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሣ (ዶ/ር) ገለጹ። የሳተላይት መረጃን መሰረተ ያደረገ ከ46 ሺ በላይ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢንሹራንስ አገልግሎት ዛሬ በአዳማ በይፋ ተጀምሯል። የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሣ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ አርብቶ አደሩ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ በእንስሳቱ ላይ ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ኢንሹራንስ ወሳኝ ሚና አለው። ይህንን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል እስካሁን ከ200 ሺ በላይ አርብቶ አደሮች የእንስሳት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን አመልክተዋል። ከእነዚህ ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት የኢንሹራንሱ ተጠቃሚዎች ሴቶች ናቸው ብለዋል። የእንስሳት ሀብት ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ አርብቶ አደሩ ከእንስሳቱ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን የኢንሹራንስ ተደራሽነትን ማስፋት ይገባል ብለዋል። በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቋቋም ከእንስሳት ኢንሹራንስ በተጓዳኝ በመኖ ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት። የእንስሳት ጤና አጠባበቅን ለማሳደግ የእንስሳት ጤና ኬላዎችና ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ክሊኒኮች እንዲሁም የክትባት አቅርቦት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ ስጋት ቅነሳና የኢኮኖሚ ማሻሻያ አካታች ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ጀማል አሊይ በበኩላቸው፣ በፕሮጀክቱ 560 ሚሊዮን ብር የኢንሹራንስ ክፍያ መፈጸሙንና በዚህም ከ46 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል። አርብቶ አደሩ ከኢንሹራንስ ተጠቃሚነት ባለፈ ቁጠባን ባህል እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል
Feb 24, 2026 48
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾች ገለጹ፡፡ ለ5ኛ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተማ አቀፍ ባዛርና ኤግዚቢሽን “ኢትዮጵያ ታምርት፤ አዲስ አበባ ትበልፅግ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መከፈቱ ይታወሳል። የመንግስት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የጨርቃጨርቅ፣ የሕክምና፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ለዕይታ ቀርበዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ዘርፉን በማነቃቃት፣ የውጭ ምንዛሬን በማዳንና አዳዲስ የገበያ ትስስሮችን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራቾችም፤ ንቅናቄው ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። የቲ ማክስ ኤሌክትሮኒክስ ተወካይ ሳሊ መሐመድ፤ ድርጅቱ ቀደም ሲል ያለቀላቸውን የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከውጭ በማስገባት ላይ ተሰማርቶ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ላይ ግን ትኩረቱን ወደ ሀገር ውስጥ ምርት ማዞሩን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ፓወር ባንኮችን፣ ቻርጀሮችን፣ ፍላሾችን፣ የማከፋፈያ ገመዶችንና የሞባይል ባትሪዎችን በማምረት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህ ስኬትም ከወረዳ፣ ከክፍለ ከተማና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚደረገው ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። የጣና የቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ስራ አስኪያጅ አቶ አብይ አበበ፤ ድርጅታቸው በገበያ ላይ ተፈላጊ የሆኑ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ግብዓት እያመረተ መሆኑን ገልጸዋል። ምርቶቻቸውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዳዲስ የገበያ ትስስሮችን ለመፍጠር እንደረዳቸው አስረድተዋል። የዶሪ ኢንጂነሪንግ ተወካይ አቶ ምስጋናው ወልደሰንበት፤ ድርጅታቸው በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ እያመረተ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ ለቴሌኮም እና ለባቡር መሰረተ ልማት የሚሆኑ ግብዓቶችን እንዲሁም የተለያዩ የማሽንና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በማምረት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ምርቶቻቸውን ለአዲስ አበባና ለተለያዩ ክልሎች እያቀረቡ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል
Feb 24, 2026 72
ጎንደር ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦በግብርና ኢንቨስትመንት ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ሽግግርና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ሥራ አስፈጻሚ ደረጀ አበበ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በደንና እንስሳት ሀብት፣በአበባና ፍራፍሬ እንዲሁም በሰብል ልማት ላይ የተተገበሩ ኢንቨስትመንቶች ውጤታማ ሆነዋል። በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ከ28 ሺህ በላይ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት መሰማራታቸውን ገልጸዋል። በዚህም ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አመልክተው፤ ከዚህ ውስጥ በሰብል ልማት ዘርፍ ከ9 ሺህ በላይ ባለሀብቶች የተሰማሩ ሲሆን በዚህም ለ4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አንስተዋል። በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ከአርሶ አደሩ ጋር ትስስር በመፍጠር የቴክኖሎጂ፣ የካፒታልና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ ምርታማነታቸውን ማሳደግ መቻላቸውንም እንዲሁ። በሁሉም ክልሎች የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው የግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፉ ከውጪ የሚገቡ የግብርና ጥሬ እቃዎችን በማስቀረት ለሀገራዊ ጥቅል ምርት ዕድገት የድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል። መንግስት በዘርፉ የሚስተዋሉ የአሰራር ማነቆዎችን በጥናት ለይቶ በመፍታት የዘርፉን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተያዘው ዓመት ብቻ ከ550 በላይ የሜካናይዜሽን መሳሪያዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የተሻሻለው የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ የግብርና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ አነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ወደ መካከለኛ አልሚነት እንዲሸጋገሩና ዘርፉን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ እያገዘ ነው ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በዲጂታል ትስስርና በመሠረተ ልማት አስደናቂ ሥራ እያከናወነች ነው
Feb 24, 2026 47
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በዲጂታል ትስስርና በመሠረተ ልማት አስደናቂ ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ገለጹ። አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያና ፊንላንድ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል። ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የትምህርት ዘርፉን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ጠንካራ የልማት ትብብር እንዳላት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በዲጂታል ትስስር ረገድ ስኬታማ ሥራዎች እየሠራች መሆኑንም አንስተዋል። እንዲሁም በመሠረተ ልማት ግንባታ እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ፊንላንድ በአካታች ትምህርት እና በማህበረሰብ አቀፍ የገጠር ውሃ አቅርቦት እንዲሁም የገጠር መሬት ምዝገባን ዲጂታላይዝ የማድረግ ፕሮጀክት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እየሠራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። አምባሳደሯ አክለውም ከልማት ትብብር ባለፈ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የቢዝነስ አጋርነት በመፍጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ነን ብለዋል።
በክልሉ የተጀመረው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተሳፋሪዎች የሚነሱ ልዩ ልዩ ቅሬታዎችን በዘላቂነት ይቀርፋል
Feb 24, 2026 48
ዲላ ፤ የካቲት 17/2018(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተሳፋሪዎች የሚነሱ ልዩ ልዩ ቅሬታዎችን በዘላቂነት እንደሚቀርፍ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ አስራ ስድስት ከተሞች ተግባራዊ የሚደረገው የኢ-ትኬት የትራንስፖርት አገልገሎት ዛሬ በዲላ መናኸርያ በይፋ ተጀምሯል። የቢሮው ኃላፊ ተወልደ ተስፋዬ ፤ በክልሉ የተጀመረው የኢ- ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተሳፋሪዎች የሚነሱ ልዩ ልዩ ቅሬታዎችን በዘላቂነት እንደሚቀርፍና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል። በክልሉ የመንገድ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይ ዲላን ጨምሮ በክልሉ ሶስት ከተሞች ዘመናዊ መናኸሪያዎች ግንባታ ለማከናወን ዝግጅት ከማድረግ ባለፈ አራት የደረቅ ጭነት መናኸሪያዎች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በከተማው ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች በዲጂታል በማስደገፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር) ናቸው።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት ስትራቴጂ ለትምህርት ሴክተሩ እድገትና ማንሰራራት ጥሩ መሰረት እያኖረ ነው
Feb 24, 2026 77
ወልቂጤ ፤ የካቲት17/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት ስትራቴጂ ለትምህርት ሴክተሩ እድገትና ማንሰራራት ጥሩ መሰረት እያኖረ መሆኑን የወልቂጤ እና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ በቀጣዮቹ አምስት አመታት የሚተገበር እቅድ ተነድፎ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በቀጣይ የሚተገበረው የ2030 ስትራቴጂ ባለፉት አምስት ዓመታት ጠንካራ መሰረት የያዘውን የዲጅታል ዘርፍ በማስቀጠል ኢትዮጵያን የዲጂታል ኢንቨስትመንት ማዕከል የማድረግ እንቅስቃሴ በመከናወን ላይ ይገኛል። በእቅዱ መሰረትም ዜጎች ሁሉ በዲጂታል ክህሎት የሰለጠኑ እንዲሆኑ የማድረግ ብሎም የዲጂታል ቴክኖሎጂን በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና ሌሎችም ዘርፎች ዲጂታል ቴክኖሎጂን በስፋት ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል። የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ለእቅዱ ስኬት ወሳኝ በመሆኑ በዚሁ ልክ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የወልቂጤ እና የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤ የኢትዮጵያ የዲጅታል ልማት ስትራቴጂ በተለይም ለትምህርት ሴክተሩ እድገትና ማንሰራራት ጥሩ መሰረት እያኖረ መሆኑን ገልጸዋል። በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ቸርነት ዘርጋ፤ በዲጅታል ልማት ትግበራና ስትራቴጂ ኢትዮጵያ የሚታይ ለውጥና የሚጨበጥ ውጤት ማምጣቷን ተናግረዋል። የዘርፉ ልማት በተለይም ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት እንዲሁም ለምርምር ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል። በዚህ ረገድ በተለየም የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የመንግስትን ጥረት በምርምር ጭምር በመደገፍና በማገዝ ለዲጅታል 2030 መሳካት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክተር አበበ ሎላሞ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው የዲጅታል አገልግሎት ከትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራትና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም የምርምር ውጤቶችን በመላው ዓለም በቀላሉ ለማስተዋወቅ መልካም እድል ስለመሆኑ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በ"ዲጂታል 2025" ስትራቴጂ ባከናወነቻቸው ተግባራት በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን የጠቀሱት ምሁራኑ መንግስት ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ለዲጂታል መሰረተ ልማት የሰጠው ትኩረት ለቀጣዩ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሳካት ትልቅ ተስፋ የሰነቀ መሆኑን አስረድተዋል።
በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያገኘነው እውቀት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ፈጥሮልናል- ሰልጣኞች
Feb 24, 2026 163
ሆሳዕና ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያገኘነው እዉቀት ተጨማሪ ገቢ ለማግኝት አስችሎናል ሲሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጠናውን የወሰዱ ዜጎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠናን በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም በርካታ ወጣቶች አቅማቸውን ለማሳደግ፣ ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን ስልጠናውን በኦን ላይን እየተከታተሉ ናቸው። በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግስት ሰራተኞች ያገኙት እውቀት ኢኮኖሚያቸውን የሚያሳድጉበትን ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን ተጠቃሚ እያደረገን ነው ይላሉ፡፡ በየም ዞን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ቸርነት ሰውነት ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ባገኙት እውቀት ተጨማሪ ገቢ ለመፍጠር መቻላቸውን ይገልፃሉ። በዚህም ከመደበኛ የመንግሥት ስራቸው ጎን ለጎን ሶፍትዌሮችን ከማበልፀግ ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን በኦን ላይ በመስራት ከ365 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘት ስለመቻላቸውም ተናግረዋል፡፡ በዚሁ ዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ባለሙያ አቶ ምስጋና ከበደ በበኩላቸው በስልጠናው ድረ ገፆችንና የሞባይል መተግበሪያዎችን በማልማት፤ መረጃዎችን የማደራጀት፤ የመተንተንና የተለያዩ ማሽኖችን በመጠቀም የተለያዩ ስራዎችን መስራት እንደሚቻል በቂ ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህርት ፀጋነሽ ሞገስ እና የሶፍትዌር ኢንጂነሪነግ መምሕር የሆኑት አቶ መሳይ አስቻለው፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከዚህ ቀደም በዘርፉ የነበራቸውን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ አለማቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ከፍ ለማድረግ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። በዚህም በዘርፉ የሚያሰለጥኗቸውን ተማሪዎች ለዓለም አቀፍ ገበያው በሚመጥን መልኩ ብቁ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረላቸው አስረድተዋል፡፡ ስልጠናው የተለያዩ መተግበሪያዎችን አልምተው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምህዳር እንደፈጠረላቸውም ገልጸዋል። በክልሉ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን እየተከታተሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ከ157 ሺህ በላይ ዜጎች የእውቅና ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስፖርት
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታዎች
Feb 24, 2026 103
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ዛሬ አራት የመልስ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ ኢንተር ሚላን ከቦዶ ግሊምት በሳን ሲሮ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ኢንተር ሚላን ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከሁለት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርበታል። ተጋጣሚው ቦዶ ግሊምት ማሸነፍ፣ አቻ መውጣት እና በአንድ የግብ ልዩነት መሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ያስችለዋል። በሌላኛው መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከካራባግ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ በሴይንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በመጀመሪያው ጨዋታ 6 ለ 1 ያሸነፈው ኒውካስትል ዩናይትድ የማለፍ እድሉ እጅጉን ሰፊ ነው። በአንጻሩ ተጋጣሚው ካራባግ በሂሳባዊ ስሌት ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት እድሉ በጣም የጠበበ ነው። ባየር ሌቨርኩሰን ከኦሎምፒያኮስ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ በቤይአሬና ስታዲየም ይጫወታሉ። የጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ከሜዳው ውጪ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ውጤቱንም ተከትሎ የማለፍ እድሉን አስፍቷል። የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከሁለት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ አለበት። ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከክለብ ብሩዥ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ሶስት አቻ ተለያይተዋል። የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ቡድን ጥሎ ማለፍ ይገባል።
ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አደረገ
Feb 24, 2026 134
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/ 2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ቤንጃሚን ሼሽኮ በ71ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ላይ ኤቨርተን የተሻሉ የግብ እድሎችን ቢፈጥርም የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የነበረው ማንችስተር ዩናይትድ ያገኘውን አጋጣሚ ወደ ግብ በመቀየር አሸናፊ ሆኗል። የዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ሴን ላመንስ የጨዋታው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል። በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ዩናይትድ በ48 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። እንግሊዛዊው ጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በሊጉ አምስተኛ ድሉን አሳክቷል። ቡድኑ በካሪክ ስር እስከ አሁን አልተሸነፈም። በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ37 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት ያጠናቀቁበት የጓድላሃራ ግማሽ ማራቶን
Feb 23, 2026 72
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16 /2018 (ኢዜአ)፡- በሜክሲኮ የጓድላሃራ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል። በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ 1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ38 ሴኮንድ አሸንፏል። በሴቶች ውድድር አትሌት ኮሎሌ መካሹ 1 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ49 ሴኮንድ አሸንፋለች። ደራርቱ ኃይሉ 1 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ06 ሴኬንድ ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወሳኝ ድል አሳክቷል
Feb 23, 2026 72
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ረድኤት አስረሳኸኝ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እፀገነት ግርማ ቀሪዋን ጎል ለንግድ ባንክ ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ሰናይት ኡራጎ እና ገነሜ ወርቁ ለሸገር ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። የወቅቱ የሊጉ ዋንጫ አሸናፊ ንግድ ባንክ ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል። በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ዛሬ በተደረገ ሌላኛው መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ 14ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከየካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የበልግ እርሻ እንቅስቃሴን ቀድመው የሚጀምሩ አካባቢዎች፣ በሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚኖረውን የእርጥበት አየር ሁኔታ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል
Feb 23, 2026 83
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦የበልግ እርሻ እንቅስቃሴን ቀድመው የሚጀምሩ አካባቢዎች፣ በሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚኖረውን የእርጥበት አየር ሁኔታ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። ኢንስቲትዩቱ ከየካቲት 14 እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፤ በሚቀጥሉት ቀናት በበልግ አብቃይ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ገልጿል። በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በመካከለኛው ዝቅተኛ አካባቢዎች የሚታየው እርጥበት፤ ለአፈር ዝግጅት፣ ለዘር ዝግጅትና ለዘር መዝራት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብሏል። የሚገኘው እርጥበት ለግጦሽ ሳር በቀል፣ ለቋሚ ተክሎች እድገትና ለሰውና ለእንስሳት የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም አመልክቷል፡፡ በላይኛው አዋሽ፣ በላይኛውና በመካከለኛው ባሮ አኮቦ፣ በኦሞ ጊቤ፣ በስምጥ ሸለቆ እንዲሁም በጥቂቱ በላይኛው ገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ መጠነኛ ዝናብ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በተጠቀሱት ተፋሰሶች ላይ መጠነኛ የገፀ-ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖር ተመላክቷል። በሌላ በኩል የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ላይ ደረቃማ ቀናት እንደሚስተናገዱ በመግለጫው ተጠቅሷል።
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቡና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ለውጥ ፈጥሯል
Feb 23, 2026 199
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቡና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ለውጥ ፈጥሯል ሲሉ የዘርፉ ተዋናዮች ገለጹ። ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 469 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ የሚታወስ ሲሆን በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 600 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ ከሦስት ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት አቅዳ እየሰራች ትገኛለች፡፡ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት በግብርናው ዘርፍ የቡና ምርታማነት ላይ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ወሳኝ መሆኑን ያረጋግጣሉ። በኦሮሚያ ክልል የቡና አልሚና ላኪ የሆኑት አቶ ፈጠነ የኋላሸት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ በተለይ አረንጓዴ አሻራ ትልቅ አስተዋጾ ማበርከቱን ተናግረዋል ባለፉት ዓመታትም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በተከታታይነት መከናወኑ ቡናን ለማምረት ተስማሚ ሥርዓተ ምህዳርና የአየር ሁኔታ እንዲኖር ማስቻሉን ነው ያነሱት። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቡና መስክ ላይ የተሰማሩት አንዷለም ፋንታ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቡና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል። ይህም በመሆኑ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ የማህበሩ አባላት በስፋት በመሳተፍ ልማቱን እያገዝን እንገኛለን ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቡና ምርታማነታችንን ለማሳደግ የአካባቢውን የተፈጥሮ ገጽታ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በሲዳማ ክልል በቡና አቅራቢነት የተሰማሩት አባተ ኪሾ ናቸው ። አስተያየት ሰጪዎቹ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን እና ዝርያዎችን ለተከላ ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ዘሪሁን ቃሚሶ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሀገራችን ከቡናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማሳለጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደ ሀገር ማከናወን ከጀመርን በኋላ ከ8 ቢሊየን በላይ የቡና ችግኞች መተከላቸውን አስታውቀዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባህል የማድረግ እንቅስቃሴ
Feb 22, 2026 94
አዲስ አበባ፤የካቲት 15/2018(ኢዜአ)፦በመዲናዋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባህል የማድረግ እንቅስቃሴ በጎ አድራጎት ያለምንም ክፍያና ጎትጓች ለህሊና እርካታ ለሰዎች የሚከወን የዕለት ተዕለት ተግባር ነው። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባህል በማድረግ በቤት እድሳት፣ በደም ልገሳ፣ ማዕድ በማጋራትና በሌሎች ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከፕሎጊንግ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ ያዘጋጀው የጽዳትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ ከሁሉም የከተማዋ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ በጎ ፈቃደኞች ተሳትፈዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አስራት ንጉሴ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት በጎ ፈቃደኝነት ለራስ የህሊና እርካታን ከመስጠት ባለፈ፣ ጠንካራና የተሳሰረ ማህበረሰብ ለመገንባት ቁልፍ ሚና አለው። የከተማ አስተዳደሩ ይህንን ተግባር የዜጎች የዘወትር ባህል ለማድረግ ባለፉት ዓመታት ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው፤ በዚህም በከተማዋ በርካታ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የበጎ ፈቃድ ስራዎች መከናወናቸውን አስታውቀዋል፡። በአሁኑ ወቅት በሙያቸውና በጉልበታቸው ለሀገራቸው ለህዝባቸው የሚደርስ ማህበረሰብ መፍጠር መቻሉን አንስተው፤ ይህ ንቁ ትውልድ የመፍጠር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። እንደ ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ ሁሉ ህብረተሰቡም ሆነ ሌሎች አካላት ብዙ ጥቅም በሚያስገኘው በጎ ፍቃድ በመሳተፍ ሀገሩንና ወገኑን ማገልገል ይገባዋል ብለዋል፡። የፕሎጊንግ ኢትዮጵያ መስራች ፕሮፌሰር ፍሬው ከፍያለው በበኩላቸው፤ አካባቢን መንከባከብ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አስታውቀዋል። ድርጅታቸው ላለፉት አምስት ዓመታት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከጽዳት ጋር በማቀናጀት (Plogging) በየሳምንቱ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል። ዝቅ ብሎ ቆሻሻን ማንሳት ለራስ ክብርንና ከፍታን ይሰጣል ያሉት ፕሮፌሰሩ ማህበረሰቡ ይህንን ልምድ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል። በዕለቱ በጽዳት ዘመቻው ላይ የተሳተፉት በጎ ፈቃደኞች ፍቅር ግርማ እና ካሱ መገርሳ በሰጡት አስተያየት፤ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በመሳተፋቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፤ በቀጣይም ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በዞኑ የለሙ ተፋሰሶች በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ኢኮኖሚያዊ አቅማችንን አሳድገውልናል-ተጠቃሚዎች
Feb 21, 2026 160
አርባ ምንጭ ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- በጋሞ ዞን የለሙ ተፋሰሶች ምርትና ምርታማነትን ከማረጋገጥ ባለፈ በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ አኮኖሚያዊ አቅማቸውን ማሳደጉን በዞኑ የሚገኙ ተጠቃሚዎች ገለፁ። በምስራቅ ሸዋ ዞን ከ119 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ዕቀባ ሥራ እየተከናወነ ነው ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ወደ ትርፍ ምርት- የአረንጓዴ አሻራ ትሩፋት በዞኑ በበጀት ዓመቱ ወደ 160 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት እየተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል። ተጠቃሚዎቹ እንደገለፁት፤ በዞኑ የለሙ ተፋሰሶች ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ኢኮኖሚያዊ አቅማችንን አሳድጎልናል ብለዋል። አርሶ አደር ሚሊዮን በየነ በዞኑ የቁጫ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፤ በአካባቢያቸው ከዚህ ቀደም በተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎች የተጎዳ መሬት ሲያገግም፣ የጠፋ ምንጭ ዳግም ሲፈልቅ እና የአካባቢው ስነ-ምህዳር ወደ ልምላሜ ሲቀየር በዓይናቸው ተመልክተዋል። አመቺ ባለመሆናቸው ለእርሻ ስራ ጥቅም ላይ ሳይውሉ የቆዩ የእርሻ ማሳዎች ጥቅም ላይ ውለው ወደ ምርታማነት ተቀይረው ሲመለከቱ ደግሞ እውን ሳይሆን ህልም መስሏቸውም ያውቃል። አሁን ላይ በተፋሰስ ልማት ስራው በለማው መሬት ላይም በእንስሳት እርባታና በንብ ማነብ ስራ ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል። ለውጡንም በማየታቸው በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን ብቻም ሳይሆን ቤተሰባቸውንም በማስተባበር እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። በአርባ ምንጭ ከተማ የ"ነህሚያ የእንስሳት እርባታ ማህበር" ሰብሳቢ ወጣት ህዝቅኤል ኦሎባ የማህበሩ አባላት የተፋሰስ ልማቱ በፈጠረላቸው ጸጋ ተነሳስተው ባለፈው ዓመት በሦስት ላሞች እና በሁለት ኮርማዎች ሥራ መጀመራቸውን አስታውሷል። በተፋሰሱ በለማው ቦታ ላይም መንግስት ባመቻቸላቸው ብድር ለእንስሳት መኖ በማምረት ተጠቃሚነታቸው እየጨመረ መሆኑንም ጠቅሷል። በአሁኑ ወቅት ከላሞቹ አምስት ጥጃዎችን ማግኘታቸውን የጠቀሰው ወጣቱ ለተለያዩ አካላት የወተት ምርት በማቅረብ የገቢ ምንጫቸው ማደጉን አስረድቷል፡፡ በአካባቢው የተከናወነው የተፋሰስ ልማት ጥሩ የስራ ዕድል ይዞልን መጥቷል ያለው ደግሞ በዞኑ ምዕራብ አባያ ወረዳ በአንኮበር ቀበሌ "የጦይሎ ንብ አንቢዎች ማህበር" ሰብሳቢ ወጣት አለማየሁ ቶጋ ነው። ማህበሩ በ2014 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚናገረው አለማየሁ በለማው ተፋሰስ ላይ በአንድ በኩል ንብ እያነቡ በሌላ በኩል የለማው ከባቢ እንዳይጎዳ ጥበቃ በማድረግ ላይ እንገኛለን ብሏል። መንግስት 30 ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን፣ አንድ የማር ማጣሪያ ማሽንና መስሪያ አልባሳት እንዳበረከተላቸው ገልጾ አስፈላጊው የሙያ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም አልሸሸገም። ''በዓመት ከ3 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ማር እየሸጥን ራሳችንን ከመቻል ባለፈም ቤተሰቦቻችንን እያገዝን እንገኛለን'' ብሏል። የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ካልሳ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የተፋሰስ ልማት በተለያየ መልክ የዞኑን ህዝብ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል። የተጎዳ መሬትን እንዲያገግም በማድረግ ብሎም ስነ-ምህዳርን በማስተካከል ምርትና ምርታማነት እንዲረጋገጥ በማስቻል የአርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል። ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር በተያያዘ የነዋሪዎች ግንዛቤ እየሰፋ በመምጣቱ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር ተዳምሮ ምርት በስፋት እየተመረተ ይገኛል ብለዋል። በያዝነው በጀት ዓመትም በ336 ንዑስ ተፋሰሶች 160 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አቶ ወርቅነህ ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢጋድ እና ሩሲያ በትብብር መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
Feb 24, 2026 99
አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ሩሲያ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ አጋርነት ዳይሬክተር ታትያና ዶቭጋሌንኮ ጋር በተቋሙ መቀመጫ ጅቡቲ ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት ኢጋድ እና ሩሲያ በፖሊሲና ደኅንነት፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን፣ ሳይንስ እና ትምህርት ዘርፎች ትብብር ማጎልበት የሚያስችላቸውን ስምምነት እና የድርጊት መርሐ-ግብር ተፈራርመዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ተቀራርበው ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ህብረት እና ሳዑዲ አረቢያ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ
Feb 23, 2026 80
አዲስ አበባ፤ የካቲት 16/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ሳዑዲ አረቢያ በሰላም፣ ልማት እና ዲፕሎማሲ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ ቢን አብዱልከሪም ኤል- ከሀርጂ(ኢ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ አፍሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ለረጅም ጊዜ የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው ትብብሩ በጥልቅ የባህል፣ የኢኮኖሚና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ላይ የተመሰረተ መሆኑን አውስተዋል። ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ ያላትን ዘላቂ ትብብር እና በአህጉሪቱ እያደገ የመጣውን ኢንቨስትመንት አልፎም በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ያላትን ገንቢ ሚና አድንቀዋል። ሳዑዲ አረቢያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመቀናጀት በሊቢያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች እያሳየች ያለውን የዲፕሎማሲ ድጋፍ እና ተሳትፎ አዎንታዊ መሆኑን አመልክተዋል። የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ ቢን አብዱልከሪም ኤል- ከሀርጂ በበኩላቸው የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ በልማት፣ በሰላም እና በባለብዙ ወገን ትብብር ያለውን የመሪነት ሚና አንስተዋል። ሳዑዲ አረቢያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ልማት፣ ሰላም፣ ደህንነት እና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች የአፍሪካ ህብረትና ሳዑዲ አረቢያ ያላቸውን ግንኙነት በጋራ መከባበር መንፈስ፣ በወዳጅነት እና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ በመመስረት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ ፍላጎት ማሳየታቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና የፈጠረውን የንግድ ትስስር ለማሳደግ የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው
Feb 21, 2026 131
አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን የንግድ ትስስር ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለ አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የስምምነቱ ትግበራ የንግድ መሰናክሎችን በማስቀረት የሀገራትን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነው። እስካሁን 50 ሀገራት ፈርመው ያጸደቁት ይህ የንግድ ቀጣና፤ በዲጂታል የኢኮኖሚ ዕድገት የፋይናንስ ቴክኖሎጂን በማስፋት የአኅጉሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ በማዘመንና የገንዘብ ዝውውርን በማቀላጠፍ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የአሰራር ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ተዳራሽ ለማድረግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ዘርግቷል የኢትዮጵያ ቱሪዝም አዲሱ ገጽታ፤ ከአማራጭ ማጣት ወደ መዳረሻዎች ብዛት በኢትዮጵያ ለግል ዘርፉ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ኢኮኖሚው እየተነቃቃ ነው የአፍሪካን የተፈጥሮ ሃብትም በተሻለ የኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነት በማልማት የመሰረተ ልማት፣ የዋጋ ግሽበትና የንግድ መሰናክሎችን ለመቀነስ አይነተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል። በዚህም አባል ሀገራት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን በማፋጠን የእርስበርስ የንግድ ልውውጥን ማሳለጥ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የፈጠረውን ዕድል ለመጠቀም የግሉ ዘርፍና የአባል ሀገራት መንግሥታት የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሰረትም የአባል ሀገራት ኢንቨስትመንትን የሚያነቃቃ የኢንቨስትመንት ጥበቃ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስረድተዋል። የስምምነቱ የኢንቨስትመንት ጥበቃም የአፍሪካን በመተማመን ላይ የተመሰረተ የእርስበርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጎልበት የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ታሪካዊ አጋርነት
Feb 16, 2026 345
የኢትዮጵያ እና ቱርኪዬ ግንኙነት ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የአፍሪካ ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ኦቶማን ኢምፓየርን ጨምሮ በታሪክ ከመካከለኛው ምስራቅ እና አውሮፓ ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ነበራት። ኦቶማን ኢምፓየር ለዘመናዊቷ ቱርክዬ መሰረት ጥሎ አልፏል። በ20ኛ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት በዲፕሎማሲ እና ንግድ ልውውጥ ላይ የተመረኮዘ ነው። ቱርክዬ አፍሪካን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር የምትቆጥር ሲሆን አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ቁልፍ አህጉራዊ ተቋማት የሚገኙባት እና የአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ የዚህ ትብብር አካል ናት። ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ 1896 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የመጀመሪያ የኦቶማን-ቱርክዬ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እ.አ.አ በ1912 በሐረር ከተማ ተከፍቷል። ቱርክዬ ከሰሃራ በታች የመጀመሪያውን ኤምባሲ የከፈተችው በኢትዮጵያ ሲሆን ወቅቱም እ.አ.አ በ1926 ነበር። ኢትዮጵያ በቱርክዬ ኤምባሲዋን የከፈተችው እ.አ.አ በ1933 ነው። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ግንኙነት ከፍተኛ እድገት ያሳየበት ነው። ኢኮኖሚ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት ምሰሶ እንደሆነ ይጠቀሳል። የቱርክዬ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በግንባታ እና በግብርና ማቀነባበሪያ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ። ቱርክዬ በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። የሀገራቱ የንግድ ግንኙነትም እየዳበረ መጥቷል። ከኢኮኖሚ ባሻገር ፖለቲካ፣ ደህንነት፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪ እና ባህል ሌሎች የትብብር መስኮች ናቸው። ባለፉት 10 ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል የከፍተኛ ባለስልጣናት የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ጉብኝቱ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር ማጠናከርን ያለመ ነው። እ.አ.አ በ2017 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቱርክዬ ጉብኝት በማድረግ ኢትዮጵያን በመወከል በቱርክዬ-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2021 በቱርክዬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ስምምነቶች መፈራረማቸው ይታወሳል። ውሃ፣ ወታደራዊ ትብብር እና ፋይናንስ ከስምምነቶቹ ትኩረቶች መካከልም ይገኙበታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የተደረገው ኢትዮጵያና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 125ኛ ዓመት ላይ መሆኑ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈረሙት ስምምነቶች የግንኙነቱን መጠናከር እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። ለኢትዮጵያ የልማት እና መረጋጋት ጉዞ ቱርክዬ የምታደርገውን ድጋፍም አድንቀዋል። የቱርክዬ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በነበራቸው ቆይታ። የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እ.ኤ.አ በ2021 በቱርክዬ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ አዲስ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲም መርቀዋል። የቱርክዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እ.አ.አ በ2024 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የከፍተኛ ባለስልጣናቱ ጉብኝት የሀገራቱን የግንኙነት መጠናከር የበለጠ የሚያጎለብቱም ናቸው። ኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማት፣ የንግድ ብዝሃነትን ማስፋት፣ መከላከያ እና ደህንነት፣ ቱሪዝም እና ባህል ሀገራቱ ትብብራቸውን ሊያሰፉባቸው እየሰሩባቸው ከሚገኙ መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ አጋርነት በጋራ ፍላጎቶች፣ ተራማጅ በሆኑ ሀሳቦች፣ በጋራ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና እየተለወጡ ያሉ የዓለም እውነታዎችን ባማከለ ሁኔታ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። በልማት ጎዳና ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ከአፍሪካ ጋር ያላት ትስስር የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ጥልቀት የሚሰጥ ነው። ሁለቱ ሀገራት በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኘው ቀጣናዊ እና የዓለም ምህዳር ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እየሰሩም ይገኛሉ።
ሐተታዎች
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 61
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 163
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 610
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 948
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1017
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 976
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1524
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3842
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3495
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2321
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8113
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6600
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ ዐሻራ ከዓድዋ - እስከ አፍሪካ ኅብረት
Feb 14, 2026 288
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የፖለቲካ፣ የታሪክ እና ዲፕሎማሲ ምኅዳር ውስጥ ልዩ ስፍራ እና ተጽዕኖ ያላት ሀገር ናት። የጥንታዊ ሥልጣኔዎች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ከመሆኗ ባሻገር ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውታለች። ይህንም ታሪክ ይዘክራል። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል አይበገሬነት፣ ሉዓላዊነት እና የፓን አፍሪካ መንፈስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ካሳረፈቻቸው ዐሻራዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በዘመናዊው ዓለምም በአፍሪካ አጀንዳዎች ላይ ወሳኝ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት እና ማንነት ተምሳሌት ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1896 በዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ኃይሎች ላይ የተቀዳጀችው ድል በአፍሪካ እና በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው። አብዛኛው የአፍሪካ አኅጉር በቅኝ ግዛት ውስጥ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ድል ሉዓላዊነቷን ከማስጠበቅ ባለፈ በአፍሪካ እና በአፍሪካ ዳያስፖራ የነጻነት ትግሎች እንዲቀጣጠሉ አድርጓል። በተለይም ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ይህ ታሪካዊ ዐሻራ ኢትዮጵያን የጥቁሮች ኩራት፣ ትግል እና ራስን የመቻል ምልክት እንድትሆን አስችሏታል። የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ ኢትዮጵያ የአኅጉሪቷ የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል አስችሏል። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት) ታሪካዊ ምሥረታ የተካሄደው በኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ ከድርጅቱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ይህም የአፍሪካ የጋራ የፖለቲካ ድምጽ እንድትሆን ምክንያት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት የሚገኙባት ኢትዮጵያ፤ በዲፕሎማሲው ምክክር እና ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና የበለጠ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ድምጽ ኢትዮጵያ በቅኝ አለመገዛቷ ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ሥር መስደድ ወሳኝ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ለአፍሪካ አንድነት እና የጋራ ምላሽ አጥብቃ ስትሞግትም ቆይታለች። በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ መድረኮች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፈታት አለባቸው የሚለውን እሳቤ ለማስረጽ አበክራ እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተኮር መፍትሔዎች ከቃላት ባለፈ በአኅጉራዊ የትሥሥር አጀንዳዎች፣ ሰላም እና ደኅንነት ማዕቀፎች እንዲሁም የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ፈተናዎች እንዲፈቱ ድጋፏን በመስጠት ቁርጠኝነቷን አሳይታለች። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትንም በፍጥነት አጽድቃ ወደ ሥራ ማስገባቷ የዚሁ አንድ ማሳያ ነው። ሰላም ማስከበር እና ቀጣናዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ስትራቴጂካዊ ሚና እየተወጣች ነው። በዚህም መሠረት ለተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ድርሻ ትይዛለች። ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ወታደሮቿን በመላክ ለሰላም እና ደኅንነት ያላትን ሚና በተግባር ገልጣ አሳይታለች። የተባበሩት መንግሥታትም ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር እየተወጣች ላለው ሚና ምሥጋናውን ማቅረቡ ይታወቃል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሀገራት ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተወጣችው የእርቅ እና የዲፕሎማሲ ሚናም ተጠቃሽ ነው። የኢኮኖሚ እድገት እና ቀጣናዊ ትሥሥር ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። በ2017 ዓ.ም ማብቂያ የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በግንባታ ላይ የሚገኘው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከግዙፍ መሠረተ ልማትነታቸው ባለፈ ቀጣናዊ ትሥሥር በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢነርጂ የስኅበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምትሸጠው ኢነርጂ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትብብርን የሚያሳልጥ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድን ጨምሮ የመንገድ መሠረተ ልማቶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢትዮጵያን የቀጣናዊ ትሥሥር ማዕከል እንድትሆን እያደረጓት ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እየተከናወነ ያለው አረንጓዴ ዐሻራም፤ ኢትዮጵያን የአረንጓዴ ትብብር እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተምሳሌት ማድረግ ችሏል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች። የባህል እና የሥልጣኔ አስተዋጽዖ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ፣ ቱባ ባህል እና ብዝኃነት መገለጫዋ ናቸው። የቋንቋ ብዝኃነት በአፍሪካ ውስጥ ገራገር የዲፕሎማሲ ኃይል (Soft Power) እንዲኖራት አስተዋጽዖ አድርጓል። የኢትዮጵያ የሀገርነት ታሪክ እና የሥልጣኔ ትርክት አፍሪካ ያሏትን ጥልቅ የታሪክ ሥሮች ይበልጥ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነቶች፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች እና አስደማሚ የሥነ-ሕንጻ ሥራዎች በአፍሪካ ባህል እና ሥልጣኔ ውስጥ ያላቸው ሚና ትልቅ ነው። ኢትዮጵያ አሁንም በአፍሪካ አንድነት እና መረጋጋት ውስጥ እንደ ቁልፍ ምሰሶ ትታያለች። በአኅጉሪቱ ውስጥ ያላት ድርሻ በታሪክ ሥር የሰደደ እና አሁን ባለው ዘመን በዲፕሎማሲ፣ በሰላም ግንባታ እና ልማት ሥራ በግልጽ ጎልቶ ይታያል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና እንዲሁም የአይበገሬነት እና የነጻነት ምልክት ናት። አፍሪካ አንድነቷን ለማረጋገጥ፣ የተረጋጋ አኅጉር ለመፍጠር እና በራስ ዐቅም ነገሮችን የመከወን ጉዞ ትልም ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ ቁልፍ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ ኑረትና ንጽህና ሥርዓት፤ ለአጀንዳ 2063 ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬና ነገ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ጉባዔው ኢትዮጵያ አኅጉራዊ የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲያዊ መድረክ መሆኗን ዳግም የምታሳይበት ነው።
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!!
Feb 6, 2026 349
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በያንተስራ ወጋየሁ -ዲላ ቀን ቀንን እየወለደ ጊዜ ሳያቋርጥ እንደ ዥረት መፍሰሱን አያቆምም። ትናንት አዲስ የነበረው አሮጌው የሚባልበት፣ ዛሬ አዲስ ሆኖ ነገ አሮጌ ለመባል ይሮጣል። ወቅቶች ይፈራረቃሉ፣ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ትናንት ለዛሬ፣ ዛሬ ለነገ እንዲህ እንዲህ እየተቀባበሉ ዘመን ዘመንን እየተካ ዛሬ ላይ ተደርሷል። በጥምር ግብርናውና በቡናው የሚታወቀው ጌዴኦ ትናንትን ሸኝቶ ዛሬን እንደ አዲስ ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው። በክረምቱ የተዘራው ሰብል ተሰብስቦ ወደ ጎተራ እንዳስገባ ጌዴኦ አዲስ ዓመቱን ‹‹ዳራሮ››ን ይቀበላል። ዳራሮ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ቂም የያዘ ቂምና ቁርሾውን የሚተውበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ አዛውንቶች ወደ ሽምግልና የሚሸጋገሩበት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው የጌዴኦ አርሶ አደር ካመረተው ምርት ለመሪው፣ ልጆች ለወላጆችና ለአሳዳጊዎቻቸው፣ አዲስ ተጋቢዎች ለአማቾቻቸው፣ ቂም የያዘ ሰው እንዲሁ የተቀየመውን ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። "ጉማታ" በጌዴኦ ዘመን መለወጫ ወቅት የሚፈጸም ስጦታ ነው። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማኅበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ነው። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። በዳራሮ በዓል አከባበር ውስጥ "ጉማታ" እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ትርጉም ያለው ባህላዊ የክብር ስጦታ የመስጠት ሥርዓት ነው። "ጉማታ" ማለት በቀጥታ ትርጉሙ "ስጦታ" ማለት ቢሆንም፣ በጌዴኦ ባህል ግን ከስጦታ በላይ ነው። ምስጋናን፣ ፍቅርን፣ አክብሮትንና በረከትን የመጋራት መገለጫ ነው። የጌዴአ ባህላዊ የባሌ ስርዓት መሪ ሆነው የሚሰየሙት አባ ገዳ ለህዝብ ከመጸለይ፣ ከማስታረቅና ክፉን በማውገዝ ህዝቡ ተፈጥሮን እንዲንከባከብ ከማስተማር ውጭ አይዘሩም፣ አይነግዱም፣ አልፎም እንሳስትን አያረቡም፡፡ የዳራሮ በዓልን ተከትሎ ህዝቡ የሚያቀርብላቸውን "ጉማታ" በመቀበል ባህላዊ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት ውጪ። ኑሮው ከጥምር እርሻ ጋር የተቆራኘው የጌዴኦ ሕዝብ ዘርቶ ካጨደው፣ አርብቶ ካገኘው ከብት፣ አንቦ ከቆረጠው ማር፣ ከሁሉም በአይነት በአይነቱ ሸክፎ ዳራሮ ወደ ሚከበርበት ሶንጎ (አደባባይ) ይተማል። ለጉማታ ከሚቀርቡ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች አንዱ ማር ነው። ማር በጌዴኦ ዘንድ የጣፋጭ ዘመንና የጤና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳልና ዋናው ስጦታ ነው። ጌዶኦዎች ቡና፣ ቅቤና ባህላዊ ምግቦች፣ የቁም እንስሳት በግና ስንጋ እንዲሁም ገንዘብ በመያዝ በበዓሉ ውስጥ የጉማታ ስርዓት ሲደርስ ተሽቀዳድመው ለአባ ገዳው በመስጠት ምርቃት ይቀበላሉ። "ጉማታ" የተቀበለው ሰው የሚመርቀው ምርቃት በሰጪው ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመናልና ከስጦታው ይልቅ ምርቃቱ ትልቅ ዋጋ አለው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው ጌዴኦ በረከትን ማካፈል ለቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ በረከት እንደሚያገኝ ስለሚያውቅ ጉማታ መስጠት የዘመናት ቅርሱ ነው። ጉማታ ከአባ ገዳና ከባህል ሽማግሌዎች ባለፈ አርሶ አደሩ ከማጋኖ (ከፈጣሪ) ያገኘውን በረከት ለሚወዳቸውና ለሚያከብራቸው ሰዎች የሚያቀርብበት መንገድ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ አባላት ላሳደጓቸውና ለሰጧቸው ምርቃት ምስጋናቸውን ለመግለጽ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። በቅርቡ ጋብቻ የመሠረቱ ወጣቶች ወደ አማቾቻቸው ቤት ጉማታ ይዞ በመሄድ ዝምድናቸውን ያጠናክራሉ። በዓመቱ ውስጥ ቅሬታ ወይም ቂም ካለ፣ በዳራሮ ወቅት ጉማታ ይዞ በመሄድ ይቅርታ ይጠየቃል። ጉማታ የሰውን ልብ ለማለስለስና አዲስ ዓመትን በሰላም ለመጀመር ያገለግላል ተብሎ ስለሚታመን። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማህበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ስለመሆኑም ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠቆሙት። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። ይህም የመደጋገፍ እሴትን ከማጠናከር በተጓዳኝ ህዝቡ የመንግስት ገቢን እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን መሰረት የጣለ ነው ይላሉ። የዘንድሮው ዳራሮ ከቤት በተለይም ከአባ ገዳው መኖሪያ አንስቶ በሶንጎዎችና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር እየተከበረ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ጉማታም ዋናው የበዓሉ እሴት ሆኖ እየተከበረ ነው ብለዋል። ባህልና ማንነትን በማስጠበቅና በማዳበር፣ ባህሉ ወደ ወጣቶች እንዲተላለፍ በማበረታታት እንዲሁም የጌዴኦ ባህልን ለሌሎች ህዝቦች ለማስተዋወቅና የማህበረሰብ አንድነትና ባህላዊ እሴትን ለማጠናከር እያገለገለ ያለው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ ጥር 29 እና 30 በዲላ ከተማ ይከበራል። የዳራሮ በዓል የጌዴኦን ሕዝብ የሥራ ባህል፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ዕውቀትና የሰላም እሴት ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህ በዓል በተለይ የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድር (Cultural Landscape) በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ፣ አሁን ላይ ከቤትና ከአደባባይ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እያገኘ ያለ ታላቅ እሴት ሆኗል። የዓመት ሰው ይበለን!!