ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትብብራችንን ማጠናከር ይገባናል-ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ
Aug 23, 2026 7
አዲስ አበባ፣ነሐሴ17/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትብብራችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የእግር ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሂደዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሐመድ ጃናቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን እና የእግር ጉዞውን አስጀምረዋል። የእግር ጉዞው “ንግግርን ወደ ተግባር” (Walk the Talk) በሚል መሪ ሐሳብ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ ተካሂዷል። በወቅቱም ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ የአካል እንቅስቃሴ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት አክሞ ከማዳን ባሻገር ቅድመ መከላከል ስራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ለዚህ ደግሞ አንድነታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ገልጸዋል። በአፍሪካ ደረጃ ያለውን የጤና ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር አባል ሀገራት አብሮ የመስራት ባህላችንን ማጎልበት ይገባናል ብለዋል። የጤና ችግሮችን ለመፍታት ከመደበኛ የአዳራሽ ስብሰባ እና ከፅንሰ-ሃሳባዊ ውይይቶች ባሻገር በተግባር ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባም አክለዋል። በጉባኤው ከሚነሱ ጉዳዮች በተጨማሪ፣ በተግባር የተደገፉና ሁሉንም ያቀፉ የጤና መፍትሔዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት በጋራ መስራት ለአህጉሪቱ የጤና ሉዓላዊነት መሰረት መሆኑን አብራርተው፤ እያንዳንዱ ሀገር ለሌላው አጋርነቱን በማረጋገጥ እና በመደጋገፍ መንፈስ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። የጤና ሉዓላዊነትን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻለው የአህጉሪቱ ትብብር ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ ሁሌም ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሐመድ ጃናቢ በበኩላቸው፤ የአህጉሪቱ ህዝቦች ተባብረው ከተነሱ ማሳካት የማይችሉት የጤና ግብ እንደሌለ በአጽንኦት ተናግረዋል። በአህጉሪቱ በየጊዜው የሚወሰዱ እርምጃዎችና የሚደረጉ የጋራ ጥረቶች በሙሉ ለወደፊቱ የአፍሪካ የጤና ዘርፍ የሚደረጉ ዘላቂ ኢንቨስትመንቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ብሩህ ነገ ዛሬ በሚወሰዱ ውሳኔዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን አስገንዝበው፤ አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ዛሬ ላይ የተግባር ውሳኔዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በግሉ ዘርፍ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 23, 2026 123
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 17/ 2018(ኢዜአ)፦በግሉ ዘርፍ በርካታ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነባውን ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በግሉ ዘርፍ በርካታ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል። በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ዘመናዊ ሆስፒታሎችን ሲመለከቱ ይቆጩ እንደነበር አስታውሰው፤ ባለፉት ዓመታት በግሉ ዘርፍ ይህን ቁጭት የሚቀይሩ ትላልቅ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ የሚያደርጉ ትላልቅ ዘመናዊ የጤና ተቋማት መገንባታቸውንም አስታውቀዋል። አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ ተጨማሪ አቅም መሆኑን ገልጸዋል። በአጠቃላይ በከተማዋ የተከናወኑት ተግባራት የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑና ሌሎች ሀገራትም የሚተማመኑበት የጤና ዘርፍ መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመው ይህ በጎ ጅምር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በጤናው ዘርፍ የሚደረግ ኢንቨስትመንት መልሶ ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅም በመሆኑ በዘርፉ የሚደረግ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የከተማ አስተዳደሩ በጤናው ዘርፍ ለተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት አበረታችና ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። ከጤና መሰረተ ልማት ግንባታ አንጻር በርካታ ስራዎች በመሰራታቸው የአገልግሎት ተዳራሽነትን ማሳደግ መቻሉን ለአብነት አንስተዋል። በዘርፉ የሚታየውን እድገት የበለጠ ለማጠናከር የበርካታ አዳዲስ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ግንባታ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢማም አብዱራህማን በበኩላቸው፤ የህክምና ኮምፕሌክሱ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን አሟልቶ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡን ለማገልገል በጤናው ዘርፍ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ዘመናዊ ሽግግር፦ለአስተማማኝ የሕክምና አገልግሎት
Aug 23, 2026 87
ለዘመናት የሕዝብን ሕመም ተሸክመው፣ ሕይወትን በሕክምና ታድገው በርካታ ትውልዶችን ሲያገለግሉ የቆዩ የመንግሥት ሆስፒታሎች ዛሬ ሁለንተናዊ መታደስና ዘመናዊነትን ተላብሰዋል።ከጊዜ ብዛት ያረጁ ሕንፃዎች፣ ጊዜ ያለፈባቸው የመሣሪያዎች እጥረትና መጨናነቅ የትናንት ገጽታቸው የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባካሄደው የጤና ዘርፍ ማሻሻያ አዳዲስ ሕንፃዎች፣ የላቁ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችና የተቀላጠፈ የአገልግሎት ስሪት ተተክተዋል። የዚህ ታሪካዊ ለውጥ ህያው ማሳያ የሆነው የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል በግቢው ውስጥ በተገነባው ባለ ሰባት ወለል ዘመናዊ ማዕከል፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) የታገዙ ኤምአርአይ (MRI)፣ ሲቲ ስካን፣ አልትራሳውንድ፣ ተንቀሳቃሽ ኤክስሬይ እና በሰዓት 30 ሺህ ሊትር ኦክስጅን የሚያመርት ፕላንት ተገጥሞለታል። በተጨማሪም ለሕክምና ባለሙያዎች የተዘጋጁ የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት፣ ዘመናዊ ቢሮዎች፣ የስብሰባ አዳራሾችና ካፌቴሪያዎች የሥራ አካባቢውን የላቀና ምቹ አድርገውታል። ይህ የጤና ዘርፍ እድገት በአንድ ተቋም ብቻ ሳይወሰን፣ የሀገሪቱን የምርመራና የፍትሕ ሥርዓት አቅም ወደ አዲስ ደረጃ ያሸጋገረው የዘረመል (DNA)፣ የፎሬንሲክና የሥነ-ምርዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከል እንዲሁም በቅርቡ ሥራ የጀመረው ላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዚሁ ዘመናዊነት አካል ሆነዋል። ላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለይም የካንሰርና የልብ ሕክምናዎችን የሚያግዙ የላቁ ቴክኖሎጂዎች፣ በሰዓት 80 ሜትሪክ ኪዩብ ኦክስጅን የሚያመርት ፕላንት እና ባክቴሪያን የሚቋቋሙ (Anti-bacterial) የውስጥ ንጣፎች የተገጠሙለት ነው። በተጨማሪም ዲጂታላይዝድ የተደረገው የታካሚዎች መረጃ አያያዝ ሥርዓት (EMR) አገልግሎቱን ፈጣንና ግልጽ ከማድረጉ ባሻገር፣ ከዚህ ቀደም ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ይዳርጉ የነበሩ ውስብስብ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ በመስጠት የሕክምና ቱሪዝምን ለመቀነስ ትልቅ መንገድ ከፍቷል። ሆስፒታሎችን ማደስ ማለት አዲስ ሕንፃ መገንባት ብቻ ሳይሆን በታካሚዎች ላይ ተስፋን ማደስ፣ ለሐኪሞች የተሻለ የሥራ ከባቢ መፍጠርና ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር ለሕክምና የሚሄዱበትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ በማስቀረት ሀገራዊ አቅምን ማሳደግ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል። በመሆኑም ቀደም ሲል በአሮጌ ሕንፃዎችና በነባር አቅም ይደረግ የነበረው ትልቅ አገልግሎት፣ ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ምቹ መሠረተ ልማት ታግዞ የዜጎችን ሕይወት የመታደግ አዲስ የበጎ ምዕራፍ መክፈቻ ሆኗል።
በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ናቸው
Aug 23, 2026 102
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በቅንጅት የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክተል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አፈጻጸም በመገምገም ላይ ይገኛል። በመድረኩ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፣ የከተማዋን ሰላምና ልማት ዘላቂ ለማድረግ በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት አምጥተዋል። በፖለቲካው ዘርፍም የመደመር መንግስት እሳቤዎችን መሰረት በማድረግ፣ አሰባሳቢ ትርክት የመገንባትና አሳታፊ የፖለቲካ መስመሮች መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል። ለአብነትም በ7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡን በነቂስ ወጥቶ ይበጀኛል ያለውን መንግስት በመምረጥ ሀገርን ማስቀደሙን አሳይቷል ብለዋል። ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ረገድም በትምህርት፣ በጤና እና የስራ አጥነት ችግርን በመፍታት ላይ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን አቶ ጎሹ አመላክተዋል። በከተማዋ ነዋሪዎች የቤት ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትም የቤት መስሪያ ቦታ መሰጠቱን አንስተዋል። የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ የሚሰሩ የልማት ስራዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሁም የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ መከናወናቸውን ገልጸዋል። በከተማዋ የተመዘገቡትን ልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስቀጠል ቅንጅታዊ ተግባራት በቀጣይም እንደሚጠናከር ገልጸዋል። በመድረኩ በየደረጃው ያሉ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ሕብረ ብሔራዊነት የተንጸባረቀበት የምክክር ጉባኤ
Aug 23, 2026 104
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት እና ኢትዮጵያን ወደ የተሻለ ደረጃ የሚያራምድ መድረክ መሆኑን በጉባኤው የተሳተፉ ተመካካሪዎች ገለጹ። በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተመካካሪዎች እንደተናገሩት፤ ሀገራዊ ምክክሩ አሳታፊና አካታች የሆነ እንዲሁም ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት መድረክ ነው። በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ተሳታፊ የነበሩት ተመካካሪ መሪማ ከማል እንደገለጹት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስምንቱ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅ ምክክር የተደረገበትና ሁላችንም ሀሳባችንን ያንጸባረቅንበት መድረክ ነበር። ተመካካሪዎች ሀሳብና ጥያቄዎቻቸውን ያለተጽዕኖ በማቅረብ ምክክር የተደረገበትና ምክረ ሀሳቦች የቀረቡበት መድረክ መሆኑንም ጠቁመዋል። ሌላኛው ተመካካሪ ተክለሃይማኖት ገብረእግዚ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያውያን ከአድዋ ድልና ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ታሪክ የሰሩበት መድረክ ነበር ብለዋል። በእስካሁኑ የኢትዮጵያ ታሪክ የተስተዋለው የጠመንጃ ጉዞ አውዳሚ መሆኑን በመገንዘብ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር፣ ሌሎች ሀገራትም ችግራቸውን የፈቱበት መንገድ መሆኑን ተናግረዋል። የምክክር ጉባኤው ሕብረ ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የተንጸባረቀበት እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የሚያራምድ መሆኑንም ገልጸዋል።ምክክሩ እኔነትን ትተን ሀገር ወዳድነትን ያስቀደምንበት፣ እንዲሁም አጀንዳንና ሀገርን ማዕከል ያደረገ ምክክር ነው ብለዋል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ተቀራርበን በመመካከር ወደ መግባባት የመጣንበት ሂደት ነው" ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ ተመካካሪ ተስፋነሽ ኤርትሮ ናቸው። የምክክር ጉባኤው ለትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን የምናስረክብበት ሂደት መሆኑንም አክለዋል።
ፖለቲካ

የምክክር ጉባኤው በስኬት መጠናቀቅ በመደማመጥና መግባባት ችግሮችን መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ታሪካዊ መድረክ ነው
Aug 23, 2026 119
መተማ፣ ነሐሴ17/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቅ በመደማመጥና መግባባት ችግሮችን በራስ አቅም መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ታሪካዊ መድረክ መሆኑን የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ገለጹ። በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምእራፍ የከፈተው የምክክር ሂደት አሳታፊ እና አካታች በሆነ መልኩ ለአመታት ተከናውኖ የምክክር ጉባኤ ተካሂዶ በትናንትናው እለት በስኬት ተጠናቋል። የምክክር ሂደቱ በኢትዮጵያ የምክክርና የውይይት ባህል መሰረት ያኖረ ከመሆኑም በላይ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዜጎች በአንድ መድረክ ተገናኝተውና ተቀራርበው መምከር የቻሉበት ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የሚኖሩ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር ሂደቱ የትኛውንም ልዩነትና አለመግባባት በምክክር መፍታት እንደሚቻል አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ገልፀዋል። በኮኪት ከተማ የሚኖሩት ሼህ ሱሌማን ምስጋና፤ ለአመታት የተመከረበት የምክክር ሂደት ስኬታማ በሆነ መልኩ መጠናቀቁ የግጭት ምእራፎችን በመዝጋት በምክክርና መግባባት ሀገር መገንባት የሚያስችለን ነው ብለዋል። በሂደቱ የተመለከትነውም በጉዳዮች ላይ በመምከር ተደማምጦ በመግባባት ችግሮችን መፍታት የሚቻል መሆኑን ትምህርት የሰጠ ልምድ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የምክክር ውጤቶችን ተግባራዊ የማድረግ ሂደት የሁላችንም ትብብርና ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ያሉት ሼህ ሱሌይማን፤ ችግሮቻችንን በመፍታት ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገር ለማስረከብ መትጋት አለብን ብለዋል። የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ፍስሐ ምህረቱ፤ የምክከር ሂደቱ ኢትዮጵያውያን ችግሮቻችንን በራሳችን አቅምና በካበቱ እሴቶቻቸን መፍታት እንደምንችል በተግባር ያሳየንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በሀገሪቱ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት በመምከር ስህተቶች ታርመውና መልካም ነገሮች ዳብረው እንዲዘልቁ የሚያስችል ስለመሆኑም አንስተዋል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ የግጭትና ጦርነት አዙሪት አብቅቶ በመግባባት ሀገር ለመገንባት ሁላችንም ልንዘጋጅ ይገባል ብለዋል። ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪና የሀገር ሽማግሌ አቶ ይርጋ ተሰማ፤ እርስ በእርስ መደማመጥ ስንችል መፍትሔው እጃችን ላይ እንዳለ የምክክር ሂደቱ ጥሩ ግንዛቤ ሰጥቶናል ሲሉ ተናግረዋል። በቀጣይም የምክክር ባህልን ሰንቀንና የግጭት ልምምድን ቋጭተን ለሁላችንም የምትመች ሀገር መገንባት አለብን ብለዋል። በምክክር ጉባኤው የተገኙ መልካም ልምዶችንና ስኬቶችን ወደ ተግባር በመቀየር የህዝቦችን ወንድማማችነትና የሀገርን ሰላም ለማፅናት ሁላችንም የጋራ ሃላፊነት አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ትናንት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ኢትዮጵያን ለማጽናት የሚያስችል ታሪካዊ ሂደት መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።
የምክክር ጉባኤው የጸናች ሀገርን ለመገንባት መሰረት የጣለ ነው
Aug 23, 2026 136
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የጸናች ሀገር እና በምክክር የሚያምን ትውልድ ለመገንባት መሰረት የጣለ መሆኑን የተለያዩ ተመካካሪዎች ገለጹ። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተመካካሪዎች እንደተናገሩት፤ ምክክሩ የተለያዩ ሐሳቦች በማሰባሰብ ለአዲስ ትውልድና ለሀገር ግንባታ መሰረት ለማስቀመጥ እድል የፈጠረ ነው። ከተመካካሪዎቹ መካከል አይናለም ሙና እንደገለጹት፤ ጉባኤው የቆዩ ችግሮችን እና አለመግባባቶችን መፍታት የሚያስችሉ ሐሳቦችን ያቀበለ መድረክ ነው። በጉባኤው በመሳተፋቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ምክክሩ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ለነገ ትውልድ መሰረት የሚሆኑ ሐሳቦች ላይ ጥልቅ ምክክሮችን በማድረግ ለችግሮች መፍቻ ቁልፍ መፍትሔ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ አቶ አዩ ከተማ ናቸው። ሌላኛው ተመካካሪ አቶ ፈይሰል ጅብሪል ሀገራዊ ምክክሩ አካታች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የጸናች ሀገርና በምክክር የሚያምን ትውልድ ለመገንባት መሰረት የጣለ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን መከሩ ኢትዮጵያም አሸነፈች-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Aug 22, 2026 442
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በገዛ እጇ መወሰን እንደምትችል በተግባር አሳይታለች ሲል መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያውያን መከሩ ኢትዮጵያም አሸነፈች ሲል ባስተላለፈው መልዕክት ፣ ኢትዮጵያ የኃይልና የግጭት ፖለቲካን በቃ በማለት ልዩነቶቿን በሰለጠነ የምክክር መድረክ ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ፣ የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር በአዲስ መሠረት ላይ የጣለ ታሪካዊ ድል ሆኗል ብሏል። በኢትዮጵያ የጥቂት ልሂቃን የጥቅም ድርድር የነበሩ የዝግ በር ልማዶችን የቀየረና፣ ሰፊውን ሕዝብ የውሳኔው ቀጥተኛ ባለቤት ያደረገ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። ዜጎች ለዘመናት ያጋጠሟቸውን ታሪካዊ ስብራቶች፣ ጥልቅ አለመግባባቶችና የሐሳብ ልዩነቶች በኃይል ሳይሆን በመደማመጥና በጋራ ጥበብ መፍታት እንደሚችሉ በተግባር አስመስክረዋል። በሁሉም ክልልሎች ከቀበሌ እስከ ፌዴራል በተወከሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርሶ/አርብቶ አደሮች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የብሔር-ብሔረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ምሁራንና ሊቃውንት በስምንት አጀንዳዎች ላይ ባደረጉት ሁሉን አቀፍ ውይይት የ130 ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን ድምፅ አድምጠዋል። በዚህም ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው በንግግር ብቻ መሆኑን ፍጹም አካታች በሆነ አርአያነት አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከባንዳዎቸ ጋር ተጣምረው በዲጂታል ሚዲያ የሐሰት መረጃ ና ውዥንብር ለመፍጠር ቢሞክሩም፣ የምክክር ኮሚሽኑ ተቋማዊ ገለልተኝነቱን በጥብቅ ዲስፕሊን በመመራት በጽናት አስከብሯል። ከ54 በላይ የሚዲያ ተቋማትና 461 ጋዜጠኞች ሂደቱን በቀጥታ ሽፋን በመስጠት ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ችለዋል። በልጆቿ ፍጹማዊ ጽናት በተከናወነው በዚህ ታሪካዊ ክንውን፣ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በገዛ እጇ መወሰን እንደምትችል በተግባር አሳይታለች!ኢትዮጵያውያን መከሩ ኢትዮጵያም አሸነፈች!
የምክክር ጉባኤው በሰላም ፣በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተጠናቋል-የሠላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ
Aug 22, 2026 449
አዲስ አበባ ፣ነሐሴ 16/ 2018 (ኢዜአ)፦የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ታሪካዊ ሂደት በሰላም፣በታማኝነት፣በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መጠናቀቁን የሠላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ገልፀዋል። የሠላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እድሪስ ለዘመናት የቆዩ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ በውይይት እና በምክክር ለመፍታት የተጀመረው ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ይህ ታሪካዊ ሂደት በሰላም፣ በታማኝነት፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መጠናቀቁን አድንቀዋል። ሀገርን ለማሻገር በብልሃት መክሮ፣ ትውልድን አስተሣሥሮ ሌላ ዓድዋ ሠርቶ ማለፍ መታደል ነው፤ ተከብሮ የመኖርን መሠረትም ያጸናል ሲሉ ጠቁመዋል። ሀገራችን የመከረችበት ይህ ጉባኤ የሕዝብን አሸናፊነት፣ የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የራስን ችግር በራስ የመፍታት ጥበብን እና የዓላማ አንድነትን በገሃድ ለዓለም ዳግም ያሳየ መሆኑንም አቶ መሐመድ እድሪስ አብራርተዋል። ይህም አዲስ የሽግግር ተስፋ ምዕራፍን የሚያመላክት ደማቅ ድል መሆኑን ነው የጠቆሙት። በምክክሩ የተገኙ የጋራ መግባባቶችን እና የሰላም ፍሬዎችን መንከባከብ እና መጠበቅ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ መላው ኢትዮጵያውያን ተባብረው የነገዋን ጠንካራ፣ የበለጸገች እና ሁለንተናዊ ሰላሟ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መሠረት እንዲያጸኑ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት
Aug 22, 2026 347
ኢትዮጵያ ስላሸነፈች እንኳን ደስ አለን! ባለፉት 46 ቀናት ከሁሉም አካባቢና የህብረተሰብ ክፍል የተወከሉ አራት ሺህ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ስኬቱን የምንመዝነው በተሻገርናቸው ፈተናዎች፣ በተፈጠረው አዲስ ባህል እና በተግባባንባቸው ምክረ ሀሳቦች ነው፡፡ ምክክሩ ሁሉንም ጥያቄዎች በአንድ ጀንበር አይፈታም። ሁሉንም ቁስሎች አይፈውስም። ለሁሉም ቅሬታዎች ፍጹም መፍትሄ ሊያቀርብ አይችልም። በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደታ የተፈጠሩ ችግሮችና ያልተመለሱ ጥያቄዎች ለዘመናት በየሥርዓቱ ሲዳፈኑ ኖረዋል፤ በኃይል ፍላጎትን ለማሳካትም ተሞክሯል። ይህ ደግሞ ቁስሎችን አባብሷል፤ ሀገራዊ ዕዳንም ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ አሸጋግሯል። ሀገርን እግር ተወርች አስሮ የቀፈደዳትን ችግር በምክክር ለመፍታት ሲታሰብ ምክክሩ እንዳይጀመር፣ ሲጀመርም እንዳይቀጥል፣ ሲካሄድም እንዳይሳካ ብዙ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ሁሉንም ፈተና በጥበብና በትዕግሥት በማለፍ ኢትዮጵያ አሸንፋለች። ኢትዮጵያውያን በልዩነታቸው ውስጥ መምከር፣ መደማመጥና መግባባት እንደምንችል ከእኛ ብዙ ለሚጠብቁ አፍሪካውያን በእርግጥም አስመስክረናል። በወሳኝ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ተፈጥሯል፤ የቀሩ ሌሎች ጥያቄዎች ደግሞ ተጨማሪ ሥራ ይፈልጋሉ። ይህም የጉዞው አካል መሆኑን መረዳት ያሻል። ለዘመናት ተከድነው የቆዩ፤ ታሽገው የቆሰሉ ብዙ ጉዳዮች ነበሩን፡፡ አየር ሲነካቸው የሚፈጠረው ችግር የሚጠበቅ ነው፡፡ የውይይት ባህል ከመዳከሙ ጋር ተደምሮ እንዲህና እንዲያ መባባሉ አያስገርምም፡፡ ዋናው ወደፊት መጓዛችን ነው፡፡ እየተግባባንና እየተሻገርን መቀጠላችን ነው፡፡ በመመካከራችን ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ዕንቅፋት በነበሩት ብዙ ጉዳዮች ላይ ተግባብተንባቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከጫካ ወደ አዳራሽ፣ ከግርግር ወደ ምክክር የተዛወረ አዲስ ባህል ተፈጥሯል፡፡ ነገሮችን በሐሳብ እንጂ በጠመንጃ መፍታት እንደማይቻል፣ እንደማያዋጣም ታይቷል፡፡ ይህ አዲስ ባህል ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም፡፡ እያደገና እየተሻሻለ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ልማድና መልክ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ ይህ የምክክር ባህል አሁንም ገና ለጋ ነው። ጥበቃ፣ ልምምድ፣ ትዕግስት እና ድፍረት ይፈልጋል። እንቅፋቶች ይኖራሉ። ያከራከሩ ጉዳዮች ይኖራሉ። መልካም ጅምሮችን መውሰድ እና ይበልጥ ማሻሻል ይጠበቅብናል። ቅሬታዎቻችን ከጋራ ሀገራችን እንደማይበልጡ መተማመን ይኖርብናል። ባለፉት 46 ቀናት ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን ከመጎሻሸም ይልቅ አብረን መምከር እንደምንችል አሳይተናል። ይህ ምክክር እንዲሳካ ላደረጋችሁ ኮሚሽነሮች፣ ተመካካሪዎች፣ አመካካሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ሚዲያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ታሪክ ምንጊዜም ሲያወሳችሁ ይኖራል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ በስኬት ተጠናቋል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
Aug 22, 2026 432
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሳምንታት የምክክር ሂደት በኋላ በዛሬው እለት በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በዚህ ታሪካዊ መድረክ 4ሺህ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሰባሰብ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ስምንት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ተመካካሪዎቹ በመጨረሻም ለዘመናት ለቆዩ አለመግባባቶች መፍትሄ የሚሆኑ ምክረሃሳቦችን አጠናቅረው ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን አክለዋል፡፡ በሂደቱ ተመካካሪዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በቀላሉ እየተግባቡ፣ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ጊዜ ወስደው ጠንከር ያሉ ውይይቶችን እያደረጉ በመጨረሻም በአብዛኞቹ ጉዳዮች ላይ መግባባት መቻላቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ ሂደቱን ሲከታተል ሁሉም የምክክር መድረኮች በመደማማጥ፣ በመከባባር እና በመቻቻል ሲከናወኑ እንደነበር ማረጋገጥ እንደቻለም ነው ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት የተናገሩት፡፡ የሀገራዊ ምክክሩ ዓላማ ልዩነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት ተወያይተው የጋራ መግባባት በመፍጠር በጋራ ወደፊት መራመድ የሚችሉበትን እድል መፍጠር እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ሀገራዊ ምክክር አሸናፊና ተሸናፊን የመለየት ሂደት አይደለም ያሉት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ይህ ሂደት አንዱ ወገን ተሸንፎ ሌላው ወገን የሚያሸንፍበት ውድድርም አይደለም ብለዋል። እንደ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገለፃ በዚህ የምክክር ሂደት ኢትዮጵያዊያን እርስ በእርስ ተዋውቀዋል፣ ጠንካራ ግንኙነቶችን ፈጥረዋል፣ የተለያዩ አመለካከቶችን አዳምጠዋል፣ እንዲሁም የሀገራችንን ፈተናዎች በተመለከተ ሃሳቦችን ተለዋውጠዋል፤ በመጨረሻም መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ያሉባትን የሃሳብ ልዩነቶች በምክክር መፍታት መቻሏን ያሳየችበት ታሪካዊ ምእራፍ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #EthiopianNewsAgency #ኢዜአ #ምክክር
የምክክር ጉባኤው ጠንካራ ምክረ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበትና የሕዝብን እውነተኛ ፍላጎት የሚያጸና ታሪካዊ መድረክ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ
Aug 22, 2026 407
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ጠንካራ ምክረ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበትና የሕዝብን እውነተኛ ፍላጎት የሚያጸና ታሪካዊ መድረክ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የምክክር ጉባኤው ለአሁን ብቻ ሳይሆን የነገን ትውልድ የሚያሻግርና ሕብረ ብሔራዊነት የተንጸባረቀበት የዘመናዊ ሀገር ግንባታ ካስማ ታሪካዊ ስኬት መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ ራዕይን ለማራመድ የሚያስችል የእውቀት መድረክ የፈጠረ፣ ውይይቱንም ወደ እርጋታና ስክነት ያሻገረ ነው ብለዋል። የፖለቲካ ልምምድን ከቂምና ከበቀል ወደ ይቅርታና እርቅ ጎዳና፣ ከግጭትና ከነፍጥ አዙሪት በመላቀቅ ወደ ሰላማዊ ልምምድ ማሸጋገሩ እንዲሁም ማኅበራዊ መከባበርንና ሰከን ያለ ቋንቋን ማላመዱ ከምክክሩ ፋይዳዎች መካከል መሆኑን አንስተዋል። የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሁላችንኢትዮጵያን የሚገልጹና የሚያጸኑ የጋራ መሻቶችን፣ እውቀትንና እጣ ፈንታን በአንድ ላይ ለማራመድ የሚያስችል ጠንካራ ሐሳብ የተንሸራሸረበት መድረክ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከጸብና ከደመኝነት ስሜት ወጥቶ በይቅርታ፣ በሰላምና በመደማመጥ ጎዳና እንዲራመድ መሠረት የተጣለበት መሆኑንም ጠቁመዋል። እያንዳንዱ ተዋናይ በወከለው ማኅበረሰብ ስም፣ በሀገር ጥላ ሥር በሕብረትና በመተሳሰብ የጋራ ጉዞን እንድንቀጥል የሚያስችል ሰፊ ዕድል የተመቻቸበትና የውይይት አቅም የታየበት መሆኑንም ተናግረዋል። ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉዞ መስቀለኛ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው የድል፣ የዕድገትና የሕብረት መንገድ መሆን እንዳለበት እና የሚነሱ ሐሳቦች በሰላማዊ መንገድ መዳበር እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። ሀገራዊ ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ ብሎም ሰላምና ዕድገትን ለማረጋገጥ የሕብረተሰቡን ማኅበራዊ ትስስር፣ የጥንት ሥልጣኔ እውቀትና የጋራ እሴቶች ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ችግሮች የሚፈቱት በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ግንኙነት፣ በመተሳሰብና በታሪካዊ የትዕግሥት እሴቶች ላይ ተመሥርቶ መሆን አለበት ብለዋል። የምክክር ሂደት ጊዜያዊ የፖለቲካ መፍትሔዎችን ፍለጋ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ዕድገት የሚበጅ አዲስ የፖለቲካ ባህልን የሚያስተዋውቅና የሕዝብን እውነተኛ ፍላጎት የሚያጸና መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል። የምክክሩ ሂደት በአንድ ጀምበር የተጠናቀቀ ሳይሆን እያደገና እየበለጸገ የሚሄድ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን እርምጃ ወደ ብልጽግና የሚያሻግር ሂደት ነውም ብለዋል። የሂደት ዋነኛ ዳኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ሀገራዊ ፈተናዎችን በራሳችን ማኅበራዊ እሴትና ጥበብ በመፍታት የታሪክ ባለቤትነታችንን ማጽናት ለኢትዮጵያ ከፍታ ወሳኝ ነው ብለዋል። የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጊዜያዊ የፖለቲካ መፍትሔ ፍለጋ ሳይሆን የኢትዮጵያን የፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዞ ወደ ብልጽግና የሚያሻግር ታላቅ ታሪካዊ ክንውን መሆኑ አብራርተዋል።

ማህበራዊ
የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትብብራችንን ማጠናከር ይገባናል-ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ
Aug 23, 2026 7
አዲስ አበባ፣ነሐሴ17/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ትብብራችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የእግር ጉዞ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሂደዋል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሐመድ ጃናቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን እና የእግር ጉዞውን አስጀምረዋል። የእግር ጉዞው “ንግግርን ወደ ተግባር” (Walk the Talk) በሚል መሪ ሐሳብ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ ተካሂዷል። በወቅቱም ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ የአካል እንቅስቃሴ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል። የአፍሪካ ሀገራት አክሞ ከማዳን ባሻገር ቅድመ መከላከል ስራቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ለዚህ ደግሞ አንድነታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ገልጸዋል። በአፍሪካ ደረጃ ያለውን የጤና ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር አባል ሀገራት አብሮ የመስራት ባህላችንን ማጎልበት ይገባናል ብለዋል። የጤና ችግሮችን ለመፍታት ከመደበኛ የአዳራሽ ስብሰባ እና ከፅንሰ-ሃሳባዊ ውይይቶች ባሻገር በተግባር ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባም አክለዋል። በጉባኤው ከሚነሱ ጉዳዮች በተጨማሪ፣ በተግባር የተደገፉና ሁሉንም ያቀፉ የጤና መፍትሔዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት በጋራ መስራት ለአህጉሪቱ የጤና ሉዓላዊነት መሰረት መሆኑን አብራርተው፤ እያንዳንዱ ሀገር ለሌላው አጋርነቱን በማረጋገጥ እና በመደጋገፍ መንፈስ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል። የጤና ሉዓላዊነትን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻለው የአህጉሪቱ ትብብር ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ ሁሌም ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር መሐመድ ጃናቢ በበኩላቸው፤ የአህጉሪቱ ህዝቦች ተባብረው ከተነሱ ማሳካት የማይችሉት የጤና ግብ እንደሌለ በአጽንኦት ተናግረዋል። በአህጉሪቱ በየጊዜው የሚወሰዱ እርምጃዎችና የሚደረጉ የጋራ ጥረቶች በሙሉ ለወደፊቱ የአፍሪካ የጤና ዘርፍ የሚደረጉ ዘላቂ ኢንቨስትመንቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ብሩህ ነገ ዛሬ በሚወሰዱ ውሳኔዎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን አስገንዝበው፤ አህጉሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ዛሬ ላይ የተግባር ውሳኔዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በግሉ ዘርፍ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 23, 2026 123
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 17/ 2018(ኢዜአ)፦በግሉ ዘርፍ በርካታ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነባውን ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በግሉ ዘርፍ በርካታ ዘመናዊ ሆስፒታሎች መገንባታቸው ለከተማዋ የጤና ዕድገትና ለሜዲካል ቱሪዝም መስፋፋት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል። በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ዘመናዊ ሆስፒታሎችን ሲመለከቱ ይቆጩ እንደነበር አስታውሰው፤ ባለፉት ዓመታት በግሉ ዘርፍ ይህን ቁጭት የሚቀይሩ ትላልቅ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ የሚያደርጉ ትላልቅ ዘመናዊ የጤና ተቋማት መገንባታቸውንም አስታውቀዋል። አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ ተጨማሪ አቅም መሆኑን ገልጸዋል። በአጠቃላይ በከተማዋ የተከናወኑት ተግባራት የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑና ሌሎች ሀገራትም የሚተማመኑበት የጤና ዘርፍ መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመው ይህ በጎ ጅምር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በጤናው ዘርፍ የሚደረግ ኢንቨስትመንት መልሶ ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅም በመሆኑ በዘርፉ የሚደረግ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የከተማ አስተዳደሩ በጤናው ዘርፍ ለተሰማሩ የግል ባለሀብቶች የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ በተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት አበረታችና ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። ከጤና መሰረተ ልማት ግንባታ አንጻር በርካታ ስራዎች በመሰራታቸው የአገልግሎት ተዳራሽነትን ማሳደግ መቻሉን ለአብነት አንስተዋል። በዘርፉ የሚታየውን እድገት የበለጠ ለማጠናከር የበርካታ አዳዲስ ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ግንባታ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢማም አብዱራህማን በበኩላቸው፤ የህክምና ኮምፕሌክሱ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን አሟልቶ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡን ለማገልገል በጤናው ዘርፍ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ዘመናዊ ሽግግር፦ለአስተማማኝ የሕክምና አገልግሎት
Aug 23, 2026 87
ለዘመናት የሕዝብን ሕመም ተሸክመው፣ ሕይወትን በሕክምና ታድገው በርካታ ትውልዶችን ሲያገለግሉ የቆዩ የመንግሥት ሆስፒታሎች ዛሬ ሁለንተናዊ መታደስና ዘመናዊነትን ተላብሰዋል።ከጊዜ ብዛት ያረጁ ሕንፃዎች፣ ጊዜ ያለፈባቸው የመሣሪያዎች እጥረትና መጨናነቅ የትናንት ገጽታቸው የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባካሄደው የጤና ዘርፍ ማሻሻያ አዳዲስ ሕንፃዎች፣ የላቁ የሕክምና ቴክኖሎጂዎችና የተቀላጠፈ የአገልግሎት ስሪት ተተክተዋል። የዚህ ታሪካዊ ለውጥ ህያው ማሳያ የሆነው የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል በግቢው ውስጥ በተገነባው ባለ ሰባት ወለል ዘመናዊ ማዕከል፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) የታገዙ ኤምአርአይ (MRI)፣ ሲቲ ስካን፣ አልትራሳውንድ፣ ተንቀሳቃሽ ኤክስሬይ እና በሰዓት 30 ሺህ ሊትር ኦክስጅን የሚያመርት ፕላንት ተገጥሞለታል። በተጨማሪም ለሕክምና ባለሙያዎች የተዘጋጁ የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት፣ ዘመናዊ ቢሮዎች፣ የስብሰባ አዳራሾችና ካፌቴሪያዎች የሥራ አካባቢውን የላቀና ምቹ አድርገውታል። ይህ የጤና ዘርፍ እድገት በአንድ ተቋም ብቻ ሳይወሰን፣ የሀገሪቱን የምርመራና የፍትሕ ሥርዓት አቅም ወደ አዲስ ደረጃ ያሸጋገረው የዘረመል (DNA)፣ የፎሬንሲክና የሥነ-ምርዛ ምርመራ የልህቀት ማዕከል እንዲሁም በቅርቡ ሥራ የጀመረው ላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዚሁ ዘመናዊነት አካል ሆነዋል። ላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለይም የካንሰርና የልብ ሕክምናዎችን የሚያግዙ የላቁ ቴክኖሎጂዎች፣ በሰዓት 80 ሜትሪክ ኪዩብ ኦክስጅን የሚያመርት ፕላንት እና ባክቴሪያን የሚቋቋሙ (Anti-bacterial) የውስጥ ንጣፎች የተገጠሙለት ነው። በተጨማሪም ዲጂታላይዝድ የተደረገው የታካሚዎች መረጃ አያያዝ ሥርዓት (EMR) አገልግሎቱን ፈጣንና ግልጽ ከማድረጉ ባሻገር፣ ከዚህ ቀደም ለከፍተኛ ወጪና እንግልት ይዳርጉ የነበሩ ውስብስብ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ በመስጠት የሕክምና ቱሪዝምን ለመቀነስ ትልቅ መንገድ ከፍቷል። ሆስፒታሎችን ማደስ ማለት አዲስ ሕንፃ መገንባት ብቻ ሳይሆን በታካሚዎች ላይ ተስፋን ማደስ፣ ለሐኪሞች የተሻለ የሥራ ከባቢ መፍጠርና ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር ለሕክምና የሚሄዱበትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ በማስቀረት ሀገራዊ አቅምን ማሳደግ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል። በመሆኑም ቀደም ሲል በአሮጌ ሕንፃዎችና በነባር አቅም ይደረግ የነበረው ትልቅ አገልግሎት፣ ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ምቹ መሠረተ ልማት ታግዞ የዜጎችን ሕይወት የመታደግ አዲስ የበጎ ምዕራፍ መክፈቻ ሆኗል።
የሻደይ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል
Aug 22, 2026 352
ሰቆጣ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የሻደይ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በአማራ ክልል የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሹመት ጥላሁን ገለጹ። የሻደይ በዓልን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በአማራ ክልል የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሹመት ጥላሁን ገለፁ። በሰቆጣ ከተማ "ሻደይ ባህላችንን እናከብራለን፤ እሴቶቻችንን እንጠብቃለን" በሚል መሪ ቃል የሻደይ በዓል በተለያዩ ኩነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሹመት ጥላሁን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሻደይ ከቀደሙ አያቶች የተወረሰ የሰላም፣ የአንድነትና የሴቶች ነፃነት በይፋ መታወጁን የሚያበስር ታላቅ ባህላዊ እሴት ነው። በዓሉ የሴቶችን በራስ መተማመን ከማሳደግ ባለፈ በአካባቢው ፍቅርና አብሮነትን የሚያጠናክር በመሆኑ፣ በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የብሔረሰቡ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርጋ ማርዬ በበኩላቸው፣ የአገው ሕዝብ ከኪነ-ሕንፃ አበርክቶው ጎን ለጎን የበርካታ የማይዳሰሱ ባህሎች ባለቤት መሆኑን ጠቅሰዋል። ሻደይ የእኩልነትና የፍትህ ጥበብ ማሳያ በመሆኑ፣ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በበዓሉ ላይ የተሳተፉት የፃግብጅ ወረዳ ተጫዋች ወጣት ዘውዲቱ ንጉሡ እና የሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ተጫዋች ወጣት ብርቱካን አወጣ በዓሉን በጉጉት የሚጠበቅና የአካባቢውን ባሕልና እሴተ ለማስተዋወቅ የጎላ ሚና አለው ብለዋል። በዓሉን በፍቅርና በአንድነት እያከበሩት መሆኑን አመልክተው በዓሉን ለማክበር ያገኙትን ነፃነት፣ አብሮነትና ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሠሩም ገልጸዋል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ጀምሮ የሚከበረው የሻደይ በዓል፣ የታታሪነትና የለጋስነት እሴቶችን ባካተቱ የተለያዩ ባህላዊ ኩነቶች በደማቅ ሁኔታ መቀጠሉ ተመላክቷል።
ኢኮኖሚ
በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማ ናቸው
Aug 23, 2026 102
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፡- በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በቅንጅት የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የከተማዋ ተቀዳሚ ምክተል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አፈጻጸም በመገምገም ላይ ይገኛል። በመድረኩ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት፣ የከተማዋን ሰላምና ልማት ዘላቂ ለማድረግ በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ውጤት አምጥተዋል። በፖለቲካው ዘርፍም የመደመር መንግስት እሳቤዎችን መሰረት በማድረግ፣ አሰባሳቢ ትርክት የመገንባትና አሳታፊ የፖለቲካ መስመሮች መዘርጋታቸውን ጠቁመዋል። ለአብነትም በ7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡን በነቂስ ወጥቶ ይበጀኛል ያለውን መንግስት በመምረጥ ሀገርን ማስቀደሙን አሳይቷል ብለዋል። ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ረገድም በትምህርት፣ በጤና እና የስራ አጥነት ችግርን በመፍታት ላይ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን አቶ ጎሹ አመላክተዋል። በከተማዋ ነዋሪዎች የቤት ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትም የቤት መስሪያ ቦታ መሰጠቱን አንስተዋል። የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ የሚሰሩ የልማት ስራዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሁም የኮሪደር እና የጣና ዳር ልማት ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ መከናወናቸውን ገልጸዋል። በከተማዋ የተመዘገቡትን ልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስቀጠል ቅንጅታዊ ተግባራት በቀጣይም እንደሚጠናከር ገልጸዋል። በመድረኩ በየደረጃው ያሉ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ከህዳሴ ግድብ እስከ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ - የኢትዮጵያ አህጉራዊ የመሰረተ ልማት መሪነት
Aug 21, 2026 797
(በሙሴ መለሰ) መሰረተ ልማት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕዘን ከሆኑ ቁልፍ ዘርፎች መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢትዮጵያ የነገ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግና የዜጎቿን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተፋጠነ መልኩ እየተገበረቻቸው የሚገኙት ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ቁልፍ ሚና አላቸው ። በመንገድ፣ በባቡር፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች ግንባታዎች ላይ እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የሚመጥን የኢኮኖሚ እድገት እና የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር ረገድ ያላቸው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም። ግዙፉ ፕሮጀክቶቿ መካከልም በጳጉሜን ወር 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የኢነርጂ ትስስር ውጥን ትልቅ የምስራች ሆኖ መጥቷል። የጎረቤት ሀገራት ከግድቡ የሚያገኙት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግርም በአጽንኦት ያረጋገጡት የህዳሴ ግድብ የአፍሪካ የራስን የመቻል ምልክት እና የኢትዮጵያን አይበገሬነት ተምሳሌትነት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት የተለያዩ ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እንደሚጀመር ይፋ አድርገዋል። የኒውክሌር ኃይል ማበልጸጊያ፣ የጋዝ ፋብሪካ ማስመረቅ፣ የነዳጅ ማጣሪያ እውን ማድረግ፣ በአፍሪካ ግዙፉ አየር ማረፊያ የሆነውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መጀመር፣ ሁለተኛውን የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች በመላው ሀገሪቱ ማስጀመር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረጉ ፕሮጀክቶች/የጉባ ብስራቶች/ ናቸው። በሶማሌ ክልል የጋዝ ፋብሪካ የተመረቀ ሲሆን፣ በአፍሪካ ታሪክ በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛል። ይህ ግዙፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የሀገሪቱን የሎጂስቲክስና የቱሪዝም አቅም ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሀገሪቱን የግብርና ምርታማነት በዘላቂነት ለመደገፍ ወሳኝ የሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ በየክልሎቹ ካሉ የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ ይገኛል። በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታም ለኢነርጂ አቅርቦት እድገት የበኩሉን ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢነርጂና የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥነዋል። እነዚህ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሀገሪቱ በቅርቡ ከጀመረችው አጠቃላይ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የገበያ መር ሥርዓት ጋር የተቆራኙ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። የሀገር ውስጥ ምርታማነትንና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ከመሰረቱ የሚያሻሽሉ ከመሆናቸውም በላይ፣ ሀገሪቱ በውጭ ዕርዳታና ብድር ላይ ከመደገፍ ወጥታ በሀገር ውስጥ እቅድና አቅም ላይ ተመስርታ የራሷን ዕድል የምትወስን አይበገሬነቷን በተግባር ያሳዩ የኩራት መገለጫዎች ናቸው። መንግሥት በነዳጅ፣ በጋዝ፣ በማዳበሪያ እና በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ላይ የጀመራቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል የነበረውን የመንግሥትን ብቻ ፋይናንስ ጥገኝነት በመቀነስ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የግል ባለሀብቶችን (Private Sector) በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳትፉ አዳዲስ የአጋርነት ሞዴሎችን የፈጠሩ ናቸው። የተቀናጁ መሰረተ ልማቶች ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር በማላቅ ቀጣናዊ ትብብርን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ትስስርና በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቶች ውስጥ ያላትን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉት አያጠራጥርም። በመሆኑም እነዚህን ስትራቴጂካዊ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከተጀመሩት የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር መተሳሰር፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌትና የኢኮኖሚ ማዕከል አድርጎ ለመገንባት ለተቀመጠው የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ራዕይ መሳካት አስተማማኝ ዋስትና ተደርገው ይወሰዳሉ። የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያዊያንን የእድገት መሻት ለማሳካት የሚያከናውነው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ ሁሉም ዜጋ እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገጽ 221 ላይ እንዳመለከቱት አይበገሬነት አንድ አካል ለብቻው የሚወጣው ጉዳይ አይደለም ። ከብዙዎች ጋር ተደምረን የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተግባብተን በመደጋገፍና በመተባበር የምንወጣው ጉዳይ ነው።
የኢትዮ-ቻይና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለቻይና-አፍሪካ ትብብር ትልቅ ተምሳሌት ነው - አምባሳደር ቼን ሃይ
Aug 21, 2026 457
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና ቻይና በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ በቻይና እና አፍሪካ መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ። ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ ግንኙነቱ ቻይና እና ኢትዮጵያ በሁሉም አጋጣሚዎች አብረው የሚቆሙበትና በጋራ የሚሰሩበት ማዕቀፍ መሆኑን አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ማለቱ፣ የዓለም አቀፍ ትብብርንና የጋራ ዕድገት አቅም የሚያንጸባርቅ ከመሆኑም በላይ ለቻይና እና አፍሪካ ግንኙነት መጠናከር እንደ ዋና መሠረት እንደሚያገለግልም ተናግረዋል። ግንኙነቱ ከተለመደው የዲፕሎማሲ ወሰን በመሻገር፣ በጽኑ ፖለቲካዊ እምነትና በጠንካራ ወዳጅነት ላይ ወደተመሰረተ ሁለገብ አጋርነት ማደጉን አመልክተዋል። በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጥበበኛ አመራር የሁለትዮሽ አጋርነቱ በበርካታ ዘርፎች ጉልህ ውጤት እየተመዘገበበት መምጣቱንም ነው የገለጹት። በቅርብ ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መመሪያ አማካኝነት ቻይና እና ኢትዮጵያ በፖለቲካውና በኢኮኖሚ ዘርፍ በጋራ እየሰሩ ነው ብለዋል። የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ይበልጥ ትብብራቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አንስተዋል። ሁለቱ ሀገራት የደቡብ ንፍቀ ዓለም (Global South) ድምፅ መሆናቸውን ገልጸው በብሪክስ (BRICS) ማዕቀፍ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኝም አመልክተዋል። በነዚህ መድረኮች አማካኝነት ቻይና እና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጠበቀ ትብብር እንዳላቸው ጠቅሰው፤ ፍትሃዊ የዓለም ስርዓት እንዲሰፍንም በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ አጋርነት በረጅም ዘመን ታሪካዊ ወዳጅነት ላይ የተገነባ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ አሁን ላይ የዘመኑን ጥያቄዎች በሚመልስ ፈጣን የእድገት ምዕራፍ ውስጥ እንደሚገኝ አብራርተዋል። በአዲሱ ዘመን ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነቱ በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚያድግና በጋራ እጣ ፈንታ ላይ የተመሰረተ የቻይና እና አፍሪካ ወዳጅነትን የመገንባት ውጥን ስኬታማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1970 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የተሸጋገረው እ.አ.አ በ2023 ነበር። የሀገራቱ ግንኙነት ወደዚህ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ደረጃ ማደጉ ይፋ የተደረገው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤጂንግ ከተካሄደው ሶስተኛው የቤልት ኤንድ ሮድ (Belt and Road) ጉባኤ ጎን ለጎን ወቅት ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።
ኢትዮጵያ የግብርና ምርቷን ለማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ በትኩረት እየሰራች ነው
Aug 21, 2026 243
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ የግብርና ልማትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በመስኖ ልማት፣ በተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችና በግብርና ሜካናይዜሽን ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ ገለጹ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራት አምባሳደሮች ኮሚቴና የኢጋድ ፓርላማ ፎረም በአግሪፉድ ሲስተም ዙሪያ በአዲስ አበባ ያዘጋጁት ከፍተኛ የልምድ ልውውጥ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የግብርና ልማትን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በመስኖ ልማት፣ በተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችና በግብርና ሜካናይዜሽን ላይ በትኩረት እየሰራች ነው። የክላስተር እርሻ ልማት አርሶ አደሮች የግብዓት፣ የቴክኖሎጂ፣ የባለሙያ ምክክር አገልግሎትና የገበያ ትስስሮችን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌማት ትሩፋት ተነሳሽነቶች የአካባቢ ጥበቃን፣ የግብርና ምርታማነትንና የቤተሰብ ምግብና የአመጋገብ ስርዓትን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ተወካይና በድርጅቱ የውጭ አገልግሎት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦማር ጃማ የአግሪፉድ ሲስተም ለውጥ የካምፓላ የግብርና ልማት ቃል ኪዳንን ወደ ተግባር በማሸጋገር፣ በጠንካራ ፖሊሲ፣ የሕግ ማዕቀፍ፣ በጀትና ኢንቨስትመንት በመደገፍ እንደሚሳካ ጠቁመዋል። ሀገራቱ ለምግብ ዋስትና ችግር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለዝቅተኛ ምርታማነትና ለውስን የገበያ ትስስር የተጋለጡ በመሆኑ፣ የግብርና ለውጥን ለማፋጠን አባል ሀገራት የተቀናጀ ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል። በመድረኩ የአግሪፉድ ሲስተም ልማትን ለማፋጠን የፖሊሲ ቅንጅትን፣ የግብርና ኢንቨስትመንትን፣ የቀጣናዊ ንግድ ትስስርንና የፓርላማ ክትትልን ማጠናከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሮስፔስ ዘርፍን ለማሳደግ እና ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየጣለ ነው
Aug 21, 2026 467
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሮስፔስ ዘርፍን ለማሳደግ እና የወደፊት ሙያተኞች ማፍራት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየጣለ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ላዕከ ታደሰ ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ "STEM" ትምህርት ሥልጠና መርሐ ግብር ያጠናቀቁ የምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ላዕከ እንደገለጹት፤ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የተወጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ"STEM" የትምህርት መርሃ ግብር አማካኝነት የስድስት ሳምንታት ሥልጠና ሲከታተሉ ቆይተዋል። ተማሪዎቹ በቆይታቸው ከቴክኒክ እውቀት ባሻገር የቡድን ሥራ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ ችግር ፈቺነት እና የፈጠራ ክህሎትን ማዳበር የሚያስችላቸው ሥልጠና መከታተላቸውን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያን የኤሮስፔስ ዘርፍ ለማሳደግ እና የነገ የሀገሪቷን ባለሙያዎች ለማፍራት የሚያስችል ጠንካራ መሰረት እየተጣለ መሆኑንም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ላዕከ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ሲሆን፤ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ለረጅም ዓመታት የቆየ የንግድ እና የቴክኒክ ትብብር እንዳለው ይታወቃል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስርዓት የባለስልጣኑን የአገልግሎት አሰጣጥ አቀላጥፏል
Aug 20, 2026 230
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ማስቻሉን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው (ዶ/ር) ገለጹ። ይህ የተቀናጀ የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ተናግረዋል። መንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ግልጽ አገልግሎት ለመስጠት ዲጂታል 2025 ስትራቴጂን በውጤታማነት በመተግበር ሀገሪቱ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ነድፋ እየተገበረች ትገኛለች። በዚህ መነሻ እየተተገበረ ያለው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተበታተኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከልና በተቀናጀ አግባብ እንዲመሩ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ እያሳደገ ይገኛል። የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች ቁጥጥር አገልግሎትን በአንድ መስኮት እየሰጠ ይገኛል። ይህ አሰራር አገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ የተገልጋዮችን እርካታ እያሳደገ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን የበለጠ ለማላቅ አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ የማስደገፉን ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ውስጥ የሚገቡ 48 አገልግሎቶች መለየታቸውንና በሂደቱ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። እነዚህ አገልግሎቶች የባለስልጣኑን የአገልግሎት ተደራሽነት ከማስፋት ባሻገር ጥራትና ቅልጥፍናን በማሳደግ የተገልጋዮችን እርካታ የበለጠ እንደሚያሳድጉም አክለዋል። ባለስልጣኑ አሁን ላይ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ባገኘው ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የህግ መተላለፎች ሲከሰቱ ምዝገባ፣ ትንተና እና ሌሎች ተገልጋይ ተኮር ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው ባለስልጣኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ግልጽ እና ቀልጣፋ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ እያሳደገ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ይህን የተገልጋዮች የአገልግሎት እርካታ የበለጠ ለማሳደግ አገልግሎቶቹን ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል ማስገባት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን
Aug 20, 2026 280
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በጋራ እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን ገለጹ። አምባሳደሩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም አምባሳደሩ አንደተናገሩት በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት አለ። ይሄንን ግንኙነት መሰረት በማድረግም ሁለቱ ሀገራት በምርምር ፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ይህ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት የብሪክስ አባል ሀገራት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት ለማዋል ከሚያደርጉት ሰፊ ጥረት ጋር የሚጣጣም መሆኑም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ እያከናወናቸው ያሉ ወሳኝ ስራዎችን አስመልክተው ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል። በዚህም ኢንስቲትዩቱ የሚያከናውናቸው የምርምርና የልማት ስራዎች በኢትዮጵያ ቅድሚያ በተሰጣቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ እምርታ እንዲመዘገብ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
ዲጂታል 2030፦የኢትዮጵያ አዲሱ የቴክኖሎጂ ዘመን!
Aug 20, 2026 262
የዲጂታል 2025 መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። ይህ አዲስ ምዕራፍ ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በዲጂታል ዘርፉ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች አጠናክሮ ለመቀጠል የተዘጋጀ ታላቅ አገራዊ እቅድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች ሲሉ ገልጸዋል።ተደራሽነትን ማስፋት፣እኩል እድል መፍጠር እና በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት የስትራቴጂው ቁልፍ ትልሞች ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛውና ለአፍሪካ የመጀመሪያው የሚሆነውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ግንባታ በይፋ አስጀምራለች። ይህ ዩኒቨርሲቲ ሀገሪቱን በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግና የላቀ የኤአይ ባለሙያዎችንና ተመራማሪዎችን የሚያፈራ ታሪካዊ ተቋም ይሆናል። ይህ ታላቅ የትምህርት ተቋም ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) በማመቻቸት፣ ኢትዮጵያን የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) የማድረግ ራዕይን በግንባር ቀደምትነት የሚያስፈጽም ይሆናል። በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አጋርነት የተመረቀው 'AI UniPod' ማዕከል፣ ወጣቶች በሮቦቲክስ፣ በዳታ ሳይንስና በኤአይ ምርምሮች ላይ እንዲሰማሩ ትልቅ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ፈጥሯል። አዲሱ ስትራቴጂ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠርን ያለመ ነው። ይህም ቢሮክራሲን በመቀነስ ለዜጎች ፈጣንና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል። በተጨማሪም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር የስትራቴጂው ዋና ግብ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚው ሲያድግ የመረጃ ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ፣ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችን ማጠናከር የዚሁ ዕቅድ ዋነኛ አካል ተደርጎ ተይዟል። ይህም የዜጎችንና የተቋማትን የመረጃ ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ይፈጥራል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል። ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ በጥራት እንዲያሻሽልና አገልግሎቶችን እንዲያቀልጥ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በተጨማሪም ይፋ በተደረጉ አገራዊ መረጃዎች መሰረት፣ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ደንበኞችን ቁጥር 128 ሚሊዮን ማድረስ እና የ5G አውታረ መረብ ተደራሽነትን 100% ማድረስን አልሟል።ይህም የመገናኛ አቅምን በማሳደግ የዲጂታል ክፍተቱን በከፍተኛ ደረጃ ያጠበዋል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ማካሄድ ሌላው ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራበት ሀገራዊ ግብ ነው። ይህም አሰራርን ግልጽ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው። ለዚህም ስኬት የሁሉም አካላት ትብብርና ቅንጅት ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል። በመጨረሻም፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬት ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ የበለጸገች፣ የወጣቶችን ፈጠራ የምታበረታታ እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ የሚያገለግል ታላቅ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ነው።
ስፖርት
ማንችስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ፣ ኒውካስትል ከሊቨርፑል፡ ማን ያሸንፋል?
Aug 23, 2026 136
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል። ከቀኑ 10 ሰዓት ማንችስተር ሲቲ ከቦርንማውዝ በኢትሃድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የ10 ዓመታት ስኬታማ ቆይታ በኋላ፣ ማንችስተር ሲቲ በኤንዞ ማሬስካ አዲስ ምዕራፍ ይጀምራል። የ46 ዓመቱ ጣልያናዊ የመጀመሪያ የውድድር ጨዋታቸውን ዛሬ ከቦርንማውዝ ጋር ያደርጋሉ። በአንጻሩ አንዶኒ ኢራኦላን ወደ ሊቨርፑል የሸኘው ቦርንማውዝ የ49 ዓመቱ ጀርመናዊ ማርኮ ሮስን በአሰልጣኝነት መሾሙ ይታወቃል። ቦርንማውዝ ከባለፈው የውድድር ዓመት የቀጠለውን በሊጉ የ18 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ አስደናቂ ጉዞ ለማስጠበቅ ወደ ሜዳ ይገባል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው የውድድር ዓመት በ37ኛው ሳምንት ያደረጉት ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። ይህም የማንችስተር ሲቲን የዋንጫ ፉክክር ያበቃና የአርሰናልን የሊግ ሻምፒዮንነት ያረጋገጠ ነበር። ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላኛው መርሃ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊቨርፑል ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ። ኒውካስትል ዩናይትድ ባለፈው የውድድር ዓመት በ49 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው። ተጋጣሚው ሊቨርፑል በ60 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። ሁለቱ ቡድኖች አምና ጥሩ የሚባል ጊዜ አላሰለፉም። ይህን ተከትሎም ሊቨርፑል አርን ስሎትን፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ኤዲ ሃውን አሰንብተዋል። ሊቨርፑል አንዶኒ ኢራኦላን በአሰልጣኝነት ሲሾም ኒውካስትል ማቲያስ ጃይስልን ቀጥሯል። ቡድኖቹ አዲሱን የውድድር ዓመት በአዲስ አሰልጣኝ ይጀምራሉ። ብራይተን ከአስቶንቪላ ከቀኑ 10 ሰዓት በአሜክስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ባለፈው የውድድር ዓመት ብራይተን በ53 ነጥብ ስምንተኛ፣ አስቶንቪላ በ65 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። የወቅቱ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ጠንካራ ፈተና እንደሚገጥመው ይጠበቃል። ብራይተን ዓመቱን በድል ለመጀመር ይጫወታል።
የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ማስፋፋት ዓላማ ያደረገ የእግር ጉዞ እያደረጉ ነው
Aug 23, 2026 101
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ የጋራ የእግር ጉዞ እያካሄዱ ነው። የእግር ጉዞው ከአድዋ ድል መታሰቢያ ተነስቶ በከተማዋ የእግረኛ መንገድ በመከተል መስቀል አደባባይ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። የእግር ጉዞው “ንግግርን ወደ ተግባር” (Walk the Talk) በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው። በእግር ጉዞው የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፈዋል። የጤና አመራሮቹ በጉዞው በመሳተፍ የአካል እንቅስቃሴ እንደ ስኳር በሽታ፣ የደም ግፊትና የልብ ሕመም ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል ያለውን ጠቀሜታ በተግባር ለማሳየት ነው። የእግር ጉዞው የጤና ፖሊሲ ውሳኔዎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየርና በአፍሪካ ሕዝቦች መካከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ያለመ መልዕክት ለማስተላለፍም ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ 76ኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በአፍሪካ የጤና ስልቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።
ብሬትንፎርድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን አሸንፏል
Aug 22, 2026 305
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 0 ረትቷል። ማምሻውን በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪን ሉዊስ-ፖተር፣ ቫይታሊ ጃኔሌት እና ማይክል ካዮዴ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የብሬንትፎርዱ አጥቂ ኢጎር ቲያጎ በ55ኛው ደቂቃ ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል። ባለሜዳው ብሬንትፎርድ ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን ወደ ግብ በመቀየር ውጤታማ ነበር። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በጨዋታው ላይ ደካማ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ግልጽ የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኖታል። ብሬንትፎርድ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምሯል። በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ገንዘብ ያፈሰሰው ቶተንሃም በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።
ኤቨርተን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ኤፕስዊች ታውን ድል ቀንቷቸዋል
Aug 22, 2026 312
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። ማምሻውን በሂል ዲክንሰን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ረትቷል። ኪርናን ዴውስበሪ-ሆል እና ቲዬርኖ ባሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት 13ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኤቨርተን በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ድል ቀንቶታል። ተጋጣሚው ክሪስታል ፓላስ ዓመቱን በሽንፈት ጀምሯል። በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 አሸንፏል። አንቶን ስታች የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። በፖርትማን ሮድ በተካሄደው ጨዋታ አዲስ አዳጊው ኤፕስዊች ታውን ሰንደርላንድን 2 ለ 1 አሸንፏል። ኤመርሰን እና ጃክ ክላርክ ለኤፕስዊች ግቦቹን አስቆጥረዋል። ኒልሰን አንጉሎ ለሰንደርላንድ ጎሏን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቀን ላይ በተደረገ መርሐ ግብር አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።
አካባቢ ጥበቃ
ውበትን ከስልጣኔ ጋር ያቆራኙ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች
Aug 23, 2026 84
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በኮሪደር እና በወንዝ ዳር ልማቶች የተገነቡት ቤተ መጽሐፍት እና የተለያዩ የመዝናኛ ስፈራዎች ለመጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋን የሰነቁ የስልጣኔ ማሳያዎች መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መዲናዋን ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች፣ ለነዋሪዎቿ ምቹና ዘመናዊ ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘው ግዙፍ የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። ይህ በዋና ዋና አደባባዮች፣ መናፈሻዎች፣ መንገዶችና የወንዝ ዳርቻዎች ላይ ያተኮረው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፤ ውበትን ከጥቅም ጋር አዋህዶ የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ለውጦችን እያመጣ ነው። ኢዜአ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሉት፤ የተገነቡት የመጫወቻና የማንበቢያ ስፍራዎች የከተሜነት ምህዳሩን ከማሻሻላቸው ባሻገር ለወጣቶች የማሰላሰያና አዳዲስ ሐሳቦችን ማፍለቂያ ማዕከላት እየሆኑ ነው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ጺዮን ጌታቸው፤ በቅርብ ዓመታት የተከናወኑት የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች አዲስ አበባን ለኑሮ ተስማሚ ከማድረጋቸው ባሻገር፣ ነዋሪው አእምሮውን እያዝናና እውቀት እንዲገበይበት መንገድ መክፈታቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ግርማ አለሙ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቶቹ መጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉና ለአዲሱ ትውልድ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይም የተዘጋጁት የንባብ ማዕከላት ለተለያዩ ጥናትና ምርምሮች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ተናግረዋል። የመዲናዋ ነዋሪ ወጣት ፍራኦል ናትናኤል በበኩሉ የኮሪደር ልማቱ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ በመገንባት በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብሏል። ይህም ለአገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጿል። አቶ እንዲሪስ ተሾመ እና አቶ ግርማ ንጉሴ የተባሉ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ ደረጃቸውን የጠበቁ በርካታ የመዝናኛ ስፍራዎች ተገንብተዋል ብለዋል። አሁን ላይ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የእረፍት ጊዜ ለማሳለፍ እነዚህን አካባቢዎች ምርጫቸው ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማቶቹ፣ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍትና የመዝናኛ ስፍራዎቹ የከተማዋን ውበትና የህዝቡን የማህበራዊ ህይወት ደረጃ ያሳደጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አካባቢን ከብክለት በመጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራቱ ተግባር ይጠናከራል
Aug 21, 2026 239
ገንዳውሃ፤ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ህብረተሰቡ አካባቢውን ከብክለት በመጠበቅና በማፅዳት ጤናማና አምራች ዜጋን የማፍራት ተግባርን አጠናክሮ እንዲቀጥል የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የሀገራዊ እንቅስቃሴ አካል የሆነ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ ተካሄዷል። የምዕራብ ጎንደር ዞን አካባቢና ደን ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መልካም ዋሲሁን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ፅዱና ውብ አካባቢን መፍጠር ለጤናማ ማኅበረሰብ ግንባታ መሠረት ነው። አካባቢን ከፕላስቲክና ከሌሎች ደረቅ እንዲሁም ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ በማድረግ ፅዱ አካባቢን መፍጠር አምራች፣ ጤናማና ውጤታማ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ለዚህም ማኅበረሰቡ የአካባቢ ፅዳት ሥራን የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳያደርግ የዘወትር ተግባርና የኑሮ ባህሉ በማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጉርባ በበኩላቸው፣ ከአካባቢ ንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሕብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንፅህና ዘወትር ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል። አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ እንደ ወባ፣ ኮሌራና መሰል ተላላፊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ እንዳይከሰቱ የግልና የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ ባህል ሊደረግ ይገባል ነው ያሉት። የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ አቶ አዳነ ሀሰን እንዳሉት፣ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ለባለሀብቶች ሳቢ ለማድረግ በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማኅበረሰብና የወጣት አደረጃጀቶች አካባቢያቸውን ሰላም ከመጠበቅ ጎን ለጎን ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የጀመሩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። "ለነገው ሀገር ተረካቢ ሕፃናት ፅዱ ከተማን ማስረከብ የእኛ የወጣቶች ኃላፊነት ነው" ያለው ደግሞ በፅዳት ዘመቻው የተሳተፈው ወጣት ሃብታሙ አክሊሉ ነው። ከተማዋን ከፕላስቲክና ከሌሎች መርዛማ ኬሚካሎች በማፅዳት ማራኪና ለነዋሪዎቿ የምትመች ተመራጭ ከተማ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት በቀጣይም የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል። በፅዳት ዘመቻው የከተማዋ የመንገድ ዳርቻዎች፣ የገበያ ስፍራዎችና የሕዝብ መዝናኛ አካባቢዎችን ከቆሻሻ ፅዱ የማድረግ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ በየሳምንቱም የፅዳት ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል። በተካሄደው የፅዳት ዘመቻም የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ በሰው እና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮችን ለመቆጣጠርና ለማስወገድ በትኩረት እየሰራች ነው
Aug 21, 2026 217
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15 /2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰው እና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮችን (POPs) ለመቆጣጠርና ለማስወገድ በትኩረት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተሻሻለ የብሔራዊ የትግበራ እቅድ ሰነድ ግምገማ እና ማጽደቂያ መድረክ አካሂዷል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በዚሁ ወቅት፤ የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮች በባህሪያቸው ቶሎ የማይበሰብሱ፣ በሰው እና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ቁሶች ናቸው ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥም ዲዲቲ (DDT)፣ ፒፎስ (PFOS) እና ፒኤፍኤችኤክስኤስ (PFHxS) የተሰኙትን ለአብነት አንስተዋል። የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮች (POPs) የሚያስከትሉትን ጉዳት ለመከላከልና ለማስወገድ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ወይም እንዳይመረቱ የሚያደርግ እኤአ በ2001 የስቶክሆልም ስምምነት መደረጉን አውስተዋል። ኢትዮጵያ ስምምነቱን መሰረት በማድረግ በሰው እና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያመጡ የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮችን (POPs) ለመቆጣጠርና ለማስወገድ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እንዳከናወነች ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ለተለያዩ አላማዎች በሚል ይመረቱ የነበሩ እንደ ዲዲቲ (DDT) ያሉ የማይመክኑ በካዮች እንዳይመረቱ እንዲሁም ሀገር ውስጥ ማምከኛ የሌላቸው የተለያዩ ኬሚካሎችን ወደ ውጭ በመላክ እንዲመክኑ መደረጉን አስታውቀዋል። ዛሬ ለምክክር የቀረበው ሰነድ በሀገር ደረጃ የማይመክኑ ኦርጋኒክ በካዮች አያያዝ፣ ቁጥጥር እና አስተዳደርን የሚያጠናክር ተግባራዊ የስራ መመሪያ መሆኑን ገልጸዋል። መድረኩ አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ካለው ሶስተኛ ዙር "ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" ስራ ጋር ተያያዥነት ያለው እንደሆነም አመላክተዋል። ለብሔራዊ ትግበራ መርሃ ግብሩ ስኬት የፌደራልና የክልል ተቋማት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበራት እና የልማት አጋሮች ቅንጅት ወሳኝ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ጨምረው ተናግረዋል። አዳዲስ በካይ ኬሚካሎችን መለየት፣ የላቦራቶሪ ቁጥጥር አቅምን ማሳደግ፣ ማምከኛ መሳሪያዎችን መታጠቅ፣ የመረጃ ስብሰባን ማጠናከርና የቴክኒክ እንዲሁም የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል። ከመድረኩ የተገኙት ግብዓቶችን በማካተት ሰነዱን የበለጠ ለማጠናከርና ውጤት ተኮር ለማድረግ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በኦሮሚያ ክልል ተመናምኖ የነበረው የደን ሽፋን በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት በፍጥነት እያደገ ነው
Aug 21, 2026 205
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተከናወኑ ተግባራት አማካኝነት ተመናምኖ የነበረው የደን ሽፋን መልሶ እድገት እያሳየ መሆኑን የክልሉ ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት አስታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ሰፊ የተፈጥሮ ሀብትና ብዝሃ-ሕይወት ባለቤት ቢሆንም፣ ባለፉት አሥርተ ዓመታት በሕገ-ወጥ የደን ምንጣሮ፣ ለእንጨትና ከሰል ምርት በሚደረግ ጭፍጨፋ እና ለእርሻ መሬት ማስፋፊያ ምክንያት የደን ሽፋኑ በከፍተኛ ደረጃ ተመናምኖ ቆይቷል። ይህ የደን ውድመት አካባቢውን ለአፈር መሸርሸር፣ ለወንዞችና ሐይቆች መድረቅ እንዲሁም ለምርታማነት መቀነስ ዳርጎት የነበረ ሲሆን፣ በተለይም እንደ ሐረማያ ባሉ አካባቢዎች የነበሩ የውሃ አካላት ሙሉ በሙሉ እስከመድ ረቅ ደርሰው የነበረው አካባቢያዊ ሥነ-ምህዳሩ ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጦ ስለነበር ነው። ይህንን ሥነ-ምህዳራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ አደጋ ለመቀልበስ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ በሀገር ደረጃ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉም በየዓመቱ እንደ ዋነኛ መፍትሔ ተወስዶ ሰፊ የተቀናጀ ንቅናቄ በማካሄድ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ውጤት እየመጣ ነው። የኦሮሚያ ክልል ደን እና ዱር እንስሳት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ አራርሳ ረጋሳ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ በክልሉ ባለፉት ዓመታት የደን ሽፋኑን ለማሳደግ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። በክልሉ የደን ሽፋኑን ለማሳደግ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል፣ በተለይም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተራቁተው በነበሩ ቦታዎች ላይ ሳይንሳዊ መንገድን በተከተለ መልኩ የተለያዩ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ጎን ለጎን አካባቢዎችን ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ነፃ በማድረግ እንዲሁም ሕገ-ወጥ የእርሻ መሬት ማስፋፋትን ለመግታት በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። በተለይም ችግኞችን በመትከል ላይ ብቻ ሳይወሰን ለእንክብካቤያቸው ከፍተኛ ትኩረት በመሰጠቱ ለውጤቱ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም በክልሉ ከዚህ በፊት ተመናምኖ የነበረው የደን ሽፋን ወደ 27 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። ይህ የተቀናጀ ጥረት የአፈር መንሸራሸርን መከላከል፣ የአፈር ለምነትን መመለስ እንዲሁም የደረቁ ምንጮች፣ ሀይቆችና ወንዞች እንደገና እንዲጎለብቱ ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደርቆ የነበረው የሐረማያ ሀይቅ ሙሉ በሙሉ ማገገሙን ለአብነት አንስተዋል። በአጠቃላይ የመርሃ ግብሩ ስኬት በሁሉም ወቅቶች መሬትን በማልማት፣ የአካባቢ ጥበቃን ከግብርና ስራዎች ጋር በማጣመር የምርትና ምርታማነት እድገትን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አቶ አራርሳ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በደን መልማቱን ገልጸዋል። ከአጠቃላይ መሬቱ ውስጥ 1 ሚሊዮን ሄክታር ያህሉ ለዱር እንስሳት እንክብካቤና ጥበቃ፣ ለፓርኮች፣ ለስፖርት ስፍራዎች ሲሆኑ፣ 700 ሺህ ሄክታር መሬት ደግሞ ለችግኝ ተከላ እና ለሰው ሰራሽ ደን ልማት የተመደበ ስፍራ ነው። ከአጠቃላይ መሬቱ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ደግሞ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ደን የተሸፈነ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1066
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 922
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1201
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1764
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 218
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 418
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ
Aug 19, 2026 333
ቡሄ በወርሃ ነሐሴ በ13ኛው ቀን ህፃናት ሆያ…. ሆዬ….! ሆ…. በሚል ዜማና ጅራፍ እያጮሁ የሚያከብሩት፤ እናቶች ለህፃናቱ ሙል ሙል ዳቦ በመስጠት እንኳን አደረሳችሁ እያሉ በድምቀት የሚያከብሩት በዓል ነው። ቡሄ ትርጓሜውም ብርሃን፣ብራ፣ ወጋግን ማለት ሲሆን ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገሪያ የተስፋ ምልክት ነው። በሀይማኖታዊ አንድምታው በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ብርሃን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ መገለጡ የሚታሰብበት ነው፤ በዚህም ደብረ ታቦር ይባላል፡፡ የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ የብርሃን ወጋገን የሚታይበት ሕፃናትና ወጣቶች በየቤቱ እየዞሩ «ሆያ ሆዬ» በማለት በረከትና ምርቃት የሚያፍሱበት የደስታና የፍቅር መግለጫ ነው። ህፃናትና ወጣቶች በየዕድሜያቸው ጅራፍ እያጮሁ በሕብረ ዝማሬዎች እየደመቁ በአብሮነት እና በደስታ የሚያከብሩት ትውፊታዊ በዓል ነው ቡሄ። የወጣቶችን ጉርብትና እና ማኅበራዊ ትስስር የሚያጎለብት እሴት ነው፤ በአከባበሩ ወቅት የሚንጸባረቀው የመረዳዳትና ያለውን የመካፈል ባህል ፋይዳውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሸጋገር ያስችላል። የቡሄ በዓል ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅ፣ ትውልድን በማቀራረብ እና ማኅበራዊ ትስስርን ይበልጥ በሚያጠናክር ተምሳሌትነቱ እልፍ ነው። በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከፍተኛ የቅርስ ጥናት ተመራማሪ መምህር መክብብ ገብረማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ የቡሄ በዓል የብርሃን ዘመን መምጣቱን የተስፋ ጎህ መቅደዱን ማብሰሪያ ነው፡፡ ቡሄ ከጨለማ ወደ ብርሃን ሽግግር መምጣቱን የሚያበስር በታዳጊዎች የሚዘከር የፍቅር፣ የአንድነትና የበረከት መገለጫና ተስፋ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ ታዳጊዎችና ወጣቶች በበዓሉ ወቅት የሚያዜሙት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የ«ሆያ ሆዬ» ሕብረ ዜማ ለጋራ ትርክት ግንባታ ገንቢ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። ቡሄ የትውልድ ወጋገን፤ የማኅበራዊ ትስስር አምድ በመሆኑ ማኅበራዊ ትስስርና የጋራ ዕሴቶችን ማጠናከር ያስችላል ብለዋል። ታዳጊው በሱፈቃድ አስሜ ቡሄ ከጓደኞቹ እና ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ፍቅርንና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክርበት የደስታና የተስፋ በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ ቡሄ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠብቀውና ቀጣይ ሕይወቱን በአዲስ መንፈስ ለመምራት አቅም የሚፈጥርለት የብሩህ ዘመናትን ማለሚያ መሆኑን ይገልፃል። ቡሄ ከታላላቆቹ የወረሰው ከእኩዮቹ ጋር በፍቅርና በደስታ የሚያከብረው ነገን በተስፋ የሚያይበት ውብ በዓል እንደሆነ የሚናገረው ደግሞ ታዳጊው በረከት ምናለ ነው፡፡ የተጣሉ ጓደኛሞች እርቅ የሚያወርዱበት በዓል በመሆኑ ለትውልድ አንድነት እና አብሮነትን በማስተማር ረገድ ትልቅ ድርሻ አለውም ብሏል። ወጣት ያብስራ ጸጋዬ በበኩሉ ቡሄ በዓመት አንድ ጊዜ የሚመጣ፤ ተራርቀው ከሚኖሩ የተለያዩ አካባቢ እኩዮቹ ጋር በአንድነት የሚያከብሩት በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ ከሁሉም ዓይነት ሕብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ታዳጊዎች የሚሰባሰቡበት፤ ሕብረ ብሔራዊነትን የሚያጠናክር የጋራ በዓል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ አቶ በኃይሉ ሞገስ ናቸው።
ሳምንቱን በወፍ በረር!!
Aug 16, 2026 310
ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ሳምንቱን በወፍ በረር!! በዚህ ዝግጅታችን በክልሎች የተከናወኑ ዓበይት ጉዳዮችን በወፍ በረር ቃኝተን እናስታውሳለን። በመሆኑም በሳምንቱ በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ከተከናወኑ ዓበይት ኩነቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ምን ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? 1. የሰሊጥ ልማት በጋምቤላ ከሳምንቱ ዓበይት ጉዳዮች መካከል በጋምቤላ ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት ከ86 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰሊጥ ሰብል የመልማቱ ዜና አንዱ ነው። በክልሉ የቅባት እህሎች ልማት በዋናነት በባህላዊ አርሶ አደሮችና በጥቂት ባለሀብቶች ተወስኖ ሲከናወን የነበረ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘመናዊ የግብርና ግብዓቶች እና በሜካናይዜሽን እርሻ ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታውቋል። እንደ ቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጀሉ ኡሞድ ገለጻ፤ ክልሉ የቅባት ሰብሎችን ጨምሮ ለሁሉም የግብርና ልማት ሥራዎች ምቹ ስነ-ምህዳር ያለው ነው። በክልሉ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በባለሀብቶችና በአርሶ አደሮች ከ86 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰሊጥ ሰብል ለምቷል። ከዚህም ከ516 ሺህ ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት የሰብሉ ቁመና በተሻለ ሁኔታ ላይ ስላለ ከተጠበቀው በላይ ምርት ሊገኝ እንደሚችልም ተንብየዋል። 2. የገቢ አሰባሰብን በማጠናከር ልማትን ማፋጠን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝብን የልማት ጥያቄ የመመለስ ተግባራት እንደሚጠናከሩ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የተገለጸውም በዚህ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የተናገሩት የክልሉ ገቢዎች እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮዎች በሕገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ ኑሮን ማረጋጋትና የታክስ ሕግ ተገዢነትን ለማረጋገጥ በሆሳዕና ከተማ ባዘጋጁት የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው። በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በክልሉ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች የመመለስ ተግባር እንደሚጠናከር ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት ገቢን በማሳደግ የከተሞችን ገጽታ የመቀየር፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን የማስፋትና የማህበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት ስኬቶች እንደተመዘገቡና በቀጣይም ይህን ለማጠናከር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በክልሉ የንግድ ሥርዓቱን በማዘመን የተሳለጠ አሠራር መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት እንዳሻው (ዶ/ር)፤ ለዚህም ሕገ-ወጥነትን የመከላከል፣ የግብይት ማዕከላትን የማስፋፋት፣ ምርትን በበቂ ሁኔታ የማቅረብ፣ የዋጋ ንረትን የመቆጣጠርና የሸማች ማኅበራትን የማጠናከር ሥራዎች እንደሚከወኑም አክለዋል። 3. የአፋር ክልል በጀት የክልሉ ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ያጸደቀውም በዚሁ ሳምንት ነበር። በሰመራ ከተማ ለሦስት ቀናት የተካሄደው የምክር ቤቱ 6ኛ የምርጫ ዘመን፣ 5ኛ የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የዳኞችንም ሹመት አጽድቋል። የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሳ መሐመድ በጉባዔው ተገኝተው የክልሉን የ2019 ረቂቅ በጀት ያቀረቡ ሲሆን፣ በጀቱ ከመንግሥት ድጎማ፣ ከክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌዴራል መንግሥት እና ከተለያዩ የገቢ አማራጮች የሚሸፈን መሆኑን አንስተዋል። ለበጀት ዓመቱ የተመደበው ገንዘብ የክልሉን ልማት ለማቀላጠፍና የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ይረዳል ብለዋል። 4. የኢንቨስትመንት መድረክ ሌላው የሳምንቱ ዓበይት ጉዳይ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት አስፈጻሚ አካላት በጋምቤላ ከተማ ያካሄዱት የጋራ የምክክር መድረክ ነበር። በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የኢንቨስትመንት እድሎችን በማስተዋወቅና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓቶችን በመተግበር በርካታ ባለሀብቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ መቻሉም ተገልጿል። በመድረኩም ሀገሪቱ ያሏትን የኢንቨስትመንት እድሎች ለባለሀብቶች የማስተዋወቅ እና አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ በመድረኩ እንደገለጹት የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ አልሚዎችን ለመሳብ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያስገኙ ነው። በዚህም በበጀት ዓመቱ ብቻ 528 የውጭ ሀገር ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን በማሳያነት አንስተዋል። 5. የወጣቶች ተሳትፎ የላቀበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በየአካባቢው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው የተገለጸው በዚሁ ሳምንት ነበር። በጅማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት እና ሌሎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ለማከናወን በተዘጋጀ መርሃ ግብር ላይ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ሕይወት በዘላቂነት ለመቀየር ያለመ ድጋፍ ተደርጓል። ከድጋፎቹ መካከል የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ፣ የምግብ ግብዓት፣ የንብ ቀፎዎች እና ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ምጣድ ይገኙበታል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ረሂማ ዩሱፍ፣ በክልሉ በርካቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውንና በአገልግሎቱም የወጣቶች ተሳትፎ የላቀ መሆኑን ተናግረዋል። የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፤ በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዞኑ ከ5 ሺህ 500 በላይ አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤትን ለማደስ መታቀዱንና እስካሁንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መታደሳቸውን አንስተዋል። 6. ሚኒስቴር ተቋማቱ በበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገውም በዚህ ሳምንት ነበር። ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን እንደገለጹት፤ ድጋፉ የተደረገው በሐረር ወላጆቻቸው አቅም ለሌላቸው 600 ተማሪዎች ነው። ሚኒስትር ዴኤታው ከሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ዑመር ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ያከናወኑ ሲሆን፣ በክልሉ የአቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት ግንባታንም አስጀምረዋል። ሚኒስቴሩም ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች መሰል የልማት ሥራዎችን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አስታውሰዋል። በተመሳሳይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በተያዘው ሳምንት ነበር በዱብቲ ወረዳ አሮላፍና ገበላይቱ ቀበሌ የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤቶች ግንባታና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ያከናወኑት። በዚህ ወቅትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሐኑ ጸጋዬ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተቀናጀ መልኩ ማከናወኑ ማህበራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስቴሩም በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአፋር ክልል 10 የአቅመ ደካማ ወገኖች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ መሆኑን አንስተው፣ በተጨማሪም አንድ የቅድመ መደበኛ መዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ቤት እንደሚገነባም ነው የገለጹት። 7. የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማነት ሳምንቱ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማነት ማሳደጉ የተገለጸበትም ነበር። የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ መንግሥት በተለይ የመሬት፣ የኤሌክትሪክ፣ የፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ጥያቄዎች በአፋጣኝ እንዲመለሱ መደረጉ ኢንዱስትሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ 11 ከፍተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ በመግባት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አንስተዋል። ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ የወጪ ምርቶችን አምርተው በመላክ ለሀገር የውጭ ምንዛሬ እያስገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ጉብኝት ከተደረገባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል የፈሳሽና ጠጣር ሳሙና፣ የጭማቂ፣ የውሃ፣ የሮቶ፣ የካርቶንና የእርሻ መሳሪያ ማምረቻዎች እንዲሁም የቡና ማቀነባበሪያዎች ይገኙበታል። 8. ሠራዊቱ ከወገን አለኝታነቱ ባሻገር የልማት አጋርነቱን አጠናክሯል ከሳምንቱ ዓበይት ጉዳዮች መካከል የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ዳር ድንበር የማስከበር ግዳጁን ከመወጣት ጎን ለጎን የወገን አለኝታነቱንና የልማት አጋርነቱን የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑም በዋነኝነት የተገለጸበት ነው። በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ዕዝ አመራሮችና የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቆቦ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የኮሪደር ልማት ጎብኝተዋል። የ11ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አድማሱ ዓለሙ በወቅቱ እንዳሉት፤ የቆቦ ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ዕዙ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል። በዚህም የዕዙ አመራሮችና አባላት የኮሪደር ልማቱን ለማፋጠን የወር ደመወዛቸውን 40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ድጋፉም ሠራዊቱ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ለልማት ሥራው ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር የወገን አለኝታነቱን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። የዕዙ አመራሮችና አባላት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኃይለዓብ ወንድሙ፣ ድጋፉ አሁን ላይ 43 በመቶ የደረሰውን የኮሪደር ልማት ፈጥኖ በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ለማብቃት ያስችላል ብለዋል። 9. ኢትዮጵያን በመገንባት ረገድ የወጣቱ ሚና ወጣቱ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁለንተናዊ ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ያሳሰቡትም በዚሁ ሳምንት ነበር። ከንቲባው ይህን ያሳሰቡት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ27ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ በድሬዳዋ በተከበረው ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን ላይ ተገኝተው ነው። በመልእክታቸውም ወጣቶች የተሻለች ሀገርን ለመገንባትና ለመረከብ እያደረጉት ያለው ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት አበረታች ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች በተለይም የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸውን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሀገር ተረካቢ የሆነውን ትውልድ ወደ ላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንደሚያሸጋግርም በመድረኩ ተገልጿል። 10. ዲጂታላይዜሽንን ለሙስና መከላከል የመደመር መንግሥት የፈጠራቸውን መልካም እድሎች በመጠቀም ለሀገር ልማት በጋራ መትጋትና ልሹ አሰራሮችን መዋጋት እንደሚገባ የተገለጸው በተያዘው ሳምንት ነው። የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ማጠቃለያ መድረክ "የፀረ-ሙስና ትግል ትናንት፣ ዛሬ እና ነገ" በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፤ በሙስና ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ መከላከልን፣ ምርመራንና ክስን በአንድ ተቋም በማድረግ ይሰራ እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም እንቅስቃሴው ህዝብን የትግሉ ባለቤት ያላደረገ፣ የሙስና መከላከል ስራን የረሳ እና ለትውልድ የስነ-ምግባር ግንባታ ቦታ የማይሰጥ ነበር ብለዋል። በሁለተኛው ምዕራፍ፣ ከሚሊኒየም መባቻ ጀምሮ ለውጡ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ የነበረው ወቅት በልማታዊ መንግሥት ስም ከፍተኛ ጣልቃገብነት የተካሄደበት እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋበት እንደነበር አንስተዋል። በዚህም ምክንያት የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ ሜጋ የመንግሥት ፕሮጀክቶች በሙስና እና በሌብነት ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው እንደነበር አስታውሰዋል። በሦስተኛው ምዕራፍ፣ ከሀገራዊ ለውጡ መባቻ ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ ከሙስና ትግል አኳያ መሰረታዊ ለውጥ ተደርጓል ብለዋል። በኮሚሽኑ ላይ ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል ዋነኛው የሕግ ሪፎርም መሆኑን አንስተው፤ ሙስናን በአንድ ተቋም ብቻ መታገል ስለማይቻል ሁሉም የመንግሥት ተቋማት የትግሉ ባለቤት እንዲሆኑ መደረጉን አስታውቀዋል። በተለይም የዲጂታላይዜሽንን መልካም እድሎች በመጠቀም አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነፃ እና አካታች በሆነ መንገድ ማቅረብ መቻሉና መሰረታዊ የእሳቤ ለውጥ ማምጣቱ ለፀረ-ሙስና ትግሉ ጠንካራ መሰረት እየጣለ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። 11. ኢዜአ በበጎ ፈቃድ ተግባር ላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ባደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደሰታቸውን በባህር ዳር ከተማ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችና ወላጆች መግለጻቸው የተዘገበውም በሳምንቱ ነበር። በወቅቱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ በቀለ፤ ኢዜአ ከመረጃ ተደራሽነት ባሻገር በማህበራዊ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት በስፋት እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸዋል። ኢዜአ የትምህርት ቤቶች ድጋፍ ላለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት በተከታታይ ሲያከናውን መቆየቱን አንስተው፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና በመሰል በጎ ተግባራት ተሳትፎውን አጠናክሮ መቀጠሉንም አክለዋል። በበባሕር ዳር ከተማ የአረንጓዴ አሻራን ከማኖር ባለፈ ኢዜአ ለ357 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል። የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አስራቴ ሙጨ በበኩላቸው፤ የኢዜአ አርዓያነት ያለው ተግባር በሌሎችም ዘንድ መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸው፤ ለተደረገው መልካም ተግባር ሁሉ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችና ወላጆች ኢዜአ ባደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው ለተደረገውም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ ከትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ በባህርዳር የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ቤት የሕንፃ ግንባታን አስጀምሯል። የሚገነባው የመማሪያ ክፍል ለታዳጊ ተማሪዎች ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል ሲሉ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ የገለጹትም በዚህ ወቅት ነው። የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ምንይችል ዓለማየሁ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሀገር ብሔራዊ ጥቅም፣ በገጽታ ግንባታ ሥራዎች እንዲሁም የጋራና አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።ተቋሙ ከሀገራዊ ተልዕኮው ባሻገር በማኅበራዊ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይም ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። ኢዜአ በባሕር ዳር ከተማ ምስራቀ ፀሐይ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቅድመ መደበኛ ትምህርት አስተባባሪ መምህርት አያል እምቢያለ፤ በአሁኑ ወቅት በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 150 ተማሪዎች እንደሚማሩ አስታውሰዋል። አዲሱ የመማሪያ ሕንፃ ግንባታ ይህንን የተማሪዎች የክፍል ጥምርታ በማስተካከል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል። ከዚሁ መርሃ ግብር በተጓዳኝም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን ምክንያት በማድረግም ከወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ-የቀይ ባሕር ደህንነትና የቀጣናዊ መረጋጋት ዋስትና!
Aug 23, 2026 135
ኢትዮጵያ-የቀይ ባሕር ደህንነትና የቀጣናዊ መረጋጋት ዋስትና! የቀይ ባሕር ቀጣና በዓለም አቀፍ የንግድ ዝውውር፣ በጂኦፖለቲካዊ ትስስር እና በባሕር ላይ ደህንነት ረገድ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ቦታ የሚይዝ ቀጣና ነው።ሆኖም በአሁኑ ወቅት አካባቢው የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች መራኮቻ፣የባሕር ላይ ወንበዴነት፣ የሕገ-ወጥ ንግድና የሽብር ስጋቶች የተጋረጡበት በመሆኑ፣ዘላቂ ሰላምና ደህንነቱን ለማረጋገጥ ጠንካራና አስተማማኝ አቅም ያለው ቀጣናዊ አጋር ያስፈልገዋል።ኢትዮጵያ በ130 ሚሊዮን ሕዝቧ፣ በገነባችው ግዙፍ ኢኮኖሚ፣በጠንካራ የመከላከያና የባሕር ኃይል አቅሟ እንዲሁም ቅድሚያ ለጎረቤት በሚለው የመደመር ዲፕሎማሲያዊ መርህዋ የቀይ ባሕርና የመላው ቀጣናው ደህንነት ዋስትና ሆና ወጥታለች። ኢትዮጵያ ከራሷ ባለፈ ሀገራት ግጭት ሲያጋጥማቸው፣ለችግር ሲጋለጡ ቀድማ የምትደርስ፣ ሰላምን በማስከበርና መረጋጋትን በመፍጠር በጽኑ መሠረት እንዲቀጥሉ በማስቻል የምትታወቅ ሀገር ናት።በ1950ዎቹ የኮሪያ ጦርነት ወቅት የተባበሩት መንግሥታትን ጥሪ በመቀበል ከ3 ሺህ 500 በላይ ወታደሮቿን በመላክ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የፈጸመችው ገድል የቃኘው ሻለቃ በጦር ሜዳ ላይ ያሳየው ጀግንነትና የከፈለው መስዋዕትነት እስከ ዛሬ በዓለምና በደቡብ ኮሪያ ሕዝብ ዘንድ በከፍተኛ አክብሮት ይታወሳል። ይህ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ኢትዮጵያ አፍሪካን ጭምር ያኮራችበት ነበር። ከዚያ በኋላም በኮንጎ፣በሩዋንዳ፣ በላይቤሪያ፣ በቡሩንዲ፣ በዳርፉር፣ በአብዬ እና በደቡብ ሱዳን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደር የለሽ ሀገር ያደርጋታል። በሶማሊያ ደግሞ ኢትዮጵያ የደም ዋጋ ከፍላ ሀገሪቱን በአሸባሪዎች ከመበታተንና ከመፍረስ ታድጋለች። የአልሸባብን ስጋት በመግታትና የሶማሊያን መንግሥት በመደገፍ ለቀጣናው ደህንነት የማይተካ ሚና ተጫውታለች። ዛሬም በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዋነኛዋ ሀገር ሆና ቀጥላለች።ይህ የካበተ ልምድ ኢትዮጵያን የቀጣናው የደህንነት ዋስትና እንድትሆን አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር እሳቤያቸው እንዳመላከቱት፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት ከሁሉም የውጭ ግንኙነቶች ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው። መደመር ከአጎራባች ሀገራት ጋር የምናደርገው ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅምን በአብዛኛው በጋራ ጥቅም ላይ ተመሥርቶ የሚመራ መሆን ይኖርበታል የሚል የጸና አቋም ያራምዳል። ዕጣ ፈንታችን የተሳሰረ ስለሆነ የጋራ ጥቅሞቻችንን መሠረት ያደረገ ትብብርና መተጋገዝ ያስፈልገናል የሚለው መርህም ኢትዮጵያ አሁን እየተራመደችበት ያለው የገቢር ነበብ ዲፕሎማሲ መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ በመደመር እያንዳንዱ የልማት እርምጃዋ፣ ቀጣናዊ መሻቷ ጎረቤቶቿን የሚያግዝና ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ጎረቤቶቿ ለችግር በተዳረጉ ጊዜም ቀድማ ደራሽ ናት። የሰላማቸው አምባ፣ የሀዘናቸው አጽናኝ ናት። ለአብነትም ሱዳን ከባድ ቀውስ ውስጥ በገባች ጊዜ 15 ሚሊዮን ዶላር በመደገፍ የችግር ጊዜ የአብሮነት መርሗን በተግባር አሳይታለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞችን በሯን ከፍታ ተቀብላ በማስጠለል ሰብዓዊ ኃላፊነቷን እየተወጣች ነው።ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ የጎረቤቶቿ ሕመም የሚያማት፣ እንደ ዋርካ ሆና የምታሳርፍ፣ ለጋራ ጥቅም ቀድማ የምትሰለፍ መሆኗን በግልጽ ያሳያል። ኢትዮጵያ ወንዞቿና ጅረቶቿ የቀጣናውን ሀገራት የሚያለሙ፣ ለም አፈሯ ምግብ የሆናቸው ሀገር መሆኗም የማይታበል ሐቅ ነው። የመደመር መንግሥት ይህንን ተፈጥሯዊ ሚዛን በእሴት የጨመረ የትብብር ድልድይ አጽንቷል። በዓባይ ወንዝ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በመገንባት የቀጣናው የብርሃን ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል። ግድቡ ለሱዳን፣ ለጅቡቲና ለኬንያ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር የጋራ ልማትን እውን እያደረገ ነው። ኢትዮጵያ ሌሎች የኃይል ማመንጫዎችን በመገደብ የቀጣናውን የኃይል ዋስትና የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኝነቷን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። ይህ በመደመር መንግሥት የሚተገበር ራዕይ ኢትዮጵያ የቀጣናው የጋራ የኢነርጂ ደህንነት ምሰሶ መሆኗን ያረጋግጣል። የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የምግብ ሉዓላዊነትና የቀጣናው ተስፋ የመደመር መንግሥት በተከተለው የጠራ እሳቤ ኢትዮጵያ ግዙፍ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው። ይህም ትሩፋቱ ለቀጣናው ሀገራት ጭምር እየተትረፈረፈ ነው። በመሠረተ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪና በግብርና ዘርፍ የተከናወኑት ስኬቶች ሀገሪቱ የምግብ ዋስትናን በቀጣና ደረጃ ለማረጋገጥ ምሳሌ አድርጓታል። የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በጀመረችው የስንዴ ልማት ኢኒሼቲቭ እመርታዊ ስኬት አስመዝግባለች። ለዓመታት በድርቅና በሌሎች ችግሮች የሚያጋጥማትን ሰብዓዊ ድጋፍ በእርዳታ ስትሸፍን የነበረችውና ለፍጆታ የሚሆን ስንዴንም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት ስታስገባ የቆየችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ላይ በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ስንዴን በበጋ መስኖና በክረምት በማልማት በዓመት 33 ሚሊዮን ቶን ስንዴ የምታመርት ሀገር ሆናለች። በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር፣ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ በራሷ ምርት የተካች ሀገር፣ ለሌሎች ጎረቤት ሀገራት ስንዴ የምትልክ ሀገር በመሆንም እየተጠቀሰች ነው። የምግብ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ ጉዞዋ በመስኖ የሚለሙ መሬቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በማስፋፋት፣ የክላስተር እርሻን በማጠናከር ኢትዮጵያ ከተረጂነት ራሷን ወደመቻል ተሸጋግራለች። ይህ የኢትዮጵያ ስኬት ለቀጣናው የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ተምሳሌት ሆኗል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ድርቅን መቋቋም የሚችል የግብርና ሥርዓት በመገንባትና በረሃዎቿን በማልማት ምርትና ምርታማነትን አሳድጋለች። በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ ተጋላጭ ለሆነው ቀጣና ተግባራዊ ምሳሌን በአረንጓዴ አሻራ አሳይታለች። ባለፉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ሀገርን አረንጓዴ አልብሳለች። አረንጓዴ አሻራዋ ድንበር ተሻግሮ የቀጣናው የተስፋ ምንጭም ሆኗል። የቀይ ባሕር ባለቤትነት ታሪካዊ መብትና የቀጣናው ደህንነት ኢትዮጵያ ለሺህ ዓመታት ቀይ ባሕርን ተፈጥሯዊ ወሰኗ በማድረግ የአዱሊስ፣ የምጽዋና የአሰብ ወደቦችን ስታስተዳድርና የንግድ ዝውውሩን ስታስጠብቅ የቆየች ሀገር ናት። በታሪካዊ አጋጣሚዎች ምክንያት ከባሕር ተገልላ የቆየች ቢሆንም፣ ለ130 ሚሊዮን ሕዝቧ፣ ለግዙፍ ኢኮኖሚዋ እና ለቀጣናው ደህንነት ሲባል የባሕር በር ማግኘት የህልውና ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ዳግም በጥንካሬ በማደራጀት ስትራቴጂካዊ እርምጃ ወስዳለች። ይህ ዝግጁነት የቀይ ባሕርን የንግድ መስመር ከባሕር ወንበዴዎች ለመጠበቅ፣ የሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውርን እንዲሁም የሽብር እንቅስቃሴዎችን ከሥር ለማምከን የሚረዳ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷን በሰላማዊ መንገድ፣ በዲፕሎማሲና በጋራ ጥቅም መርህ ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የመላው ቀጣናው አሸናፊነት ማረጋገጫ ይሆናል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም፣ ልማትና መረጋጋት ቀዳሚ ሚናዋን ስታበረክት የቆየች የምስራቅ አፍሪካ ምሰሶ ናት።የኢትዮጵያ አቅምና ዝግጁነት ለቀይ ባሕር ቀጣና ደህንነት ዋስትና የሚሰጥ እንጂ ማንንም ሀገር የሚጎዳ አይደለም። በጋራ ጥቅም እና በቅድሚያ ለጎረቤት መርህ የሚሳካው የኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር መመለስ ለቀጣናው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሎጂስቲክስ ቅልጥፍና እና ለጋራ ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ድርሻ ይጫወታል። ዛሬም በመደመር እሳቤ፣ በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በጠንካራ የመከላከያ ኃይልና በቅድሚያ ለጎረቤት በሚሰጥ ጠንካራ ዲፕሎማሲ የቀጣናውን የተሻለ ነገ እየገነባች ነው። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሳየችውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ የቀይ ባህር ባለቤትነት መብቷን በማሳካትም ትደግመዋለች። የልማት ተስፋና የቀጣናው የደህንነት ዋስትናነቷን በገቢር ነበብነት ታረጋግጣለች።
ከህዳሴ ግድብ እስከ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ - የኢትዮጵያ አህጉራዊ የመሰረተ ልማት መሪነት
Aug 21, 2026 797
(በሙሴ መለሰ) መሰረተ ልማት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕዘን ከሆኑ ቁልፍ ዘርፎች መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢትዮጵያ የነገ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግና የዜጎቿን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተፋጠነ መልኩ እየተገበረቻቸው የሚገኙት ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ቁልፍ ሚና አላቸው ። በመንገድ፣ በባቡር፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች ግንባታዎች ላይ እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የሚመጥን የኢኮኖሚ እድገት እና የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር ረገድ ያላቸው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም። ግዙፉ ፕሮጀክቶቿ መካከልም በጳጉሜን ወር 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የኢነርጂ ትስስር ውጥን ትልቅ የምስራች ሆኖ መጥቷል። የጎረቤት ሀገራት ከግድቡ የሚያገኙት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግርም በአጽንኦት ያረጋገጡት የህዳሴ ግድብ የአፍሪካ የራስን የመቻል ምልክት እና የኢትዮጵያን አይበገሬነት ተምሳሌትነት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት የተለያዩ ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እንደሚጀመር ይፋ አድርገዋል። የኒውክሌር ኃይል ማበልጸጊያ፣ የጋዝ ፋብሪካ ማስመረቅ፣ የነዳጅ ማጣሪያ እውን ማድረግ፣ በአፍሪካ ግዙፉ አየር ማረፊያ የሆነውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መጀመር፣ ሁለተኛውን የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች በመላው ሀገሪቱ ማስጀመር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረጉ ፕሮጀክቶች/የጉባ ብስራቶች/ ናቸው። በሶማሌ ክልል የጋዝ ፋብሪካ የተመረቀ ሲሆን፣ በአፍሪካ ታሪክ በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛል። ይህ ግዙፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የሀገሪቱን የሎጂስቲክስና የቱሪዝም አቅም ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሀገሪቱን የግብርና ምርታማነት በዘላቂነት ለመደገፍ ወሳኝ የሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ በየክልሎቹ ካሉ የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ ይገኛል። በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታም ለኢነርጂ አቅርቦት እድገት የበኩሉን ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢነርጂና የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥነዋል። እነዚህ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሀገሪቱ በቅርቡ ከጀመረችው አጠቃላይ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የገበያ መር ሥርዓት ጋር የተቆራኙ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። የሀገር ውስጥ ምርታማነትንና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ከመሰረቱ የሚያሻሽሉ ከመሆናቸውም በላይ፣ ሀገሪቱ በውጭ ዕርዳታና ብድር ላይ ከመደገፍ ወጥታ በሀገር ውስጥ እቅድና አቅም ላይ ተመስርታ የራሷን ዕድል የምትወስን አይበገሬነቷን በተግባር ያሳዩ የኩራት መገለጫዎች ናቸው። መንግሥት በነዳጅ፣ በጋዝ፣ በማዳበሪያ እና በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ላይ የጀመራቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል የነበረውን የመንግሥትን ብቻ ፋይናንስ ጥገኝነት በመቀነስ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የግል ባለሀብቶችን (Private Sector) በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳትፉ አዳዲስ የአጋርነት ሞዴሎችን የፈጠሩ ናቸው። የተቀናጁ መሰረተ ልማቶች ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር በማላቅ ቀጣናዊ ትብብርን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ትስስርና በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቶች ውስጥ ያላትን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉት አያጠራጥርም። በመሆኑም እነዚህን ስትራቴጂካዊ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከተጀመሩት የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር መተሳሰር፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌትና የኢኮኖሚ ማዕከል አድርጎ ለመገንባት ለተቀመጠው የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ራዕይ መሳካት አስተማማኝ ዋስትና ተደርገው ይወሰዳሉ። የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያዊያንን የእድገት መሻት ለማሳካት የሚያከናውነው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ ሁሉም ዜጋ እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገጽ 221 ላይ እንዳመለከቱት አይበገሬነት አንድ አካል ለብቻው የሚወጣው ጉዳይ አይደለም ። ከብዙዎች ጋር ተደምረን የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተግባብተን በመደጋገፍና በመተባበር የምንወጣው ጉዳይ ነው።
የግብጽ እኩይ ሴራ የማይገታው የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መብት
Aug 19, 2026 871
ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች የምትገኘው እና የቀጣናው የጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋት ዋና መሠረት ነች። የኢትዮጵያ፣ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ የፖለቲካ ፍላጎት ሳይሆን ሀገራዊ ሕልውናንና ደህንነትን የማረጋገጥ፣ የልማትና ብልጽግናን ዕውን የማድረግ የትውልድ ጥያቄ ነው። ትልቅ አቅም ያላት ኢትዮጵያ በመልክዐ-ምድራዊ እስር ውስጥ እንድትቀር የሚደረገው ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ፍትሕን የሚቃረን አካሄድን ለማረም ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት የነበራት የባህር በር ባለቤትነት እና የማሪታይም መብት በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ እየሰራች ነው። ይህ የኢትዮጵያ ፍትሐዊና የማይቀረው የሕልውና ጥያቄ በዓለም አቀፉ የባሕር ሕግ ኮንቬንሽን (UNCLOS) የተረጋገጠ እና በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርሕ ላይ የተመሠረተ ቢሆንም፣ የግብጽ ፖሊሲ አውጪዎች ግን ይህንን የሕልውና ጥያቄ ለማክሸፍ የሴራ እና የከበባ ስትራቴጂያቸውን ለማስፈጸም እየሰሩ ይገኛሉ። የግብጽ ሴራ በዋናነት ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ለወደብ ኪራይ እንድታወጣ በማስገደድ፣ ለትምህርት፣ ለጤና እና ለልማት የሚወጣው ካፒታል እንዲሟጠጥ በማድረግ የሀገሪቱን የኢንዱስትሪያላይዜሽንና የልማት ዕድገት ለማቀጨጭ ያለመ የኢኮኖሚ ዘመቻ ነው። በተጨማሪም ግብጽ የቀይ ባሕርን ማሪታይም ቀጣና “የባሕር ዳርቻ ሀገራት ብቻ (Littoral States) ይዞታ" አድርጋ በመሳል፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊና ሕጋዊ የመጠቀም መብት በመካድ ከማንኛውም የቀይ ባሕር የደህንነትና የኢኮኖሚ ስብስብ እንድትገለል እየሰራች ትገኛለች። ግብጽ ከኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ጋር የምታደርጋቸው ወታደራዊ ስምምነቶች በሰሜንና በምሥራቅ ድንበሮች አካባቢ አዲስ የደህንነት ስጋት በመፍጠር፣ ኢትዮጵያ ሀብቷንና ትኩረቷን ወደ የብስ ጥበቃ እንድታዞርና ለባህር ኃይል ግንባታ የምታውለውን አቅም እንድታበታትን የታለመ የከበባ ስልትም ነው። በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የኢንቨስትመንት ተቋማት ዘንድ የምታደርገው የዲፕሎማሲ ጫና፣ ኢትዮጵያ ለወደብ እና ለትራንስፖርት ኮሪደሮች ልማት የሚሆን የውጭ ኢንቨስትመንት እንዳታገኝ እና የቀይ ባሕር አካባቢ የስጋት ቀጠና ተደርጎ እንዲቆጠር በማድረግ ኢንቨስተሮች እንዲሸሹ በማድረግ ላይ ናት። በጎረቤት ሀገራት ዘንድ የጥርጣሬ እና የስጋት ግንብ በመገንባት፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር የምታደርጋቸው ፍትሐዊና የጋራ ዕድገትን ያለሙ የወደብ ስምምነቶች የሉዓላዊነት መጣስ ተደርገው እንዲቆጠሩ የማስፈራራትና የሐሰት ትረካና ዘመቻ ታካሂዳለች። ግብጽ የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ አባል ሀገራት በኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ላይ አንድ ወጥ አቋም እንዳይዙ ለማድረግ ድርጅቶቹን የፖለቲካ ፍልሚያ መድረክ በማድረግ የቀጣናውን ተቋማዊ ትብብር የማደናቀፍ ተግባር እያከናወነች ይገኛል። የግብጽ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የረጅም ጊዜ ሕልውና እና የትውልድ ጥያቄ መሆኑ እየታወቀ ጠባብ የፖለቲካ አጀንዳ በማስመሰል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዝ የማድረግ ስራ ላይ ተጠምደዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና (AfCFTA) ውስጥ የምታደርገውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ፣ የወደብ ትራንዚት ወጪዋ ከፍተኛ ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ ምርቶቿ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነት ላይ ጫና ለመፍጠር ትሰራለች። የግብጽ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያን ለዘለቄታው የመልክዐ-ምድር እስረኛ አድርጎ በማስቀረት፣ በምሥራቅ አፍሪካ የሚኖራትን ጂኦ-ፖለቲካዊና የኢኮኖሚ የበላይነት መግታት ነው። ሆኖም የግብጽ ሴራ የኢትዮጵያን የልማት መንገድ ሊያስቆመው አይችልም። ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሕዝቦቿ የማይበገር ጽናትና ቁርጠኝነት እውን እንደሆነ ሁሉ፤ በቀይ ባህር ላይ ህጋዊና ፍትሃዊ መብትን የማረጋገጥ ጉዞም የቀጣናውን የታሪክ ሂደት የሚቀይር የማይቀለበስ ብሔራዊ የህልውና ጉዳይ ነው።
መደመር የደረመሠው የጠላት ካምፕና የባንዳዎች እሪታ
Aug 19, 2026 681
በምስራቅ አፍሪካና በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የካይሮ እጅ ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረጉ እኩይ ስትራቴጂዎችን በመተለም ይታወቃል። የዓባይ ወንዝ ዋነኛ ምንጭና የተፈጥሮ ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን ማዳከም፣ የውስጥ ግጭቶችን ማበረታት እና በቀይ ባሕር እንዲሁም በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ላይ ያላትን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ፍላጎት ማደናቀፍ የግብፅ የረጅም ጊዜ የውጭ ፖሊሲ መሠረት ሆኖ ቆይቷል። ግብፅ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በወታደራዊ ኃይል ኢትዮጵያን በግልጽ ወርራ ለመቆጣጠር ባደረገችው ሙከራ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 1875 በጉንደት እንዲሁም 1876 በጉራዕ ጦርነቶች በኢትዮጵያ አሳፋሪ ሽንፈት አስተናግዳለች ። ከዚህ የቀጥታ ወታደራዊ ሽንፈት በኋላ ካይሮ ኢትዮጵያን በግልጽ ጦርነት ማንበርከክ እንደማትችል ተረድታ ወደ ተዘዋዋሪ የውስጥ ሴራና የእጅ-አዙር ጦርነት ተሸጋግራለች። ካይሮ ኢትዮጵያ ጠንካራና የበለፀገች ሀገር ሆና ከተነሳች በዓባይ ውሃ ላይ ያላትን አጠቃላይ የበላይነት እንደምታጣ ስለሚሰማት፣ የሀገሪቱን እድገት የማደናቀፍና በጂኦፖለቲካው መስክ ወደብ አልባ አድርጎ የመዝጋት ስትራቴጂን ለዘመናት ስትከተል ኖራለች። ይህም የታሪክ እውነታ ከትላንት እስከ ዛሬ በስውርና በግልጽ የሴራ መረቦች ተሸርቦ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ሲፈታተን የኖረ መራራ እውነት ነው። የቡትሮስ ብትሮስ ጋሊ የዲፕሎማሲ ሽፋን እና ኢትዮጵያን ወደብ የማሳጣት ሴራ በታሪክ አጋጣሚዎች እንደምናየው፣ በግብፅ የፖለቲካ ልሂቃን የታቀዱ ሴራዎች በዓለም አቀፍ መድረኮች እንዴት ተግባራዊ እንደሆኑ አንደኛው ማሳያ የቀድሞው ግብፃዊ ዲፕሎማት ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ አካሄድ ነው። ቡትሮስ-ጋሊ በ1970ዎቹ መጨረሻ በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራር በነበሩበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ በውስጥ ግጭት እንድትታመስና የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ ስጋት እንዳትሆን ከበስተጀርባ የዓመፅ ኃይሎችን የማጠናከር ስራ ሲሰሩ እንደነበር የሚታወቅ ሃቅ ነው። ቡትሮስ-ጋሊ በውሃ ፖለቲካ ረገድ በሰጡት የታወቀ ንግግራቸው “ቀጣዩ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና የሚካሄደው ጦርነት በፖለቲካ ምክንያት ሳይሆን በውሃ ምክንያት የሚደረግ ይሆናል” በማለት ለቀጣናው ያሰቡ መስለው የካይሮን የውሃ የበላይነት ስጋትና ፍላጎት በግልጽ አንጸባርቀው ነበር። ይህ ንግግራቸው ግብፅ የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት የመቆጣጠር ፍላጎቷንና ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ የልማት ፕሮጀክቶችን እንዳታካሂድ ለማድረግ የምታደርገው ሴራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኝ ዓላማ ያደረገ አደገኛ ንግግር ነው። በኋላም እ.ኤ.አ በ1993 ኤርትራን ከኢትዮጵያ በመገንጠል ሂደት ውስጥ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ የስድስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ ነበሩ። በወቅቱ 99 ነጥብ 8% የሚሆኑት ኤርትራዊያን በሕዝበ ውሳኔ ነጻ ሀገርንትን መርጠዋል በሚል ሕወሃትና ሻዕቢያ የሰሩት ድራማ ተቀባይነት አንዲያገኝ የተመድ ዋና ጸሐፊው ከፍተኛ ሴራ ሰርተዋል። ይህ የኤርትራ ህዝብን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በሻዕቢያ ባርነትና ግዞት እንዲማቅቅ ያደረገው የሕዝበ ውሳኔ ድራማ ላይ ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ የመሪ ተዋናይነትን ሚና ተጫውተዋል። በሂደቱም ዋነኛ ዓላማቸው የሆነውን ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በሯን እንድታጣ አድርገዋል። ይህም የካይሮ የረጅም ጊዜ “ኢትዮጵያን የመዝጋት” ስትራቴጂ አካል እንደነበር ግልጽ ነው። የካይሮ መጥረቢያ እና አሁናዊው የጥፋት መንገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት የመጥረቢያ ተምሳሌታዊ ማብራሪያ፣ ሕገ ወጡ ሕወሃትን እንደ መጥረቢያ ብረት፤ ሻዕቢያን ደግሞ እንደ መጥረቢያ ዛቢያ ያስቀመጡ ሲሆን፤ መጥረቢያውን የሚያዘውና የሚወረውረው ሌላ ሶስተኛ አካል መኖሩንም ተናግረዋል። እንደሚታወቀው መጥረቢያ አንድን ነገር የመቁረጥና የማፍረስ ስራ ለማከናወን የሶስት አካላት ቅንጅት ያስፈልገዋል፦ ወርዋሪው (እጁ)፣ ዛቢያው (መያዣው) እና ብረቱ (ቁራጩ)። በዚህ ተምሳሌት ውስጥ ወርዋሪው ወይም መጥረቢያውን ጨብጦ ስራ ላይ የሚያውለው አካል ግብፅ ናት። ወርዋሪው ሁልጊዜም ከበስተጀርባ ሆኖ ስትራቴጂ ይነድፋል፣ ፋይናንስና ወታደራዊ ድጋፍ ያቀርባል፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሽፋን ይሰጣል። በሌላ በኩል የመጥረቢያ ብረት ያለ ዛቢያው (መያዣው) ኃይል አግኝቶ ማረፍ አይችልም፤ ዛቢያውም ያለ ወርዋሪው እጅ መንቀሳቀስ አይችልም። በዚህ ሂደት ሻዕቢያ (እንደ ዛቢያ) በቀጣናው ውስጥ የካይሮን ፍላጎት ለማስፈጸም የመያዣነት ሚና ይጫወታል። ቀጣናውን ለማተራመስ በሞመከር የካይሮን ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ለማሳካት መንገድ ይከፍታል። ህገ-ወጡ ህወሓት ደግሞ እንደ መጥረቢያ ብረት በሀገር ውስጥ ሆኖ የሀገሪቱን መዋቅር፣ የህዝቦችን አንድነት እና ስትራቴጂካዊ ብሔራዊ ጥቅም ለመሸርሸር የሚሰራ ተላላኪ መሳሪያ ነው። በዚህ የሴራ ትስስር አሁን ላይ ኢትዮጵያ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ማደናቀፍ ዋነኛ ዓላማው አድርጎም እየሰራ ይገኛል። ግብፅ “የቀይ ባሕርና የኤደን ባሕረ-ሰላጤ የባሕር ወሰን ያላቸው ሀገራት ብቻ ናቸው በውሃው ላይ መወሰን ያለባቸው” የሚል መርህ በማንሳት፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላትንና በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ትልቁን ኢኮኖሚ (ኢትዮጵያን) ያገለለ ህገ-ወጥ ስብስብ ለመፍጠር እየሰራች ነው። በተጨማሪም በቅርቡ ከሶማሊያና ከሌሎች የአካባቢው ሀገራት ጋር የተደረጉ የውትድርናና የደህንነት ስምምነቶች፣ የሶማሊያን ሰላም ለማስጠበቅ ሳይሆን ቀጣናውን ለማተራመስና ወታደራዊ ስጋት ለመፍጠር የተቃኙ ናቸው። ይህ ሁሉ አካሄድ ዋነኛ ዓላማው ቀጣናውን የውክልና ጦርነት ማዕከል በማድረግና ኢትዮጵያ ወደ ባሕር እንዳትቀርብ ሆነ ተብሎ የተሰላ ሴራ ነው። ከቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ እስከ ዛሬው የቀይ ባሕር ሴራዎች ድረስ የተዘረጉት መረቦችም ይህንኑ እውነት ያሳያሉ። የካይሮ መጥረቢያዎችን ያዶለዶመው የመደመር መንግሥት ጥንካሬ ግብጽ እያከናወነችው ባለው አሁናዊ ሴራ ውስጥ የካይሮ ስትራቴጂስቶች የሳቱት ትልቅ እውነታ አለ። የግብጽ የሴራ መጥረቢያዎች ለመቁረጥ የሚሞክሩት በፈተናዎች የማትበገረውን እና እንደ ወርቅ በእሳት ውስጥ ተፈትና ያለፈችውን ኢትዮጵያን መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎችን አሸንፎ መውጣት እንግዳ የሆነባት ሀገር አይደለችም። ባለፉት ክፍለ ዘመናት በወረራ፣ በውስጥ አለመረጋጋትና በጂኦፖለቲካዊ ከበባዎች ውስጥ አልፋ የጸናች ሀገር ናት። ወርቅ በእሳት ውስጥ ሲያልፍ ቆሻሻው ተወግዶ ይበልጥ እንደሚበራ ሁሉ፣ ኢትዮጵያም በተጋረጡባት የህልውና ፈተናዎች ሁሉ አልፋ ይበልጥ እየጠነከረችና እየተደራጀች መምጣቷ የታሪክ እውነታ ነው። አሁን ባለንበት ዘመን ደግሞ ይህ ጥንካሬዋ ይበልጥ ጎልብቷል። የመደመር መንግሥት ቁልፍ ፍልስፍና እና እየተገበራቸው ያሉ እርምጃዎች የካይሮን የረጅም ጊዜ የእጅ አዙር ጦርነትና ሴራዎችን ከንቱ ያደረገ ነው። የመደመር መንግሥት የውጭ ጫናዎችንና ሴራዎችን ለመመከት የመጀመሪያው ምሽግ የውስጥ አቅምን ማጠናከር መሆኑን በመገንዘብ፣ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለፍፃሜ ማብቃትና ግዙፍ የግብርና፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን እውን አድርጓል። ይህም ግብፅ ኢትዮጵያን በልማት እንዳትበለፅግ ለማድረግ ያቀደችውን ስትራቴጂ ሙሉ በሙሉ አክሽፎታል። ካይሮ ኢትዮጵያን በጂኦፖለቲካዊ ከበባ ለማዳከምና በውስጥ ልዩነቶች ላይ እሳት በማንደድ ሀገሪቱን ለማፍረስ የነደፈችው የረጅም ጊዜ የሴራ መረብ፣ የመደመር መንግሥት ባስመዘገባቸው የልማትና የዲፕሎማሲ ድሎች ምክንያት ሙሉ በሙሉ ተደርምሷል። ይህ የጠላት ካምፕ መደርመስና የኪሳራ ስሌት ደግሞ በካይሮ ስትራቴጂስቶችና በውስጥ ተላላኪዎቻቸው (ባንዳዎች) ዘንድ ታላቅ ድንጋጤንና ተስፋ የመቁረጥ እሪታን ፈጥሯል። በመሆኑም የተበተነው የጠላት ካምፕና የተበሳጩት ባንዳዎች ብቸኛ አማራጭ አድርገው የያዙት በሳይበርና በሚዲያ ምህዳር የሃሰት መረጃዎችን ማንደድና የፕሮፓጋንዳ ማዕበል መፍጠር ቢሆንም፣ ይህም የተስፋ መቁረጥ ድምፅ ብክለት እንጂ የኢትዮጵያን የጽናት ጉዞ የሚያስተጓጉል አይሆንም። በሌላ በኩል ግብፅ “የቀይ ባሕር ሀገራት ጥምረት” በሚል ስም ቀጣናውን ለማተራመስና እርስ በርስ ጥርጣሬ ለመፍጠር የምታደርገውን የሴራ መረብ፣ የመደመር መንግሥት የጋራ እድገትና የጋራ ተጠቃሚነት መርህን በማስቀደም በዲፕሎማሲው መስክ እየመከተው ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊያን በሀገራዊ ምክክር የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በጋራ እንዲወስኑ በማድርግም የካይሮ ስትራቴጂስቶች በኢትዮጵያ የውስጥ ልዩነቶች ላይ እሳት በማንደድ ሀገሪቱን ለማፍረስ የጠነሰሱትን ሴራ ከንቱ አድርጎታል። በአጠቃላይ ታሪክ እንደሚነግረንና የወቅቱ እውነታ እንደሚመሰክረው፣ የግብፅ የሴራ መጥረቢያዎች በፈተናዎች እሳት ተፈትና ባላለፈች ደካማ ሀገር ላይ ያረፉ አይደሉም። ለመቁረጥ የሞከሩት በጽናት፣ በህዝቦቿ መስዋዕትነትና በፅኑ ታሪካዊ መሰረት ላይ የቆመችውን ኢትዮጵያን ነው። አሁን ላይ በመደመር መንግሥት መሪነት እየተገነባ ያለው የውስጥ አቅም፣ የልማት ስኬትና በራስ መተማመን የካይሮን የረጅም ጊዜ የከበባ ሴራ ሙሉ በሙሉ ወድቅ ማድረጉን ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ አሸንፎ ማለፍ የሰርክ ተግባሯ እንደመሆኑ መጠን፣ የዛሬውንም የጂኦፖለቲካ ውጥረትና የሴራ መረብ በጽናት አልፋ የቀጣናው የልማትና የሰላም ማዕከል ሆና መቀጠሏ የማይቀየር እውነት ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12170
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 21850
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14880
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20625
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 433
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 472
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።