ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ምቹ የሆነ የኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ምቹ የሆነ የኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች እንደምትገኝ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ የሆኑት ሚሪያም ሰዒድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ የሆኑት ሚሪያም ሰዒድ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ተበታትነው የነበሩ አሠራሮችን በዲጂታል ማንነት፣ በክፍያ እና በዳታ ልውውጥ የተቀናጁ የኢኮኖሚ መዋቅሮች ውስጥ በማስገባት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምቹ የሆነ የኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች መሆኑ አመልክተዋል።

ሀገሪቱ የመንግሥት አገልግሎቶችን በማገናኘት እንዲሁም የሃገር በቀል አቅምን በጋራ በማሳደግ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

አማካሪዋ አክለውም ኢትዮጵያ ይህንኑ የዲጂታል ሪፎርም ወደ ምርታማነት እየቀየረችው እንደምትገኝ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም