የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልፅግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በx ገጻቸው ባወጡት መልዕክት “ለወዳጄ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፓርላማ ምርጫ ላስመዘገቡት ድል የተሰማኝን ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለሁ" ብለዋል።
ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ፣ ዘርፈ ብዙ እና ስር የሰደደ ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጠዋለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት በደስታ እንደሚያስታውሱት ጠቅሰው፥ “ስትራቴጂካዊ አጋርነታችንን እና በሕዝቦቻችን መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አብረን በቅርበት እንሠራለን” ብለዋል።