ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ጥቂት ስለ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ
Feb 18, 2025 29
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አዲሱ የዓለም የፉክክር መድረክ እየሆነ መጥቷል። በልብወለድ ወይም በምናብ የሚታሰቡ ፈጠራዎች፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እውን እየሆኑም ይገኛሉ። እ.ኤ.አ ከ2012 ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት ያሳየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአሁኑ ጊዜ ከሰዎች የቀን ተቀን ሕይወት ጋር እየተዛመደ መጥቷል። በዕለት ተዕለት የሰዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያዎች እንመልከት። 👉ቻት ጂፒቲ (ChatGPT): ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ሀሳቦችን ለማመንጨት እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዳ ነው። 👉ግራመርሊይ (Grammarly) : በፅሁፍ ውስጥ የግራመር (ሰዋሰው) እንዲሁም የስርዓተ ነጥብ ስህተቶች የሚያርም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው። 👉ካንቫ (Canva) : የተለያዩ ግራፊክስ ስራዎችን በቀላሉ የሚሰራልን መጠቀሚያ ነው። 👉ኦተር ኤአይ (Otter.ai) : በድምፅ የምንናገራቸውን ወደ ፅሁፍ (text) የሚቀይር መጠቀሚያ ሲሆን በአብዛኛው በትምህርት ቤት ውስጥ ለሌክቸር ይጠቀሙታል:: 👉ክራዮን (Craiyon) : ፅሁፍ ብቻ በመፃፍ የምንፈልገውን ፎቶ ለመፍጠር የሚረዳ መጠቀሚያ ነው። 👉ሬፕሊካ (Replica) : የኤ አይ ቻት ቦት ሲሆን ስለ አዕምሮ ህክምና የሚያማክር እንዲሁም የግል የአዕምሮ ህክምና ምክር የሚሰጥ ነው። 👉ማይክሮሶፍት ቱ ዱ (Microsoft To Do): የቀን ሥራዎቻችንን ለማቀድ እና ለማደራጀት የሚያግዝ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው። 👉ሄሚንግዌይ ኤዲተር (Hemingway Editor): የኦንላይን መፃፊያ ሲሆን አፃፃፋችን የጠራ እና ሀሳብን የያዘ እንዲሆን የሚያግዝ መጠቀሚያ ነው። 👉ጎግል አሲስታንት (Google Assistant): የቨርቹዋል አጋዥ መጠቀሚያ ሲሆን የቤት ውስጥ ስማርት መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር፣ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም አስታዋሽ በመሆን ያገለግላል። 👉ጎግል ፎቶ (Google Photos): ፎቶዎችን ለማደራጀት እንዲሁም ለመፈለግ የሚረዳ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የጀመረው ሥራ ውጤታማ ነው - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Feb 18, 2025 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የኢትዮጵያውያን የጋራ ፕሮጀክትን ስኬታማ ለማድረግ የጀመራቸው ስራዎች ውጤታማ ናቸው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሶስት ዓመት የስራ አፈፃፀም በማድመጥ የሥራ ዘመኑንም ለአንድ ዓመት አራዝሟል። አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ያሉትን ችግሮች በመፍታት ከጥርጣሬ እና ሥጋት በመላቀቅ ሀገርን ለማጽናት ምክክሩ መልካም አጋጣሚ ነው። ለሀገርና ለትውልድ ቀጣይነት በቅንነትና በስክነት ተናጋግረን ለመውጪ ትውልድ ጥሩ ነገር ማስተላለፍ እንደሚገባ ያመለከቱት አፈ ጉባዔው፤ ኮሚሽኑ የጀመራቸው ተግባራት እጅግ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። የቀጣይ ጉዟችንን ለማሳካት ኮሚሽኑ የጀመረውን አስደናቂ ሥራ ማገዝ ይገባናል ሲሉም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህም የምክክር አጀንዳዎችን አስመልክቶ በተከናወኑ ተግባራት በ10 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የምክክር፤ የአጀንዳ ልየታ እና ለሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ስራዎች ተጠናቋል ብለዋል። በሀገራዊ ኮንፍረንስ ላይ የሚሳተፉ 1 ሺህ 105 የወረዳ ማህበረሰብን በመወከል የሚሳተፉ ተወካዮች መለየታቸውንና አጀንዳ መሰብሰቡን ተናግረዋል። በዚህም በድምጽ፣ በምስል እና በጽሁፍ የተለያዩ መረጃዎች መሰብሰብ መቻሉንና በዲጂታል መንገድ እንዲሰነዱ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል። ኮሚሽኑ 1ሺህ 234 ወረዳዎችን በመለየት አካታችና አሳታፊ የሆነ ምክክር ለማካሄድ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ሀገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሥራ እንዲሳካ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሚሽኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቁርጠኝነቱን አሳይቷል ብለዋል። የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቅ የፈቱ በሀገራዊ የምክክር መድረክ መሳተፋቸውንም ጠቁመዋል። በሚያቀራርቡ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መስራት ይኖርብናል ሲሉም የመንግስት ተጠሪው ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ ኮሚሽኑ የጀመራቸውን ታላላቅ ሀገራዊ ስራዎች እንዲያጠናቅቅ የሥራ ዘመኑን ለአንድ ዓመት አራዝሟል። የምክር ቤቱ አባላትም የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ምክክሩ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ኮሚሽኑ እስከ አሁን ያከናወነው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፤ የኮሚሽኑ የስራ ጊዜ ለአንድ አመት መረዛሙ ቀሪውን ስራ እንዲያጠናቀቅ ያግዘዋል ብለዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቀቀ
Feb 18, 2025 29
አሶሳ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ):- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የዳኞችን እና አስፈጻሚ አካላት ሹመቶችን በመስጠት ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። ምክር ቤቱ 18 የፍርድ ቤት ዳኞቾ ሹመት እንዲሁም የ2 ዳኞችን ስንብት ያፀደቀ ሲሆን የፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ረቂቅ አዋጆችንም መርምሮ አጽድቋል። በመጨረሻም በርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የቀረቡ ሹመቶችን አጽድቋል። በዚህም መሠረት፡- 1. ወይዘሮ እናትነሽ ማሩ የክልሉ ኦዲት ቢሮ ዋና ኦዲተር 2. አቶ ኢብራሂም ፍሌል ምክትል ዋና ኦዲተር 3. አቶ ከማል ሀሰን የክልሉ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር 4. አቶ ሙሀመድ አቡድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
ኢትዮጵያ በምግብ እራስን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ የስንዴ ምርት ላይ በትኩረት እየሰራች ነው
Feb 18, 2025 32
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ባለው ጉዞዋ የስንዴን ምርትን እንደ ቁልፍ ምሰሶ በመጠቀም በጀመረችው ስራ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለውን ጥረት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ምርታማነት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በዘለለ በረጅም ጊዜ ራስን ለመቻል ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰዱን አመልክቷል። የተጀመሩ ጥረቶች ኢትዮጵያ ከተረጂነት ተላቃ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ያላትን መሻትና ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጿል። የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የፖሊሲ ግብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ህዝቧቹ የህልውና ጉዳይ ነው ብሏል ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው። ኢትዮጵያ ስንዴን በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ባለው ጉዞዋ ውስጥ እንደ ቁልፍ ምሰሶ በመጠቀም በጀመረችው ስራ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏን ጠቅሷል። የግብርና ምርትን ለማሳደግ መንግስት በስፋት ከወሰደው አማራጭ አንዱና ዋናው ኢኒሼቲቭ የመስኖ ግብርና እንቅስቃሴን ማሳደግ በመሆኑ ውጤቱ በጉልህ እየታየ ነው። ለዘመናዊ ግብርና የሚያገለግሉ ማሽኖችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ከማድረግ ጀምሮ የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል። በዚህ መነሻነትም እ.አ.አ በ2022/23 የምርት ዘመን 151 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ስንዴ አምርታለች። ከዚህ ውስጥ 104 ሚሊዮን ኩንታል በመኸር እና 47 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በበጋ መስኖ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በቀጣዩ ዓመት እ.አ.አ በ2023/24 ደግሞ 230 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማምረቷንና በመኸር 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን እና 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ቶን ደግሞ በበጋ መስኖ በመሰብሰብ ከፍተኛ እመርታ ማሳየቷን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። ይህ አሃዝ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በግብርና ምርት ላይ የምታሳየው እመርታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየተሻሻለ መሆኑን ነው። በመስኖ ላይ የተመሰረተ ግብርና፣ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች፣ የግብርና ዘርፍ ማበረታቻዎች፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የግብርና ምርቶች ክላስተሮች እና አገልግሎቶች የግብርና ምርታማነትን ለመጨመር ትልቅ ሚና እንደተወጡ ገልጿል። የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግብርና ናሙና ቆጠራ፣ አስተዳደራዊ መረጃዎች ፣ የመስክ ጥናቶች እና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለረጅም ጊዜ ተአማኒነት ያላቸው ቁጥራዊ መረጃዎችን የማውጣት ልምድ እንዳለ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ በምግብ እራስን የመቻል አጀንዳ ከብሔራዊ የትኩረት አቅጣጫነት ባለፈ የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅም ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። አጀንዳው የአፍሪካ ሀገራት የግብርና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚችሉ የሚያሳይ መሆኑንም እንዲሁ። በምግብ ራስን መቻል የኢትዮጵያ ዋንኛው የስትራቴጂ ምሰሶ መሆኑና ውጥኑ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ አህጉራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጿል። ኢትዮጵያ አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል እያሳየች እንደምትገኝ እና ይህም መጪው ትውልድ የምግብ ዋስትናዋ የተረጋገጠ እና የበለጸገች አህጉር እንዲረከብ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አመልክቷል። ኢትዮጵያ በጀመረችው በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ ትልቅ ኩራት ይሰማታል ሲል ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አትቷል።
ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል - የደሴ ከተማ አስተዳደር
Feb 18, 2025 31
ደሴ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ አካላትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በደሴ ከተማ ህገ ወጥ ንግድ ሲያከናውኑ የተገኙ 82 የንግድ ድርጅቶች እንዲታሸጉ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል። በዘርፉ ጎላ ያለ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ 13 ግለሰቦችም ጉዳያቸው በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ገበያውን ለማረጋጋት በትኩረት እየሰራ ባለበት ወቅት የኑሮ ውድነት እንዲከሰት የሚሰሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን አንታገስም ብለዋል፡፡ በዚህም ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡ ህገወጦችን ሥርዓት ለማስያዝ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ትብበር ማጠናከር እንዳለበትም አመልክተዋል። በቂ ምርት ከተለያየ አካባቢ ወደ ከተማው እየገባ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው አረጋግጠዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በበኩላቸው፤ በቅንጅት በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር ያለ ምክንያት በምርት ላይ ዋጋ የጨመሩ፣ ምርት የደበቁ፣ ያለ ንግድ ፍቃድ ሲሰሩ የተገኙ 82 የንግድ ድርጅቶች ታሽገዋል ብለዋል፡፡ በተደረገ ክትትል እና ቁጥጥር በአምስት ሊትር ዘይት ላይ የ400 ብር እና በአንድ ኩንታል ስንዴ ዱቄት ላይ የ1ሺህ 600 ብር ጭማሪ የተደረገባቸው ምርቶችን መገኘታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። ተከማችቶ የተገኘው ምርትም በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዘርፉ ጎላ ያለ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ 13 ግለሰቦችም ጉዳያቸው በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር ለገበያ ማረጋጊያ ከተመደበው ገንዘብ በ20 ሚሊዮን ብሩ የተለያየ ምርት ተገዝቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑም ታውቋል፡፡
ፖለቲካ

የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አዲስ አበባ ገቡ
Feb 18, 2025 32
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪየንኮ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። አፈ ጉባዔዋ ማትቪየንኮና ልዑካቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አገኘሁ ተሻገር አቀባበል አድርገውላቸዋል። ልዑኩ ለሁለት ቀናት በሚኖረው የኢትዮጵያ ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይትና ጉብኝት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
የመጀመሪያው የኢትዮ-ቬትናም የጋራ የፖለቲካ ምክክር ተካሄደ
Feb 18, 2025 37
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና የሶሻሊስት ሪፐብሊክ ቬትናም የጋራ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በፖለቲካ ምክክሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የፈጠረ በመሆኑ የቬትናም ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ጥሩ አቅርበዋል። አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ከቬትናም ፈጣን የኢንዱስትሪ እድገት ልምዶችን ለመቅሰም ፍላጎት እንዳላትም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የቬትናም ልዑካን ቡድን መሪ የሶሻሊስት ሪፐብሊክ ቬትናም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ኑየን ሚን ሄን በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለውን ፈጣን የማኀበረ-ኢኮኖሚ ዕድገት በቅርብ እንደሚከታተሉ መናገራቸውም ተጠቅሷል። ምክትል ሚኒስትሯ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውም እንዲሁ። ሁለቱ ሀገራት ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባሻገር በባለብዙ ወገን መድረክ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር በፖለቲካ ምክክሩ ወቅት ተስማምተዋል። ኢትዮጵያ እና ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ቬትናም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት በቀጣይ ዓመት እንደሚያከብሩም ተገልጿል። ሁለተኛውን የፖለቲካ ምክክር በቀጣይ ዓመት ለማካሄድ ሚኒስትር ዴኤታዎቹ ተስማምተዋል።
የእንግሊዟ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ተቋማትን ጎበኙ
Feb 18, 2025 42
ሃዋሳ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ተቋማትን ጎበኙ። የእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሲዳማ ክልል ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ሀዋሳ ከተማ በተለይም የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ለአብነትም የሀዌላ ቱላ ጤና ኬላ በመገኘት የክትባት፣ የቅድመ ወሊድ የወሊድ እና የድህረ ወሊድ አገልግሎቶችን የተመለከቱ ሲሆን የንግሥት ፉራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንም ጎብኝተዋል። በሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችንም ተመልክተዋል። በትናንትናው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የእንግሊዟ አቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያና እንግሊዝ ኩባንያዎች የ600 ሚሊዮን ዶላር የወተትና የንግድ እርሻ ልማት ፕሮጀክት ስምምነት በአዲስ አበባ መፈረሙ ይታወቃል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራው እንዲሳካ መንግስት ቁርጠኛ ነው
Feb 18, 2025 42
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራው እንዲሳካ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ/ር) ገልፀዋል። ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ለረጅም ጊዜ የተከማቹ ቅሬታዎችንና ችግሮችን ይፈታል ተብሎ የታመነበትና በብዙ የሀገሪቱ ዜጎች ቅቡልነት ያገኘ እና ተስፋ የተጣለበት ተቋም መሆኑን አብራርተዋል። ኮሚሽኑ በገለልተኛነት ለሚያከናውናቸው ተግባራት መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቁርጠኝነቱን እያሳየ መሆኑንም አስረድተዋል። ለአብነትም በቅርቡ የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቅ የፈቱ ታጣቂ ሀይሎች በሀገራዊ የምክክር መድረክ መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል። በቀጣይም ከጠመንጃ ውጪ በጠረጴዛ ዙሪያ እነጋገራለሁ ለሚል ማንኛውም አካል መንግስት በሩን ክፍት እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ለስኬቱም ሁሉም አካል ከሚያራራርቁ ሀሳቦች ይልቅ በሚያቀራርቡ ጉዳዮች አተኩሮ መስራት እንዳለበት መግለጻቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል። የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የስራ ዘመኑ የሚጠናቀቀውን የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለአንድ አመት እንዲራዘም ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳቡን አቅርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የጀመራቸውን ታላላቅ ሀገራዊ ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ የስራ ዘመኑን በሶስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ለአንድ ዓመት አራዝሟል።
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል ሃላፊ ጋር ተወያዩ
Feb 18, 2025 45
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል ሃላፊ ሞኒካ ዛኔቴ ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም በስደተኞች ጉዳይ ያላቸውን የጋራ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ፖሊሲ ልማት ማዕከል የኢትዮጵያ ቢሮውን መከፈት በሚችልበት ሁኔታ መነጋገራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ነው - የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ(ዶ/ር)
Feb 18, 2025 61
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጌዜ ጀምሮ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ዛሬ በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ 3 ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጂጌ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጌዜ ጀምሮ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመቋቋም ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔ እንዲሁም ባህላዊ የግጭት አፈታት፣ የሽምግል እና በርካታ ሀገር በቀል እሴቶች ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ ይሁንና ላለፉት 60 ዓመታት ያክል ያልተፈቱና በአሁኑ ጊዜ ስር የሰደዱ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡት ችግሮቻችን ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት እንዳንገነባ፣ አሰባሳቢ ትርክት እንዳይኖረን በዚህም ድሃ እና ተመጽዋች እንድንሆን አድርገውናል ብለዋል። በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያ ከችግሮቿ ለመውጣት የተለያዩ እድሎች ተፈጥረው የነበረ ቢሆንም፤ በተለይ በፖለቲካ ፓርቲዎች እና በተለያዩ ምሁራን በተፈጠረ አለመግባባት እድሎችን መጠቀም ሳይቻል መቅረቱንም አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለእነዚህ የተወዘፉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑንና ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ማብራራታቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ኮሚሽኑ የምክክሩ ሂደት አሳታፊ እና አካታች እንዲሆን ያከናወናቸው ተግባራት አበረታች እንደሆነም የመንግስት ዋና ተጠሪው ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ሀገራዊ መግባባት እንዳይፈጠር ያደረጉት ሀሳቦች በሙሉ መካተታቸውን ማረጋገጥና ሁሉም የተለያዩ ሀሳቦች እንዲወከሉ ማድረግ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

ማህበራዊ
የካቲት 14 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ይሰጣል- የጤና ሚኒስቴር
Feb 18, 2025 28
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ ከየካቲት 14 ጀምሮ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) መከላከያ የነጻ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የልጅነት ልምሻ በሽታ(ፖሊዮ) ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ ያለው በመሆኑ በየጊዜው ክትባቱ ይሰጣል። ጤና ሚኒስቴር በፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዙሪያ ለሚዲያ ባለሙያዎች ዛሬ የግንዛቤ ማስጨባጫ መድረክ አካሂዷል። በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም ባለሙያ አቶ መስፍን ካሳዬ እንዳሉት የፊታችን የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሀገር አቀፍ የልጅነት ልምሻ ክትባት ዘመቻ ይካሄዳል። በክትባቱ በመጀመሪያ ዙር በ10 ክልሎች በማካሄድ ወደ 14 ሚሊየን የሚጠጉ ህፃናትን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል። የመጀመሪያው ዙር ከተጠናቀቀ ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ በቀሪ ክልሎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ዘመቻ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ክትባቱ ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤቶች፣ በህፃናት መዋያና በጤና ተቋማት በነፃ የሚሰጥ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። መገናኛ ብዙሀን የክትባት ዘመቻው በተሳካ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ሙያዊ ሀላፊነት እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጁ 104 የቀበሌ አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች ለህዝቡ የተሻለ አገልግሎት እየሰጡ ነው።
Feb 18, 2025 31
ነገሌ ቦረና ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጁ 104 የቀበሌ አስተዳደር ጽህፈት ቤቶች ለህዝቡ የተሻለ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በነገሌ ቦረና ከተማ በ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የህዝብ ተሳትፎ የተገነባ ባህላዊ ፍርድ ቤትና የቀበሌ አስተዳደር አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የምስራቅ ቦረና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ያሲን መሀመድ፤ በዞኑ 104 ቀበሌዎች በአዲስ መልክ መደራጀታቸውን አስረድተዋል፡፡ አደረጃጀቶቹ ቀደም ሲል ከወረዳ ወደ ዞን በተደጋጋሚ የሚመጡ ቅሬታዎችን በመፍታት የጊዜና የሀብት ብክነትን እየፈቱ ነው ብለዋል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ በሁሉም ቀበሌዎች ከ700 በላይ አመራሮችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች መመደባቸውን ጠቁመዋል፡፡ የቀበሌ አደረጃጀቶቹን ለማጠናከር በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች በህዝብ ተሳትፎ የቀበሌ ጽህፈት ቤት ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በነጌሌ ቦረና ከተማም በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ ባህላዊ ፍርድ ቤቶችና የቀበሌ መስተዳደር ጽህፈት ቤቶችም የዚሁ ጥረት አካል መሆናቸውን ተናግረዋል። ከነጌሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ መብራቱ ባህሩና ወይዘሮ ታየች ወርቅነህ፤ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ለማገኘት ከወረዳ እስከ ዞን ድረስ በሚደረግ ምልልስ ገንዘብና ጊዜ ሲባክን ነበር ብለዋል፡፡ አዲሱ አደረጃጀት የጊዜ፤ ቀጠሮና የስራ መንዛዛትን በማስቀረት ፈጣን አገልግሎት ለማግኘት እንደረዳቸው ተናግረዋል። ለባህል ፍርድ ቤቱ ግንባታ በሚችሉት አቅም ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው በቀጣይም ለጋራ ልማት ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል - የክልሉ ጤና ቢሮ
Feb 18, 2025 46
ጂንካ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነብዩ ቤዛ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከየካቲት 14 እስከ 17 ቀን 2017 ዓም ባሉት ቀናት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የመጀመሪያ ዙር የልጅነት ልምሻ ክትባት ቤት ለቤት በዘመቻ ይሰጣል። በዘመቻው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ1 ሚሊዮን በላይ ህፃናት እንደሚከተቡ ተናግረው ለዚህም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። ከዘመቻው ጎን ለጎን በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናት፣ ነፍሰ-ጡር እና አጥቢ እናቶችን በመለየት ህክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል። የልጅነት ልምሻ የህፃናትን ነርቭ በማወክ ለውስብስብ የጤና ችግሮች የሚዳርግ በሽታ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክተርና የክትባት ዘመቻው አስተባባሪ አስራት ቦሻ ናቸው።
በደብረ ማርቆስ ከተማ ተማሪዎችን በማካካሻ ትምህርት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ ነው
Feb 18, 2025 37
ደብረ ማርቆስ፤ የካቲት 11 /2017(ኢዜአ)፡- በደብረማርቆስ ከተማ ትምህርት ቤቶች በማጠናከሪያና በማካካሻ ክፍለ ጊዜ በማመቻቸት ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ሃላፊው አቶ ያምራል ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአካባቢው የነበረው ችግር በመማር ማስተማሩ ተግባር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል። ችግሩ እየተቃለለ አሁን ላይ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ የአመራር አባላትና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ባካሄዱት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በርካቶች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። ወደ ትምህርት ገበታቸው ለተመለሱ ተማሪዎች የማጠናከሪያና የማካካሽ የትምህርት ክፍለ ጊዜ በማመቻቸት ለማብቃት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንዳለባቸው አመልክተዋል። ወደ ትምህርት ገበታቸው የሚመለሱ ተማሪዎችን ቅዳሜና አሁድን ጨምሮ ባላቸው የትርፍ ሰዓት የማስተማሩን ስራ በማጠናከር የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ እቅድ መዘጋጀቱን አስረድተዋል። በከተማ አስተዳደሩ የአምበሽ የመጀመሪያደረጃ ትምህርት ቤት መምህር አበራ ዲንቃ በበኩላቸው፤ ህጻናትን በትምህርታቸው ለማብቃት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከተማሪ ወላጆች መካከል የወንቃ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሸጋው ጌጡ፤ ከመንግስት ጎን በመሆን የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ልጆቻቸው ተረጋግተው በመማር ውጤታማ እንዲሆኑ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ27ሺህ በላይ ተማሪዎችን በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ከአስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ በምግብ እራስን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ የስንዴ ምርት ላይ በትኩረት እየሰራች ነው
Feb 18, 2025 32
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ባለው ጉዞዋ የስንዴን ምርትን እንደ ቁልፍ ምሰሶ በመጠቀም በጀመረችው ስራ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ያለውን ጥረት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ምርታማነት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በዘለለ በረጅም ጊዜ ራስን ለመቻል ጠንካራ የፖሊሲ እርምጃዎችን መውሰዱን አመልክቷል። የተጀመሩ ጥረቶች ኢትዮጵያ ከተረጂነት ተላቃ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ያላትን መሻትና ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልጿል። የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የፖሊሲ ግብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ህዝቧቹ የህልውና ጉዳይ ነው ብሏል ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው። ኢትዮጵያ ስንዴን በምግብ ራሷን ለመቻል እያደረገች ባለው ጉዞዋ ውስጥ እንደ ቁልፍ ምሰሶ በመጠቀም በጀመረችው ስራ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏን ጠቅሷል። የግብርና ምርትን ለማሳደግ መንግስት በስፋት ከወሰደው አማራጭ አንዱና ዋናው ኢኒሼቲቭ የመስኖ ግብርና እንቅስቃሴን ማሳደግ በመሆኑ ውጤቱ በጉልህ እየታየ ነው። ለዘመናዊ ግብርና የሚያገለግሉ ማሽኖችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ከማድረግ ጀምሮ የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል። በዚህ መነሻነትም እ.አ.አ በ2022/23 የምርት ዘመን 151 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ስንዴ አምርታለች። ከዚህ ውስጥ 104 ሚሊዮን ኩንታል በመኸር እና 47 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በበጋ መስኖ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በቀጣዩ ዓመት እ.አ.አ በ2023/24 ደግሞ 230 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ማምረቷንና በመኸር 12 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን እና 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ቶን ደግሞ በበጋ መስኖ በመሰብሰብ ከፍተኛ እመርታ ማሳየቷን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። ይህ አሃዝ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በግብርና ምርት ላይ የምታሳየው እመርታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየተሻሻለ መሆኑን ነው። በመስኖ ላይ የተመሰረተ ግብርና፣ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች፣ የግብርና ዘርፍ ማበረታቻዎች፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የግብርና ምርቶች ክላስተሮች እና አገልግሎቶች የግብርና ምርታማነትን ለመጨመር ትልቅ ሚና እንደተወጡ ገልጿል። የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግብርና ናሙና ቆጠራ፣ አስተዳደራዊ መረጃዎች ፣ የመስክ ጥናቶች እና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለረጅም ጊዜ ተአማኒነት ያላቸው ቁጥራዊ መረጃዎችን የማውጣት ልምድ እንዳለ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ በምግብ እራስን የመቻል አጀንዳ ከብሔራዊ የትኩረት አቅጣጫነት ባለፈ የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አቅም ለመገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። አጀንዳው የአፍሪካ ሀገራት የግብርና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚችሉ የሚያሳይ መሆኑንም እንዲሁ። በምግብ ራስን መቻል የኢትዮጵያ ዋንኛው የስትራቴጂ ምሰሶ መሆኑና ውጥኑ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ አህጉራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጿል። ኢትዮጵያ አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል እያሳየች እንደምትገኝ እና ይህም መጪው ትውልድ የምግብ ዋስትናዋ የተረጋገጠ እና የበለጸገች አህጉር እንዲረከብ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አመልክቷል። ኢትዮጵያ በጀመረችው በምግብ ራስን የመቻል ጉዞ ትልቅ ኩራት ይሰማታል ሲል ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው አትቷል።
ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል - የደሴ ከተማ አስተዳደር
Feb 18, 2025 31
ደሴ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ አካላትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በደሴ ከተማ ህገ ወጥ ንግድ ሲያከናውኑ የተገኙ 82 የንግድ ድርጅቶች እንዲታሸጉ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል። በዘርፉ ጎላ ያለ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ 13 ግለሰቦችም ጉዳያቸው በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑንም ተገልጿል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ገበያውን ለማረጋጋት በትኩረት እየሰራ ባለበት ወቅት የኑሮ ውድነት እንዲከሰት የሚሰሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን አንታገስም ብለዋል፡፡ በዚህም ምርት በመደበቅ፣ ዋጋ በመጨመርና በሌሎችም ህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩትን በመለየት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡ ህገወጦችን ሥርዓት ለማስያዝ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በመደገፍ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ትብበር ማጠናከር እንዳለበትም አመልክተዋል። በቂ ምርት ከተለያየ አካባቢ ወደ ከተማው እየገባ መሆኑንም ምክትል ከንቲባው አረጋግጠዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በበኩላቸው፤ በቅንጅት በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር ያለ ምክንያት በምርት ላይ ዋጋ የጨመሩ፣ ምርት የደበቁ፣ ያለ ንግድ ፍቃድ ሲሰሩ የተገኙ 82 የንግድ ድርጅቶች ታሽገዋል ብለዋል፡፡ በተደረገ ክትትል እና ቁጥጥር በአምስት ሊትር ዘይት ላይ የ400 ብር እና በአንድ ኩንታል ስንዴ ዱቄት ላይ የ1ሺህ 600 ብር ጭማሪ የተደረገባቸው ምርቶችን መገኘታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። ተከማችቶ የተገኘው ምርትም በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዘርፉ ጎላ ያለ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል የተባሉ 13 ግለሰቦችም ጉዳያቸው በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር ለገበያ ማረጋጊያ ከተመደበው ገንዘብ በ20 ሚሊዮን ብሩ የተለያየ ምርት ተገዝቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ መሆኑም ታውቋል፡፡
በመተማ ከተማ የተገነባው የእንስሳት ማቆያን/ኳራንታይን/ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው - መምሪያው
Feb 18, 2025 29
ገንዳ ውሃ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በመተማ ከተማ የተገነባው የእንስሳት ማቆያን/ኳራንታይን/ ፈጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ። የእንስሳት ኮንትሮባንድ ንግድ መከላከል ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ በገንዳ ውሃ ከተማ ተካሂዷል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌትነት በሊሁን በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ዞኑ ጠረፋማ በመሆኑ በአብዛኛው ለኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ የተጋለጠ ነው። በአካባቢው ያለውን የእንስሳት እምቅ ሃብት በህገ ወጥ ነጋዴዎች አማካኝነት እየባከነ መሆኑን ተናግረዋል። ችግሩን ለማቃለል በ30 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን የእንስሳት ማቆያ ወደ ስራ ለማስገባት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር የተቀናጀ ጥረት እየደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃለፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ እንዳሉት፤ ዞኑ ለወጭ ንግድ ከሚመረተው ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ጥጥና ሌሎች ምርቶች ባሻገር ሰፊ የእንስሳት ሀብት ባለቤት ነው። በፀጋው ልክ በመስራት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ ለዚህም ህገወጥ የቁም እንስሳት ንግድን ለመከላከል የሚያግዝ ማቆያው(ኳራንታይኑ) ስራ እንዲጀምር ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማቆያው (ኳራንታይኑ) ስራ አስኪያጅ ፀጋዬ ብርቱዓለም(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ማቆያው(ኳራንታይኑ) የተሟላ የሰው ኃይልና ግንባታ ያለው በመሆኑ ወደ ስራ መግባት ለሚፈልጉ ላኪዎች የፈቃድ ማረጋገጫ መስጠት እንደሚቻል አብራርተዋል። የመተማ ዮሃንስ ጉምሩክ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አማረ ብርሌ በበኩላቸው፤ የቁም እንስሳት ኮንትሮባንድን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 318 የቁም እንስሳት ወደ ውጭ ለማሻገር ሲሞከር መያዙን ጠቅሰው፤ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር እንቅስቃሴውን ማስቆም ይቻላል ብለዋል። በውይይት መድረኩ የዞኑ፣ የከተማ አስተዳደር አመራር አባላት፣ የጉምሩክ ስራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ 23ኛ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ጉባኤ ተካሄደ
Feb 18, 2025 38
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ 23ኛው የፋይናንስ ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢንሼቲቭ ሊቀመንበርና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ጉባኤውን ሲከፍቱ ኢኒሼቲቩ ከአምስት አመታት በፊት እንደተመሰረተ ገልጸዋል። ኢኒሼቲቩ በቀጣናው ያሉትን ሀገራት በኢኮኖሚ ትብብር የሚያስተሳስሩ የልማት ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚረዳ የሚኒስትሮች ማዕቀፍ ነው ብለዋል። ኢኒሼቲቩ በልማት አጋሮች እንደሚደገፍም አቶ አህመድ ሺዴ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በጉባኤው የልማት አጋሮች ቃል ከገቡት 15 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሽ ያህሉ መገኘቱንና ኢንሼቲቩን ሲደግፉ ከነበሩ 3 የልማት አጋሮች ወደ አምስት ማደጋቸውም ተመልክቷል፡፡ የኢንሼቲቩ የፕሮጀክት አፈጻጸም በአመዛኙ መልካም ቢሆንም የአንድ አራተኛ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግን አጥጋቢ በሚባል ደረጃ ላይ ባለመሆኑ ይህንኑ ማሻሻልና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ በጉባዔው ላይ ተገልጿል፡፡ በስብሰባው የቀጣናውን የልማት ትስስር ለማሳደግና ኢኒሼቲቩን ለማጠናከር የአየር ንረት ለውጥ እቅዶችንና የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሚጠቅሙ አዳዲሰ የፋይናንስ አማራጮች የበለጠ በሚሰፉበት፣ ተጨማሪ ቀጣናዊ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ስለሚደረጉበት እንዲሁም ከአጋሮች የተጠናከረ ድጋፍ በሚፈለግባቸው ዘርፎች ላይ አቅጣጫ መቀመጡም ተገልጿል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ኢንሼቲቭ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን መናቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዓለም የንግድ ምሕዳር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ንግድ ምልክቶችና ብራንዶች የሕግ ጥበቃ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል- ባለስልጣኑ
Feb 18, 2025 44
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፦ በዓለም የንግድ ምሕዳር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የኢትዮጵያ የንግድ ምልክቶችና ብራንዶች የሕግ ጥበቃ ማግኘት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ገለፀ፡፡ ባለስልጣኑ በዘርፉ ላይ ግልጽነት ለመፍጠር ያለመ የብራንድ አምባሳደሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄዷል፡፡ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳሉ ሞሲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ባለስልጣኑ አዕምሯዊ ንብረት ስርዓትን የመምራት እና ዘርፉ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወት የማድረግ ስራ እያከናወነ ነው። የአዕምሯዊ ንብረት፣ የንግድ ምልክትና ብራንድ፣ የስነ ጥበብና ኪነ ጥበብ ውጤት ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የመመዝገብ፣ የማስተዋወቅ፣ ህጋዊ ጥበቃ እንዲያገኙ የማስቻል ስራ እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ጠንካራ ጥበቃ እንዲያገኙ የወጡ ሕጎች ተፈጻሚ በማድረግ አበረታች ስራዎች ቢከናወኑም ከሀገሪቷ ህዝብ ቁጥር፣ ከአገልግሎትና ምርት ብዛት አኳያ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ጨምሮ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ንግድ ምሕዳር ውስጥ እየገባች መሆኑን አስታውሰዋል። በዚህም በዓለም የንግድ ምሕዳር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ንግድ ምልክቶችና ብራንዶች የሕግ ጥበቃ ማግኘት እንደሚጠበቅ አንስተዋል። በባለስልጣኑ የንግድ ምልክት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ትዕግስት ቦጋለ በበኩላቸው፤ የንግድ ምልክቶች ልዩ፣ የማህበረሰቡን እሴት የማይነኩና የፈጠራ ሀሳብ የታከለበት መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ 33 ሺህ ገዳማ የንግድ ምልክቶችመኖራቸውን ጠቅሰው፤ 18 ሺህ የሚሆኑት የሀገር እንደሆኑ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ነው
Feb 18, 2025 33
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017(ኢዜአ)፡- በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ Commit to life በሚል መሪ ቃል በሞሮኮ ማራካሽ በተጀመረው 4ኛው የአለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያ ልዑካንን በመምራት እየተሳተፍን እንገኛለን ብለዋል። ኮንፍረንሱ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚቆይም አስታውቀዋል። ይህ ኮንፍረንስ በአለም ሀገራት በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ያሉ ቁልፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የትራፊክ አደጋዎችንና ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እንዲሁም ቃልኪዳኖችን ይበልጥ ለማጠናከር ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የጅማ ከተማን ሰማርት ሲቲ ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
Feb 18, 2025 53
ጅማ፣የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፡- የጅማ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግና አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የ"ሰማርት ሲቲ ፕሮጀክት" የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮ ቴሌኮምና በጅማ ከተማ አስተዳደር መካከል ነው። በትናንትናው እለት በጅማ ከተማ አምስተኛው ትውልድን ሞባይል ኔትወርክ (5G) ያስተዋወቀው ኢትዮ- ቴሌኮም ዛሬ ደግሞ ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ መስማማቱን ገልጿል። ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ ያሳልጣል፣ መረጃ አስተዳደርን ያቀላጥፋል፣ ደህንነትና ትራንስፖርትን ዘርፉን ለማሻሻልም ያግዛል ተብሏል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የጅማ ከተማን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ኩባንያው የሚጠበቅበትን ይወጣል ብለዋል። ኢትዮ-ቴሌኮም የተቀናጀ የቴሌኮምና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሰረተ ልማትን ለማቅረብ እንደሚሰራም አመልክተዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው ከተማዋን 'ስማርት ሲቲ' ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። ጅማ ከተማ የተሻለ መሰረተ ልማት ያላት፣ ሰላምና ደህንነቷ የተረጋገጠ ትሆን ዘንድ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀሟ ተገቢነት ያለው መሆኑንም እንሰተዋል።
በክልሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የማድረግ ስራዎች ተጀምረዋል
Feb 18, 2025 28
መቱ፤ የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የጤና አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ። የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ቦኮና ጉታ እንደተናገሩት፥ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። ከተጀመሩ ጥረቶች መካከል በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ብለዋል። በዚህ ዓመትም በክልሉ በአስር ሆስፒታሎችና በአምስት ጤና ጣቢያዎች ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ተደርጓል ነው ያሉት። በቀጣይም በክልሉ በሁሉም የጤና ተቋማት ከወረቀት ነጻ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ከወረቀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ከተጀመረባቸው ተቋማት መካከል የመቱ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ካርል ሆስፒታል አንዱ ነው። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሶላን በቀለ፤ በአሁኑ ወቅት በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው የሕክምና አገልግሎት ከወረቀት ነጻ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ለተገልጋዩ የተቀላጠፈ የሕክምና አገልግሎት መስጠት እያስቻለ ሲሆን ከዚህ በፊት ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችም መቀነሳቸውን ተናግረዋል። የመቱ ሆስፒታል ከወረቀት ነጻ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በጤና ሚኒስቴር አመራሮችና በክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮች ተጎብኝቷል።
ስፖርት
ስፖርት ለሀገር ገፅታ ግንባታ የሚጫወተውን ሚና የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ
Feb 13, 2025 109
ሀዋሳ ፤ የካቲት 6/2017(ኢዜአ)፡- ስፖርት ለሀገር ገፅታ ግንባታና ለአብሮነት እሴቶች መጎልበት የሚጫወተውን ሚና የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ። የሚኒስቴሩ የግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የሚገመግም የሁለት ቀናት መድረክ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል የዘርፉ ባለድርሻ ተቋማት ሃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው። ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ስፖርት ለሀገር ገፅታ ግንባታና ለአብሮነት እሴቶች መጎልበት የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ ለዘርፉ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጥቷል። ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርታዊ ውድድር መጀመራቸውም የአብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ ለማስቻል ጥረት መደረጉንም ጠቅሰዋል። ስፖርት ለሀገር ገፅታና ለህዝቦች አብሮነት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግም ቅንጅታዊ አሰራሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያላቸውን አቅም ለመጠቀም የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የኪነ ጥበብ ንቅናቄ መካሄዱን ጠቁመዋል፡፡ የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ በበኩላቸው፤ ክልሉ በርካታ ማህበራዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች ያሉበት መሆኑን ገልጸው፤ የ“አፊኒ” ሥርዓት እና ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ መሆን የቻለው የ"ፊቼ ጫምባላላ” የዘመን መለወጫ በዓልን ለአብነት ጠቅሰዋል። እነዚህን እሴቶች በማስተዋወቅ ለሠላምና ለአብሮነት የሚጫወቱትን ሚና ከፍ ለማድረግ መስራቱን እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል
Feb 10, 2025 144
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3 /2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድን ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወገኔ ገዛኸኝ፣ መሐመድ አበራ እና ሚሊዮን ሰለሞን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በ35 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። ከተከታዩ ሀድያ ሆሳዕና ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። መድን በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን በማስመዝገብ በሊጉ የመጀመሪያ ዙር በመሪነት አጠናቋል። በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ20 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ተጠናቋል። ሁለተኛው ዙር የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ስፖርትን ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል - ቋሚ ኮሚቴው
Feb 10, 2025 113
አርባ ምንጭ፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ስፖርትን ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ገለጹ። "ለሀገራችን ስፖርት ዕድገት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሚና ማላቅ" በሚል መሪ ሃሳብ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ እንደገለጹት፣ ለዘርፉ ውጤታማነት ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። በተለያዩ ስፖርቶች ብቁ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚና ሌሎች ባለድርሻዎች ጉልህ ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባም ገልጸዋል። የስፖርቱ ዘርፍ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ተገቢውን ሚና መጫወት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። ምክር ቤቱ በስፖርት ዘርፍ ያለው ስብራት እንዲጠገን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑንና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በሳይንሳዊ ስልጠና ታንጸው ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርጉ ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት አካዳሚዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ክለቦች ለታዳጊዎች ይበልጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸውም አመልክተዋል። በመድረኩ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው፣ በስፖርት ኢንዱስትሪው የሚፈለገውን የሰው ሃይል ለማፍራት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል። የስፖርት አካዳሚዎች የስፖርት ኢንዳስትሪን ያገናዘበ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለዘርፉ ዕድገት እንዲሰሩም አስገንዝበዋል። ተሰጥኦ ላላቸው ወጣቶችና ለስፖርት ሙያተኞች ሳይንሱን የተከተለና ወቅቱን ያገናዘበ ስልጠና መስጠት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። አቅምን አሟጦ በመጠቀም በሀገር፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ስፖርተኞችን ማፍራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ዘርፉን ለማሳደግ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አምበሳው እንየው ናቸው። አካዳሚው ከ2009 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ 531 ሠልጣኞችን በ10 የስፖርት አይነቶች አስተምሮ ማስመረቁን ገልጸዋል። ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ የፌዴራልና የክልል አመራር አባላት፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ቀንቶታል
Feb 10, 2025 133
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3 /2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ሀብታሙ እና እዮብ ገብረማርያም የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አንዷለም አስናቀ ለአርባምንጭ ከተማ ግቡን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። በ19ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
አካባቢ ጥበቃ
በትግራይ፣ አማራና በድሬዳዋ የተከናወኑ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራዎች መሬቶች እንዲያገግሙና ምርታማ እንዲሆኑ አስችሏል
Feb 18, 2025 132
መቀሌ፤ ባሕር ዳር፤ ድሬደዋ፤ የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፦ በትግራይና አማራ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር የተከናወኑ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራዎች የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙና የግብርና ምርታማነት እንዲጨመር እያገዙ መሆኑ ተገለፀ። የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን፣ የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ውሃ ሃብቶችን ከመጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባሻገር የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው። ከዚህ አኳያ ኢዜአ በትግራይና አማራ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን ቃኝቷል። በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሐውዜን ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል ወይዘሮ ኪዳን መረሳ የእስካሁን የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች መሬታቸው እንዲያገግም በማስቻል የተሻለ ምርት እንዲያገኙ ማስቻሉን አስችሎናል ይላሉ። አርሶ አደር ገብረአነንያ ገብረ ሕይወት በበኩላቸው የተፋሰስ ልማት ስራዎች በአካባቢው ያመጡትን ተጨባጭ ለውጥ ተከትሎ አሁን ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደ ባህል በየዓመቱ እየተከናወነ ስለመሆኑ ይገልጻሉ። በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አለምብርሀን ሀሪፈዮ እንዳሉት ዘንድሮ በክልሉ 62 ሺህ ሄክታርን በሚሸፍን መሬት ላይ ነፃ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተካሄደ ነው። በተመሳሳይ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምህረት፤ በክልሉ የተፋሰስ ልማት ስራዎች በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እንዲጨመር የራሱ አስተዋጽኦ እያደረገ ስለመሆኑ ገልጸዋል። በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራዎች በተከናወነባቸው ስፍራዎች አርሶ አደሮች በንብ ማነብና በሌሎች የግብርና ልማቶች እየተሳተፉ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዘንድሮውም ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በማሳተፍ ከ366 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በድሬደዋ የገጠር ቀበሌዎች እየተካሄደ የሚገኘው የተፋሰስ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኑረዲን አብደላ ገልጸዋል። የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራው ጎርፍ በመከላከልና አፈር ለምነቱን በመጠበቅ በግብርና ልማት ላይ ተጨባጭ ውጤት ማመጣቱን አረጋግጠዋል። በድሬዳዋ ዘንድሮ በ5 ሺህ ሄክታር ማሬት ላይ የተፋሰስ ልማት ስራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
ለፅዳት ቅድሚያ የሚሰጥ ትውልድ ከመገንባት አንፃር የተሰሩ ሰፋፊ ስራዎችን ባህል ማድረግ ይገባል - የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
Feb 17, 2025 50
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ ለፅዳት ቅድሚያ የሚሰጥ ትውልድ ከመገንባት አንፃር የተሰሩ ሰፋፊ ስራዎችን ባህል ማድረግ እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ የምክር ቤት አባል እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ገለጹ። ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫን በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም የአካባቢ ልማት ስራ የሁሉንም ዜጎች አስተዋፅኦ የሚፈልግ በመሆኑ ማህበረሰቡ ፅዱ ኢትዮጵያን ከማረጋገጥ አንፃር ቆሻሻን መፀየፍ ይገባዋል ነው ያሉት። በ2ኛው ጉባኤ ፓርቲያችን ትልቅ ትኩረት ከሰጠበት የአቋም ነጥብ ውስጥ አንዱ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ወደ ቋሚ ሕዝባዊ ባህልነት የማሸጋገር ትልም ነው ሲሉም ገልጸዋል። ቆሻሻን እንድንፀየፍ የሚያደርጉ ልማቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አንስተው ለፅዳት ቅድሚያ የሚሰጥ ትውልድ ከመገንባት አንፃር የተሰሩ ሰፋፊ ስራዎችን ባህል ማድረግ ይገባል ነው ያሉት። የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን በማስፋት ቆሻሻ በየቦታው መጣል የሚፀየፍ ትውልድ ማፍራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ህብረተሰቡ እንዲሁም ህፃናት ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንዲያውቁ የሚያደርግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። ብልፅግና የልማት ስራዎችን በመደመር እሳቤ እውን ለማድረግ እየተጋ መሆኑን ገልጸው ለትውልዱ እዳን ሳይሆን ምንዳን ለማውረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል። አክለውም የአረንጓዴ አሻራ በስፋት በመላው ሀገሪቱ ባህል እየሆነ በመምጣቱ በቀጣይ ክረምት የሚተከሉ እፅዋትን ከወዲሁ መዘጋጀት መጀመሩንም ገልፀዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ እያስከተለ ያለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ዘላቂነት ያለው መፍትሔ ላይ ማተኮር ይገባል-አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
Feb 16, 2025 88
አዲስ አበባ፤የካቲት 9/2017(ኢዜአ)፦የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ እያስከተለ ያለውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ዘላቂነት ያለው መፍትሔ ላይ ማተኮር ይገባል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ። ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የአፍሪካ አገራት የአየር ንብረት ለውጥ የመሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ በኮሚቴው አስተባባሪ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሰብሳቢነት ተካሂዷል። አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ አፍሪካ እና የተቀረው በማደግ ላይ ያለው የዓለም ክፍል የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለውን ለውጥ ለመቋቋም ልዩ ትኩረት ያሻቸዋል ነው ያሉት። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ አፋጣኝ መፍትሔ የሚያሻው ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ ግኝች ዘዴዎችን መከተል እንደሚገባም ጠቁመዋል። ከበለጸጉ አገራት ቃል በተገባው መሠረት በቂ የፋይናንስ ድጋፍ ሊያደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በአፍሪካ ሕብረት ለማካሄድ ዕቅድ እንዳላት ገልጸዋል። ጉባዔው ለአሕጉሪቱ ዘላቂ ብልጽግና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ረገድ ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው አምባሳደር ምስጋኑ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ልማት እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲመጣ ከኮሚቴው ጋር በትብብር መሥራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የተፋሰስ ልማት ስራ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው - ግብርና ሚኒስቴር
Feb 14, 2025 92
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2017(ኢዜአ)፡- ባለፉት አመታት በተከናወነው የተፋሰስ ልማት ስራ እንደ ሀገር ተጨባጭ ውጤት እየተገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በተያዘው አመት ህብረተሰቡን በንቃት ባሳተፈ መልኩ ከጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን እንደገለጹት በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ክስተቶች ምክንያት የሀገሪቱ መሬት ለጉዳት ተጋላጭ ነው፡፡ መንግስት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት የተፋሰስ ልማት ስራዎች በየግዜው በትኩረት እንዲከናወኑ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎ በተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በተሰሩ ስራዎች በኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚከሰተውን የአፈር መሸርሸር በከፍተኛ መጠን መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል። በ2017 ዓ.ም የበጋ ወቅት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በሁሉም በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ለማከናወን ወደ ተግባር መገባቱንም ተናግረዋል፡፡ የተፋሰስ ልማት ስራው በሀገር አቀፍ ደረጃ በጥር 2017 ዓ.ም የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ክልሎች ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጸዋል። አጠቃላይ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራዎቹ በአብዛኞቹ አካባቢዎች መጋቢት አጋማሽ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቅሰዋል። አቶ ፋኖሴ አክለውም የተፈጥሮ ሀብትን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና የማልማት ተግባር ለነገ የማይባል ጉዳይ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል። ሀገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ፀጋዎችን ለመጠበቅ በሚሰራው ስራ ህብረተሰቡ በተለያዩ አካባቢዎች በሚከናወኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የአፍሪካን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሻሻል አለባቸው
Feb 12, 2025 130
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የአፍሪካን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሻሻል እንዳለባቸው በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ። 46ኛው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እየተካሔደ ይገኛል። በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት፤ አፍሪካውያን የተፈጥሮ ሀብታቸውን በአግባቡ መጠቀም አልቻሉም ብለዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የምታሳድረው ተፅዕኖ ጥቂት ቢሆንም የጉዳቱ ገፈት ቀማሽ መሆኗን ገልጸዋል። በመሆኑም የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የአፍሪካን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ ሪፎርም መደረግ አለባቸው ብለዋል። የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት በመሰረታዊነት መቀየር እንዳለበትም ገልጸዋል። አፍሪካውያን አህጉራዊ ሀብታቸውን እሴት ጨምረው መጠቀም እንዲችሉ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በአህጉሪቱ ጥሬ ምርትን ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ በምርቶች ላይ እሴትን ጨምሮ የመላክ አቅምን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል። አፍሪካውያን ለደረሰባቸው ግፍና በደል ተገቢ የፍትሕ ካሳ ሊያገኙ እንደሚገባም ገልጸዋል። ይህ ችግር የዓለም የንግድ ስርዓትን በማዛባት የአፍሪካውያንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በእጅጉ የጎዳ መሆኑን ተናግረዋል። አፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላት አሉታዊ ተፅዕኖ ውስን ቢሆንም የጉዳቱ ሰለባ ከመሆን አልዳነችም ብለዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ አፍሪካን የአህጉራዊ ጥቅል ምርቷን አምስት በመቶ እንደሚያሳጣት በመጥቀስ፣ በዓለም ዙሪያ ለኢንቨስትመንት ከሚመደበው ሀብት የአፍሪካ ሁለት በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ይሄ የአፍሪካን ጥቅም የሚጎዳ ኢፍትሃዊነት በቃህ ሊባል ይገባል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት መሰረታዊ ሪፎርም ሊደረግባቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።
የቀድሞው ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
Jan 30, 2025 208
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017(ኢዜአ)፦ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በሙስና በመደለል ከግብፅ መንግስት ጉቦ የተቀበሉት አሜሪካዊው የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። በኒው ዮርክ በ12 ዳኞች የተሰየመው ችሎት የፍርድ ውሳኔውን ትናንት ማስተላለፉን የአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኤንቢሲ ዘግቧል። ችሎቱ ከዚህ ቀደም የ71 ዓመቱን የሕግ ባለሙያና ፖለቲከኛ በ16ቱም የሙስና ወንጀሎች ጥፋተኛ ብሏቸዋል። የአሜሪካ ፌደራል ዐቃቤ ሕጎች የቀድሞውን ሴናተር ጉቦ ተቀብለው የግብጽ ወኪል ሆኖ በመስራት፣ ፍትሕ እንዲዛባ በማድረግና የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወንጀል መክሰሳቸው ይታወቃል። ዐቃቤ ሕጉ ሜኔንዴዝ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ በነበሩበት ወቅት የግብጽን ፍላጎት በማንጸባረቅ፣ ለዚህም ከግብጽ መንግስት ገንዘብ ማግኘታቸው በሰነድና በሰው ማስረጃ አረጋግጧል። የቀድሞው ሴናተር በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ በኒው ጄርሲ በንግድ ስራ ላይ ከተሰማሩ 3 የግብጽ ሰዎች እጅ ወርቅ እና ጥሬ ገንዘብ ጉቦ ተቀብለዋል። ይህም ሴናተሩ ራሳቸውን ለግብጽ መንግሥት ወኪል አድርገው በመቆም ሰርተዋል የሚል ክስ ሲቀርብባቸው እንደነበረ ይታወቃል። በዚህም በዘረፋ፣ ጉቦ በመቀበል፣ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ በሴራ፣ ፍትህን በማደናቀፍና መሰል 16 ወንጀሎች ላይ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገልጿል። በ16 የሙስና ወንጀሎች ጥፋተኛ የተባሉት ሜኔንዴዝ የግብፅ መንግስት በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት የአሜሪካ መንግስት ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያገኝ ረድተዋል የሚል ክስ እንደቀረባበቸውም እንዲሁ። ሜኔንዴዝ የውጪ መንግስታትን ፍላጎት ለማስፈጸም ከተቀበሏቸው ስጦታዎች መካከል 100 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ወርቅና ቅንጡ መርሰዲስ መኪና የተጠቀሱ ሲሆን፣ በመኖሪያ ቤታቸውም 480 ሺህ ዶላር ጥሬ ገንዘብ በቤታቸው መገኘቱን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከዚህ ቀደም በስፋት ዘግበውታል። የቀድሞው ሴናተር ከግብጽ የንግድ ባለቤቶች ጋር የጥቅም ትስስር እንደነበራቸው ተጠቁሟል። በክሳቸው ላይ ከግብጽ በተጨማሪ ከሌሎች የውጭ መንግስታት ጉቦ መቀበላቸው በምርምራ እንደተረጋገጠም ተመላክቷል። እ.አ.አ በ2021 የ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤች አር 6600 ረቂቅ ሕግ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የሆነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2022’ ወይም ‘ኤስ.3199’ የተዘጋጀው በ70 ዓመቱ ፖለቲከኛና የሕግ ባለሙያ ቦብ ሜኔንዴዝ ዋና አርቃቂነት ነው። በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ደብዳቤ በመጻፍ፣ፊርማ በማሰባሰብና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት አድርገዋል። ሕጉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት የሚጎዳና ሉዓላዊነቷን የሚጥስ እንደነበር በተደጋጋሚ ጊዜ ሲገለጽ ቆይቷል። እነዚህ ሕጎች እንዲፀድቁ ግብጽ ግፊት ስታደርግ እንደነበር ይታወቃል።
አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ ማጤን አለባት - የአፍሪካ ህብረት
Jan 22, 2025 279
አዲስ አበባ፤ ጥር 14/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣት ውሳኔዋን እንድታጤነው ጠይቀዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸውም አሜሪካ ከድርጅቱ አባልነት ለመውጣት መፈለጓ እንዳሳዘናቸው ሙሳ ፋኪ ገልጸዋል። ውሳኔውን መለስ ብሎ በማጤን በአባልነቷ ትቀጥላለች የሚል ተስፋ እንዳላቸውም አስታውቀዋል። አሜሪካ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል(አፍሪካ ሲዲሲ) መስረታ ላይ ቀደምት እና ጠንካራ ደጋፊ ነበረች ሲሉም በመግለጫቸው አስታውሰዋል፡፡ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዓለም አቀፉን የህብረተሰብ ጤና ደህንነት እንደ አንድ የጋራ ጥቅም የማረጋገጥ ተልዕኮውን ለመወጣት በዓለም ጤና ድርጅት ላይ ጥገኛ መሆኑን የገለፀው ህብረቱ፤ የድርጅቱ ቁልፍ መስራች አባል የሆነችው አሜሪካ ከተቋሙ የመውጣት ውሳኔዋን በድጋሚ እንድታጤነው ጠይቋል።
26ኛውን የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤን ኢትዮጵያ ታዘጋጃለች - ግብርና ሚኒስቴር
Jan 15, 2025 292
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ 26ኛውን የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ ልታስተናግድ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት ጉባኤ በየዓመቱ በግንቦት ወር በፈረንሳይ ፓሪስ የሚካሄድ ሲሆን በየሁለት ዓመቱ ደግሞ በየአህጉራቱ እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ በአፍሪካ ደረጃ 25ኛው ጉባኤ እአአ በ2023 ቦትስዋና ያስተናገደች ሲሆን 26ኛውን ጉባኤ ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ መመረጧንም አስታውቋል። ጉባኤው "የእንስሳት ጤና ለምግብና ስነ-ምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለሕብረተሰብ ጤና" በሚል መሪ ሀሳብ ከጥር 27 እስከ 30/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ለጉባኤው መሳካት ከዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት ዋናው ጽህፈት ቤት፣ የአፍሪካ እና የምስራቅ አፍሪካ ተወካዮች ጋር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ሲደረጉ መቆየታቸውም ተገልጿል። የግብርና ሚኒስቴርም ግብረ-ሃይል በማቋቋም ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡ በጉባኤው ከየአፍካ ሀገራት የጤና ኃላፊዎችና ቋሚ ተወካዮች፣ ከዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት፣ በየአህጉሩ ያሉ የእንስሳት ጤና አመራሮች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍና የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች እንደሚታደሙም ተጠቁሟል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ(ዶ/ር) በጉባኤው በአፍሪካ የእንስሳት ጤና አገልግሎት፣ ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎችን መቆጣጠርና መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ብሎም ከበሽታ ነጻ የሆነ አህጉር ለመፍጠር የሚረዱ ውይይቶች ይደረጋሉ ብለዋል። በጉባኤው በእንስሳት ጤናና ልማት፣ በምግብና ስነ-ምግብ ዙሪያ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚገኙና የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉበት ገልጸዋል። በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር እየተሰሩ ያሉ እንደ ዝርያ ማሻሻል፣ መኖ፣ የእንስሳት ጤና እና የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ በስፋት ውይይት ይደረግባቸዋል፤ አቅጣጫዎች ይቀመጡበታል ሲሉም ተናግረዋል። የእንስሳት ጤና በንጥረ ነገር የበለጸገ ምግብ ለማምረት እንደሚረዳ፣ መቀንጨርን ከመከላከል አንጻር የእንስሳት ጤና ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳለውም የምናይበት መድረክ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራትና በአህጉር ደረጃ ካሉ ሀገራት ጋር ድንበር ዘለል የእንስሳት በሽታዎችን ለመቆጣጠር፣ የገበያ ተደራሽነትን ለማስፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ብለዋል። ሀገራት ያላቸውን የእንስሳት በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ስትራቴጂና ተሞክሮ፣ ኢትዮጵያም በእንስሳት ጤና፣ መሰረተ ልማት እና ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ለዓለም የምታስተዋውቅበት፣ ልምድ የምንጋራበት መድረክ ነው ሲሉም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። ከመቶ ዓመት የዘለለ የእንስሳት ጤና አገልግሎትና የምርምር ተቋማት፣ በእንስሳት ጤና ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ፣ ክትባትና መድሃኒት የሚያመርቱ፣ በእንስሳት ጤና የሰው ሃይል የሚያፈሩ ተቋማት መኖራቸው መልካም አጋጣሚዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሚካሄደው የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉባኤ የእንስሳት ጤና እንዲጠበቅ ብሎም ዘርፉ እንዲነቃቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ማለታቸውም በመረጃው ተመላክቷል።
ሐተታዎች
የሕብረቱን ኮሚሽን ሊቀመንበርና ኮሚሽነሮች ማን ይተካቸው ይሆን?
Feb 10, 2025 1166
አፍሪካዊያን ርዕሰ መንግስታት በየዓመቱ የሚመክሩበት የአህጉሪቷ ቁንጮ መድረክ ነው-የሕብረቱ መሪዎች ጉባዔ። በያዝነው ሳምንት መጨረሻ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይደረጋል። አፍሪካ-አቀፍ ዕቅዶችና ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ የሚዘከሩበትና የሚመከርበት ወሳኝ ሁነት ነው። ለ38ኛ ጊዜ የሚደረገው የዘንድሮው የመሪዎች ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል። ከመሪዎቹ ጉባዔ ቀደም ብሎ 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ይደረጋል። የአፍሪካ ሕብረት የ2025 መሪ ቃል፣ የሕብረቱ ተቋማዊ ማሻሻያ ሪፎርሞች፣ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት የያዘቸው ውጥን፣ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር፣ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የምግብ ዋስትና ጉባዔው የሚመክርባቸው አንኳር አጀንዳዎች ናቸው። ከአህጉራዊና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ባሻገር የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ጉዳይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የከፍተኛ ባለስልጣናት ምርጫ ነው። የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም በኮሚሽኑ ስር የሚገኙ ስድስት ኮሚሽነሮችን ምርጫ ይካሄዳል። ተመራጮችም የሃላፊነት ዘመናቸው የሚያጠናቅኑ አመራሮች ይተካሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዕጩዎች በየቀጣናው በተሰጠው የዕጩነት ኮታ መሰረት ለሕብረቱ አስገብተዋል። የዕጩዎች የማቅረቢያ ጊዜ የተጠናቀቀው ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር። ዕጩዎች የትምህርት ማስረጃቸው፣ የአፍሪካን የለውጥ አጀንዳ እንዴት ውጤታማ ማድረግ እንደሚችሉና አህጉሪቷ እያገጠሟት ያሉ የቆዩና አዳዲስ ፈተናዎችን በምን መልኩ ለመፍታት እንዳሰቡ ከሚያሳይ የራዕይ መግለጫ ሰነድ ጋር አቅርበዋል። ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ሰሜን ዕጩ የሚቀርብባቸው የምርጫ ቀጣናዎች ናቸው። ኢትዮጵያዊቷ አንጋፋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስን ጨምሮ ከአምስቱ ቀጣናዎች የተወጣጣ አምስት አባላት ያሉት ቡድን ደግሞ የቀረቡ ዕጩዎች ያጣራል። ከአምስቱ ቀጣናዎች ጊዜ ጠብቆ በሚቀያየረው የዕጩ ማቅረቢያ መርህ አለ። በዚህም የዘንድሮው የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዕጩ ከምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሆኗል። የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ደግሞ ከሰሜን አፍሪካ ይመረጣል። የዕጩዎች ማንነትም ታውቋዋል። በዚህም መሰረት የጅቡቲ የውጭ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ፣ የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካሩ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ በኮሚሽኑ ዕጩ ሊቀ መንበር ሆነው ለምርጫ ቀርበዋል። ባለፈው ወርሃ ታህሳስ 2017 ዓ.ም የምርጫ ክርክር ያካሄዱ ሲሆን ዕጩዎቹ የስራ ዕቅዳቸውን የትኩረት ነጥቦችም አቅርበዋል። የጅቡቲ የውጭ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሆነው ቢመረጡ በሰላም እና ደህንነት በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ሌላኛው ዕጩ የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሆነው ቢመረጡ የሕብረቱ መስራች አባቶች ሕልም የሆነውን አፍሪካን አንድ የማድረግ ውጥን ማሳካት ዋነኛ ትኩረታቸው እንደሆነ ተናግረዋል። የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሆነው ቢመረጡ አካታች የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲፈጠርና የዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰሩ በክርክሩ ወቅት አንስተው ነበር። ከዕጩዎቹ አንዱ ከእ.አ.አ 2017 አንስቶ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የ64 ዓመቱ የቻድ ፖለቲከኛ እና ዲፕሎማት ሙሳ ፋቂ ማህማት መንበረ ስልጣን ይረከባሉ። በሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ከሰሜን አፍሪካ ይመረጣል። በዚሁ መሰረት ሳላህ ፍራኒስስ አልሃምዲ እና ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ከአልጄሪያ፣ ሃናን ሞርሲ እና መሐመድ አህመድ ፋቲ ከግብጽ፣ ናጃት አል-ሃጃጂ ከሊቢያ እና ላቲፋ አክሃርባች ከሞሮኮ በዕጩነት ቀርበዋል። ከቀረቡ ዕጩዎች መካከል ተመራጩ ሰው የወቅቱን የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ (ዶ/ር) ይተካል። የ53 ዓመቷ ሩዋንዳዊት ሞኒክ(ዶ/ር) የምጣኔ ሀብት ባለሙያ፣ ፖለቲከኛ እና ዲፕሎማት ሲሆኑ በምክትል ሊቀመንበርነት የተመረጡት በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2021 ነበር። የመጀመሪያዋ ሴት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ናቸው። በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ስር የሚገኙ የስድስት ኮሚሽነሮች ምርጫ ይካሄዳል። እነሱም የግብርና፣ገጠር ልማት፣ “ብሉ ኢኮኖሚ “ እና ዘላቂ ከባቢ አየር፤ የኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ኢንዱስትሪና ማዕድን፤ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፤ የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ፤ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም የጤና፣ ሰብአዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ናቸው። ስድስቱ ኮሚሽነሮች ምርጫ ከማዕከላዊ፣ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ቀጣናዎች ነው። ለስድስቱ ኮሚሽነሮች ዕጩዎችን ቀርበዋል። በዚህም መሰረት 1. የ’ግብርና ገጠር ልማት ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ከባቢ አየር’ ኮሚሽን በአንጎላዊቷ ጆሴፋ ሳኮ፤ 2. የኢኮኖሚ ልማት፣ የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽን - በዛምቢያዊው አልበርት ሙቻንጋ፤ 3. የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽን - በአልጄሪያዊው ፕሮፌሰር መሐመድ ቤልሆሲን፤ 4. የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽን - በግብጻዊቷ አማኒ አቡ-ዘይድ የሚመራ፤ 5. የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽን - በናይጄሪያዊው አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ 6. የጤና፣ ሰብአዊ ጉዳዮችና የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን - በቡርኪናፋሷዊቷ አምባሳደር ሚናታ ሳማቴ ሴሱማ እየተመራ ይገኛል። አንድ የኮሚሽኑ አመራር ለአራት ዓመት የሚያገለግል ሲሆን አመራር ለመሆን በሚደረግ ምርጫ በድጋሚ ለመመረጥ መወዳዳር እንደሚችል የሕብረቱ መተዳደሪያ ደንብ ያመለክታል። በቀረቡ ዕጩዎች መሰረት የሕብረቱ መሪዎች ጉባዔው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀ መንበርን ይመርጣል። የየሀገራቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያቀፈው የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ደግሞ ስድስቱን ኮሚሽነሮች ይመርጣሉ። የሕብረቱን ቁልፍ የአመራርነት ቦታዎች እነማን ይቆናጠጡ ይሆን?
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አቋም መግለጫ አንኳር ሃሳቦች
Feb 3, 2025 500
ብልፅግና ፓርቲ ላለፉት ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ማጠናቀቁን ገልጿል። ፓርቲው ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁለተናዊ ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ባደረጋቸው ጥረቶች የተገኙ አስደማሚ ውጤቶችን ለማስቀጠል እና በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ የሚገባቸውን ወሳኝ ነጥቦችን በተመለከተ ባለስምንት ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባዔውን አጠናቋል። የአቋም መግለጫ አንኳር ሀሳቦችን እንደሚከተለው በአጭሩ ቀንጭበን አቅርበናል። *ጠንካራ ፓርቲ ግንባታን በተመለከተ፦ ባለፉት ሶስት ዓመታት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተከናወኑ ስራዎች ፓርቲው ከዕድሜው የቀደመ የዕድገት ምዕራፍ ላይ እንዲገኝ አስችለዋል። ጠንካራ፤ ጤነኛና ውጤታማ ፓርቲ ለመገንባት ቋሚ ትግል እንደሚያሻ ተገንዝበናል። ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በማሳተፍ በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ የፖለቲካ ባህል በመገንባት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ውጤት ተመዝግቧል። ጉድለቶችን ለማረም አቅም ያለው፣ ሀገራዊ የመንግስት ኢኒሸቲቮችን በሃሳብ የሚመራ እና የህዝብን ንቅናቄዎች በብቃት የሚያስተባብር ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የጋራ አቋም ወስደናል። የአመራርና አባላትን አቅም በማሳደግ በአስተሳስብና በተግባር ብልፅግና የሆኑ፤ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በውጤታማነት እየፈጸሙ የህዝቡን ሕይወት የሚለውጡ፤ የጠንካራ ዲሲፕሊን እና የመልካም ስነ ምግባር መገለጫ የሆኑ፤ የኢትዮጵያን ህልም ዕውን የሚያደርጉ አመራርን አባላት ለማፈራት ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የምንሰራ ይሆናል። ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እንዲቻል ዘመኑን ማላመድ የሚያስችሉ የሃሳብና የታሪክ ውህደት በመፍጠር፣ መዋቅራዊ ልህቀት በማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ስክነትን ዕውን በማድረግ እና የውጤት ዘላቂነትን በቁርጠኝነት ለመፈፀም ዳግም ቃል እንገባለን። *የጠንካራ ሀገራዊ ተቋማት ግንባታን በተመለከተ፦ የሀገረ መንግስት ቅቡልነት ለማረጋገጥ የጠንካራ ተቋማት ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን በማብዛት ለጠንካራ የሀገረ መንግስት እና የደሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ እንሰራለን። የተጀመረውን የተቋማት ረፎረም በማጠናከር ተቋማቱ ነጻነታቸው ተጠብቆ የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በማስጠበቅ አስተማማኝና ነጻነታቸው የተጠበቁ፣ የሀገር ጋሻ እና መከታ ሆነው በዘላቂነት እንዲገነቡ እንደግፋለን። የህዝቡን ፍትህ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ የፍትህ ስርዓትን የማዘመን፣ ባለሙያዎችን የማብቃት፣ የዳኝነት አገልግሎት ነጻነትን እና ተጠያቂነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንታገላለን። *ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥን በተመለከተ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን በማረገጋጥ በአጭር ጊዜ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ የገነባች ሀገር ማየት እንሻለን። ህልማችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የተረጋገጠባትና አፍሪካዊት የብልጸግና ተምሳሌት የሆነች እና ዓለም አቀፋዊ የተፅዕኖ አድማሷ የሰፋ ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ ነው። ለኢኮኖሚ ብልፅግና ግቦች ስኬት በጋራ በመቆም ኢኮኖሚው ነባር አቅሞችን የሚያጠናክር፣ ወደ አዳዲስ ዘርፎች የሚሸጋገር እና ወደ መጪው የፈጠራ ዘመን የሚያስፈነጥር ይሆን ዘንድ ለመታገል ወስነናል። ዘላቂ የልማት ፋይናንስ ስርዓት በመፍጠር ኢኮኖሚውን ከብድር ጫና የሚያላቅቅ አቅጣጫ አስቀምጠናል። ገቢ የመሰብሰብ አቅም በማጎልበት የህዝቡን አዳጊ የልማት ፍላጎት ለመመለስ እንሰራለን። አረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ለማስተባበር አቋም ወስደናል። በቀጣይ ሶስት ዓመታት የተቃና የኢኮኖሚ ለመገንባት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና ዲጂታል ኢኮኖሚ ተደምሮ መዋቅራዊ ሸግግር የኢኮኖሚ ሽግግር ያመጣ ዘንድ አበክረን እንሰራለን። *ማህበራዊ ልማትን ከማረጋገጥ አኳያ፦ ማህበረሰቡ ሁለተናዊ ብልፅግና ተረጋገጦለት ሁለንተናዊ ክብሩ እንዲጠበቅ አካታቸ ማህበራዊ ልማት ዕውን እንዲሆን እንሰራለን። ትውልዱ ጥራት ባለው ትምህርት እንዲያገኝ እና የወንድማማችነት፣ የመቻቻል፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እና አርበኝነት እሴቶች እንዲማር የተጀመሩ ስራዎች ይጠናከራሉ። በጤና መድህን አገልግሎት፣ ጤና ተቋማት ተደራሽነት እና ጥራት የማሻሻል እንዲሁም አካታች የሆኑ ሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። የተጀመሩ የማህበራዊ ልማት ስራዎቻችን ሁለንተናዊ ማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ አጠናክረን እንቀጥላለን። *ሕብረ ብሔራዊ አንድነትና ገዥ ትርክት ግንባታን በተመለተከ፦ ሕብረ ብሄራዊ አንድነት እንዲጠናከር ከነጣጣይ ትርክቶች ይልቅ አስተሳሳሪ ትርክቶች አሸናፊ ሆነው ወጥተው ገዥ ትርክት እንዲሆኑ እንሰራለን። ለሕብረ ብሔራዊ አንድነትና ገዥ ትርክት ለማስረጽም በመላ ሀገሪቷ በተለያዩ አማራጮች ህዝባዊ ውይይቶች ይደረጋሉ። የሃሳብ ነጻነት መከበር እንደተጠበቀ ሆኖ ማህበራዊ ሚዲያ ከአፍራሽ ተልዕኮ ይልቅ ለገዥ ትርክት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ እንዲሁም የኢትዮጵያን ዕውነት ለመግለጥ እንዲውል አበክረን እንስራለን። *የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ሪፈሮምን በተመለከተ፦ የሀገራችን ሲቪል ሰርቪስ ለማሻሻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሳሰረና ከብልሹ አሰራርና ሌብነት የተላቀቀ ሲቪል ሰርቪስ ስርዓት ለመገንባት ገቢር ነበብ ሪፎርም በትኩረት እየተሰራ ነው። በሲቪል ሰርቪስ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ብልሹ አሰራሮች ህዝብ ለእንግልትና ለሮሮ እየዳረጉ በመሆ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የፍትህ ስርዓት ሪፎርም በማጠናከር የመንግስትን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር ጠንከራ አቋም ወስደናል። በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እና ገቢር ነበብ ሪፎርም በማከናወን ቅሬታ ምንጭ በሆኑ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የተጀመረው ሪፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላል። *ሀገራዊ ክብርና አንድነትን የሚያጠናክሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች በተመለከተ፦ ባለፉት ዓመታት የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ስራዎች ብሔራዊ ጥቅሞችን ያስቀደሙ፣ የመሪና የፓርቲ አቅም ያሳዩ ሲሆኑ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ የዲፕሎማሲ ትግሉ ሁነኛ ማሳያ ነው። የትውልድ ጥያቄ የነበረው የባሕር በር አጀንዳ በዓለም አደባባይ ተገቢ ትኩረት እንዲያገኝ ሆኗል። ዲፕሎማሲያችን ከመሽርመም ተላቆ ብሔራዊ ጥቅምን፣ መርህና ዕውነትን እንዲሁም የዜጎችን ክብር መሰረት ያደረገ አቅጣጫ ይዟል። ዘላቂ የባሕር በር የማገኘት ፍላጎት በሰላማዊና በዲፕሎመሲያዊ መንገድ ምላሸ እንዲያገኝ በተገኘው የዓለም መድረከ ሁሉ ለመታገል ቆርጠን መነሳታችንን እናረጋግጣለን። *ሀገራዊ ምክክር በተመለከተ፦ ዘላቂ ሰላም የሁለንተናዊ ብልጽግና ወሳኝ በመሆኑ አካታች ሀገራዊ ምክከር ተደርጎ የኢትዮጵያ የዘመናት የችግር ስንክሳር በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ የተጀመረውን ጥረት እንደግፋለን። የተጀመረው የሽግግር ፍትህ ሂደት ተግባራዊ እንዲሆን የተጣለብንን ሃላፊነት በብቃት ለማስፈጸም እንሰራለን። ከታጣቂ ሃይሎች ጋር የሚደረግ ውይይትና ድርድር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ግጭት እንዲቀር ተጨማሪ አቅጣጫ አስቀምጠናል። ሁሉም የፓርቲው አመራርና አባላት ለሰላም ግንባታ እንዲሰራ ተስማምተናል። የጉባዔውን ውሳኔዎችን በመተግበር ሀገራዊ ሰላም ለማረገጋጥና ህብረ ብሄራዊ አድንድነታችንን አጠናክረን ለማስቀጠል ሁላችንም በአንድነትና በጽናት እንቆማለን። ለጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊነትም ተግተን እንሰራለን።
በትናንት ታሪኳ ለአፍሪካ ነጻነት ውለታዋ፤ ዛሬ ደግሞ በብልፅግና ጉዞዋ ለኢትዮጵያ አድናቆትን የቸሩት የዚምባቡዌው አንጋፋ ፖለቲከኛ- ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ
Jan 31, 2025 200
የ79 ዓመቱ ዕድሜ ባለጸጋ ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ በትውልድ ሀገራቸው ዚምባብዌ ጉምቱ ፖለቲከኛና የዲፕሎማሲ ሰው ናቸው። በ1940ዎቹ አጋማሽ በቅኝ ገዥዎች አስተዳደር ዘመን የተወለዱት ሙቤንጌግዊ ግዛት ዘመን የተወለዱት የፖለቲካ ትግል የጀመሩት በሀገረ አውስትራሊያ የውጭ ሀገር ተማሪ እያሉ ነበር። ይሄውም በፈረንጆቹ 1960ዎቹ አንጋፋውን የዚምባብዌ የአፍሪካ ብሔራዊ አንድነት አርበኞች ግንባር ወይም የዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ(Zimbabwe African National Union Patriotic Front- Zanu PF) የተማሪዎች ተወካይ እንዲሁም የኤዥያ ቀጣና ተወካይ ሆነው ነበር ንቅናቄውን የተቀላቀሉት። ሀገራቸው ከቅኝ ግዛት ነጻ እስከትወጣ ድረስ በተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው ድሕረ ነጻነት በዛኑ ፒኤፍ ማዕከላዊ ኮሚቴነትና በሌሎች የተለያዩ ከፍተኛ የፓርቲ አመራርነት ደረጃ አገልግለዋል። ዛሬም እያገለገሉ ነው። ሙቤንጌግዊ ከዘመነ ሮበርት ሙጋቤ ጀምሮ በዚምባብዌ የዲፕሎማሲ ታሪክ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እና በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ሀገራቸውን ወክለው ለረጂም ጊዜ በዲፕሎማትነት አገልግለዋል። በሚኒስትርነት ደረጃም በውጭ ጉዳይ፣ በማክሮ ኢኮኖሚክ ፕላኒንግና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣ በውሃ ሀብትና ልማት፣ በትራንስፖርት፣ በቤቶች ልማትና በሌሎች የሚኒስቴር ተቋማት ሚኒስትር ሆነው መንግስታዊ ሃላፊነቶች ተወጥተዋል። በዚምባብዌ ፓርላማ አባልነትና የቋሚ ኮሚቴዎች ሃላፊነትም እንዲሁ። ዛሬም በሀገሪቷ ገዥ ፓርቲ በሆነው በዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዋና ጸሃፊ ሲሆኑ የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት ከፍተኛ አማካሪ እንደሆኑም መረጃዎች ያሳያሉ። የኢትዮጵያዊያን የአርበኝነት መንፈስ ለፀረ ቅኝ ግዛትና አፓርታይድ ስርዓት ትግል እንዲቀጣጠል አድርጓል- የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መካሄድ መጀመሩ ይታወቃል። ከእንግዶቹ መካከልም የዚምባቡዌው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ዋና ጸሃፊ ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ ይገኙበታል። በአድዋ መታሰቢያ በተደረገው የጉባዔው መክፈቻ ላይ ተገኝተው የሀገሪቷን ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና የፓርቲያቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ኢትዮጵያ አፍሪካ ውስጥ ብቸኛዋ ቅኝ ገዢዎች ያልተንበረከከች ሀገር በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ዕውቅና ይቸራታል ብለዋል። የኢትዮጵያዊያን የአርበኝነት መንፈስ ለፀረ ቅኝ ግዛትና አፓርታይድ ስርዓት ትግል እንዲቀጣጠል ቁልፍ አበርክቶ እንደነበረው ጠቅሰዋል። አብዛኛው የአፍሪካ ነጻነት ትግሎች በኢትዮጵያዊያና በቆራጥ ኢትዮጵያዊያን ቁሳዊ፣ ሞራላዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎች የታጀቡ ነበሩ ብለዋል። የዚምባብዌ ነጻነት ሃይሎች ታሪክም ከዚህ የተለዩ አይደለም ያሉት ዋና ፀሐፊው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች ከኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠናዎች እንዲሁም የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዳገኙ አውስተዋል። ዚምባብዌ ቅኝ ገዥዎችን ታግላ ድል ስትቀዳጅ የኢትዮጵያና የህዝቧን ውለታ እንደማትረሳ በመጠቆም። ፓርቲያቸው በብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ ሲጋበዝ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት የነበራትን ቁልፍ ሚና ዕውቅና በመስጠት የእንኳን ደስ አላችሁ ደስታውን ያበስራል ብለዋል። ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ብልፅግና በሀገር በቀል እሳቤ ሀገር ለመለወጥ የተነሳ ፓርቲ መሆኑን መጥቀሳቸውን አድንቀው፤ ሀገር የሚለወጠው በሀገሬው ሀሳብና በሀገሬው ሰው ሲመራ ነው የሚለውን የሀገራቸው ስነ ቃል አጣቅሰው የሀሳቡ ተጋሪ መሆናቸውን አስረድተዋል። ብልፅግና ፓርቲ በታሪካዊቷ ሀገር ኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ለማምጣት በመታተር በአጭር ጊዜ ያሳካቸውን ድሎች አድንቀዋል። እስካዛሬ በርካታ ጉባዔዎችን ብታደምም እንደ ብልፅግና ፓርቲ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በማሳተፍ አካታችንቱን ያሳዬ ፓርቲ አላየሁም ሲሉ ለዲሞክራሲ ምህዳር መስፋት የተደረገውን ጥረት አወድሰዋል። የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ በእርግጥም አስደናቂና የማይተማን ሲሉ አሞካሽተውታል። እንዴትስ ይህ ሁሉ ስኬት መጣ ሲሉ ተጠየቅ ሰንዝረዋል። በአዲስ አባባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች እኔን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የውጭ ዜጋ ያማለሉ ተጨባጭ የለውጥ ምስክሮች ናቸው ብለዋል። በርግጥም አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የሆነችውም በአጋጣሚ አይደለም፤ አዲስ አበባ ሁላችን የምንመካባት ውብ ከተማችን ናት ሲሉም በኩራት ተናግረዋል። በኢትዮጵያና በዚምባብዌ መንግስታት መካከል የሁለትዮሽ ዕውነተኛ ትብብር እንዲጎለበት እንዲሁም ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የሚደረጉ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶች ከምንጊዜውም በተሻለ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ አረጋግጠዋል።
የአንካራው ስምምነትና የኢትዮ- ሶማሊያ አጋርነት
Jan 27, 2025 186
በአፍሪካ ቀንድ በስትራቴጂክ አጋርነታቸው ስማቸው ጎልቶ የሚነሳው ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከወደብ ጋር ተያይዞ በመሃከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ወደ ተርኪዬ አንካራ በመጓዝ በሰላም መቋጨት ችለዋል፡፡ ይህ አካሄድ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው መንገድ መፍታት እንደሚችሉ በድጋሚ ያሳዩበት አዲስ የግጭት መፍቻ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በሶማሊያ የነበረው ውስጣዊ የሰላምና መረጋጋት ችግር ለአልቃይዳንና አልሸባብ አሸባሪ ቡድኖች መጠናከር ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮ ቆይቷል። በቀጣናው የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለአካባቢው አገራትም ስጋት በመሆኑ በትብብር መስራትን የሚጠይቅ ይሆናል። ለዚህም የኢትዮ - ሶማሊያ ግንኙነት መጠናከር የላቀ ትርጉም እንዳለው ይታመናል። ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት በመቀጠል አፍሪካ በእርስ በርስ ግጭት የምትናጥ አህጉር ሆና ትጠቀሳለች። በአህጉሪቱ አሁን ላይ ከ35 በላይ የእርስ በርስ ግጭቶች መኖራቸው የሚጠቀስ ሲሆን በግጭቱ ውስጥም በርካታ የታጠቁ ሃይሎች ተሳታፊ መሆናቸው ይነገራል። ጉዳዩን አሳሳቢ የሚያደርገው በቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ ፣ ናይጄሪያና ሶማሊያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን የውጭ ሃይሎችም ሲያባብሱት ይስተዋላል። በመሆኑም የውስጥ ሰላምን ማስጠበቅና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር ለዘላቂ መፍትሄ ወሳኝ አርምጃ መሆኑ ይታመናል። በኮሎምቢያ፣ ፊሊፔንስና አፍጋኒስታን ከተከሰቱት ግጭቶች አንጻር በአፍሪካ የሚታዩ ግጭቶችን በንግግር መፍታት ቀላል መሆኑን በተርኪዬ ሀልዱን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተባባሪ ፕሮፌሰር አህመት ዩሱፍ ይናገራሉ፡፡ ለዚህ ማሳያው ደግሞ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ልዩነታቸውን በሰላም ለመፍታት በቅርቡ በአንካራ የደረሱበት ስምነት ነው ይላሉ ፡፡ ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት "ሁለቱ አገራት የደረሱበት ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ ሊፈጠር ይችላል ተብሎ የተፈራውን ግጭት ያረገበ መሆኑን “ ኢማኑኤል ኦያንጎና ቱግሩል ኦጉዛን የተባሉ የአፍሪካ ጉዳይ ፀሃፊዎች ቲአርቲ በተባለ ድረ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ጠቅሰዋል፡፡ ጉዳዩ በሰላም እልባት ማግኘቱ ያስደሰታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ ለሁለቱ አገራትና ለአደራዳሪዋ ለተርክዬ ምስጋናቸውን በማቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የሶማሊያ ፈተና በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን የግጭት ማዕከል ለማድረግ በርካታ ሴራዎችን በመጠንሰስ ግጭት ጠማቂነቱን በግልጽ እያሳየ ይገኛል። ከዚህ ባለፈ ወደ ሶማሊያ እግራቸውን በማስገባት ላይ የሚገኙ አለም አቀፍ ተዋንያንና የተለያዩ አገራት ፍላጎታቸውን ለመጫን በሚያደርጉት ጥረት አገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከተዋታል፡፡ በዚህ ረገድ በሶማሊያ የሰፈረው ሰላም አስከባሪ ኃይል ፈተና የተጋረጠበት ሲሆን ይህ እሽቅድድም ለአልሸባብ መጠናከር በር ይከፍታል የሚል ስጋት አሳድሯል። የዚያድ ባሬ መንግስት ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ ሶማሊያ በእርስ በርስ ግጭት ስትናጥ ቆይታ በኋላም በአልሸባብ በእጅጉ እየተፈተነች ቢሆንም በተለይም የቁርጥ ቀን ጎረቤቷ ኢትዮጵያ በከፈለችው መስዋእትነት ህልውናዋ ተጠብቆ ቆይቷል። ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሰላም ለማስጠበቅ ያሳየችው ቁርጠኝነትና በተግባርም የከፈለችው መስዋእትነት ቀላል የሚባልም አይደለም። የዲፕሎማሲ ስኬት ከአዲስ አበባ እስከ አንካራ ክፍተቱን መሙላት የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አገሪቱን ለቀው ሲወጡ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ግንባር ቀደም ተሰላፊ የነበረችው ኢትዮጵያ መሆኗን ፀሃፊው ያስታውሳሉ ፡፡ እኤአ በ2005 የእስላማዊ ፍርድ ቤት ህብረት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የጦር አበጋዞችን ድል በመንሳት እኤአ 2006 ላይ ስልጣኑን እንደተቆጣጠረ አዝሎት የመጣውን ስጋት ለማስወገድ ቀድማ የተገኘችው ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ ኢትዮጵያ የአገሪቱን ሰላም በማስከበር ተልዕኮ ላይ ቆይታ እኤአ በ 2009 አገሪቱን ለቃ ስትወጣ የተከፈተውን ቀዳዳ በመጠቀም አልሸባብ የሶማሊያን ደቡባዊ ክፍል በመቆጣጠር የራሱን መንግስት ለማዋቀር በቅቷል፡፡ ቡድኑ እኤአ በ2012 ከአልቃኢዳ ጋር ያለውን አጋርነት በይፋ አደባባይ ካወጣ በኋላ የአለም ስጋት መሆኑ ታውቋል፡፡ አልሸባብ በኢትዮጵያ በደረሰበት ወታደራዊ ሽንፈት ለ18 አመታት በሶማሊያ ብሎም በጎረቤት አገር ኬኒያ ሲያደርስ የነበረውን ጥፋትና ስጋት በእጅጉ መቀነስ ተችሏል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት የሶማሊያን ሰላም በማረጋጋት፤ እንደ አልሸባብ ያሉ አሸባሪ ኃይሎችን በመዋጋትና ቀጣናዊ መረጋጋትን በመፍጠር የኢትዮጵያ ሠራዊትየላቀ ሚናውን መወጣቱን በርካቶች ያነሳሉ። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆኑ ሃይሎች በዓባይ ጉዳይ በተለይም በህዳሴ ግድብ የጀመሩት የማሰናከል ዕርምጃ አልሳካ ሲል በሶማሊያ በኩል ኢትዮጵያ አፍንጫ ሥር ጦር ለማስፈር መፍጨርጨራቸው በኢትዮጵያ ላይ ቀጥተኛ የብሔራዊ ደኅንነትና ጥቅም ሥጋት እንደሚደቅን ይታመናል፡፡ ይህ ደግሞ በአካባቢው ካለው የኃያላን አገሮች ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና ዓለም አቀፍ የፀጥታ ችግር ጋር ተዳምሮ ቀጣናውን የከፋ ቀውስ ውስጥ ሊከት እንደሚችል እየተገለጸ ነው ፡፡ የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ኢትዮጵያ ወታደሮቿን እንድታስገባ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ለአስራ ሰባት ዓመታት ያህል በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ሰራዊቷን አሰማርታ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ በአትሚስ ስር እንዲሁም ከሶማሊያ ጋር ባላት የሁለትዮሽ ስምምነት በብዙ ሺህ የሚቀጠር ሰራዊት በማሰማራት ለሶማሊያ ሉዓላዊነትና ለህዝቧቿ ደህንነት በዋጋ የማይታመን ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍላለች። የአንካራ ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐመድ፤ ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ. ም. በቱርክ፣ አንካራ ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ "በሶማሊያ ሉዓላዊ ሥልጣን ሥር አስተማማኝ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር መተላለፊያ" እንድታገኝ በቅርበት እንደሚሠሩ ተጠቅሷል። ከዚህ ባለፈ ውይይቱ ባለፈው አንድ ዓመት በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ማስቻሉን አመልከተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር የማግኘት ፍላጎት ጎረቤቶቻችንን ጭምር የሚጠቅም ሰላማዊ ጥረት ነው። ይህ ፍላጎት በትብብር መንፈስ እንጂ በጥርጣሬ ሊታይ አይገባውም" ሲሉ የአገራቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ገንቢ ውይይት" ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን "በትብብር፣ በወዳጅነት እና በጠላትነት ሳይሆን በጋራ ለመሥራት ከሚኖር ፈቃደኝነት ጋር ወደ ቀጣዩ ዓመት ያሸጋግራል" ብለዋል። በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ስምምነት ከጋራ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ባሻገር አልሸባበን በጋራ ለመዋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ አልሸባብ አሁን ላይ የሶማሊያና ኢትዮጵያ ብሎም የቀጣናው ስጋት መሆኑን ሁሉም ያውቀዋል፡፡ በመሆኑም በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚቻለው የጋራ ራዕይ በማንገብና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን በማጽናት ሲቻል መሆኑን በተርኪዬ ሀልዱን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተባባሪ ፕሮፌሰር አህመት ዩሱፍ ለቲአርቲ የሰጡት ማብራሪያ ያመልክታል።
ትንታኔዎች
የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አሻራ ያረፈበት የኢትዮ-ታንዛንያ ወዳጅነት
Dec 17, 2024 690
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና ምሥራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በስብስባው ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ስብስባው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ትብብር የማጠናከር ዓላማ የያዘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከነበሩት ጃንዋሪ ማካምባ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት የኮሚሽኑን ስብስባ ለማካሄድ ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ወዳጅነት በቅርበት ለመረዳት የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄን ማየት ግድ ይላል። የመላው ጥቁር ሕዝቦች ንቅናቄ የሆነው ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት የሆነችው ኢትዮጵያ የንቅናቄው ፋና ወጊ በመሆን ወሳኝ ሚና ተጫውታለች። የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው በመቆም ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት አገራት መካከል ታንዛንያ ትገኝበታለች። በፓን አፍሪካኒዝም ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ እና የታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊዬስ ኔሬሬ ተጠቃሽ ናቸው። መሪዎቹ ለአፍሪካ አገራት ከቅኝ አገዛዝ መውጣት ትልቅ ሚና በመጫወት ሕያው አሻራቸውን አሳርፈዋል። የኢትዮጵያና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በእነዚህ መሪዎች ጊዜ የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አገራቱ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጣር ግንቦት 25 ቀን 1963 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (በአሁኑ መጠሪያው የአፍሪካ ኅብረት) መቋቋሙ ሲበሰር መስራች አባል አገራት ነበሩ። ኢትዮጵያና ታንዛንያ በየአገራቱ ኤምባሲያቸውን በይፋ በመክፈት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናክር እየሰሩ ይገኛሉ። አገራቱ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸው በርካታ አቅሞች አሉ። ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ባላቸው የቁም እንሥሳት ኃብት ከአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። ሁለቱ አገራት በሚያደርጓቸው የጋራ ምክክሮች ይሄን ሰፊ ኃብት በመጠቀም የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ያነሳሉ። ግብርና፣ የሰብል ምርት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ እና አቪዬሽን ከሁለቱ አገራት የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ በርካታ ታንዛንያውያን ፓይለቶች እና ኢንጂነሮችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አቪዬሽንም የሁለቱ አገራት ቁልፍ የትብብር መስክ በሚል ይነሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየካቲት ወር 2016 ዓ.ም በታንዛንያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አገራቱ በወቅቱ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በግብርና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቶቹ የሁለቱ አገራት ትብብር ይበልጥ ለማጠናክር ትልቅ ፋይዳ አላቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም የስምምነቶችን አፈፃጸም በመገምገም ትግበራውን ማፋጠን የሚያስችል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰሞኑ የምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ይታወቃል። የቀጣናው ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውኃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው። የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ከኢትዮጵያ እና ታንዛንያ አልፎ በቀጣናው ያለውን ትስስር ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል። ሁለቱ አገራት በቅርቡ ወደ ትግብራ ምዕራፍ የገባው የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን በአገራቸው ፓርላማ ማጽደቃቸው ይታወቃል። ስምምነቱ በናይል ተፋስስ የውኃ ኃብትን ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በበጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ነው። አገራቱም በውኃ ኃብት ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ያስተሳሰራቸው ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ትብብራቸውን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ማሸጋግር የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረው የኢትዮ-አልጄሪያ ወዳጅነት
Dec 16, 2024 879
የኢትዮ-አልጄሪያ ግንኙነት ታሪካዊ ነው፡፡ታሪካዊነቱ በዘመንም፣ በጸና ወዳጅነትም ይለካል።ትናንት ማምሻውን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የሀገሪቷን ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልክዕት ይዘው አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዛሬ ማለዳ ደግሞ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል። የፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔን መልዕክትም ተቀብለዋል። ጉብኝቱን አስመልክቶ የሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ እና የኢትዮጵያን ወዳጅነት የትመጣ እና ሂደት በወፍ በረር እንቃኝ። የኢትዮ-አልጀሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሰባት አስርት ዓመታትን ተሻግሯል። ሁለቱ ሀገራት ከመደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ወንድማማችነትና ወዳጅነት መስርተዋል። የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ የነበረችው አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መባቻ ነጻነቷን ለመቀዳጀት ትንቅንቅ ላይ በነበረችበት ዘመን ኢትዮጵያ አጋርነቷን አሳይታለች። ይህን ደግሞ በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር የነበሩት ኤልሃምዲ ሳላህ ‘አልጀሪያ የኢትዮጵያን ውለታ አትረሳውም’ ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2022 ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀው ነበር። አልጀሪያ በ1962(በአውሮፓዊያኑ) ነበር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ያረጋገጠችው። ከዚህ ዘመን ጀምሮ ሁለቱ ሀገራት ወዳጅነታቸውን መሰረቱ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረት እና የፓን አፍሪካኒዝም እንዲያብብ ንቅናቄ አድርገዋል። በ1960ዎቹ መጨረሻም ይፋዊ ዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን በይፋ ጀመሩ። አልጄሪያ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በ1976(እ.ኤ.አ) ከፈተች። ኢትዮጵያም በ2016 ኤምባሲዋን በአልጀርስ ከፍታለች። ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2014 በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ባህል እና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የጋራ ኮሚቴ ፈጥረዋል። ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ጥበቃ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም ተደራራቢ ታክስ ማስቀረትን ጨምሮ ከ20 በላይ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት ስምምነት ተፈራርመዋል። ከሁለትዮሽ ባሻገርም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የትብበር መስኮች ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት አላቸው። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም በኒውዮርክ በተካሄደው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ይታወቃል። በዚሁ ውይይት ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አልፎም በዓለም የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። አምስተኛውን የኢትዮ-አልጄሪያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቅርብ ጊዜ ለማከናወን የተጀመረውን ዝግጅት ለማፋጠን ተስማማተዋል። አልጄሪያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ምክር ቤት ከአውሮፓዊያኑ ጃንዋሪ 2024 አንስቶ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና በመስራት ላይ ትገኛለች። ይህም ሁለቱ ሀገራት በባለብዝሃ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጎለብት ነው። አልጄሪያ በአውሮፓዊያኑ በ2021 የአረብ ሊግ ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት ተቋሙ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዛባ አረዳድ ለማስተካከል እና ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረው ጥረት አድርጋለች። የኢትዮ-አልጄሪያ የሁለትዮሽ ትብብር የሚያጠናክሩ የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እያደጉ መጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም በአልጄሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በወቅቱም ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ ጋር ተወያይተው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮ-አልጄሪያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ በሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር የሚቻለባቸው ዘርፎች እንዳሉ ገልጸው ነበር። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በሀገራቱ መካከል የጉብኝት ልውውጦች እና ውይይቶች እየጨመሩ መጥተዋል። ለአብነትም በአውሮፓዊያኑ በ2021 የያኔው የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር፤ የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውም አይዘነጋም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ደግሞ በሩሲያ ሶቺ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ከተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ የትብብር ፎረም የሚኒስትሮች ስብስባ ጎን ለጎን ከአልጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር መክረዋል። በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስጠብቁ ቀጣናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እናም ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙነታቸውን ማጎልበት ቀጥለዋል። በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ በቅርቡ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጂድ ቴቡኔ ሲያቀርቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴን ልባዊ ሰላምታ እና የወዳጅነት መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ዛሬ ደግሞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ የፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ቴቡኔን መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አድርሰዋል። የሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጉብኝት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እና የኢትዮ-አልጀሪያ ሁለትዮሽ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ስለመሆኑ የአልጄሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋርም ተወያይተዋል። በውይይቱ በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር እና አዳዲስ የትብብር አድማሶችን በመፈለግ አጋነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብስባን በቅርቡ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። እናም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከተለምዷዊ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የተሻገረ ነው። ሁሉን አቀፍ በሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረጉ ትብብር መስኮች እየተወዳጁ ነው። የስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ እየጎለበተ ይመስላል። የአገራቱ መጻዒ የትብብር ጊዜ ብሩህ እና ፍሬያማ እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ቀጣና ዘለል አንድምታ ያለው የአንካራው ስምምነት
Dec 13, 2024 1151
የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ አንድምታ ከቀንዱ ሀገራት የተሻገረ ነው። የቀጣናው ሀገራት ትስስርና ትብብርም እንደዚያው። በነዚህ ሀገራት መካከል የሚፈጠር መቃረን የሚያሳድረው ተጽዕኖም አድማስ ዘለል ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የግንኙነት መሻከር ከሁለቱ ሀገራት ባሻገር በቀጣናው ስውርና ገሀድ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎችን ያሳሰበና ያስጨነቀ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። በቱርክዬ ርዕሰ ከተማ አንካራ የተደረሰው የኢትዮ-ሶማልያ ሥምምነት ግን ለበርካቶች እፎይታን ይዞ መጥቷል። ከኢትዮጵያና ሶማልያ ጋር መልካም ወዳጅነት ያላት ቱርክዬ የሁለቱን አገራት ለማሸማገል ጥረት ከጀመረች ውላ አድራለች። ምንም እንኳ ጥረትና ድካሟ በተደጋጋሚ ሳይሳካ ቢቆይም ካለፈ ሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚኒስትሮች ደረጃ ለማረቅ ተግታለች። በሦስተኛው ዙር በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረገው ድርድር ግን ፍሬ አፍርቶላታል። ቱርክዬ እየተገነባ ባለው የብዝሃ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ጎልተው እየወጡ ካሉ ኃያላን ሀገራት መካከል አንዷ ናት። በአፍሪካ ውስጥ ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪነትም እያደገ መምጣቱ ይታወቃል-በተለይ በአፍሪካ ቀንድ። ቱርክዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ታሪካዊና ዘርፈ ብዙ ትስስር ጠንካራ የሚባል ነው። ቱርክዬ ከቻይና ቀጥላ በኢትዮጵያ ግዙፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሀገር ናት። ከኢኮኖሚያዊ ቁርኝቱ ባሻገር ሁለቱ አገራት በፖለቲካዊና ማኅበራዊ እንዲሁም ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ያላቸው ትብብርም የላቀ ነው። ቱርክዬ ከሶማልያ ጋር ያላት አጋርነትም እየተጠናከረ የመጣ ነው። እናም የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ለቱርክዬ ሳንካ ነበር። ስለዚህ የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት በአንካራው ድርድር ዲፕሎማሲያዊ እልባት ማግኘቱ ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ወሳኝ እርምጃ ሆኖላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአንካራ ተገኝተው ያደረጉት ውይይት የቀንዱን ውጥረት አርግቧል። ስምምነቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል። በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት መስማማት ችላለች። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማልያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት ዙሪያ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የወደብ አማራጮችን በስፋት ለመጠቀም ለምትፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያና የሶማልያ ሕዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በጉርብትና ብቻ ሳይሆን በደም የተሳሰሩ ወንድማማቾች እና እህታማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተዋል። ይልቁንስ ሶማልያን ከአሸባሪዎች ለመከላከልና ሠላሟን ለማረጋገጥ ሲባል በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አባላት በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር የተሳሰረ መሆኑን ነው ግልጽ ያደረጉት። ኢትዮጵያ ለጋራ ሠላምና ልማት ከሶማልያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። የሶማልያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድም ለዚህ ሀቅ ጠንካራ እማኝነታቸውን ሰጥተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለአገሪቱ ሠላም መጠበቅ ለዓመታት የከፈለውን ዋጋ መቼም አይዘነጋም ሲሉ የሚገባውን ክብር አጎናጽፈውታል። ሶማልያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሠላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግሥታቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። በጥቅሉ የአንካራው የአቋም መግለጫ የሁለቱን አገራት የጋራ አሸናፊነት ያንጸባረቀ ነው። ለዘመናት በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ፈጽሞ የተዘነጋ እና የማይታሰብ ይመስል የነበረውን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ በድፍረት ዓለም አቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ያስቻለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከሃገር አልፎ ለቀጣናው ሁለንተናዊ ትስስር ጭምር ወሳኝ መሆኑ መግባባት የተደረሰበት ሆኗል። በተለያዩ አሰራሮች እና አግባቦች፣ በሠላማዊ መንገድ እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘላቂ የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ መግባባት የፈጠረ ነው። ይህን ሥምምነት ዕውን ለማድረግ በዝርዝር ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ ድርድሮች በማካሄድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ መግባባት ችለዋል። በዚህ ረገድ ቱርክዬ ሂደቱን ለማሳለጥ እና ለማገዝ ኃላፊነት መውሰዷ ደግሞ ዘላቂነት እንዲኖረው እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ነው። ኢትዮጵያና ሶማልያ በአንካራ የደረሱት ስምምነት ከአውሮፓ ኅብረት እስከ አፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እስከ ተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት አድናቆት የቸሩት ሆኗል። ይህ ስምምነት የሁለት አገራት ስምምነት ብቻ አይደለም። የጥይት ድምጽ የማይሰማባት አፍሪካ የመፍጠር ህልም አካልም ጭምር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የውዳሴው መነሻና መድረሻውም ደግሞ ስምምነቱ የአፍሪካ ቀንድን ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ብሎም ወደ አህጉራዊ ትብብር የሚወስድ መሆኑ ነው። በእርግጥም ሥምምነቱ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ከመባቱ በፊት ለቀንዱ አገራት የቀረበ ሥጦታ ነው። እናም የአንካራው ስምምነት ከኢትዮጵያና ከሶማልያ ባለፈ አንድምታው ቀጣናውን የተሻገረ በመሆኑ የአፍሪካውያንና የወዳጅ ሀገራት በቅን መንፈስ የተቃኘ ድጋፍ ያሻዋል። ሠላም!
ህዳሴ - በመስዋዕትነት የተገነባ ነገ
Nov 2, 2024 2453
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የኢትዮጵያውያን በጋራ የመቻል ትምህርት ነው። የወል ዕውነታቸው፣ የወል አቅማቸው፣ የጋራ ተስፋቸው በግልጽ የተንጸባረቀበት የአይበገሬነት ምልክት ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን እንዴት በጋራ መገንባት እንደሚችሉ በሚገባ ያሳዩበት ዳግማዊ አድዋ ነው - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ። አድዋ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የተዋደቁበት ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ደግሞ ለኢኮኖሚ ሉአላዊነት የደም ዋጋ የተከፈለበት የትውልዱ የብሄራዊነት ማሳያ ነው። ህዳሴን ዕውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ከሴራ ዘመቻዎች እስከ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የደረሱ እንቅፋቶችን አልፋለች። በተለይም የግድቡ ግንባታ ወደማይቀበለስበት ደረጃ በደረሰባቸው ያለፉት 6 ዓመታት ፈተናዎቹ በርትተው ነበር። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተጓጉዘው እንዳይደርሱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት እንዳያመርቱና እንዳያቀርቡ በተለየዩ ቦታዎች ጥቃቶች ይሰነዘሩ ነበር። ቢሆንም ግን የማያባሩ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የተንኮል ወጥመዶች በጣጥሶ ለማለፍ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወታቸውን ጭምር ገብረው ነገን ዛሬ መስራትን በህዳሴ ዕውን አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በርካታ መስዋዕትነት መከፈሉን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሁሌም በጋራ የመልማት እሳቤ ማዕከል መሆኗን ገልጸው፤ታላቁ ህዳሴ ግድብም በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ልጆች ከአፍሪካ ለአፍሪካ የተሰጠ ገጸ በረከት እንዲሁም ጣፋጭ ፍሬውም ከኢትዮጵያ ባለፈ ለተፋሰሱ አገራትም ብስራት መሆኑን ነው ያስረዱት። የታላቁ የኢትዮጵየ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ አኩሪ ደረጃ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያውያን ከገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀታቸው ባሻገር የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል።
ልዩ ዘገባዎች
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 853
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 2235
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል። በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል። የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
ያ ሆዴ የአዲስ ብርሃን ተስፋ
Sep 21, 2024 4061
በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና የኢዜአ ቅርንጫፍ ከብት የሚጠብቁ ህፃናት አዲስ ዓመት እየመጣ ስለመሆኑ ማብሰሪያ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ የዋሽንት /የገምባቡያ/ ድምፅ ማሰማት ይጀምራሉ። በመስከረም ከጉምና ጭጋግ ፀለምት ጨለማ የሚወጣበትና ምድሩ በአበባ ሀምራዊ ቀለም የሚታጀብበት ወቅት በመሆኑ በሀዲያ ብሄር ዘንድ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ወቅት ነው። ያ ሆዴ የሀዲያዎች አዲስ የዘመን መለወጫ በዓል መባቻ ነው። ያ ሆዴ ማለት በሀዲያዎች ዘንድ “ብርሃን ሆነ፣ መስቀል መጣ፣ ገበያው ደራ፣ በይፋ ተበሰረ ብሎም እንኳን ደስ አላችሁ” የሚል ስያሜ እንዳለውም ይነገራል። “ያ ሆዴ " በሀዲያ ካሉ እሴቶችና ወጎች እንዲሁም ክንዋኔዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ አንድነት፣ መቻቻል፣ ለውጥን ለማሳለጥ፣ አብሮነትና ሰላም ለማጠናከርም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይወሳል። የሀዲያ አገር ሽማግሌ አቶ መንገሻ ሂቤቦ እንዳጫወቱን ከሆነ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ ከብት የሚጠብቁ ህፃናት አዲስ ዓመት መምጣቱን የዋሽንት /የገምባቡያ/ ድምፅ በማሰማት አዋጅ ማብሰር ይጀምራሉ። ይህም የበዓሉ መቅረብን ለማሳሰብና ለማስታወቅ የሚደረግ ነው። በዓሉ ብርሃን፣ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት በረከት የሚሞላበት ተምሳሌታዊ ወር ተደርጎ ይታመናል። ያ ሆዴ በሀዲያ ዘንድ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። ለምሳሌ አባት ለእርድ የሚሆን ከብት በማቅረብ፣ እናት ደግሞ ሌሎች የቤት ስራዎች በማከናወንና ልጆችም ልዩ ልዩ የስራ ድርሻቸውን በመወጣት በዓሉን ያከብራሉ። “አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማህበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ /ሼማታ/ ነው” ይላሉ የሀዲያ አገር ሽማግሌ አቶ መንገሻ፤ ይህም ከአራት አስከ ስምንት አባላትን ይዞ የሚደራጅ የስጋ ማህበር ነው። የማህበሩ አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን፤ በዓሉ ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ። ለስጋ መብያ የሚሆን ቆጮ ብሎም ለአተካና የሚሆን ቡላ በማዘጋጀት ከጥቅምት እሰከ ጥር ባሉት ወራት ውስጥ እንሰት በመፋቅ እናቶች በቡድን ተሰባስበው ዝግጅታቸውን ማከናወን ይጀምራሉ። በተጨማሪም ዊጆ |የቅቤ እቁብ| በመግባት ቅቤ በማጠራቀም ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ቅመማ ቅመሞችን በማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። የዳጣ፣ የአዋዜ ዝርያዎችንና ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ባህላዊ የሆኑ መጠጦችን ጭምር ያዘጋጃሉ። ልጃገረዶች በዓሉ እንዲደምቅ ቤት መደልደል፣ የተለያዩ ቀለማትን በመጠቀም የግርግዳ ቅርጻ ቅርጾችን በመስራት እንዲሁም ግቢ በማጽዳት የማሳመር ስራቸውን ያከናውናሉ። ወጣት ወንዶች ለማገዶ የሚያገለግል በአባቶች ተለይቶ የተሰጣቸውን እንጨት ፈልጠው እንዲደርቅ ያደርጋሉ። ጦምቦራ ለደመራ የሚሆን ችቦ በማዘጋጀት ግዴታቸውን ይወጣሉ። የሀዲያ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያ ወይዘሮ አመለወርቅ ሃንዳሞ እንደሚሉት፤ በዓሉን ለማክበር በአገር ውስጥ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ አብሮነት ለማክበር ከእሩቅም ከቅርብም ይሰበሰባሉ። ይህም በዓሉ ለአብሮነትና ለሰላም ያለውን ፋይዳ የላቀ ያደርገዋል። ዓመቱን ሙሉ ለበዓሉ የሚደረጉ ዝግጅቶችና የስራ ክፍፍሎች ልዩ ትርጉም ያላቸው ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ “ወጣቶች የትዳር አጋራቸውን የሚመርጡበት በመሆኑ በዓሉን ልዩ ድባብ ይሰጠዋል” ይላሉ ወዘሮ አመለወርቅ። የበዓሉ ዋዜማ /ፉሊት ሂሞ/ ወጣቶች ያዘጋጁትን ጦምቦራ /የደመራ ችቦ/ የአካባቢውን ነዋሪዎች በሚያዋስን ቦታ ላይ ይሰራሉ። እናቶች ከቡላ፣ ቅቤና ወተት የሚያዘጋጁት ጣፋጭ የሆነ እና ጣት የሚያስቆረጥመውን አተካና በማዘጋጀት የበዓሉን ዋዜማ/ፉሊት ሂሞን/ ያደምቁታል። የበዓሉ አመሻሽ ዋዜማ ላይ ወጣቶች “ያ ሆዴ ያ ሆዴ “በማለት ይጨፍራሉ። ይህም ለበዓሉ “የእንኳን አደረሳችሁ” መልእክት አለው። በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የአገር በቀል እውቀቶች ምርምር ዳይሬክተር አቶ እያሱ ጥላሁን “ይህ በዓል የሚሰጠው የስራ ክፍፍል፣ የሰላምና አብሮነት ዕሴቶች ለጠንካራ ዕድገት፣ ነገን በተስፋ ለመመልከት ወሳኝ ነው” በማለት ይገልጹታል። በወቅቱ ወጣቶች በአካባቢው እየዞሩ በመጫወት ከአባቶች ምርቃት ይቀበላሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች ደመራው በተዘጋጀበት ቦታ ማምሻውን ይሰባሰቡና አባቶች ደመራውን የሚያቀጣጥሉበትን ችቦ በመያዝ ልጆችን በማስከተል ዓመቱ የብርሃን፣ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እንዲሆን ፈጣሪያቸውን በመማጸን ደመራውን ይለኩሳሉ። ደመራው ተቀጣጥሎ እንዳለቀ በእድሜ ከፍ ወዳሉ አባወራ ቤት እንደሚሰባሰቡ ነው አቶ እያሱ የተናገሩት። የእርድ ስርዓቱ በሚከናወንበት ቤት ደጃፍ አባላቱ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ በአንድነት በመሰባሰብ የጋቢማ ስርዓት ይከናወናል። ይህም እድሜ ጠገብ ሽማግሌዎች ቅቤ እና ወተት በሚታረደው በሬ ላይ እያፈሰሱ” ለምለም ሳር "በመያዝ በሬውን እያሻሹ አዲሱ ዓመት ለህዝብ እና መንግስት የሰላም ዓመት የሚመኙበት መንገድ ነው። ልጆች ለወግ ለማዕረግ የሚበቁበት፣ መካኖች የሚወልዱበት፣ የተዘራው ለፍሬ የሚበቃበት ዓመት እንዲህን ፈጣሪያቸውን ይማፀናሉ። በሦስተኛው ቀን የቱታው አባላትና የአካባቢ ሰዎች ተጠርተው በአባቶች ምርቃት ተደርጎ በአንድነት ሆነው ምክክር በማድረግ ለቀጣይ ዓመት የሚሆን እቅድ በማዘጋጀት ተጨዋውተው ይለያያሉ። “በየቤቱ የሄደው ቅርጫ በፍጹም ለብቻ አይበላም” ያሉት አቶ እያሱ፤ በየአከባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን አፈላልጎ ማብላትና ማጠጣት በማከናወን በዓሉን በጋራ ያሳልፋሉ። ይህም በዓሉ አንዱ ለአንዱ ያለውን ወዳጅነትና አብሮነትን በማጠናከር ትስስርን የማጉላት አቅሙ ከፍተኛ ነው። በሌላ በኩል ተጣልቶ የከረሙ ነዋሪዎች ከተገኙ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር እርቀ ሰላም በማውረድ በንጹህ ህሊና፣ በአዲስ ምዕራፍ፣ በአዲስ ተስፋና በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዓመት ይጀምራሉ። ይህም “ባህሉ በዜጎች መካከል የሰላምና አብሮነት ምሰሶ መሆኑን ያመለክታል” ያሉት አቶ እያሱ፤ በንጹህ ልቦና በብርሃንና በተስፋ መጪውን ዘመን ለማሳለፍ እንዲቻል ጉልህ ሚና እንዳለው አጽንኦት ይሰጡታል።
መጣጥፍ
ጥቂት ስለ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ
Feb 18, 2025 29
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አዲሱ የዓለም የፉክክር መድረክ እየሆነ መጥቷል። በልብወለድ ወይም በምናብ የሚታሰቡ ፈጠራዎች፤ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እውን እየሆኑም ይገኛሉ። እ.ኤ.አ ከ2012 ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት ያሳየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአሁኑ ጊዜ ከሰዎች የቀን ተቀን ሕይወት ጋር እየተዛመደ መጥቷል። በዕለት ተዕለት የሰዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያዎች እንመልከት። 👉ቻት ጂፒቲ (ChatGPT): ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ሀሳቦችን ለማመንጨት እንዲሁም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዳ ነው። 👉ግራመርሊይ (Grammarly) : በፅሁፍ ውስጥ የግራመር (ሰዋሰው) እንዲሁም የስርዓተ ነጥብ ስህተቶች የሚያርም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው። 👉ካንቫ (Canva) : የተለያዩ ግራፊክስ ስራዎችን በቀላሉ የሚሰራልን መጠቀሚያ ነው። 👉ኦተር ኤአይ (Otter.ai) : በድምፅ የምንናገራቸውን ወደ ፅሁፍ (text) የሚቀይር መጠቀሚያ ሲሆን በአብዛኛው በትምህርት ቤት ውስጥ ለሌክቸር ይጠቀሙታል:: 👉ክራዮን (Craiyon) : ፅሁፍ ብቻ በመፃፍ የምንፈልገውን ፎቶ ለመፍጠር የሚረዳ መጠቀሚያ ነው። 👉ሬፕሊካ (Replica) : የኤ አይ ቻት ቦት ሲሆን ስለ አዕምሮ ህክምና የሚያማክር እንዲሁም የግል የአዕምሮ ህክምና ምክር የሚሰጥ ነው። 👉ማይክሮሶፍት ቱ ዱ (Microsoft To Do): የቀን ሥራዎቻችንን ለማቀድ እና ለማደራጀት የሚያግዝ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው። 👉ሄሚንግዌይ ኤዲተር (Hemingway Editor): የኦንላይን መፃፊያ ሲሆን አፃፃፋችን የጠራ እና ሀሳብን የያዘ እንዲሆን የሚያግዝ መጠቀሚያ ነው። 👉ጎግል አሲስታንት (Google Assistant): የቨርቹዋል አጋዥ መጠቀሚያ ሲሆን የቤት ውስጥ ስማርት መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር፣ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲሁም አስታዋሽ በመሆን ያገለግላል። 👉ጎግል ፎቶ (Google Photos): ፎቶዎችን ለማደራጀት እንዲሁም ለመፈለግ የሚረዳ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መጠቀሚያ ነው።
የአድዋን መንፈስ እንልበስ- ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሌይ
Feb 18, 2025 66
ወርሃ የካቲት የጥቁሮች ወር ነው። ካሪቢያን ጥቁሮች በጥቁሮች የትግል ታሪክ ጉልህ አሻራ ያላቸው መሰረተ አፍሪካ ህዝቦች ናቸው። ካሪቢያን ዜጎች ኢትዮጵያን አብዝተው ይወዳሉ። ለመላው ጥቁር ሕዝቦች አንድነትና ትግል ንቀናቄ አድዋን እንደ እርሾና እሴት ያወሳሉ። በቅርብ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የታደሙት የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሌይ በሕብረቱ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር በርካቶችን ያስደመመና ያስደነቀ ነበር። ከመልዕክታቸው ውስጥ ተከታዮቹን ሃሳቦች መዘናል፦ 👉 አድዋ በ24 ሰዓታት ውስጥ የአውሮፓዊያንን የራስ መተማመን ትምክህት ያሽመደመደ፤ የአፍሪካዊያንና ትውልድ አፍሪካዊያንን ልጆች መንፈስ ያጎመራ፣ መልካምነት ድል ያደረገበት፣ ብርሃን በጨለማ ላይ የነገሰበት ሁነት ነው። 👉 ዛሬ እናንተ ፊት የቆምኩት ይህን መንፈስ ታጥቄ ነው። አድዋ የፓን አፍሪካኒዝም እርሾ ነበር። 👉 የአድዋ ድል ለነጻነትና ትግል እንድንነሳሳ ባቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ነጻነት ድል እንድንቀዳጅ ምዕራፍ የከፈተ ድል ነው። አድዋ የአንድነት ውጤት ነው። 👉 እናንተ ፊት የቆምኩት የፓን አፍሪካዊነት ፈር ቀዳጆችን ሕልም ሰንቄ ነው። 👉 እኛ የካረቢያን ትውልዶች ከአፍሪካ ወንድምና እህቶቻችን ጋር ሕብረታችንን ማጠናከር እንሻለን። 👉 ትናንት በእኛ መከፋፈል ራሳቸውን ለበላይነት ያነገሱ ሃይሎችን እያሰብን አንድነታችንን አጠናክረን ነገን እንገንባ ወይም እንደ ትናንቱ ተነጣጥለን እንጥፋ የሚለው ምርጫ የኛ ፋንታ ነው። 👉 ስለዚህ የአድዋን መንፈስ ተላብሰን ከፊታችን የሚጠብቀንን መልከ ብዙ ፈተና በአንድነት እንጋፈጥ። 👉 ከአፍሪካ ውጭ የጥቁሮች ምድር ከሆነችው ባርባዶስ ተነስቼ ኢትዮጵያ የተገኘሁት ለአፍሪካና ካረቢያን ህዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት ጥሪ ነው። 👉 ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥለሴ በዓለም ላይ አንደኛና ሁለተኛ መደብ ዜጋ መኖር የለበትም እንዳሉት ዛሬም በየትውልዱ በዓለም ላይ ኢ-ፍትሃዊነትና አግላይነት ስርዓት ይወገድ ዘንድ መታገል አለብን። ለዚህ ደግሞ የአድዋ ድልና የፓን አፍካዊነት መንፈስን እንልበስ። 👉 የጋራ መዳረሻችንን ለመቀየስ ከወሬ ይልቅ ተግባር ላይ አተኩረን በትጋት እንስራ። የትናንት ቁስልን እያከክን ሳይሆን ብሩህ ነገን ለመገንባት በጋራ እንቁም። 👉 ከፊታችን የተደቀነ አደገኛ ፈተና እንዳለ ተገንዝበን ፈተናውን በአንድነት ለመጋፈጥ ሞራላዊ ግዴታችንን እንወጣ። 👉 የአድዋን መንፈስ እንልበስ!