የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ ነው
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ የልማት አጀንዳ መሆኑን በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ገለጹ።
አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ችግኞችን በመትከል የካርቦን ልቀትን መቀነስ የሚያስችል ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
ከብክለት ነፃ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን በማስፋት በኩልም ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር አረንጓዴ የኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ እየወሰደች እንደምተገኝም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ የልማት አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አስተማማኝ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታም ለሌሎች የአፍሪካ እና የዓለም ሀገራት ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል።
ሕንድም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አስተማማኝ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
በቅርቡ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ መያዣዎች ላይ የእግድ ውሳኔ መተላለፉ ለአካባቢ ደኅንነትና ሥነ-ምኅዳር ጥበቃ ጉልህ ፋይዳ ያለው ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይም ሕንድ በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ሥርዓት ያላትን ልምድና ተሞክሮ በማጋራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።