ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ቼልሲ ከፒኤስጂ የሚያደርጓቸው ተጠባቂ የመልስ ጨዋታዎች 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራት የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት አምስት ላይ ማንችስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንት በፊት በበርናባው ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ሪያል ማድሪድ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ሪያል ማድሪድ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሉ ሰፊ ነው።

ማንችስተር ሲቲ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ከሶስት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል። 

በሌላኛው መርሐ ግብር ቼልሲ ከፒኤስጂ ምሽት አምስት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።


 

ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ፒኤስጂ 5 ለ 2 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

ባለሜዳው ቼልሲ ውጤቱን የመቀልበስ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሉ የሰፋ ነው።

አርሰናል ከባየር ሌቨርኩሰን ምሽት አምስት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይጫወታሉ።


 

ቡድኖቹ በመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው አርሰናል በዘንድሮ የውድድር ዓመት አቻ የወጣበት መርሐ ግብር ነው። በጨዋታው የሚያሸንፈው ቡድን ለሩብ ፍጻሜ ያልፋል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከቦዶ ግሊምት በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በመጀመሪያው ጨዋታ ቦዶ ግሊምት 3 ለ 0 አሸንፏል።  የኖርዌው ቡድን ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሉ ሰፊ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም