ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምትኬ ብርሃኑ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥራለች።
ብሩክታዊት አየለ ለአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ሁለት ግቦችን ያስቆጠረችው የሲዳማ ቡናዋ ምትኬ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃ ይዟል።
አዲስ አበባ ከተማ በሊጉ በርካታ ሽንፈቶችን ያስተናገደ ቡድን ነው። በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት ሁለት ብቻ ናቸው።