የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ጀመረ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ማድረግ ጀምሯል።
ቡድኑ የመጀመርያ ልምምድ ላይ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ከሀገር ውጪ ክለቦች ከሚገኙት ጋቶች ፓኖም እና ከነዓን ማርክነህ በቀር ሁሉም ተጫዋቾች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለማጣሪያ ጨዋታው ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት እ.አ.አ ጁን 2027 ይካሄዳል።