ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
Jul 22, 2026 2
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ መሰረት፣ ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የዝናብ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የበለጠ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሰታወቋል። በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ሥርጭት መጠን ይኖራቸዋል። በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ብሏል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ኢንስቲትዩቱ የጠቆመው። በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም በኤሊ ዳር፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ቡሬ፣ አሳይታ፣ ሁንዱፎ፣ ገዋኔ፣ ሚሌ፣ ዳሊፋጊ፣ አይሻ፣ ጉሊና፣ አዋሽ አርባ፣ ባቲ፣ ዶሎ አዶ፣ ዳዋ፣ አሶሶ፣ ጎዴ፣ ቋራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ጭፍራ፣ ላሬ፣ መተሀራ እና፣ ላሬ፣ ፉኙዶ አካባቢዎች ከሚኖረው የቀን ከፍተኛ የፀሀይ ሀይል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል። ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክር ሀሳብን ከወዲሁ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል
Jul 22, 2026 31
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ። የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በመድረክ ላይ እንደገለጹት፤ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎች ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል። በበጀት ዓመቱ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የርቀት ሥራ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል። በዚህም መሠረት በሶስቱ ዋና ዋና አማራጮች ለአምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ከአምስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን በላይ ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል። ለዜጎች የተፈጠሩት የስራ እድሎች በግብርና፣ በአገልግሎት፣ በኢንዱስትሪ፣ በውጭ አገር የስራ ስምሪት እና በርቀት የተፈጠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የፓርቲው ቅርብ አቅጣጫና ድጋፍ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል፡፡ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከ 631 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ስምሪት በማመቻቸት ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል። ከተለያዩ የአረብ ሀገራት በተጨማሪ ወደ ስድስት የአውሮፓ ሀገራትም ዜጎችን መላክ መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡ ሀገራት እያሳዩ ባሉት ፍላጎት መሠረት ስምምነቶች ተፈራርመው ዜጎች አስፈላጊውን የሙያና የቋንቋ ስልጠና አግኝተው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የዲጂታል እና የርቀት ሥራ (Remote Work) የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በርቀት ሥራ ከ41ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ ለዚህም የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ጋር የተደረገ ማስተሳሰር ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ 70 የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ ማዕከላት የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም እንዲቀርፁ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል
Jul 22, 2026 45
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በ2018 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል ከተከናወኑ ተግባራት እና የገበያ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል። በዚህ መድረክ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የክልል አመራር አባላት ተሳትፈዋል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እና ገበያን ለማረጋጋት በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሪፖርት አቅርበዋል። በቀረበው ሪፖርት መሠረት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ 15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት መገኘቱን አመልክተው፤ ይህም ከእቅዱ እኳያ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የነዳጅ አቅርቦትን በተመለከተ፤ ከዓለም አቀፍ የነዳጅ መስመር መዛባት እና የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ተግዳሮቶች ቢኖሩም ታቀዶ ከነበረው 5 ነጥብ 23 ሚሊዮን ሜትሪክ ኩብ የእቅዱን 91 በመቶ ነዳጅ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል። በሕገ-ወጥ አሰራር እና በከፍተኛ የፍላጎት እድገት ምክንያት በገበያው ላይ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የገበያ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሀገር ደረጃ ከተለዩት 7 ሺህ 628 የአካባቢ ገበያዎች መካከል የ3 ሺህ 670ዎቹ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተጠናቋል ብለዋል። በተጨማሪም 804 አዳዲስ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም 32 ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የግብይት ትስስርን ለማጠናከር 1 ሺህ 352 የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በትስስሩ የተሳተፉ ሲሆን፤ ለነዚህ ማህበራት ከ3 ነጥብ 33 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የሪቮልቪንግ ፈንድ ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል። በተከናወኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና የምግብ ድጋፍ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከገበያ ጋር ተያይዞ ያሉትን ችግሮችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ሕገ-ወጥ ኬላዎችን የማንሳት ሥራ መከናወኑን ጠቁመው፤ ለኑሮ ውድነት መባባስ ምክንያት የሆኑ ችግሮች እየተቃለሉ መምጣታቸውን ገልጸዋል። በገበያ ቁጥጥር እና ሕግ ማስከበር ተግባራት፤ በሕገ-ወጥ ንግድ በተሰማሩ 347 ሺህ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል። በነዳጅ በሕገ-ወጥ አሰራር በተሳተፉ 688 አካላት ፣የንግድና ፀጥታ አካላትን ጨምሮ ሕጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ተወርሶ 781 ሚሊዮን ብር በቅጣት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል። በቀጣይ በ2019 በጀት ዓመት ምርትና አቅርቦትን ማጠናከርን ዋና ትኩረቱ ያደረገ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ መያዙን ገልጸው፤ በዚህም የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርና እንቅስቃሴዎችን በልዩ ትኩረት የማስፋት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል። በሁሉም የምርት ዓይነቶች ላይ የ10 በመቶ እድገት ታሳቢ በማድረግ ለመስራት የተያዘ ሲሆን፤ ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ልዩ ድጋፍ በማድረግና የገበያ ትስስርን በማጠናከር የግብይት ስርዓቱን ለማረጋጋት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። የገበያ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት ሁለተኛው ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስከ 2019 ዓ.ም ድረስ ሙሉ ለሙሉ የይዞታ ማስከበርና ማረጋገጥ ስራዎችን የማጠናቀቅ እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ ቢያንስ የ500 ገበያዎችን ደረጃ የማሻሻል ስራ ይሰራል ብለዋል። የእሁድና ቅዳሜ ገበያዎችን ቁጥር ወደ 3 ሺህ 439 ለማድረስ እቅድ መያዙን ጠቁመው፤ በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን በህግና አሰራር ብቻ ለመፍታት የቁጥጥርና የሬጉላቶሪ አቅምን የማሳደግ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል።
አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት የተሻለች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ምክክር እያደረግን ነው
Jul 22, 2026 45
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት የተሻለች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ምክክር እያደረግን ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ምክክር የሚደረግባቸውን ስምንት አጀንዳዎች መለየቱ ይታወሳል። በአጀንዳዎቹ ላይ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በተገኙበት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛል። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ተመካካሪዎች፣ ሂደቱ በግልጽነትና በሃላፊነት ስሜት እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡ ለሀገር የሚበጁ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ መንገድ ምክክር እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከተመካካሪዎቹ መካከል አቶ ቀጄላ መርዳሳ እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ ለምክክሩ አካታች በሆነ መንገድ ተመካካሪዎቹን መምረጡን በአካል በመሳተፍ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ከጣልቃ ገብነት የጸዳ፣ ዜጎች በራሳቸው ፍላጎትና ባለቤትነት የሚመራ በመሆኑ ለሌሎች ሀገራትም ትልቅ አርዓያ የሚሆን ልዩ ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል። አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ምክክር እንዲደረግ ሊቃውንት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀገር ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ዜጎች ለዘመናት ሲጠይቁት የነበረ ጉዳይ መሆኑን አስታውሰዋል። አሁን የጀመርነው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለዚያ ጥያቄ መልስ የሰጠ ነው ያሉት አርክቴክት ዮሐንስ፤ ሁሉም በጋራ ሆኖ ልዩነቱን ተመካክሮ መፍትሔ የሚያበጅበት ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል ብለዋል። ምክክሩ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወደፊት ልዩነቶችን ለመፍታት ኃይል ሳይሆን የሰለጠነ አካሄድ መፍትሄ እንዲሆን መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ሌላኛው ተመካካሪ መምህር ሞገስ ፍሥሓ በሰጡት አስተያየት፣ ሂደቱ እጅግ በሚያበረታታ መልኩ እየቀጠለ መሆኑን በመጥቀስ፤ መድረኩ በምክክር አዲሷን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ታላቅ ዕድል የከፈተ መሆኑን ገልጸዋል። ምክክር አንዱ የሌላውን ሐሳብ በማዳመጥ መግባባት መፍጠር ነው ያሉት ሌላኛው ተመካካሪ ናስር አብደላ፤ በምክክር ጉባኤውም ሁሉም ተመካካሪ ሐሳቡን በነፃነት እየገለጸና እየመከረ ነው ብለዋል። ሌላኛዋ ተመካካሪ ዝማማ አቡሃይ በበኩላቸው፣ በምክክሩ ሀገርን የሚያሻግር መፍትሔ እንዲመጣ ሀገርና ሕዝብ አደራ ጥሎብናል ብለው ይህንን ታሪካዊ አደራ በብቃት ለመወጣት ሙሉ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ተመካካሪ ሊዲያ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በአጀንዳዎች ላይ ሐሳባችንን በነፃነት በማቅረብ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ብለን ያሰብነውን መፍትሔ ለማምጣት እየተጋን ነው ብለዋል፡፡ በምክክሩ ሂደት ባለቸው ተሳትፎም የራሳቸውን ሐሳብ ከማካፈል ባለፈ፣ ከሌሎች ተመካካሪዎች የሚነሱ ሃሳቦችን በማዳመጥ ጥሩ የምክክር ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ተመካካሪ ሲሳይ ዘለቀ በበኩላቸው፤ የምክክር መድረኩ የሀገሪቱን የጋራ የወደፊት ዕድል ለመወሰን ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ገልጸዋል። ሌላኛው ተመካካሪ ባንዲራ በላቸው በበኩላቸው፣ ሀገራዊ ምክክር አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት የተሻለችና የጸናች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል ታላቅ ዕድል ነው ብለዋል፡፡
በዞኑ የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለኩታ ገጠም እርሻና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቷል
Jul 22, 2026 47
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ፡፡ በዞኑ በአበሽጌ ወረዳ የኩታ ገጠም የመኸር አዝመራ ልማት የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በዞኑ የመኸር ሰብልን ውጤታማ ለማድረግ በ177 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የተለያዩ ሰብሎች ለምተዋል፡፡ በኩታ ገጠም እርሻውም በቆሎ፣ ማሽላ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ሩዝ እና ጤፍ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ለግብአት አቅርቦት፣ ለባለሙያ ድጋፍ፣ ለሰብል እንክብካቤና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር በበኩላቸው፤ በወረዳው በዘንድሮው የመኸር ወቅት ግብአትና የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴን በመጠቀም አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የአበሽጌ ወረዳ የአቡኮ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዘሪሁን ቱሉ፤ የግብርና ባለሙያዎች የሚያደርጉላቸውን ድጋፍ ተጠቅመው አራት ሄክታር ኩታ ገጠም መሬታቸውን በበቆሎ ማልማታቸውን ተናግረዋል። የበቆሎ ሰብሉን ከአረም እና ከበሽታ በመከላከል የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አርሶአደር ሃይሉ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ ሶስት ሄክታር የበቆሎ ማሳቸውን እየተንከባከቡ በመሆናቸው የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ አመላክተዋል። ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በ30 ሄክታር መሬት ጤፍን በኩታ ገጠም በማልማት እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ዳዊት አሰፋ ናቸው። ምርታማነታቸውን ለማረጋገጥም የተሻሻለ የጤፍ ዝርያን መጠቀማቸውንና የባለሙያ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ፖለቲካ

መመካከር ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚጣል መሠረት ነው - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
Jul 22, 2026 50
ኢትዮጵያ የሺህ ዓመታት የታሪክ ባለቤት፣ የበርካታ ቋንቋዎች፣ ባሕሎች፣ እምነቶችና ማንነቶች መኖሪያ ሀገር ናት። ይህ ብዝኃነት የሀገሪቱ ሀብትና ጥንካሬ ቢሆንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ የልዩነትና የአለመግባባት ምንጭ ሊሆን ይችላል። ልዩነቶችን በግጭት ሳይሆን በውይይት ለመፍታት፣ የተለያዩ ዕይታዎችን በአክብሮት ለማዳመጥ እና የጋራ መፍትሔ ለመፍጠር የሚያስችለው መንገድ ሀገራዊ ምክክር ነው። በመከናወን ላይ ያለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ይህንን እሳቤ በተግባር እያሳየ ያለ አስፈላጊ መድረክ ነው። ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሀገር ወሳኝ ጉዳዮችን በግልጽነትና በኃላፊነት በመወያየት፣ ልዩነቶቻቸውን በመደማመጥ እና የጋራ መፍትሔ ለማግኘት በቁርጠኝነት እየተሳተፉ ነው። ይህም ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት የሚጥል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ማለት ዜጎቹ በሕግ ፊት እኩል የሚሆኑበት፣ ተቋማት በአግባቡ የሚሠሩበት፣ የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት የሚፈቱበት እና የሕዝብ መተማመን የተጠናከረበት ሀገር ማለት ነው። ይህንን መሠረት ለመገንባት ደግሞ ሁሉን ያሳተፈ ምክክር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ሲገልጹ፣ ሌሎችንም በአክብሮት ሲያዳምጡ የጋራ እምነት ይጠናከራል። በዚህም የግጭት እድሎች እየቀነሱ የመግባባት ባሕል ይጎለብታል። ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦችን አንድ ላይ በማምጣት የጋራ ራዕይን ለመገንባት የሚረዳ ሂደት ነው። በሀገር ደረጃ የሚነሱ ውስብስብ ጉዳዮች የሚፈቱት በአንድ ወገን አሸናፊነት ሳይሆን፣ በጋራ መግባባትና በሁሉም ወገኖች ተሳትፎ መሆኑን የዓለም ልምዶችም ያሳያሉ። በመሆኑም የሀገራዊ ምክክር ሂደት የዛሬን ችግሮች ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ የሚጠቅም የመግባባት ባሕል ለመፍጠር ያግዛል። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ላይ እየታየ ያለው የተሳታፊዎች የመደማመጥ ፍላጎት፣ የልዩነት ሀሳቦችን በአክብሮት የመቀበል አመለካከት እና የሀገርን ጥቅም ከሁሉ በላይ ለማስቀደም የታየው ቁርጠኝነት ለሂደቱ አበረታች ምልክት ነው። እንዲህ ያሉ መድረኮች ዜጎች በጋራ የሚወስኑትን ውሳኔ እንዲያከብሩ ያግዛሉ። በተቋማት ላይ ያለውን መተማመንም ያጠናክራሉ። ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የጀመረው ሂደት ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ሁሉም ዜጎች የራሳቸው ሚና እንዳላቸው ሲያምኑ እና በንቃት ሲሳተፉ ነው። መመካከር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ቡድን ተግባር ብቻ ሳይሆን የመላው ሕዝብ ኃላፊነት ነው። የውይይት ባሕል በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤት፣ በማኅበረሰብ እና በሀገር ደረጃ ሲጠናከር ብቻ ዘላቂ ሰላምና የተረጋጋ ሀገረ መንግሥት ሊገነባ ይችላል። የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው መመካከር ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለፍትሕ እና ለአንድነት የማይተካ መሣሪያ መሆኑን በተግባር እያስሰከረ ቀጥሏል። የኢትዮጵያ የወደፊት ጥንካሬ በልዩነቶችን በመቻቻል፣ በመደማመጥ እና በጋራ መፍትሔ በመፈለግ ላይ የሚመሠረት እንደሆነ ጉባኤው ግልጽ መልዕክት እያስተላለፈ ይገኛል። ይህን ሂደት በትዕግሥት፣ በኃላፊነት እና በቀጣይነት ማስቀጠል የሁሉም ዜጎችና ተቋማት የጋራ ኃላፊነት ነው።
የምክክር ጉባኤው ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ መሠረት የሚጥል ታሪካዊ አጋጣሚ ነው
Jul 22, 2026 74
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የዘመናት ቁርሾና አለመግባባቶችን በመፍታት ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ መሠረት የሚጥል ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ምሁራን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና አራት ሺህ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች በተገኙበት ዋናው የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞ በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል እርምጃ የመቋጨት ባህል ያለበት ሆኖ መቆየቱን ታሪክ ያስረዳል። ይህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ከማረጋገጥ፣ ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ እንዲሁም የውስጥ ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ አሉታዊ ጥላ ያጠላበት ሆኖ መቆየቱን አስረድተዋል። በዚህም የሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የሚያስችላትን ''ብዕርና ብራና” ያገኘችበት ታሪካዊ አጋጣሚ መክፈት እንደቻለ አብራርተዋል። ኢትዮጵያውያን በምክክር ሂደቱ መግባባትን በመፍጠር ለአንድ የሀገር አንድነት ዓላማ በመቆም፤ ለፈተናዎች የማይበገርና ታሪካዊ ሴራዎችን የምትመክት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በበኩላቸው፤ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪል ኢትዮጵያውያን በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ ተገናኝተው የሚመክሩበት ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዞ የሚያቀና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ምቹ ምኅዳር የፈጠረ መሆኑንም በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ አብስረዋል። የዋናው የምክክር ጉባኤ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም የኢትዮጵያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን መፍትሔ ለማምጣት በግልፅነትና በታማኝነት ሐሳባቸውን የሚያካፍሉበት ሁኔታ መፈጠሩን አንስተዋል። በዚህም ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ሕዝብ የወከላቸው ተመካካሪዎች በንዑስ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳ ላይ እየተመካከሩ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ ልማት ከፍ ለማድረግና በአፍሪካ ቀንድ ያላትን አህጉራዊ ተጽዕኖ ለማረጋገጥ በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር ወሳኝ ነው። የሀገራዊ ምክክር ጉባኤም ለዘመናት የዘለቁ ሀገራዊ ችግሮችን መፍትሔ በመስጠት ረገድ ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል አስገንዝበዋል። ለዘመናት የዘለቁ የቁርሾና የልዩነት ማነቆዎችን በምክክር ለመሻገር የተሰነዱ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎችም ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለማነፅ መሠረት መሆናቸውን አንስተዋል። የምክክር ሐሳቦቹ ከሕዝቡ የልብ ትርታ ተነስተው በባለቤትነት መንፈስ የሚመሩ በመሆናቸው፣ የምክክር ሂደቱ ፍሬያማና ኢትዮጵያን ለነገ የተሻለች ሀገር አድርጎ ለማዋቀር የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። የታሪክ ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በበኩላቸው፤ በግጭትና በአለመግባባት የምትገነባ ሀገር እንደሌለች በመጥቀስ፣ ምክክር የጋራ መግባባት ላይ ለማድረስ የሚያግዝ የሀገር ግንባታ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ምክክርም የተለያየ ሐሳቦችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማሰባሰብ፣ ማሸነፍና በመሸነፍ የዘለቀውን የዘመናት አለመግባባትና የታሪክ ስብራት ለመጠገን የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል። ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤም ልዩነቶችን ከማስተናገድ ባለፈ፣ የተለያዩ ድምፆች የሚደመጡበትና የሀገር ግንባታ አቅጣጫ በጋራ የሚቀመጥበት ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካሪ ፕሮፌሰር አድማሱ ገበየሁ እንደሚሉትም፤ ምክክር የጋራ አሸናፊነትን የሚያቀዳጅ የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ የጋራ መድረክ ነው። በምክክር አሸናፊና ተሸናፊ እንደሌለና አሸናፊዋ ሀገር ናት ያሉት አማካሪው፤ ምክክር የተለያዩ አመለካከቶችን በማቀራረብ የዛሬን ልዩነቶች ወደ መግባባት የሚያሻግር የነገን ጠንካራ ሀገር መገንቢያ ድልድይ ነው ብለዋል።
ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል መኖር የማያስችል ስርዓት አልበኝነት ፈጥሯል
Jul 22, 2026 98
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/2018(ኢዜአ)፦ ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል መኖር የማያስችል ስርዓት አልበኝነት መፍጠሩን የስምረት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀፍቱ ኪሮስ ገለጹ። በአሁኑ ወቅት ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ወጣቶች ለሌላ አሳልፎ መሸጥን ጨምሮ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ በማካሄድ ከፍተኛ ግፍና መከራ እያደረሰ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በክልሉ ህግና ስርዓት በመፍረሱ ምክንያት የህዝቡ ሰላምና ደህንነት ለአደጋ መጋለጡን አንስተዋል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት እንዲያገኝና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ማስቻሉን አስታውሰው፤ አሁን ላይ ግን ህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ሕዝብ አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን ጠቁመዋል። ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን የሰላም ስምምነቱን በማፍረስና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ይህ ህገ ወጥ ቡድን በፈጠረው ስርዓት አልበኝነት በክልሉ ወጣቶች ላይ ኢ-ሰብዓዊ ተግባራት እየፈጸመና በግዳጅ አፈሳ እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። የህዝቡን ሰላም እና መረጋጋት ለመመለስ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሊተገበር እንደሚገባም ነው አቶ ሀፍቱ ኪሮስ የተናገሩት። አሁን በትግራይ ክልል ውስጥ የሚስተዋለው አፈሳ እና ኢ-ሰብዓዊ ተግባራት ወጣቶች አካባቢያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እያደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። ህዝቡ በተደራጀ መንገድ የራሱን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር መቆም እንዳለበትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ችግሩ መልክ መያዝ እንደሚገባው ጠቁመዋል። ህገወጡ የሕወሓት ቡድን በክልሉ እየፈጠረ ያለው ችግር አሳሳቢ መሆኑን በመጥቀስ፣ ህዝቡ በራሱ አቅም ተደራጅቶ ሰላሙንና ደህንነቱን ማስጠበቅ እንደሚገባውና ህገ ወጥ ቡድኑ እየፈጠረ ያለው ቀውስ በአፋጣኝ መፍትሄ ማግኘት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ የፌዴራል መንግስት በክልሉ ህግና ስርዓትን የማስከበር እንዲሁም የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራ መሥራት እንዳለበትም አንስተዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ለሁሉም የምትመችና የጸናች ሀገር ለመገንባት ፅኑ መሰረት የሚያኖር ነው
Jul 22, 2026 125
ጎንደር ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በምክክር በመፍታት ለሁሉም የምትመችና የጸናች ሀገር ለመገንባት ፅኑ መሰረት የሚያኖር መሆኑን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ባሰባሰባቸው ስምንት አንኳር አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ የምክክር ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ከአራት ሺህ በላይ ጉባኤተኞች የተሳተፉበት መድረክ የኢትዮጵያን የቆዩ ችግሮች በመፍታትና ስብራቶችን በመጠገን ለሁሉም የምትመች ጠንካራ ሀገር የመገንባት ትልም ለማሳካት እየተሰራ ነው። የጉባኤው መክፈቻ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በችግሮች ውስጥ እድሎች ያሉ በመሆኑ የምክክሩን ታሪካዊ እድል በመጠቀም የጸናችና ለዜጎቿ የምትመች ሀገር መገንባት አለብን ብለዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በምክክር በመፍታት ለሁሉም የምትመችና የጸናች ሀገር ለመገንባት ፅኑ መሰረት የሚያኖር መሆኑን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ቴዎድሮስ ተሰማ ፤ ኢትዮጵያዊያን ያለ ምንም ልዩነት እየተሳተፉበት ያለው ምክክር ለኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል። ለኢትዮጵያ ከምክክር ውጭ የተሻለ መፍትሄ የሚያመጣ የለም የሚሉት አስተያየት ሰጪው ችግሮቻችንን በምክክር በመፍታት ለዜጎቿ ሁሉ የምትመች ሀገር መገንባት አለብን ብለዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ምስጋናው ደሴ፤ የምክክሩ ውጤት የሀገርን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት በመሆኑ ለስኬቱ ሁላችንም መትጋት አለብን ሲሉ ተናግረዋል። የምክክር ትርፉ ብዙ መሆኑን አንስተው ከዋልታ ረገጥ እሳቤና ከግጭት አዙሪት በመውጣት ሀገር ለመገንባት በጋራ መቆም አለብን ብለዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ተማሪ ሳሙኤል ተስፋሁን፤ የምክክሩ ዓላማ ለአሁንም ይሁን ለቀጣዩ ትውልድ የሚበጅ ቁልፍ መፍትሄ መሆኑን አንስቶ ለስኬቱ የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል ሲል ተናግሯል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በአጀንዳዎች ላይ በጥልቀት በመምከር ለሀገር የሚበጅ መልካም ውጤት እንዲመጣ አደራቸውን እየተወጡ መሆኑ ይታወቃል።
ምክክሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት አቅም ይፈጥራል- ነዋሪዎች
Jul 22, 2026 122
ቦንጋ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት አቅም የሚፈጥር መሆኑን በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። ኢትዮጵያ ለዘመናት ከቆዩ ችግሮቿን በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ በምክክር የምትፈታበት ወርቃማ ጊዜ ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለው አካታችና አሳታፊ የምክክር ጉባኤ የሀገሪቱን መፃኢ እድል የመወሰን አቅም ያለው ትልቅ መድረክ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት ለሰላም እጦትና ለእድገት ማነቆ ሆነው የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት አቅም ይፈጥራል ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል ወጣት አብነት ተመስገንና ወጣት ፈጠነ ወንድሙ እንደተናገሩት፥ ሀገራዊ ምክክሩ የውስጥ ችግርን በራስ አቅም መፍታት የሚያስችል ትልቅ እርምጃና የዘመናዊነት መገለጫ ነው። ምክክሩ አካታች በሆነ መልኩ መካሔዱ ቅቡልነትን ያተረፈ ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት እንደሚያስችል ተናግረዋል። በተለይም ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ እንዲመክሩና እንዲወስኑ መደረጉ ለሀገር መፃኢ እድል ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ወጣቶቹ ምክክሩ ለዘመናት ለሰላም እጦትና ለእድገት ማነቆ ሆነው የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ያስችላል ብለዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ተቹሬ ተክሌ በበኩላቸው፥ የምክክር ጉባኤዉ ኢትዮጵያን ከሚከሰቱ ግጭቶች በማላቀቅ ወደ ተሻለ ሰላምና ብልፅግና ያሸጋግራታል ሲሉ ተናግረዋል። ሴቶችን ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እንዲመክሩና በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ መደረጉ ትልቅ እምርታ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ ግርማ ገብረሚካኤል የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው፥ የምክክር መድረኩ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶችንና ቅራኔዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ በምክክር በመፍታት ሰላምን የሚያፀና እና አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል። በግጭትና በጦርነት የተገነባ ሀገር የለም ያሉት አቶ ግርማ ምክክሩ፥ ኢትዮጵያዊያን ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሳቸውን ችግሮች በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ የሚያሳይ ወርቃማ እድል ነው ብለዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ውይይት እየተደረገባቸው ያሉ ስምንት አጀንዳዎች ተገቢነት ያላቸውና የሀገርን የእድገትና የሰላም መፃኢ እድል የሚወስኑ በመሆናቸው ትልቅ ትስፋ እንዳላቸው አስተያየት ሰጪዎቹ አመልክተዋል።
ምክክሩ ኢትዮጵያ ወደ አዲስ የታሪክ እና የልማት ምዕራፍ የምትሸጋገርበትን ዕድል የሚፈጥር ነው-ተመካካሪዎች
Jul 22, 2026 168
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ለዘመናት ስር ከሰደዱ ችግሮቿ ተላቃ ወደ አዲስ የታሪክ እና የልማት ምዕራፍ የምትሸጋገርበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ እየተሳተፉ ያሉ ተመካካሪ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጰያዊያን ማህበረሰብ አባላት ገለፁ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ምክክር የሚደረግባቸውን ስምንት አጀንዳዎች መለየቱ ይታወሳል። በአጀንዳዎቹ ላይ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በተገኙበት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛል። ከሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በንዑስ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር ጀምረዋል። በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የዲያስፖራ ተወካይ ተመካካሪዎች ምክክሩ ኢትዮጵያ ከገጠሟት ዘመናት የተሻገሩ ችግሮች ወጥታ ወደ ተሻለ የታሪክ እና የልማት ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚያስችላት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ገልፀዋል። ይህ የምክክር ሂደት ከታች ጀምሮ ችግሮቹን በምክክር እና በመግባባት እንዲፈታ መንገድ የከፈተ አዲስ ምዕራፍ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ አስተያየታቸውን ከሰጡን መካከል ከአውስትራሊያ የመጡት ፓች አኩዌር እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት እንዲህ ባለው ሁኔታ ተመካክረው እንደማያውቁ ጠቁመው፤ ጥሪው በደስታ እና በሙሉ ስሜት የተቀበሉት መሆኑን ተናግረዋል። ከሁሉም ክልሎች የመጡ ኢትዮጵያውያን የተሰበሰቡበት ድባብ እጅግ ደስ የሚል መሆኑን ጠቅሰው፤ ምክክሩ ለተተኪ ትውልድ የምትሆን ሀገር ለማስተላለፍ ትልቅ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ ከአሜሪካ የመጡት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በበኩላቸው፤ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ጅምረናል ብለዋል። የምክክር ሂደቱ የጋራ መግባባትን በመፍጠር ከግጭትና ከመነቃቀፍ ወጥቶ በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። አራት ሺህ ተመካካሪዎች ተሳትፎ የሚያደርጉቡት ይህ ምክክር ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድል ብሩህ መሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካና ለዓለም ህዝብ ጭምር ትሩፋትና ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ታላቅ ሂደት ሲሉ ገልፀዋል። ከእንግሊዝን የመጡት አለባቸው ደሳለኝ እንደተናገሩት፤ ከተለያዩ ብሔረሰቦች እና ሲቪክ ማህበራት የተወጣጡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ያሳዩት ቁርጠኝነትን አድንቀዋል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጰያዊያን ማህበረሰብ አባላት ለሀገር የሰላም ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በመመካከር የማይፈታ ችግር እንደሌለ ጠቁመው፥ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት ለማምጣት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የመሪነት ሚና እየተወጣች ነው
Jul 22, 2026 150
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የመሪነት ሚና እየተወጣች መሆኑን የናይጄሪያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አግቤዲ ፍሬደሪክ ገለጹ። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ትብብርን በማጠናከር እና ልማትን በራስ አቅም ለማረጋገጥ የተጫወተችው ታሪካዊ ሚና እጅግ የሚደነቅ መሆኑንም ገልጸዋል። የምክር ቤቱ አባል ለኢዜአ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ በፓርላማ ሥርዓት ረጅም ታሪክ ካላቸው ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እያበረከተች ያለው ሚና የሚደነቅ ነው። በተለይም አህጉራዊ ትብብርን እና በራስ አቅም የመቆም አቅጣጫን ለማጎልበት የተጫወተችው አዎንታዊ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማጠናቀቋም ለዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየችበት መሆኑን ተናግረዋል። ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በዋነኝነት የሚያስፈልገው የዜጎችን ፍላጎት የሚመልስ፣ ሰላምን የሚያሰፍንና ሀገራዊ እድገትን የሚያፋጥን ኃላፊነት የሚሰማው አመራር መሆኑንም አስገንዝበዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገው ተጨባጭ ጥረት እና እያስመዘገበችው ያለው ስኬት ለአፍሪካ ብርሃን ፈንጣቂ አድርጓታል ብለዋል። የኢትዮጵያና ናይጄሪያ ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ያነሱት የምክር ቤት አባሉ በሀገራቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች መካከል የተመሰረተው የፓርላማ ወዳጅነትና የፓርላማ ግንኙነትን ለማጠናከር የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ይህም የሀገራቱን የዲሞክራሲ ተቋማት የማጠናከር ተግባር ያላቸውን ዘርፈ ብዙ የልማት ትብብርና ሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ ትብብርና በራስ አቅም መቆም በማጎልበት ረገድ የተጫወተችውን ታሪካዊ ሚና አድንቀዋል። የአፍሪካ ሀገራት የእርስ በእርስ አጋርነትና ትብብርን ለማጠናከር በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ማህበራዊ
ደም በመለገስ የወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ ሀላፊነታችንን እየተወጣን ነው
Jul 22, 2026 73
ዲላ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ደም በመለገስ የወገኖችን ህይወት ለመታደግ ሰብአዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን በዲላ ከተማ በጎ ፈቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። በከተማው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ በአንድ ጀንበር 100 ዩኒት ደም የማሰባሰብ ዘመቻ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ እየተካሄደ ነው፡፡ ደም ለጋሾቹም በበጎ ተግባራቸው የሰው ህይወት በመታደጋቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት መካከል በአሽከርካሪነት ሙያ የተሰማሩት አቶ ከድር አሊ፤ የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎችን ለማከም በሚደረግ ጥረት የደም እጦት ጫና ሲፈጥር ማስተዋላቸውን አንስተዋል። የተመለከቱትን ችግር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በዛሬው ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል። ደም መለገስ እናቶች በወሊድ ወቅት የሚገጥማቸውን የደም እጥረት ለመሸፈን ድርሻው የጎላ መሆኑን ያነሳቸው ደግሞ ወጣት ናርዶስ ተሾመ ናት። በዘመቻው በመሳተፍ ደሟን በመለገሷ የተለየ ደስታ እንደፈጠረባት ተናግራ በቀጣይም በሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፍ የክረምት ወራትን በበጎ ተግባራት ለማሳለፍ እየሰራች መሆኑን ገልጻለች። አቶ ታምራት አሰፋ በበኩላቸው፤ ደም መለገስ በቀላሉ ልናደርገው የምንችለው በጎ ተግባር በመሆኑ በቀጣይም አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል። የዶርቃ በጎ አድራጎት ህብረት ሰብሳቢ ወጣት እሱባለው ገብረሕይወት በበኩሉ፤ ህብረቱ ከ100 በላይ የዩኒቨርሲቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በስሩ ይዞ በከተማው በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሳተፈ መሆኑን ጠቅሷል። በበጎ ፈቃድ ደም መለገስ የመንፈስ እርካታን የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሶ በተለይ የደም ልገሳ ሕይወት የማዳን ተግባር በመሆኑ ለየት ያደርገዋል ብሏል። የዲላ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መላኩ አየለ በበኩላቸው፤ በከተማው በክረምት በጎ ፈቃድ ከ143 ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን ጠቅሰዋል። በዛሬው ቀንም ወጣቱን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር 100 ዩኒት ደም የማሰባሰብ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል። በከተማው የደም ልገሳን ጨምሮ በ19 ዘርፎች ከ98 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በከተማው እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ልጆች ሁሉ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው
Jul 22, 2026 79
ዲላ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በዲላ ከተማ በመጪው የትምህርት ዘመን እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ልጆች ሁሉ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ከወዲሁ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የከተማው ትምህርት መምሪያ ገለጸ። በከተማው የትምህርት ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው። የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ ታሪኩ በየነ በወቅቱ እንዳሉት፤ በመጪው የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎች ምቹ በማድረግ የትምህርት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ከወዲሁ እየተሰራ ነው። በተለይ የተማሪዎችን ውጤት፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃና መሰረተ ልማት በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ጥረት ይጠናከራል ብለዋል። የተማሪዎች ቅበላን በአግባቡ ከማከናወን ባለፈ የመምህራንን አቅም ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። በከተማው ህብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር በትምህርት ልማት ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ያነሱት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ሆርዶፋ ናቸው። በተለይ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ከ80 በላይ መማሪያ ክፍሎችን በመገንባት ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቁመው ይህም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ በትምህርት ልማት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል በመጪው የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት የተጠናከረ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጪው የትምህርት ዘመን ከ41 ሺህ 528 በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ልጆች ሁሉ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ለማድረግ ከወዲሁ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል ። በዲላ ከተማ የቆፌ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አብነት ሽፈራ በበኩላቸው፤ በትምህርት ቤቱ በመንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በአጋር አካላት ድጋፍ የተገነቡ 12 መማሪያ ክፍሎች የትምህርት ቤቱን ደረጃ ማሻሻላቸውን ጠቅሰዋል። በመጪው የትምህርት ዘመን የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በአማራ ክልል የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ የህብረተሰቡ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እየተሰራ ነው
Jul 22, 2026 90
ባህር ዳር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ የህብረተሰቡ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሴቶች ፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ዝና ጌታቸው በባህር ዳር ከተማ በተካሄደ የደም ማሰባሰብ ስነስርአት ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ በክረምት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት 30 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው። እስካሁን ከ5ሺህ 400 በላይ ዩኒት ደም መሰብሰቡን ተናግረዋል። በዛሬው እለትም በሃገር አቀፍ ደረጃ የታቀደውን የአንድ ጀንበር 10 ሺህ ዩኒት ደም የመሰብሰብ ግብ ለማሳካት በክልሉ እስከ ቀበሌ ድረስ የደም ልገሳ መርሐግብር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። የደም ልገሳ ፕሮግራሙ የወላድ እናቶችን እንዲሁም በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ደም የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ህይወት መታደግን አላማ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በክልሉ የደም ልገሳ ተግባርን ከዘመቻ ስራ ባለፈ የህብረተሰቡ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ደም ከለገሱ ዜጎች መካከል አቶ ሙሉሰው ጌጡ እንደገለጹት፤ ደም በመለገስ በደም እጦት የሚቸገሩ ህሙማንን ህይወት መታደግ ይገባል ። በበጎ ፈቃድ ደም በመለገስ ሌሎችን ከመርዳት ባለፈ የህሊና እርካታ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል። ዛሬ ደም ሲለግሱ ለ2ኛ ጊዜያቸው መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሙሉሰው፤ ተግባሩን ለማስቀጠል ከመወሰናቸው ባለፈ ሌሎችም አርአያነታቸውን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል። ወይዘሮ ውዴ እምቢያለ በበኩላቸው፤ ደም በመለገስ በደም እጦት ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በመድረስ ለወገን አለኝታነታቸውን ለማሳየት መገኘታቸውን ጠቁመዋል። ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉትን የደም ልገሳ ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል። በክልሉ የዛሬው የደም ልገሳ ዘመቻም በሁሉም ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች ሁሉንም ህብረተሰብ በማሳተፍ እየተካሄደ መሆኑን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
በነቀምቴ ከተማ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ ቅድመ ጥንቃቄ ተደርጓል
Jul 22, 2026 109
ነቀምቴ፤ ሀምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፡- የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ክረምቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ የቅድመ ጥንቃቄ ስራ ማከናወኑን አስታወቀ። የከተማው ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሀላፊ ረጋሳ ሞሲሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የክረምቱን መግባት ተከትሎ የከተማው ውሀ ማፋሰሻዎች በቆሻሻ በመዘጋት ለአደጋ እንዳያጋልጡ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መንገድ ሰፊ የማፅዳት ስራ ተከናውኗል። የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን የማጽዳት ተግባር ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በተያያዘም በጎርፍ ሳቢያ ሊከሰት የሚችል የመሬት መንሸራተትና የተለያዩ ተላላፊ በሽታዎችን አስቀድሞ ለመከላከል አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል። ህብረተሰቡም በአካባቢ ፅዳትና ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃትና በባለቤትነት ስሜት እንዲሳተፍ ተከታታይ የህዝብ ንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በከተማው የኬጀማ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ማቲያስ ሁንዴሳ በበኩላቸው በከተማው በክረምት ወቀት ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል ዘንድሮ በተጀመረው የፅዳት ስራ ላይ መሳተፋቸውን ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ በቆሻሻ የተዘጉ የውሀ ማፋሰሻዎችን አስቀድሞ ማስከፈቱ ጎርፍ ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ያደርስ የነበረውን ጉዳት ማስቀረት ማስቻሉን አመልክተዋል። ሌላኛው የጨለለቂ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ጥላሁን በቀለ በበኩላቸው፤ በከተማው እየተከናወነ ያለው የውሃ ማፋሰሻዎችን የማፅዳት ስራ ህብረተሰቡን ከጎርፍና ከተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። ከተማ አስተዳደሩ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ የአደጋ ስጋቶችን ለመቀነስ በየቀበሌው የሚሰጠው ተከታታይ ትምህርትና መረጃ ህብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅና ስራውን በስኬት እንዲያከናውን ትልቅ አቅም መፍጠሩን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
ኢኮኖሚ
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል
Jul 22, 2026 31
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ። የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በመድረክ ላይ እንደገለጹት፤ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማጠናከር የዜጎች ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል። በበጀት ዓመቱ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የርቀት ሥራ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል። በዚህም መሠረት በሶስቱ ዋና ዋና አማራጮች ለአምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ከአምስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን በላይ ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል። ለዜጎች የተፈጠሩት የስራ እድሎች በግብርና፣ በአገልግሎት፣ በኢንዱስትሪ፣ በውጭ አገር የስራ ስምሪት እና በርቀት የተፈጠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ይህ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የፓርቲው ቅርብ አቅጣጫና ድጋፍ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመዋል፡፡ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ከ 631 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ስምሪት በማመቻቸት ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል። ከተለያዩ የአረብ ሀገራት በተጨማሪ ወደ ስድስት የአውሮፓ ሀገራትም ዜጎችን መላክ መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡ ሀገራት እያሳዩ ባሉት ፍላጎት መሠረት ስምምነቶች ተፈራርመው ዜጎች አስፈላጊውን የሙያና የቋንቋ ስልጠና አግኝተው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የዲጂታል እና የርቀት ሥራ (Remote Work) የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም በርቀት ሥራ ከ41ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ ለዚህም የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ጋር የተደረገ ማስተሳሰር ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ 70 የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ ማዕከላት የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራም እንዲቀርፁ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል
Jul 22, 2026 45
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በ2018 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል ከተከናወኑ ተግባራት እና የገበያ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል። በዚህ መድረክ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የክልል አመራር አባላት ተሳትፈዋል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እና ገበያን ለማረጋጋት በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሪፖርት አቅርበዋል። በቀረበው ሪፖርት መሠረት የምርት አቅርቦትን በዘላቂነት ለማሻሻል ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ 15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት መገኘቱን አመልክተው፤ ይህም ከእቅዱ እኳያ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የነዳጅ አቅርቦትን በተመለከተ፤ ከዓለም አቀፍ የነዳጅ መስመር መዛባት እና የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ተግዳሮቶች ቢኖሩም ታቀዶ ከነበረው 5 ነጥብ 23 ሚሊዮን ሜትሪክ ኩብ የእቅዱን 91 በመቶ ነዳጅ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል። በሕገ-ወጥ አሰራር እና በከፍተኛ የፍላጎት እድገት ምክንያት በገበያው ላይ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የገበያ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በሀገር ደረጃ ከተለዩት 7 ሺህ 628 የአካባቢ ገበያዎች መካከል የ3 ሺህ 670ዎቹ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ተጠናቋል ብለዋል። በተጨማሪም 804 አዳዲስ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም 32 ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የግብይት ትስስርን ለማጠናከር 1 ሺህ 352 የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በትስስሩ የተሳተፉ ሲሆን፤ ለነዚህ ማህበራት ከ3 ነጥብ 33 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የሪቮልቪንግ ፈንድ ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል። በተከናወኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፤ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና የምግብ ድጋፍ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከገበያ ጋር ተያይዞ ያሉትን ችግሮችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት ሕገ-ወጥ ኬላዎችን የማንሳት ሥራ መከናወኑን ጠቁመው፤ ለኑሮ ውድነት መባባስ ምክንያት የሆኑ ችግሮች እየተቃለሉ መምጣታቸውን ገልጸዋል። በገበያ ቁጥጥር እና ሕግ ማስከበር ተግባራት፤ በሕገ-ወጥ ንግድ በተሰማሩ 347 ሺህ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል። በነዳጅ በሕገ-ወጥ አሰራር በተሳተፉ 688 አካላት ፣የንግድና ፀጥታ አካላትን ጨምሮ ሕጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፤ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ነዳጅ ተወርሶ 781 ሚሊዮን ብር በቅጣት ገቢ መደረጉን ገልጸዋል። በቀጣይ በ2019 በጀት ዓመት ምርትና አቅርቦትን ማጠናከርን ዋና ትኩረቱ ያደረገ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ መያዙን ገልጸው፤ በዚህም የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርና እንቅስቃሴዎችን በልዩ ትኩረት የማስፋት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል። በሁሉም የምርት ዓይነቶች ላይ የ10 በመቶ እድገት ታሳቢ በማድረግ ለመስራት የተያዘ ሲሆን፤ ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ልዩ ድጋፍ በማድረግና የገበያ ትስስርን በማጠናከር የግብይት ስርዓቱን ለማረጋጋት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። የገበያ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት ሁለተኛው ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስከ 2019 ዓ.ም ድረስ ሙሉ ለሙሉ የይዞታ ማስከበርና ማረጋገጥ ስራዎችን የማጠናቀቅ እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ ቢያንስ የ500 ገበያዎችን ደረጃ የማሻሻል ስራ ይሰራል ብለዋል። የእሁድና ቅዳሜ ገበያዎችን ቁጥር ወደ 3 ሺህ 439 ለማድረስ እቅድ መያዙን ጠቁመው፤ በግብይት ሰንሰለቱ ውስጥ ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን በህግና አሰራር ብቻ ለመፍታት የቁጥጥርና የሬጉላቶሪ አቅምን የማሳደግ ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል።
በዞኑ የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለኩታ ገጠም እርሻና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቷል
Jul 22, 2026 47
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ፡፡ በዞኑ በአበሽጌ ወረዳ የኩታ ገጠም የመኸር አዝመራ ልማት የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በዞኑ የመኸር ሰብልን ውጤታማ ለማድረግ በ177 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የተለያዩ ሰብሎች ለምተዋል፡፡ በኩታ ገጠም እርሻውም በቆሎ፣ ማሽላ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ ሩዝ እና ጤፍ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ለግብአት አቅርቦት፣ ለባለሙያ ድጋፍ፣ ለሰብል እንክብካቤና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር በበኩላቸው፤ በወረዳው በዘንድሮው የመኸር ወቅት ግብአትና የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴን በመጠቀም አርሶ አደሮች ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የአበሽጌ ወረዳ የአቡኮ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዘሪሁን ቱሉ፤ የግብርና ባለሙያዎች የሚያደርጉላቸውን ድጋፍ ተጠቅመው አራት ሄክታር ኩታ ገጠም መሬታቸውን በበቆሎ ማልማታቸውን ተናግረዋል። የበቆሎ ሰብሉን ከአረም እና ከበሽታ በመከላከል የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አርሶአደር ሃይሉ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ ሶስት ሄክታር የበቆሎ ማሳቸውን እየተንከባከቡ በመሆናቸው የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ አመላክተዋል። ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በ30 ሄክታር መሬት ጤፍን በኩታ ገጠም በማልማት እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ዳዊት አሰፋ ናቸው። ምርታማነታቸውን ለማረጋገጥም የተሻሻለ የጤፍ ዝርያን መጠቀማቸውንና የባለሙያ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በዞኑ እየተካሔደ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
Jul 22, 2026 73
ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው የ2018 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድረክ በጎንደር ከተማ ዛሬ ተካሒዷል። የመምሪያ ኃላፊው አቶ ገድፍ ጌትነት በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የለውጡ መንግስት አሻራ የሆነው የኮሪደር ልማት ከተሞችን በማዘመን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዞኑ ስር በሚገኙ በአራት የከተማ አስተዳደሮችና በዘጠኝ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል። ለኮሪደር ልማት ስራው ህብረተሰቡ ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዋጽኦ በማድረግ ለልማት ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጡን ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል ባለፈ፤በ2019 በጀት ዓመት የልማት ስራውን ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋፋት ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው አንስተዋል። ከተሞችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋሲል ሠንደቁ ናቸው። ይህም ከተሞቹን በማዘመን ለነዋሪዎች፣ ለጎብኝዎችና ለንግድ የተመቹ ከማድረግ ባለፈ የክልሉን ገጽታ ለመገንባት ተደማሪ አቅም እንደሚሆኑ አስረድተዋል። በዞኑ የአንባ ጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ፅህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ወልዴ ባዘዘው እንደገለጹት ፤ የኮሪደር ልማቱ የማሕበረሰቡን አኗኗር ለማዘመን የሚያስችል ነው። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር ልማት ሁለት ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የሳይክልና የእግረኛ መንገድ መገንባት መቻሉን አመልክተዋል። ሌላው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የማክሰኝት መሪ ማዘጋጃ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉአለም ሙጨ በበኩላቸው፤ የኮሪደር ልማት ስራው ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው ብለዋል። በአዲሱ በጀት ዓመትም የኮሪደር ልማት ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል የከተማዋን እድገት ለማፋጠንና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በመድረኩ ላይ በዞኑ የሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች፣የወረዳ ከተማ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የባዮጋዝ የምርምር ማዕከል ለአፈር ለምነት እና ለግብርና ምርታማነት እገዛ እያደረገ ነው
Jul 22, 2026 154
ሀምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፡- ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው የባዮጋዝ የምርምር ማዕከል ለአፈር ለምነት እና ለግብርና ምርታማነት እድገት እገዛ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን የግብርና ስራን በማዘመን እና በማስፋፋት ዙሪያ የድርሻውን እየተወጣ መሆኑ ተመላክቷል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤፍሬም ዋቅጅራ ለኢዜአ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተገነባው የባዩ ጋዝ የምርምር ማዕከል ሀይልን ከማመንጨት በተጨማሪ የስልጠና አገልግሎት እየሰጠ ነው። በዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ይጣል የነበረውን ተረፈ ምርት በመሰብሰብ ባዮ ጋዝ በማምረት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ማእከሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት የአፈር ለምነት ለመጠበቅና ለግብርና ምርታማነት እድገት እገዛ እንዲያደርግ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ቱሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የግብርና ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። በተለይም የምርምር ማዕከሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማዘጋጀት ለአርሶ አደሩ ከማሰራጨት በተጨማሪ፣ ዩኒቨርሲቲው በ150 ሄክታር መሬት ላይ ለሚያከናውነው የግብርና ሥራ ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የመካኒካል ትምህርት ክፍል መምህርና የባዩ ጋዝ የምርምር ማዕከል ፕሮጀክት አስተባባሪ ሸዋንግዛው ወርቃገኘሁ የምርምር ማዕከሉ በዘርፉ ብቁ ባለሞያዎችን ለማፍራት የስልጠና ማዕከል ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በሁለተኛ ዲግሪ 18 ተማሪዎች በዘርፉ እየሰለጠኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የባዩ ጋዝ የምርምር ማዕከሉ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመሆን በትብብር እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አስተባባሪው እንደ ሀገር ባዩ ጋዝን ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ታዳሽ ኃይል ምህንድስና ተማሪ የሆኑት ኢየሩስ አንተነህ እና ቤተልሔም አባዲ፤ ባዮ ጋዝ እንዴት እንደሚመረትና ወደ ጠቃሚ ኃይል እንደሚቀየር በተግባር የተደገፈ በቂ እውቀት እያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም ህብረተሰቡን በተጨባጭ ሥራዎች ለማገልገል የሚያስችላቸውን የማጠናቀቂያ የጥናት ጽሑፍ እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሌላኛዉ ተማሪ ፊሊጶስ ከፈለኝ በዩኒቨርሲቲው በዘርፉ እያገኘ ያለው እውቀት በምርምር ማዕከሉ ውስጥ በሚሰሩ ተጨባጭ ስራዎች የተደገፈ መሆኑን ተናግሯል። ተማሪው አክሎም በቀጣይ የኢትዮጵያን የባዩጋዝ ምርት አቅም ለማሳደግ እንደሚሰራ አመላክቷል።
በክልሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታ ለሚያጎለብቱ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷል
Jul 20, 2026 708
ጅግጅጋ፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚያጎለብቱ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አስታወቁ። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የክልሉን ኢኖቬሽን ማዕከል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማጎልበት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ ትኩረት ተሰጥቷል። በዚህም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ የኢኖቬሽን ማዕከልም በቴክኖሎጂ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት እና በዘርፉ አቅማቸውን ለማጠናከር ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት ለቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት የሰጠው ትኩረት አበረታች ለውጦች እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመው ይህንኑ ለማስፋት እየተሠራ ነው ሲሉ አክለዋል። በቀጣይም ማዕከሉን የማስፋት፣ በግብአትና፣ በሙያተኞች የማጠናከር ስራ በትኩረት እንደሚከናወን አመላክተዋል። የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ መሀመድ አሊ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅም የሚገነባና ክህሎታቸውን የሚያጎለብት መሆኑን ተናግረዋል። ማእከሉ የ2030 የዲጂታል እቅድ ስትራቴጂን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቁመው ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የተቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል። ማዕከሉ በድረገጽ ልማት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በመረጃ ትንተና፣ ሳይበር ሴኩሪቲ፣ ዲጂታል ዲዛይን አገልግሎት በመሳሰሉት ስልጠና የሚሰጥበት መሆኑን ተናግረዋል። ማዕከሉ በተጨማሪም አነስተኛ ንግዶችን የማልማትና የምርምር አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። በስነ ስርአቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ወጣቶች፣ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ የማቋቋም ርዕይ ሀገሪቱን የአፍሪካ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል ያደርጋታል
Jul 20, 2026 760
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ (AIU) የማቋቋም ርዕይ ሀገሪቱን የአፍሪካ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል የሚያደርግ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት ክፍል ኃላፊ ሶፊያ አሺፓላ ገለጹ። ኢትዮጵያ የጀመረችውን ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ዲጂታል ቴክኖሎጂን የኢኮኖሚ ምሰሶና የልማት ማሳለጫ መሣሪያ በማድረግ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂና የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ መርሐ ግብርም የዜጎችን የዲጂታል፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎትና የዳታ ሳይንስ ዕውቀትና ክህሎት የሚያበለጽግ አቅም እየፈጠሩ ነው። የዲጂታላይዜሽን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የመንግሥት አገልግሎቶችን ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ በቁልፍ የኢኮኖሚ መሣሪያነት በማገልገል ስኬት አስገኝቷል። የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት ክፍል ኃላፊ ሶፊያ አሽፓላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መስክ ወሳኝ መደላድል በመፍጠር አበረታች ውጤት እያመጣች ነው። በተለይም የሰው ሠራሽ አስተውሎትን ልማት ለማፋጠን ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የወሰደችው ተነሳሽነት ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የተጀመረው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት አብዮትም በሌሎች የአፍሪካ አገራት ተመሳሳይ ኢንቨስትመንቶች እንዲስፋፉ በር የሚከፍት ታሪካዊ ክስተት እንደሆነ አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልማት የለውጥ ጉዞ ላይ ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ የማቋቋም ርዕይ የወደፊቱን ትምህርትና ምርምር በተሻለ ጥራት በመቅረጽ አገሪቱን ፈር ቀዳጅ እንደሚያደርጋት አስረድተዋል። ይህም የሰለጠነና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት፣ በአፍሪካ የፈጠራ፣ የምርምርና የሰው ኃይል ልማትን የሚያፋጥን ዓለም አቀፍ የልማት አብዮት መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ የትምህርት መሠረተ ልማትን የማስፋፋት ተግባር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለአፍሪካ አገራት ጭምር በአርአያነት የሚወሰድ መሆኑን አስገንዝበዋል። በአንደኛና በቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤታማነትም ሕፃናትንና ታዳጊዎችን በተሻለ ዕውቀትና ክህሎት በማበልጸግ ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የመንግስት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው
Jul 20, 2026 161
ባህር ዳር፤ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የመንግስት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የታገዙ በማድረግ ስኬታማ ስራዎች ማከናወን መቻሉን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ። የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የነበረውን ስራ አፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ፤ የመንግስት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ በማዘመን የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ተችሏል። በተለይም ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ቴክኖሎጂን በማዘመን በኩል የተሰጠው ልዩ ትኩረት ዘርፉ በፍጥነት እንዲያድግና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻሉን ተናግረዋል። ለዚህም የቴክኖሎጂ የእውቀት ክፍተትን በስልጠና ለመሙላት፣ የፈጠራ አቅምን ለማሳደግ እና በዘርፉ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል። በክልሉ ከ725 ሺህ በላይ ወገኖችን ለማሰልጠን ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በሁለት ዙር ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ወገኖችን ስልጠናውን መውሰዳቸውን ተናግረዋል። በዘርፉ ስኬታማ ስራዎችን ለማከናወን የተቻለው በየደረጃው የሚገኘው አመራር በልዩ ቁርጠኝነት ስራዎችን ለማከናወን በመቻሉ ነው ብለዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ6 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ወገኖችን የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ባለቤት ማድረግ እንደተቻለ አመልክተዋል። በአዲሱ በጀት ዓመትም በገጠርና በከተማ 12 ሚሊዮን ለሚደርሱ ዜጎች የዲጅታል መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከዚህ ባለፈም የተቋማትን አገልግሎትን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከእጅ ንክኪ የራቀ ለማድረግም በዋና ዋና ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም በክልል ደረጃም በባህር ዳር፣ ደሴና ወልዲያ ከተሞች አገልግሎቱን በማስጀመር የህዝብ ቅሬታዎችን መፍታት መቻሉን ገልፀዋል። በክልል ደረጃ በተቋቋመው መሶብ የአንድ ማዕከል ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ በ15 ተቋማት 65 አገልግሎቶችን መስጠት መቻሉን አስገንዝበዋል። በቀጣይም በጎንደር፣ ደብረ ታቦር ፣ ደብር ብርሃንና ኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን ለማስፋት የግንባታና ሌሎች ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አብራርተዋል። ቴክኖሎጂን ማስፋፋት የህዝብን እንግልትና ድካም የሚቀንሱ አሰራሮችን ይበልጥ በማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተው፤ ለውጤታማነቱ ሁሉም በላቀ ቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ስፖርት
የስፔኑ ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
Jul 20, 2026 393
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተጠናቋል። በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የኮከብ ተጫዋቾች ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በዚሁ መሰረት የስፔኑ አምበል ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች በመባል ተመርጧል። የስፔኑ ተከላካይ ፓዎ ኩባርሲ የወጣት ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አግኝቷል። ኡናይ ሲሞን (ስፔን ) የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኗል። ፈረንሳዊው ኪሊያን እምባፔ 10 ግቦች በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሽልማት ወስዷል።
ስፔን አርጀንቲናን በመርታት የዓለም ዋንጫን አነሳች
Jul 20, 2026 280
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ መርሐ ግብር ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። ማምሻውን በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የአርጀንቲና የአማካይ ተጫዋች ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ93ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በ90 ደቂቃ አሸናፊ ባለመገኘቱ ቡድኖቹ ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርቷል። ተቀይሮ የገባው ፌራን ቶሬስ በ106ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ስፔን ፍጹም የበላይነት ወስዳለች። የአርጀንቲናው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በርካታ ያለቀላቸው ኳሶችን አድኗል። ተጋጣሚዋ አርጀንቲና በጨዋታው ደካማ እንቅስቃሴ አድርጋለች። ቡድኑ የግብ እድል መፍጠር ተስኖታል። ውጤቱን ተከትሎ ስፔን ለሁለተኛው የዓለም ዋንጫን አንስታለች። አውሮፓዊቷ ሀገር እ.አ.አ በ2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 19ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ እንደነበረች ይታወሳል። አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ክብሯን ማስጠበቅ አልቻለችም። ለአራተኛ ጊዜ ዋንጫ የማንሳት ህልሟ አልተሳካም።
“ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ” ታላቁ ሩጫ በሐረር ከተማ ተካሄደ
Jul 19, 2026 256
ሀረር ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ 2018” የ10 ኪሎ ሜትር ታላቁ ሩጫ ውድድር በሐረር ከተማ ተካሄደ። በውድድሩ በተለያየ የዕድሜ ክልል ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አትሌቶች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የውጪ አገር ቱሪስቶች፣ አርቲስቶችን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ የሩጫ ውድድር ቀደም ሲል በደብረብርሃን፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ አርባ ምንጭና በቆጂ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን የፍጻሜ ውድድሩ ዛሬ በሐረር ከተማ ተካሂዷል። በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ በተካሄደው የታላቁ ሩጫ ውድድርን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሀመድና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው አስጀምረዋል። በ10 ኪሎ ሜትር በተካሄደው በዚህ ውድድር በወንዶች ሴና ገመቹ ሲያሸንፍ፤ ምህረት አወቀና ኢብራሂም መሀመድ በቅደም ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል። በሴቶች ራሔል እምቢበል ስታሸንፍ አምረን ሸምሱና አዚዛ መሀመድ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል። በሁለቱም ጾታ ከተደረገው የአትሌቶች ውድድር በተጨማሪ በአዋቂዎች፣ በወጣቶች፣ በታዳጊ ሕጻናትና በሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በሁለቱም ጾታዎች የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ተከሂዷል። ውድድሩን ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዳ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሀመድ አበርክተዋል። “ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ 2018” ታላቁ ሩጫ ውድድር ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ በመተባበር ያዘጋጁት የጎዳና ላይ ውድድር መሆኑ ተገልጿል። ውድድሩ በሕዝቦች መካከል አብሮነትን የማጠናከር፣ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን የማሳደግ እንዲሁም አዲስ የስፖርት መነቃቃትን የመፍጠር ዓላማ እንዳለውም ተመላክቷል።
አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ክብሯን ታስጠብቃለች ወይስ ስፔን ከ16 ዓመታት በኋላ ዳግም አሸናፊ ትሆናለች?
Jul 19, 2026 501
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ መርሐ ግብር ስፔን እና አርጀንቲና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም አይኖች አርፈውበታል። ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም ይካሄዳል። ስፔን በግማሽ ፍጻሜው ለዋንጫ ታልፋለች ተብላ የተጠበቀችውን ፈረንሳይን 2 ለ 0 በመርታት በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ለፍጻሜ ቀርባለች። የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት አርጀንቲና እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለተከታታይ ሁለት የዓለም ዋንጫዎች ለፍጻሜ ደርሳለች። አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስታልፍ የአሁኑ ለሰባተኛ ጊዜ ነው። ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም በዓለም ዋንጫው አንድ ጊዜ ተገናኝተዋል። እንግሊዝ እ.አ.አ በ1966 ባዘጋጀችው ስምንተኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ በምድብ ሁለት ተገናኝተው አርጀንቲና 2 ለ 1 አሸንፋለች። ሉዊስ አርቲም ለአርጀንቲና ሁለቱን ግቦች አስቆጥሯል። ፒሪ የስፔንን ጎል በወቅቱ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ሀገራቱ በውድድር እና ወዳጅነት ጨዋታዎች 14 ጊዜ ተጫውተው በተመሳሳይ ስድስት ጊዜ ድል ቀንቷቸዋል። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ስፔን በ14ቱ ጨዋታዎች ላይ 22 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ አርጀንቲና 18 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፋለች። እ.አ.አ በ2018 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 19ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ስፔን ብቸኛ ክብሯን ያገኘችበት ነው። ተጋጣሚዋ አርጀንቲና ከዚህ ቀደም ስድስት ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ ሶስቱን በማሸነፍ በውድድሩ ስኬታ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። አርጀንቲና የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈች ከጀርመን እና ጣልያን ጋር በተመሳሳይ አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያነሳች ሀገር ትሆናለች። በተጨማሪም የደቡብ አሜሪካ ሀገር ከጣልያን እና ብራዚል በመቀጠል ዓለም ዋንጫን በተከታታይ ያነሳች ሀገር ለመሆን ትጫወታለች። ሌላኛው ትኩረት የሳበው ጉዳይ ሀገራቱ የየአህጉራቸው ውድድሮች የወቅቱ አሸናፊ መሆናቸው ነው። ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ፣ አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካ አሸናፊ ናቸው። የአውሮፓ እና የደቡብ አሜሪካ ቁንጮዎች የሚያደርጉት ፍልሚያ ትኩረትን ስቧል። አውሮፓዊቷ ስፔን እ.አ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫን ከማንሳቷ በፊት የ2008 የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ ነበረች። ስፔን የወቅቱ የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት ሆና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ መቅረቧ ገጠመኙን የተለየ አድርጎታል። በዘንድሮው ዓለም ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በዛሬው ጨዋታ ልዩ ትኩረት አግኝቷል። የ39 ዓመቱ ሜሲ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ስምንት ጎሎችን በማስቆጠር እና አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል ከኪሊያን እምባፔ (10 ጎሎች ሲያስቆጥር እና አራት የግብ እድሎችን ፈጥሯል) በኮከብ ግብ አግቢነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዓለም ዋንጫው 21 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ በምንጊዜውም የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ዝርዝር ውስጥ በእምባፔ አንድ ጎል ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ሜሲ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ለማጠናቀቅ እና የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መሪነት ይዞ ለመቀጠል ሁለት ግቦችን ማስቆጠር እና ለግብ የሚሆን ኳስ ማቀበል ይጠበቅበታል። አርጀንቲናዊው ኮከብ በዓለም ዋንጫ በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ (33) እና በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል (12) የክብረ ወሰን ባለቤት ነው። እድሜው በገፋበት ሰዓት እያሳየ ያለው ብቃት አድናቆት እንዲጎርፍለት አድርጓል። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አንድ ግብ ያስቆጠረው የ18 ዓመቱ ላሚን ያማል ከስፔን በኩል ትኩረት የተሰጠው ተጫዋች ነው። ስፔን በጨዋታው ላይ የኳስ ቁጥጥርን መሰረት ያደረገ እና የክንፍ መስመር የማጥቃት እንቅሰቃሴ ላይ ያተኮረ የአጨዋወት ስልት ወደ ሜዳ ይዛ ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል። ተጋጣሚዋ አርጀንቲና የተደራጀ የመከላከል ቅርጽ በመያዝ ኳስ ሲያገኙ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ግብ የማስቆጠር አጨዋወትን ትከተላለች ተብሎ ይጠበቃል። ጨዋታው ጠንካራ እና በታክቲክ የታጠረ እንደሚሆን ይጠበቃል። የ46 ዓመቱ ስሎቬኒያዊ ስላቫኮ ቪንቺች ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። አሸናፊው ሀገር ከዋንጫው በተጨማሪ የ50 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያገኛል። ሁለተኛ የሚወጣው ቡድን የ33 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ይበረከትለታል። የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አጠቃላይ በውድድሩ ላይ ለተሳተፉ ሀገራት የ871 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጅቷል። አሜሪካዊው ዝነኛ ድምጻዊና ራፐር ፖስት ማሎን (Post Malone) የዓለም ዋንጫው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ዋና አቅራቢ (Headline Performer) ነው። ከእሱ በተጨማሪ ሮቢ ዊሊያምስ፣ ኒኮል ሸርዚንገር እና ላውራ ፓውሲኒ የተባሉ ታዋቂ ድምጻውያን እንዲሁም ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፣ የሆሊውድ ተዋናዩ ቶም ክሩዝም ልዩ እንግዳ ሆኖ ይቀርባል። በእረፍት ሰዓት (Halftime Show) ላይ ደግሞ ማዶና፣ ሻኪራ፣ ጀስቲን ቢበር፣ ቢቲኤስ (BTS) እና በርና ቦይ ከኮልድ ፕለይ (Coldplay) ጋር በመሆን በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀርበው የእረፍት ሰዓት ትዕይንት ላይ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።
አካባቢ ጥበቃ
በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ
Jul 22, 2026 2
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦በቀጣዮቹ አስር ቀናት የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ መሰረት፣ ከሐምሌ 14 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት አስር ቀናት ውስጥ የዝናብ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የበለጠ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ አሰታወቋል። በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቷ ክፍሎች የተሻለ የዝናብ ሥርጭት መጠን ይኖራቸዋል። በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ሰሜን የሀገራችን አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ የሀገሪቷ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ ብሏል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ነው ኢንስቲትዩቱ የጠቆመው። በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቷ አካባቢዎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ገልጿል። በተጨማሪም በኤሊ ዳር፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ ቡሬ፣ አሳይታ፣ ሁንዱፎ፣ ገዋኔ፣ ሚሌ፣ ዳሊፋጊ፣ አይሻ፣ ጉሊና፣ አዋሽ አርባ፣ ባቲ፣ ዶሎ አዶ፣ ዳዋ፣ አሶሶ፣ ጎዴ፣ ቋራ፣ አዋሽ ፈንታሌ፣ ጭፍራ፣ ላሬ፣ መተሀራ እና፣ ላሬ፣ ፉኙዶ አካባቢዎች ከሚኖረው የቀን ከፍተኛ የፀሀይ ሀይል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሙቀት ይኖራቸዋል። ኢንስቲትዩቱ በቀጣይ ቀናት የሚኖረውን መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀም እና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክር ሀሳብን ከወዲሁ መተግበር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ መሳተፋቸው የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጎልበት ያግዛል
Jul 22, 2026 89
ደብረብርሃን ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ መሳተፋቸው የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጎልበት ያግዛል ሲሉ የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ገለጹ። ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ያሳተፈው የክረምት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ -ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጠባሴ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር ዛሬ ተጀምሯል። ወጣቶቹ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና መሰረት የሚጥሉ በመሆናቸው ተሳታፊነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ መካከል ከጌዲዮ ዞን ዲላ ከተማ የመጣችው ወጣት ትንሳኤ ትዕዛዙ እንደገለጸችው፤ የአገራችን ከፍታ የሚረጋገጠው አንድነታችን በመጠበቅ ለጋራ አላማ በአንድነት ስንቆም ነው። የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች የአረንጓዴ አሻራቸውን በማስቀመጥ የሀገር አንድነትና እድገትን ለማጽናት የምንሰራበት ነው ስትል አንስታለች። ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የመጣው ወጣት አላዛር ታሪኩ በበኩሉ ፤በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በጋራ የሚተከሉት ችግኞች በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣ አብሮነትንና አንድነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ናቸው ብሏል። ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ስራ ወጣቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባሀል፣ ወግና እሴትን እንዲረዳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው የተናገረው። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የተከልናቸው ችግኞች አገራዊ አንድነትና ትብብርን ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው ያለችው ደግሞ ከአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከሚሴ ከተማ የመጣችው ሰዓዳ ኢንድሪስ ናት። በተለይም በህዝቦች መካከል በተሳሳተ ትርክትን በማጥፋት ዘላቂ ፍቅርን፣ ሰላምና ልማትን ለማጎልበት የሚያስችል ነው ስትል ተናግራለች። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በከተማዋ ተስማሚ የአየር ንብረትና ስነ ምህዳር ለመጠበቅ ሰፊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። በተለይም እየተስፋፋ የመጣው የኢንዱስትሪ ልማትና የኢንቨስትመንት ፍሰትን ይበልጥ ለማሳደግ የላቀ ድርሻ እንደሚኖረው ነው የገለጹት። የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክቦ ለታለመለት ግብ በማብቃት ከተማዋን ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች የተመቸች ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል። ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ መሳተፋቸው አንድነት፣ ሰላምና ፍቅርን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚረዳም ነው የተናገሩት። የደብረ በርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መርሻ አይሳነው በበኩላቸው፤ በተያዘው የክረምት ወቅት ዘጠኝ ነጥብ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ የደን፣ የውበትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች እየተተከሉ ነው ብለዋል። በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከሁለት ሺህ 300 ሄክታር መሬት በላይ ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት ዓመታት የለሙ አካባቢዎች አሁን ላይ ጥቅም መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል።
በዞኑ ከ26ሺ ሔክታር መሬት ላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞች እየተተከሉ ነው
Jul 22, 2026 84
መቱ፣ሐምሌ 15/2018(ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን በተያዘዉ ክረምት ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ዝርያቸው የተሻሻሉና በአጭር ጊዜ ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ እንደተናገሩት፤በዞኑ በሽታን የሚቋቋሙ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጡ እና ምርታማነታቸው የተረጋገጠ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በማቅረብ የተከላ ስራ እንዲጀመር ተደርጓል። በዚሁ መሰረት በተያዘው የክረምት ወቅትም ከ26ሺ ሔክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ ከ200 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝን የመትከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ወቅት የቡና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እንዲቻል ልማቱን የማስፋትና የእንክብካቤ ስራዎችም እንዲጠናከሩ እየተደረገ ነው ብለዋል። በአዲስ መሬትና በደረቁ የቡና ተክሎች ምትክ የቡና ችግኝ የመትከል ሥራ በሰፊው እየተከናወነ ሲሆን፣ ያረጁና ምርት የማይሰጡትን በመጎንደል ውጤታማ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ የሁሩሙ ወረዳ አርሶ አደር ታምሩ ፈሪሳ ፤ከቡና ልማቱ በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን በበጋው ወቅት የጎነደሏቸውን የቡና ተክሎች በመንከባከብ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የቡና ልማቱን በማስፋት ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን እየተከሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። አርሶ አደር ጌታቸው ጂፋርም በግብርና ባለሙያዎች በመታገዝ የቡና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት ላይ መሰማራታቸውን ነው የሚገልጹት። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የተሻሻሉ የቡና ችግኝን በስፋት በመትከል ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በኢሉባቦር ዞን ከ72 ሺ በላይ አርሶ አደሮች በቡና ልማት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መሆናቸውን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአፍጥር የተፈጥሮ ደን ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር እያስቻለ ነው
Jul 22, 2026 185
ወልቂጤ ፤ ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአፍጥር የተፈጥሮ ደን ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር እያስቻለ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የአፍጥር የተፈጥሮ ደን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ከሚገኙ የተፈጥሮ ደኖች ከቀዳሚዎች መካከል ይጠቀሳል። ደኑን በመጠበቅ ብዝሃ-ህይወትን ለማቆየትና የአየር ጸባይ ለውጥን ለመከላከል እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚኖረውን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፋይዳ ለማጉላት እየተሰራ ነው። ተግባሩን ለማስቀጠልም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ትልቅ አጋዥ ሆኖ እያገለገለ መሆኑም ተጠቅሷል። የቸሃ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጠቅልል አባድየ እንዳሉት 40 ሄክታር መሬት የሚሸፍነው የአፍጥር ደን ከሰውና እንስሳት ንክኪ ነጻ እንዲሆን ጥበቃ እየተደረገለት ነው። ደኑ የአካባቢውን የስነ-ምህዳር ሚዛን እንዲጠበቅና ወጣቶች በደኑ በንብ ማነብ እንዲሁም በመኖ ሳር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ደኑ ለአፍጥር ከተማም ውበትና የመስህብ ስፍራ በመሆን እያገለገለ መሆኑን አመልክተዋል። የደን ጥበቃው የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ ለከርሰ-ምድር ውሃ ምንጭነት ያለውን አቅም ለማስቀጠል በክፍት ቦታዎች ላይ ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ስራ መከናወ ኑን ጠቅሰዋል። ህዝቡ ለደኑ ጥበቃና እንክብካቤ ከማድረግ ባለፈ ሳሳ ባሉ የደኑ ክፍሎች የሀገር በቀል ዛፎች እየተከለ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በአፍጥር ደን ዙሪያ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ ደንጭዛ ጃጃተ ናቸው። እንደ ዝግባ፣ ጽድ፣ ዋንዛና ሌሎች የሀገር በቀል ዛፎች ጥበቃ የማድረግ ማህበረሰባዊ እሴትም ለስራው ውጤታማነት ማገዙን ተናግረዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ ደንን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ ባህልን ከአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ጋር በማጣመር እየሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ፍቃዱ አመርቻ ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ደኑን በመንከባከብና በክፍት ቦታዎች ላይ ሃገር በቀል ችግኝ በመትከል ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ዘጠኝ ሆነው በመደራጀት የሃገር በቀል ዛፎች ችግኝ በማፍላትና በማዘጋጀት ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር እያቀረቡ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ወጣት ያለው ተረጋ ነው። በአካባቢው ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የገበያ እድል እንደፈጠረላቸውና የአፍጥር ደንም ለሚያዘጋጇቸው ችግኞች የዘር ምንጭ መሆኑን አመልክቷል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 20197
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 13088
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 11886
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 11785
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የሌማት ትሩፋት፡ የኢትዮጵያ ግብርና በአዲስ ምዕራፍ
Jul 22, 2026 101
በሳባ ስለሺ መግቢያ ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ የምግብ ዋስትና ለመቀየር ተግዳሮት ሆኖባት የቆየ ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግስት በተጀመረው ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ጉዞ የዘርፉ ታሪክ በተጨባጭ እየተቀየረ ነው። የዚህ ለውጥ አብይ ማሳያ የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ የሆነው "የሌማት ትሩፋት" መርሃ ግብር አንዱ ነው። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ልማት ጉዞ በአዲስ ምዕራፍ የቃኘ ነው። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ሲሆን፣ በዋናነት በእንስሳት ሀብት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኩራል።በእንስሳት ሀብት ልማት ረገድ የወተት ላሞችን፣ የዶሮ (ሥጋ እና እንቁላል)፣ የንብ ማነብ (ማር) እና የዓሣ እርባታን በስፋት የሚያካትት ነው።የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ከምግብ ሸማችነት ወደ አምራችነት በማሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው። በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የኑሮ ውድነትን በማቃለል፣ የአርሶና አርብቶ አደሩን ገቢ በማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ ያለመ ነው። የሌማት ትሩፋት ለምን አስፈለገ? ፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል በመጠቀም፣ ለዘመናት የዘለቀውን የምግብና ሥነ-ምግብ ዋስትና ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተነደፈ ነው። መንግስት ለዚህ መርሃ ግብር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የሚገኘውም፣ ሀገሪቱ ያላትን ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተጨባጭ እሴትና የሀገር ውስጥ ተጠቃሚነት ለመቀየር እንዲሁም የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ነው። ባለፉት አራት ዓመታት ምን ተከናወነ?፡- ባለፉት አራት ዓመታት በተተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወተት፣ የእንቁላል፣ የሥጋ፣ የዓሣ እና የማር ምርቶችን ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ተከናውኗል። ለዚህ ስኬት በቂና ጥራት ያለው የእንስሳት ተዋጽኦ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሰፊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና የማዳቀል ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ የአዳቃይ ቴክኒሻኖችን አቅም መገንባት፣ የፈሳሽ ናይትሮጂን አቅርቦትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለዘርፉ ተዋናዮች ማስተላለፍ ተችሏል። እንዲሁም የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የእንስሳት እርባታ ደህንነታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ እና አስፈላጊውን መሰረተ ልማት በማሟላት ረገድ ላለፉት አራት ዓመታት ቅድሚያ ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል። በመስኩ ምን ተጨባጭ ውጤት ተገኘ ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገሪቱን የምግብና ስነ-ምግብ ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በዜጎች ዘንድ የቆየውን አመለካከት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግቧል። በተለይም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ተወስኖ የነበረውን የግብርና እንቅስቃሴ ወደ ከተሞች በማስፋት፣ ህጻናት፣ እናቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከእንስሳት ተዋጽኦ ማግኘት የሚገባቸውን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እንዲያገኙ አስችሏል። ይህ ተነሳሽነት የከተማ ግብርናን በማስተዋወቅ ዜጎች በቤታቸው እንስሳትን በማርባት ከራስ ፍጆታ ባለፈ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በመሆኑም፣ ባለፉት ዓመታት በመስኩ የተመዘገቡት ስኬቶች እንደሚያሳዩት፣ መርሃ ግብሩ ዜጎች በተቋማት ተቀጥረው ከመስራት ይልቅ በዘርፉ ተሰማርተው የራሳቸው ስራ ኖሯቸው ለሌሎችም የስራ እድል እንዲፈጥሩ አድርጓል። ይህ የመንግስት ያላሰለሰ ጥረት፣ የዜጎችን የስነ-ምግብ ፍላጎት ከማሟላት አልፎ፣ ጤናማ እና ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ትውልድ በመገንባት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በአሀዛዊ መረጃ የተደገፉ የዘርፉ ስኬቶች ፡- የግብርና ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው አኃዛዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተጀመረ በአራት ዓመታት (2014 ዓ.ም -2018 ዓ.ም) ውስጥ በእንስሳት ምርታማነት አስደናቂ ለውጥ ተመዝግቧል። በወተት ምርት፦ መርሃ ግብሩ ሲጀመር የነበረው 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር አድጓል። በእንቁላል ምርት፦ ከነበረበት 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ፣ ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ከፍ ብሏል። በዶሮ ሥጋ ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 90 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 253 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በማር ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 146 ነጥብ 7 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 428 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በአሳ ምርት፦ የውሃ አካላትንና ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በአግባቡ በመጠቀም የተከናወነው የአሳ ጫጩት ስርጭት፣ ከ300 ሺህ ወደ 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን አድጓል። ይህ ውጤት ሀገሪቱ በእንስሳት ተዋጽኦ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንዴት ማጎልበት እንደተቻለ በግልጽ ያሳያል። ዘርፉ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ምን አበረከተ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገር ውስጥ የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ኢትዮጵያ ከእንስሳት ተዋፅኦ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ብቻ 24 ነጥብ 2 ሺህ ቶን የተቀነባበረ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ 128 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል። ማጠቃለያ፦ በዘርፉ የተመዘገበውን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ አርብቶ አደር እና አርሶ አደሩ ከተለመደው ባህላዊ የእንስሳት አረባብ ዘዴ ለማላቀቅ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ጤና አገልግሎትን የማዘመን፣ እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማምረት አቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው። በተጨማሪም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የማህበረሰቡን ቅንጅት ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አሰራር መዘርጋት፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያለው የገበያ ትስስር መፍጠርና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ እንዲሁም አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ጠንካራ መሰረት ማኖር ይቻላል። በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ ሀገራዊ ብልፅግና ለመቀየር የተጀመረ ውጤታማ መንገድ መሆኑን ባለፉት አራት ዓመታት አሳይቷል። ይህ ከተጠናከረ ሀገሪቱ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥ ያለመችውን ትልም ከማሳካት የሚያስቆማት ነገር እንደማይኖር አመላካች ነው።
ሀገራዊ ምክክር፡ለተሻለች ኢትዮጵያ የተከፈተ በር
Jul 22, 2026 91
በኢትዮጵያ ለዓመታት የቆዩ አለመግባባቶችና ችግሮች ብዙ ናቸው።እነዚህ አለመግባባቶች የሀገር ሰላም፤አንድነት፤ልማት እድገትና የዜጎችን የወደፊት ተስፋ የሚፈታተኑ ሆነው ቆይተዋል። አለመግባባቶችን በኃይል ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ አልቻሉም። ስለዚህ የጥላቻን፣የበቀልንና የመከፋፈልን ዑደት ለማቆም የሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ውይይት፣መደማመጥና መግባባት መሆኑ በስፋት እየታመነ መጥቷል። በዚህ መነሻ፣ኢትዮጵያ በታሪኳ ታላቅ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ እያካሄደች ትገኛለች።ይህ ምክክር ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበትና የጋራ መፍትሄ የሚፈልጉበት መድረክ ሆኗል። የሀገራዊ ምክክሩ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር ሳይሆን፣ የሁሉንም ወገን ድምጽ በማዳመጥ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። ይህ ምክክር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተወከሉ ዜጎች ድምጽ የሚሰማበት፣አመለካከቶች የሚተነተኑበትና የጋራ መፍትሄዎች የሚፈለጉበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኗል። ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ ወገኖችን በአንድነት በማሰባሰብ፣የከረሙ ችግሮችን በተቀናጀ መንገድ በመፍታት፣ የፖለቲካዊ፣የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ለውጦችን ለማምጣት ይረዳል። እንዲሁም ኢትዮጵያን ወደ አንድነት፣ሰላምና ብልጽግና ለማሸጋገር የሚያገለግል ታላቅ መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ብለው ያመኑ ኢትዮጵያዊያንም ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ እና ከውጭ ጭምር በመምጣት በአዲስ አበባ ተገናኝተው ስለሀገራቸው እየመከሩ ይገኛል። በሁሉም ክልሎች፣በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች ሕዝብ የወከላቸው ተመካካሪዎችም በንዑስ ቡድኖች በመከፋፈል በተመደቡበት አጀንዳ ላይ መመካከር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል። በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ሂደት ጠንካራ መግባባትን የሚፈጥር ግልፅና ተስፋ ሰጪ ምክክር እያደረግን ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመካካሪዎች በበኩላቸው ገልጸዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ጋር የሚያያዝ ነው። ዛሬ በምክክር የምንገነባው መግባባት፣ነገ ለመጪው ትውልድ የተረጋጋች፣የተባበረች፣ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን የሚያስረክብ መሠረት ይሆናል። ይህ ሀገራዊ ምክክር የጋራ መግባባት ባህልን ለማጠናከር፤ለፀናችና ለተሻለች ኢትዮጵያ የተከፈተ ትልቅ በር ነው።
የኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት፤ ራስን ለመቻል የተደረገ ሽግግር
Jul 21, 2026 364
በ አሸናፊ በድዬ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት፣ የብዙኃኑ ዜጋ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ፣ እንዲሁም ለአጠቃላይ ሀገራዊ ዕድገት (ጂዲፒ) ከ33 በመቶ በላይ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሠረታዊ ዘርፍ ነው። ይሁን እንጂ ላለፉት አሥርት ዓመታት የሀገሪቱ ግብርና በዝናብ ጥገኝነት፣ በባህላዊና ኋላ ቀር የሞፈርና ቀንበር የአመራረት ዘይቤ፣ በአፈር መሸርሸር እንዲሁም በዝቅተኛ ምርታማነት ምክንያት የወቅቱን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት መመጠንና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ተስኗት ቆይቷል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለረድኤት እና ለውጭ እርዳታ እጇን እንድትዘረጋ፣ እንዲሁም ለዕለት ጉርስ የሚሆን እህል ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታስገባ ተገዳ ነበር። ይሁን እንጂ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች፣ በእርሳቸው የቅርብ አመራር ሰጪነት የተጀመሩት አዳዲስ ፖሊሲዎችና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ዘርፉን ሙሉ በሙሉ እየቀየሩት ይገኛሉ። ይህ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የሀገሪቱን ግብርና ከባህላዊና ለዕለት ፍጆታ ብቻ ከሚመረተው የህልውና ግብርና ወደ ዘመናዊ፣ በቴክኖሎጂ ወደታገዘና ከፍተኛ ትርፍ ወደ የሚያስገኝ የንግድ ግብርና እያሸጋገረው ይገኛል። በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችን፣ የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመገንባት የተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎችን እና የዘርፉን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎች እንመልከት፦ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስኬት ኢትዮጵያ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በየዓመቱ ለስንዴ ፍጆታ ማሟያ የሚሆን እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የውጭ ምንዛሬ ታወጣ ነበር። ይህን ከፍተኛ ወጪ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እና የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የቆረጠችበት ትልቁና ህያው ማሳያ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ፕሮጀክት ነው። ይህ ተግባር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ልዩ ክትትል፣ የመስክ ምልከታና አነሳሽነት የተጀመረ ሲሆን፣ በአጭር ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ የግብርና ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ተጨባጭ ተአምር ያሳየ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ሆኗል። ሀ. የአመራረት ስር ነቀል ለውጥ ቀደም ሲል ስንዴ በኢትዮጵያ ይመረታል ተብሎ የሚታሰበው በክረምት ዝናብ ብቻ እና በደጋማ አካባቢዎች ነበር። ይህንን የተለመደ አሠራር በመለወጥ፣ በበጋ ወቅት ምንም ዝናብ በሌለበት ያሉትን ወንዞች፣ የውሃ አማራጮችን እና የከርሰ-ምድር ውሃን በመጠቀም በመስኖ የማልማት ሥራ በስፋት ተተገበረ። ይህም አርሶ አደሩ በአንድ መሬት ላይ በዓመት ሁለት እና ሦስት ጊዜ ሰብል እንዲያመርት በማስቻል የምርት ወቅትን በእጥፍ አሳድጎታል። ባህላዊውን ዝናብ ጠባቂነት ወደ ቴክኖሎጂና ውሃ መሪ ግብርና የለወጠ ታሪካዊ ሽግግር ነው። ለ. የመሬት ስፋትና የምርት ዕድገት ፕሮጀክቱ በ2012 ዓ.ም. አካባቢ በጥቂት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በሙከራ ደረጃ የተጀመረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሄክታር መሬቶችን ማሸፈን ችሏል። የመሬት ስፋት አድማስ፦ መጀመሪያ ላይ በደጋማ ቦታዎች ብቻ የነበረው ስንዴ፣ አሁን ላይ ሰፊና ምቹ ሜዳዎች ወደሚገኙባቸው ዝቅተኛና ሞቃታማ የቆላ አካባቢዎች (Lowlands) እንዲስፋፋ ተደርጓል። የምርታማነት መጨመር፦ በኩታ ገጠም (Cluster) እርሻ አሠራር፣ በምርጥ ዘር አቅርቦት እና በሜካናይዜሽን (በትራክተርና ኮምባይነር) አጠቃቀም ምክንያት በሄክታር የሚገኘው የምርት መጠን በአማካይ ከ35 እስከ 45 ኩንታል እና ከዚያ በላይ አድጓል። ይህም በአጠቃላይ ሀገራዊ የስንዴ ምርትን በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኩንታሎች እንዲጨምር አድርጓል። ሐ. ከገቢ ምርት ወደ ውጭ ንግድ፡- ይህ ስልታዊ ስኬት ኢትዮጵያን ለዓመታት ተጭኗት ከነበረው የስንዴ ተረጂነትና ከውጭ የማስገባት ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በኩራት ያላቀቃት ታላቅ ድል ነው። ራስን መቻል፦ ሀገሪቱ በውስጥ ምርቷ ፍላጎቷን ማሟላት መቻሏ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠሩ የጂኦፖለቲካ ቀውሶች (ለምሳሌ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ያስከተለው የስንዴ እጥረት) በኢትዮጵያ ላይ የከፋ የምግብ እጥረት እንዳያመጡ ትልቅ ጋሻ ሆኗል። ወደ ውጭ መላክ፦ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈውን ምርት ለጎረቤት ምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ገበያ በይፋ መላክ የተጀመረበት ታሪካዊ ምዕራፍ ተመዝግቧል። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የምግብ ዋስትናዋን በራሷ አቅም ከመገንባቷም በላይ፣ ግብርናን አዲስ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል። የሌማት ትሩፋት" ንቅናቄና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ማለት የዜጎችን ሆድ በካሎሪ (በእህል ምርት) መሙላት ብቻ ሳይሆን፣ የአዕምሮና የአካል እድገትን የሚወስነውን የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ ማለት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ያስጀመሩት የሌማት ትሩፋት ሀገራዊ ንቅናቄ ዋና ስትራቴጂካዊ ግብም ይሄው ነው፦ በሀገሪቱ የተመጣጠነ ምግብ በየቤተሰቡ ደረጃ ማሳደግ የታለመለት ግብ ነው።ይህ ንቅናቄ በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ተገንብቶ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል። የእንስሳት ሀብትና የወተት ልማት፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚውን የእንስሳት ሀብት የያዘች ቢሆንም፣ ቀደም ሲል የሚገኘው የወተት ምርት እጅግ ዝቅተኛ ነበር። አራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን የወተት ላሞችን ለማዳቀል የተያዘው እቅድ እየተሳካ ይገኛል። በንቅናቄው ከፍተኛ የወተት ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ በማቅረብ፣ ዘመናዊ የእንስሳት መኖ አጠቃቀምን በማስፋፋት እና በኩታ ገጠም አሠራር የወተት ማቀነባበሪያዎችን በመገንባት የወተት ምርት በዓመት ከሰባት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማሳደግ አስችሏል። የዶሮና የእንቁላል ምርት ማዕበል፦ በዝቅተኛ ቦታና ወጪ ፈጣን የፕሮቲን ምንጭ ለማግኘት የዶሮ እርባታን ማዘመን ቁልፍ እርምጃ ነበር። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የ45 ቀናት የውጭ ድቅል ጫጩቶች ለገጠርና ለከተማ ነዋሪዎች ተሰራጭተዋል። ይህ አሠራር ቀደም ሲል በዓመት ጥቂት እንቁላል ብቻ ከምትጥለው የሀገር ውስጥ ዶሮ ተሻሽሎ፣ በቀጣይነት ለገበያና ለቤት ውስጥ ፍጆታ የሚውል የእንቁላልና የሥጋ ምርትን አሳድጓል። ባለፉት ዓመታት 160 ሚሊዮን ጫጩቶችን ለማሰራጨትና 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን እንቁላል ለማምረት የተያዘው ግብም በውጤታማነት እየተጓዘ ይገኛል። የንብ ማነብ (የማር ልማት)፦ ኢትዮጵያ ያላትን የበለጸገ የተፈጥሮ ዕፅዋት እምቅ አቅም በመጠቀም ባህላዊ ቀፎዎችን በዘመናዊ ቀፎዎች የመተካት ሥራ በስፋት ተከናውኗል። ይህም በአንድ ቀፎ የሚገኘውን የማር ምርት ከ7 ኪሎ ግራም ወደ 20-30 ኪሎ ግራም በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጨማሪ የገቢ ባለቤት አድርጎታል። ለዚህም የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ጉልህ ሚና በማበርከት ላይ ይገኛል። የአሳ ሀብት ልማት፦ በተፈጥሮ ሐይቆች ላይ ብቻ የነበረውን ጥገኝነት በመስበር፣ በየገጠሩ ሰው ሠራሽ የውሃ ማቆሪያዎችና ኩሬዎችን በመጠቀም የዓሣ እርባታ ተጀምሯል። ይህ ሥራ በተለይ የወንዝ ተፋሰስ ባላቸው አካባቢዎች ማኅበረሰቡ የዓሣ ምርትን በምግብ ሰንሰለቱ ውስጥ እንዲያካትት አግዟል። የብዙኃኑ ተስፋዎች በኢትዮጵያ ግብርና ላይ የመጣው ለውጥ ወቅታዊ ስኬት ብቻ ሳይሆን የወደፊቷን ጠንካራ ሀገር የመገንባት መዋቅራዊ መሠረት ነው። ሀገሪቱ ለዘመናት ከነበረችበት የድርቅና የእርዳታ እህል ጠባቂነት ታሪክ ወጥታ፣ ስንዴን ወደ ውጭ የምትልክ፣ በሌማት ትሩፋት የተመጣጠነ ምግብን የምታረጋግጥ እና አረንጓዴ ዐሻራን በመጠቀም የአየር ንብረቷን የምትጠብቅ ታላቅ ሀገር መሆን እንደምትችል በተግባር አሳይታለች። እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሲቀጥሉ፣ የኢትዮጵያ ግብርና የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በራስ አቅም ከማሟላት አልፎ የምሥራቅ አፍሪካና የመላው አህጉሪቱ የምግብ ዋስትና ማዕከል (Breadbasket of Africa) የመሆን ዕቅዷን ሙሉ በሙሉ እውን እንደሚያደርገው ምንም ጥርጥር የለውም።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 383
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 93
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 383
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4396
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 3503
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 10555
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20776
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 13812
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 19563
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 6861
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ
Jun 26, 2026 4708
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ፍኖቷ ለአፍሪካ አርአያ ሆና አሳይታለች... የአፍሪካውያን ቀንዲል ናት። የክፉ ቀን መሸሸጊያቸው፣ የመከራ ጊዜ መጽናኛቸው፣ የነጻነት ተምሳሌትና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በረጅም ዘመናት ታሪካዊ መስተጋብር የተፈጠረ የሀገረ መንግሥት መዋቅር ባለቤት ናት። በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ ምድሯን ሰንጥቀው በሚያልፉ ወንዞቿ የምትታወቅ አገር ናት። የተለያዩ ማዕድናት በብዛት የሚገኙባት ከመሆኗም በላይ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች ሕብር ሠርተው፣ ተስማምተው የሚኖሩባት የታሪክ ማህደር ናት። ይሁን እንጂ ይህ ታሪካዊ ግርማ ሞገስና የነጻነት አርማነት፣ በውስጣዊ የፖለቲካ ጉዞዋ ውስጥ ካጋጠሟት መዋቅራዊ ስብራቶችና የሥልጣን ፍትጊያዎች ሊታደጋት አልቻለም። ለዘመናት በሀገሪቷ የሰፈነው የሥልጣን ሥርዓት የሰፊውን ሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ፣ በጥቂት የሕብረተሰብ ክፍሎችና ልሂቃን ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር። ይህ አካሄድ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አንዱን ሥርዓት በሌላው እየተካ፣ የተተካው አገዛዝ ደግሞ የባሰ ጭቆናን ይዞ የሚመጣበትን አዙሪት ፈጥሯል። ከብዙ መቶ ዓመታት የዘውድ አገዛዝ በኋላ የመጣው ወታደራዊ ሥርዓት፣ በመቀጠልም ለ30 ዓመታት ገደማ የዘለቀው የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀገሪቱንና ዜጎቿን ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርገው አልፈዋል። ይህ ዓይነቱ የመከራና የጭቆና ሰንሰለት ግን በ2010 ዓ.ም በተቀጣጠለው ሀገራዊ ለውጥ ተገርስሶ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምሕዳር ተሸጋግሯል። ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ስንመረምር፣ ሀገሪቷ ከአሮጌውና ከተለመደው የአፈና ሥርዓት ወጥታ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ አቅም ይዛለች። ይህ ወቅት የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት በተግባር የተረጋገጠበትና የሐሳብ ብዝኃነት የተስተናገደበት ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም የሥልጣን ማራዘሚያ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ዋና ዋና ተቋማት ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲደራጁ መደረጉ የለውጡ ትልቁ ስኬት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የለውጡ የመጀመሪያ ፍሬ የታየው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቆቁሞ ሕዝቡ ያሳየው የባለቤትነት ስሜት የዴሞክራሲ ናፍቆቱን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህንን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ፣ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ የነቃ አስደናቂ የፖለቲካ ተሳትፎ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ታሪካዊ መድረክ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን የማይናወጥ አቋም አሳይተውበታል። ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ረጅም ሰዓታትን ተሰልፈው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችንና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በሙሉ በትዕግሥት በመሻገር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህ ሂደት የሚያሳየው ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭነቱን በተግባር የተረዳበትና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞና የውስጥ መረጋጋት ሁልጊዜም በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ጉዳይ ነው። ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችና የጂኦፖለቲካ ጫናዎች ቢኖሩም፣ ይህ በስኬት የተጠናቀቀው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቷን የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊነት በተግባር ያስመሰከረ ሆኗል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነፃነትና በሰላም ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳይ በራሷ ዜጎች ፍላጎት የመወሰን ሙሉ አቅም እንዳላት ለዓለም አሳይቷል። ምርጫው ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት አስከብሯል። የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በሁከት ሳይሆን በሕዝብ የላቀ ውሳኔ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካለፈችባቸው የፖለቲካ ስብራቶች በላይ ከፍ ብላ እንድትቆም አድርጓታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተደማጭነትና የድርድር አቅም ከፍ የሚያደርግ ነው። የምርጫው ዝርዝር ስኬቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ስንመለከት፦ 👉የአፈሙዝ ድምፅንና የጽንፈኛ ዛቻን ያሸነፈው የሕዝብ ጽናት ግንቦት 24 ታሪካዊ ቀን ናት። በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ በየምርጫ ጣቢያው በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠው ሕዝብ ያሳየው የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጽናት ማረጋገጫ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍና ሕዝቡን ለማስፈራራት የተቃጡ የአፈሙዞች ድምፆችና የሁከት ዛቻዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ሕዝብ ከመምረጥ አላፈገፈገም። መራጮች የጽንፈኛ ኃይሎችን ዛቻ ወደ ጎን ትተው፣ የአካላቸውን ሕመም፣ የበሽታን ሥቃይ፣ አልፎ ተርፎም የወሊድ ምጥንና የቅርብ ዘመድ ሞት ያመጣውን ጥልቅ ሐዘን በሕሊናቸውና በሥጋቸው ተሸክመው ነበር ረጅሙን ሰልፍ ተሰልፈው ይበጀኛል ያሉትን በካርዳቸው የመረጡት። ይህ የሚያሳየው እውነት ለኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ሰላማቸውን የሚገዙበት፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚወስኑበት ብቸኛ የነጻነት አዋጃቸው መሆኑን ነው። ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ፣ በኃይል ወይም በሁከት ሥልጣን ለመያዝ ምኞትና የቆየ የሥልጣን ናፍቆት ላላቸው ወገኖች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግልጽና የማያሻማ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይልና የሁከት አካሄድን እንደማይቀበል፣ በድምፅ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሕጋዊ ሥርዓትን ለማፅናት እንደሚታገል አረጋግጧል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአፅንኦት ሲያነሱ፤ "የዘመናችን ዲሞክራሲ አስተምህሮቱ ሰላምና ዕድገት፣ ቋንቋው ደግሞ መምረጥና መመረጥ ብቻ በመሆኑ የፖለቲካ ቅኝታችሁንና አካሄዳችሁን ከዚሁ ስልጡን መስመር ጋር ማስተካከል ይበጃችኋል። ካሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ መሆኑን እነሆ እንዳየነው መሠረት የጣለ ስለሆነ ይህኑ ስልጡን መንገድ ለመቀበል የማትፈቅዱ ሁሉ ግን ግፋ ቢል የዘመናችን የፖለቲካ ድርሳን ሲጻፍ ልትሆኑ የምትችሉት የግርጌ ማስታወሻ ብቻ ነው።" ብለዋል። ስለሆነም ከዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ አካሄድ ውጭ የሚደረግ ሙከራ የጥፋት ተዋናይ ከመሆን ባሻገር ለሀገር የሚያተርፈው አንዳች ነገር እንደሌለ በዚህ ስሑት መንገድ ላይ የሚገኙ አካላት ሊገነዘቡ ይገባል። 1. ምርጫው በቁጥሮች ሲገለጽ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጉልህ የሚጠቀሱ አኃዛዊ መረጃዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በውጭ ሀገር አሳትሞ ካስመጣ በኋላ፣ ከምርጫው 4 ቀናት በፊት በሀገሪቱ ባሉት ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በታማኝነትና በጥንቃቄ ማድረስ ተችሏል። ይህንን እጅግ ግዙፍና ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑት የቦርዱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ብቻ መሆናቸው ተቋማዊ አቅሙ ምን ያህል እንደጎለበተ ማሳያ ነው። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ እንደተናገሩት፤ የቦርዱ ሠራተኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎች በዕረፍት ቀናትና በሌሊት በመጋዘን ውስጥ ጭምር እያደሩ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራዎችን በትጋት አከናውነዋል። ሩቅና ተደራሽነታቸው አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳቁሶችን በእግር፣ በእንስሳት ጀርባና በጀልባ ጭምር በማጓጓዝ፣ ወንዞችን ለመሻገር የራሳቸውን የፕላስቲክ ጀልባ ሠርተው ሀገራዊ አደራቸውን ተወጥተዋል። በድምፅ መስጫ ቀን ሥራቸውን ከንጋት እስከ ንጋት በልዩ ብርታት ፈጽመዋል። ይህ ልብ የሚነካ እውነታ የሚያሳየው፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የተናጥልና የጋራ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ሰፊ ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 80 የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል። 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች ተወዳድረዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲዎች ፖሊሲዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት የክርክር መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ፓርቲዎች ከምርጫው ውጭም ራሳቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበትን ባህል ያዳብራል። የመራጮችና አስፈጻሚዎች ቁጥር፦ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ምርጫውን ለማስፈጸም ከ350 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ታዛቢዎችና ወኪሎች፦ ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያሰማሯቸው ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ እንዲሁም 63 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል። ለመራጩ ሕዝብ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት መስፈርቱን ላሟሉ 169 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። እንዲሁም 21 ሚሲዮኖችና አንድ የውጭ ሀገር የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ምርጫውን ተመልክተዋል። የአየር ሰዓት አጠቃቀም፦ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ነፃ የአየር ሰዓት የማግኘት መብት ስለነበራቸው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 752.5 ነፃ የሬዲዮ ሰዓት፣ 57.5 ነፃ የቴሌቪዥን ሰዓትና 576 የጋዜጣ ኮለምን በዘመናዊ የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ተደልድሎ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። መገናኛ ብዙኃን፦ 73 የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን የወከሉ 1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥና 45 የውጭ ጋዜጠኞች ለዘገባ ሥራ ተሰማርተዋል። የሕግ ማሻሻያ እና ዲጂታላይዜሽን፦ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ተሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተተክቷል። ቦርዱ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚመራ፣ እያንዳንዳቸው 2 ሰዓት የሚወስዱ 19 የክርክር መድረኮች በቦርዱ ተዘጋጅተዋል። 14ቱ በአማርኛ፣ 5ቱ በክልል ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ አፋርኛ) ተካሂደው በሰባት መገናኛ ብዙኃን በፕራይም ታይም ተላልፈዋል። አካታችነት፦ 28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ከ20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ተደርጓል። የቅሬታ አፈታትና ክትትል፦ የቅድመ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት (Early Warning System) ተዘርግቷል። 663 የምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ልዩ የአጣሪ ጉባኤ ተደራጅተው 129 አቤቱታዎችን መርምረዋል። የሕግ ጥሰት በተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል። 2. ጠንካራና ገለልተኛ ተቋም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሀገር ውስጥ አቅም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠነ ሰፊ ተቋማዊና ሕጋዊ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ከመሆኑም በላይ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ሀገራዊ አቅምን በተግባር ያሳየ ነበር። የዚህ ምርጫ ትልቁ ትርፍ ጠንካራና የማይናወጡ ብሔራዊ ተቋማትን መገንባት መቻላችን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳየው ፍጹም ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ብቃት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተግበር አቅም፣ ተቋማት ከግለሰቦችና ከፖለቲካ ጫና በላይ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው። ይህም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አስተማማኝ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ነው። ለምርጫው ስኬት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮችን በትዕግሥት በማስተናገድ፣ ብቁ አስፈጻሚዎችን በማሰማራትና ሂደቱን በታማኝነት በመምራት ረገድ ቦርዱ አድናቆት የተቸረው ሥራን ፈጽሟል። የሠራተኞቹ ቀንና ሌሊት መትጋት እንዲሁም በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት አመራር አባላት ያሳዩት ቁርጠኝነት የላቀና ለሀገር ኩራት የሆነ ተግባር ነው። በዚህ ምርጫ ውስጥ ትልቁን ትኩረት የሳበውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት ነው። ይህ ዘመናዊ አሠራር ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መጓዝ ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በነፃነት እንዲመዘገቡ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው የመራጮችን ማንነት በፎቶግራፍ ጭምር በማረጋገጡ በድምፅ መስጫ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ ግድፈቶችንና ማጭበርበሮችን በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል። የዚህ ሥርዓት ዋነኛውና ትልቁ ድል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የዚህን የቴክኖሎጂ ስኬት አስፈላጊነት ሲያብራሩ፤ "እነዚህ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቶች በውጭ ሀገር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የለሙ ሳይሆን በራሳችን ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው። ይህም ተቋሙን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነት ነፃ በማድረግ በራሱ አቅም እንዲቆምና ለወደፊቱ ማሻሻያዎችን በራሱ እንዲያከናውን መሠረት ጥሏል።" ይህ እርምጃ ቦርዱ የውጭ የቴክኒክ ጥገኝነትን በመቀነስ የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባትና የሉዓላዊነትና የደኅንነት ዋስትናን በራስ ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ የቻለበትን ስትራቴጂካዊ አካሄድ በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በውጭ ዜጎች ይሠራ የነበረው የቴክኒክ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መተካቱ የተሳካ የእውቀት ሽግግር መኖሩን አሳይቷል። 3. ሕጋዊ ማሻሻያዎች፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ዴሞክራሲ እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ዜጎች፣ በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ያለ ፍርሃትና ጫና፣ ደኅንነታቸው ተጠብቆ በፖለቲካዊ ሂደቶች እኩል መሳተፍ ሲችሉ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በታዛቢነት በመሳተፍ፣ ሴቶች የዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዲጠቀሙና በሂደቱ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል። ቦርዱ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም በላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አቋቁሟል። በተጨማሪም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ቀድሞ የነበረው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፣ ቦርዱ ይህንን መነሻ በማድረግ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። በነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ዋና መርህ የተወሰደ ነው። 4. ፈተናዎችን መጋፈጥና ገለልተኝነትን ማስከበር ይህ ሁሉ ስኬት ግን ያለ ፈተና አልመጣም። ምርጫው በተያዘለት ጊዜ አይካሄድም የሚሉ ጥርጣሬዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ተቋሙን ፈትነውት ነበር። ሆኖም ቦርዱ ጫናዎችን በመቋቋም ሕግና መርህን ብቻ ተከትሎ በመሥራት ምርጫውን ለስኬት ማብቃቱን ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ያረጋግጣሉ። ቦርዱ በምርጫው ወቅት የተቋሙን ነፃነት ከማንኛውም ዓይነት ጫናና ጣልቃገብነት በመጠበቅ በሕግና በመርህ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል። በምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ግድፈቶች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች በድምፅ መስጫው ቀን ጭምር አስፈጻሚዎችን አሰናብቷል፤ በምርጫ ውጤቶች ላይም ውሳኔ ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ ለሕግ የበላይነትና ለምርጫ ታማኝነት ያለውን ጽኑ አቋም ያሳያል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአንድ ተቋም ወይም በጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች በፀሐይና በዝናብ ሳይበገሩ በትዕግሥት የሰጡት ድምፅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች (እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ) እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው። 5. የምርጫው ግልጽነትና ዓለም አቀፍ እውቅና የምርጫውን ታሪካዊ ሂደትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል። ሂደቱን ለመዘገብ 73 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1 ሺህ 827 ጋዜጠኞች የዘገባ ሥራቸውን አከናውነዋል። ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እና ከ64 ሺህ በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። በተለይም በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 60 ሺህ 277 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን፤ 169 ድርጅቶች ደግሞ ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። በአህጉር ደረጃም የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና 26 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ታዛቢዎች ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ግልጽ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት መካሄዱንም አረጋግጠዋል። 👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምስክርነት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው ዕለት ሰላማዊ፣ ሥነ ሥርዓት የሰፈነበት እና ግልፅነት የታየበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ መተግበሩ ወጣቶችን መሳቡን፣ ዜጎች በትዕግሥት ሰልፍ በመያዝ ጥልቅ ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን፣ የሎጂስቲክስ ዝግጅቱ የተሟላ መሆኑንና የምርጫ ሰዓት መራዘሙ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በመስተንግዶ ረገድም ወንበሮችና የምግብ አቅርቦቶች መኖራቸው ረጅሙን ሰልፍ ታጋሽ እንዳደረገውና ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት "ቅኝ ግዛትን በአንድነት የተከላከለች Couch፣ ለአፍሪካ ነፃነት የቆመች እና የአህጉሪቱ ዋና ከተማ በሆነች ሀገር ውስጥ የተደረገው ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሊኮሩ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድም በሕዝቦች መካከል ያለውን የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ውይይት ይበልጥ ማሳደግ፣ ወደ ኋላ የተተዉ የሚሰማቸውን አካላት ወደ መድረኩ በማምጣት እና አካታችና የተባበረች ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የኡጋንዳ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 28 ጣቢያዎችን በመጎብኘት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቡድኑ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው መከፈታቸውን፣ በቂ ቁሳቁስና አስፈጻሚዎች እንደነበሩ፣ የሳጥኖች አስተሻሸግ የድምፅ ምስጢራዊነትን ያረጋገጠ መሆኑንና የድምፅ አሰጣጡ ያለምንም መሰናክል በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመታዘብ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ለአረጋውያን፣ ሕፃናት ለያዙ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱንና መራጮች የሚቀመጡባቸው ወንበሮች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማዘጋጀትና በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ኦፕሬሽናል አቅም ማሳየቱን አጉልቷል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት ያደነቀ ሲሆን፣ "ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ በተለይም የምርጫ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ አካታችነትን እና ተዓማኒነትን ለማሳደግ የተነደፉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂያዊ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተስተዋሉበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲል ቡድኑ ምስክርነታቸውን በአፅንኦት የገለጹት። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ "ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመዘገብ አብረን ለመሥራት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ሲሉ ነው የተደመጡት። 6. የምርጫው ውጤት፣ የሕዝቡ ጽናትና የአሸናፊው ፓርቲ ከባድ ሸክም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎችም በምክር ቤቶቹ ወንበሮችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስድስት፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሦስት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሦስት፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሦስት፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለት ወንበሮችን አሸንፈዋል። በሌላ በኩል ኦብነግ፣ ጉህዴን፣ አርጎባ አንድነት ጀበርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ኅብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ የጌዴዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው አንድ ወንበር ሲያገኙ 8 የግል ተወዳዳሪዎችም ምክር ቤት ለመግባት አሸንፈዋል። ይህን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች ጊዜያት ለየት የሚያደርገው ታላቅ ክስተት፣ መራጩ ሕዝብ በታጋሽነት ተሰልፎ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ወደር የለሽ ጽናት ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ይህንን የሕብረተሰብ አደራ "አሸናፊው ፓርቲ ትልቅ ሀገራዊ ሸክም የተጣለበት መሆኑን ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል። ፓርቲያችን በማኒፌስቷችንና በአጠቃላይ በምርጫ ቅስቀሳችን ወቅት ለሕዝብ ቃል የገባናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል" ብለዋል፡፡ 👉የፉክክርና የትብብር ሚዛን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር በቀጣይነት ሊመራበት የሚገባው ስልጡን መስመር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሀገር ግንባታ ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር በብሔራዊ ጥቅም ላይ በትብብር ለመሥራት ያለው አቋም የጸና መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በሰጡት አስተያየት፤ "ባለፉት ዓመታት የጀመርነውን በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ የሚሄድ ጥረታችንን በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሕዝቡን በማሳተፍ፣ በየጊዜው የሕዝቡን ግብረ መልስ በመስማት፣ ያንን እንደ ግብዓት ተጠቅመን የእቅድ አካል አድርገን ወደ ተግባር ለመተርጎም በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን።" ብለዋል። ይህ ዕይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሕዝብን ድምፅና ግብረ መልስ በየጊዜው የሚያዳምጥ፣ እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሀገር ጥቅም በጋራ የመሥራትን ስልጡንና አካታች የአሠራር ሥርዓት መከተል መጀመሩን ያሳያል። 7. ዴሞክራሲና ምርጫው የሚገለጽባቸው አራቱ ምሰሶዎች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማለት አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይና የሁለንተናዊ ብልጽግናችን መሠረት ነው። ብዝኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው በዴሞክራሲያዊ ምሰሶዎች ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። መንግሥት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና የማይተካና አዎንታዊ ሚና አላቸው። መራጩን ሕዝብ ከማስተማር፣ ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም ከማስቻል፣ እስከ ሰላም እሴት ግንባታና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የዜጎችን ባለቤትነት ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንደገለጹት፣ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። አንደኛው ምሰሶ፦ ምርጫ የሰላም ዋስትና መሆኑን መረዳት ነው። ሕዝቡ ልዩነቶችን በፀብና በአምባጓሮ ከመፍታት አዙሪት ተላቆ፣ በሰላማዊ መንገድ የመሻገር ባህልን መርጧል። በነቂስ ድምፁን መስጠቱ ኋላ ቀር የአመፃ መንገድን ለሚከተሉ ሁሉ "በቃችሁ" የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የሰፊው ሕዝብ ማዕበላዊ ድምፅ ከአሮጌው የብጥብጥ ባህል መላቀቅ እንደሚፈልግ ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛው ምሰሶ፦ የምርጫ ውግንና ከሕዝብ ጋር መሆኑን ማወቅ ነው። የምርጫ ተዓማኒነትና ክብሩ የሚገለጠው ሥልጣን ከሚመነጭበት ከሰፊው ሕዝብ ሉዓላዊ መብትና ፍላጎት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። ምርጫ ከሚሰጠው ኃላፊነት በላይ ለእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ሕይወት መሻሻልና ከሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል ተገንዝቧል። ሦስተኛው ምሰሶ፦ የምርጫው የፖሊሲ ሐሳቦችና አማራጮች ከፍታ የታየበት ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረኮች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያነሷቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሕዝቡ በጥንቃቄ አዳምጧል። እነዚህ ሐሳቦች ለሀገር ዕድገት፣ ለጠንካራ መንግሥትና ለሰከነ የፖለቲካ ባህል ግንባታ መሠረት እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕሊና ማስረፅ፣ በሰነድ በማዘጋጀትም መተግበር ይገባል። አራተኛው ምሰሶ፦ ምርጫ እንደ ማኅበራዊ ሀብት፤ ምርጫ ፖለቲካዊ ኩነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማኅበራዊ ሀብት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የዚህን ማኅበራዊ እሴት አንድምታ ሲያብራሩም "ሕዝባችን ስለ ኢትዮጵያዊ ቀናነቱና ፍቅሩ ጩኸቱን ሳይሆን የምርጫ ካርድ ድምፁን፣ ስላቅና ሃኬትን ሳይሆን ትሑትነቱን፣ የትኛውንም የፖለቲካ ሐሳብ ቢያራምድ እንኳን ማኅበራዊና ሀገራዊ ፍቅሩን ከጎኑ ላለው ወገኑ አለመንፈጉን ያየንበት እጅግ የተዋበ መድረክ ነበር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ምርጫ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ባልተናነሰ ሁኔታ ማኅበራዊ ፋይዳውም ከፍ ያለ ትልቅ የማኅበራዊ መሠረትን የሰጠው ነው።" ብለዋል። 8. የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ሚና፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስብራቶች የመፈወስ ዕድል ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት ጉዞዋ ውስጥ በርካታ አኩሪ ታሪኮችን ብታስመዘግብም፣ በሂደቱ ውስጥ የተፈጠሩና ዛሬም ድረስ ሀገራዊ አንድነቷን፣ ሰላሟንና የዴሞክራሲ ግንባታዋን እየተፈታተኑ ያሉ ሥር የሰደዱ የፖለቲካ ስብራቶች መኖራቸው አይካድም። እነዚህን ለዘመናት የዘለቁ ስብራቶች በመጠገን ረገድ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግር የሚችል ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ዕድል ይዞ መጥቷል። ምርጫው በበሰለና አካታች መንገድ በመመራቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ጉልህና አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ የሚችልባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አሉት። እነዚህም፦ የቅቡልነት ስብራትን ማከም፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመንግሥታት ሥልጣን አመጣጥ አብዛኛውን ጊዜ ከኃይል ፖለቲካ ወይም ሙሉ በሙሉ ነፃ ካልሆኑ ምርጫዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ለግጭቶች መነሻ ሲሆን ቆይቷል። ይህ ምርጫ ነፃና ታማኝ ሆኖ መካሄዱ አሸናፊው አካል ከሕዝብ የሚሰጠው እውነተኛ የሥልጣን አደራ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ይህም በገዥው አካልና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን በማደስ ረገድ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ባህልን መገንባት፦ ሥልጣንን በአፈሙዝ የመያዝ ልምድ ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ለድቀት የዳረጋት መሆኑ ብዙ ትምህርት ሰጥቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁሉም ወገኖች የሕዝብን ድምፅ አክብረው የሚቀበሉበት ድባብ መፈጠሩ ምርጫን ብቸኛ የሥልጣን መያዣና መልቀቂያ መንገድ የማድረግ አዲስና ጤናማ የፖለቲካ ባህል በሀገሪቷ ውስጥ እንዲለመድ ያደርጋል። በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ ማደስ፦ ሕዝቡ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት ባሉ ገለልተኛ መሆን በሚገባቸው ተቋማት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ሌላው ስብራት ሲሆን፣ ይህንንም ምርጫ በስኬትና በገለልተኝነት ማካሄድ መቻሉ የተቋማቱን ነፃነትና ብቃት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቷ የሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት መልሶ እንዲያገግም ያደርጋል። ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፦ አካታች የሆነ ምርጫ ማካሄድ መሣሪያ ያነሱ ወይም በሰላማዊ መንገድ የሚያምፁ የፖለቲካ ኃይሎች ቅሬታቸውን በሕዝብ ድምፅ እንዲፈትሹ በር ይከፍታል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶች ለመፈወስ የራሱ አሻራ ሊያኖር የሚችለው ሂደቱ ፍትሐዊ፣ ግልጽና በርካታ የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በንቃት የተሳተፈበት በመሆኑ ነው። በዚህም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ በራሱ ወደ ሰፊው ብሔራዊ ምክክር ለመሻገር እንደ ትልቅ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ማጠቃለያ፦ ምርጫው ለአፍሪካ ዴሞክራሲ የብርሃን ፍኖት አፍሪካ በፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፣ በወታደራዊ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ኢ-ሕገመንግሥታዊ መንገድ መምራት፣ የመንግሥት ግልበጣዎች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ስልጡን መንገድ ምርጫዋን ማጠናቀቋ ለአህጉሪቱ አዲስ ፍኖተ ዴሞክራሲ ሆና እንድትወጣ አድርጓታል። 'የአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካውያን መፍትሔዎች' የሚለውን መርህ በተግባር በማሳየት፣ የራሳችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በራሳችን አቅም መቅረጽ እንደምንችል ለዓለም አሳይተናል። በዚህ አስቸጋሪ አህጉራዊ ድባብ ውስጥ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከልና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ፍትሐዊ መንገድ በስኬት ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ለጫናዎች ሳትበገር፣ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ መድረክ ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ አህጉሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዲሞክራሲ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ ሰላምና ልማት ሊመጡ የሚችሉት በጠመንጃ ኃይል ሳይሆን ሕዝብ በነፃነት የራሱን መሪ በሚመርጥበት ስልጡን መንገድ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፦ "አህጉራችን ከዲሞክራሲ ውጭ ሌላ ምርጫ የላትም። ወደፊት ለመራመድ፣ ዕድገትን ለማረጋገጥና በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ዴሞክራሲ ብቻ ነው" ሲሉ በአፅንኦት ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና ሕጋዊ መሠረቷን በማጠናከር ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የተሻገረችበት እና የጋራ የትብብር አቅምን ያሳየችበት አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል። ለዚህም ስኬት በየሚናቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ታዛቢ ድርጅቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል። በምርጫው ወቅት የተሰጠው የሕዝብ አመኔታና ድምፅ ለተመራጮች ትልቅ አደራና ኃላፊነትን ጥሏል። ያሸነፉ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በመሸከም ለሕዝብ ፍላጎት ቅርብ የሆነ አገልግሎት በመስጠት፣ በታማኝነት፣ በቅንነትና ንጹሕ በሆነ ሕሊና በመሥራት የሕዝቡን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ግዴታ አለባቸው። የምርጫው ትልቁና የመጨረሻው ስኬት የሚለካው በተመራጮችና በሕዝብ መካከል በሚገነባው መተማመን፣ በሚረጋገጠው ዘላቂ ሰላምና ለሁሉም ተጠቃሚነትን በሚያሰፍነው ሀገራዊ ዕድገትና ብልጽግና ብቻ ነው።