በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች መካከል 12ቱን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በ13ቱ ጨዋታዎች 32 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሰባት ጎሎችን አስተናግዷል።
ቡድኑ በ36 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።
ተጋጣሚው መቻል በበኩሉ 13 ጨዋታዎችን አከናውኖ በዘጠኙ ድል ሲቀናው ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። 23 ጎሎችን ሲያስቆጥር ሰባት ግቦች ተጠቆጥረውበታል።
መቻል በ29 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና መቻል በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
በሌላኛው መርሐ-ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች መካከል አራቱን ያሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ በስምንቱ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪው አንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 12 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 21 ግቦችን አስተናግዷል።
ድሬዳዋ ከተማ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ 14 ጨዋታዎችን አድርጎ በሶስቱ አሸንፎ በዘጠኙ ተሸንፎ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል። ስምንት ግቦችን ሲያስቆጥር 16 ጎሎች ተቆጥረውበታል።
ባህር ዳር ከተማ በ10 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ ዙር በነበራቸው ግንኙነት ባህር ዳር ከተማ 2 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።