ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከመርሐ-ግብሮቹ መካከል ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ምሽት 12 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠቃሽ ነው።

ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ17 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

ሲዳማ ቡና ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናቸውም።

ጨዋታው ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት መንገድ ለመመለስ የሚያደርጉት ነው። 

ቡድኖቹ በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ሲዳማ ቡና 4 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

በሌላኛው መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሃዋሳ ከተማ በ35 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።  ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። 

ሃዋሳ ከተማ በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ድሬዳዋ ከተማ ካሸነፈ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል። 

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር በመጀመሪያ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

አርባምንጭ ከተማ ከነገሌ አርሲ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በሊጉ አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፈው አርባምንጭ ከተማ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።

ነገሌ አርሲ በ35 ነጥብ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።  

ነገሌ አርሲ ካሸነፈ በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። 

ቡድኖቹ በመጀመሪያው ዙር በነበራቸው ግንኙነት አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ21 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ27 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

ሸገር ከተማ ከ19ኛ ሳምንት የአቻ ውጤት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። ባለፉት አራት የሊጉ ጨዋታዎች ያላሸነፈው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ይፋለማል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም