የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተከበረ ነው
የካቲት 15/2018 (ኢዜአ):- የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሀዋሳ እየተከበረ ነው::
በበዓሉ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፣ ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።