በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል፤ ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል፤ ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል፤ ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከዚህ ቀደም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ቦታዎች አሁን ላይ በመስኖ ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ ነው ብለዋል።
የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ ደግሞ ለዚህ ተጠቃሽ አብነት ነው ሲሉም ነው የተናገሩት በመልዕክትቸው።
በአካባቢው የግል ባለሃብቶችን በማሳተፍ ሰፋፊ የፍራፍሬ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል።