ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር  ማንችስተር ሲቲ  ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የ20 ዓመቱ ታዳጊ ኒኮ ኦራይሊ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

ሉዊስ ሆል ለኒውካስትል ዩናይትድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ሁለቱም ቡድኖች ተቀራራቢ በሚባል ሁኔታ ግልጽ የግብ እድሎችን ፈጥረዋል። 

ሁለተኛው አጋማሽ ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 17ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ በ56 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። 

ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።  በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ በ36 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የሊጉ መሪ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር ነገ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው  የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም