ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ግንቦት 24ን እየጠበቅን ነው - የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 31
ጂንካ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በተመቻቸልን ዕድል ተጠቅመን የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ በመውሰዳችን ግንቦት 24ን በጉጉት እየጠበቅን ነው ሲሉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለፁ።   ተማሪ በቀለ ባሪሶ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ምርጫው የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በንቃት ተሳትፎ ለማድረግ መቻል ልዩ ስሜት አለው። ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድ ሥርዓት አካል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መሳተፍ አለበት ያለው ደግሞ ተማሪ አምሳሉ ዓባይነህ ነው።   በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያበቃውን የድምፅ መስጫ ካርድ በመውሰዱ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አንስቷል።   የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት መቅደስ አድማሱ በበኩሏ አብዛኛው ተማሪ በምርጫው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ ይህም ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድታለች።   ዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽ ኮሙኒኬሽን እና የቤተ ሙከራ ማዕከላትን በበይነ መረብ በማስተሳሰር ተማሪዎች ዲጂታል የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ ዘሮ (ዶ/ር ) ተናግረዋል።
በከተማዋ ‎የተገነባው የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሕንፃ ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠርና ገቢን ለማጠናከር ያስችላል
May 2, 2026 18
ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ ‎የተገነባው የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሕንፃ ምቹ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ ገቢን ለማጠናከር እንደሚያስችል የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በባህር ዳር ከተማ የተገነባው ባለ 9 ወለል ዘመናዊ መንትያ ሕንፃ ወደ ሥራ ገብቷል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በምረቃው እንደገለጹት ከጣና ሐይቅ በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባው ሕንጻ በአካባቢው ከለማው የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ ጋር ተዳምሮ የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ነው። መንትያ ሕንፃው ከቢሮ አገልግሎት በተጨማሪ ለመዝናኛ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ፣ ለስብሰባና ለቱሪዝም አገልግሎት የሚውል መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ለተቋሙ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን ኢኮኖሚያዊ አቅምን ከማጠናከር ባለፈ ምቹ የሥራ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አስቻለው ሞላ በበኩላቸው መንትያ ሕንጻው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል። በጠቅላላ 2ሺህ 640 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሕንጻ ከቤዝመንት በተጨማሪ ዘጠኝ ወለል እንዳለውና ግንባታውም በተያዘለት ጊዜ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል። ሕንጻው ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውል በርካታ ክፍሎች ያሉትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት መሆኑንም አመልክተዋል። የሕንጻው ግንባታ ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑንም አክለዋል።
የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስጋቱን ወደ መልካም አጋጣሚ ቀይሯል -የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ
May 2, 2026 34
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንፃዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።   የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ይህንኑ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል። አፈ ጉባኤው እንደገለጹት ተቋሙ ላለፉት ሰባት ዐሥርተ ዓመታት የመንግሥት ሠራተኛው ዋስትና ሆኖ ቢቆይም፣ የጡረታ ፈንዱን በአግባቡ የማንቀሳቀስ እና ወደ ኢንቨስትመንት የመቀየር አቅም ማጣቱ ለረጅም ጊዜ ስጋት ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት እና በወሰዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች አዳዲስ አዋጆች እና የአስተዳደር ደንቦች እንዲጸድቁ ተደርጓል። ይህም ተቋሙ የነበረበትን ስጋት ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ፈንዱን ከማስጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማራ እና በሀገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል። አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አክለውም፣ ዛሬ የተመረቁት ዘመናዊ ሕንፃዎች ከግዙፍ ቁሳዊ ሀብትነታቸው ባሻገር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ እና የነገው ብሩህ ተስፋ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። "ሕንፃዎቹ የተገነቡት ከድንጋይ እና ከብረት ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ ጡብ ውስጥ የጡረታ ባለመብቶች ክብር፣ የሠራተኞች ላብ እና የሀገራችን ተስፋ ታትሞባቸዋል" ሲሉ የምረቃው ዋና ዓላማ የባለመብቶችን ክብር እና እርካታ ማረጋገጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ለወደፊቱም የፈንዱን ዘላቂነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋፋት እና አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል። አፈ-ጉባኤው መንግሥት ለተቋሙ የሚያደርገው ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት ለስኬቱ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ ነው
May 2, 2026 26
ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ። ’’አርብቶ አደሮችና ትምህርት’’ በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ዛሬ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።   በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በኮንፍረንሱ እንደገለጹት፣ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስፋፋት በሰራቸው ተግባራት ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይም የተጀመሩ ኢንሼቲቮችና ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በማህበራዊ ልማት በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል። በዚህ ረገድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውሉ ሲያከናውኑ የቆዩትን ስራዎች ማጎልበት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ለልማት እንዲውል በምርምር በማገዝ የአርብቶ አደሩ ሕይወት እንዲለወጥ በማድረግ በኩል የላቀ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ የሚያግዙ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።   የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ወደ ልማት የሚቀየርበትን አቅም በምርምር እንዲያግዙ ጠይቀዋል። ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስም በቀጣይ ለሚወጡ ሀገራዊ የልማት ፖሊሲዎች ጠቃሚ ግብዓቶች ለማፍለቅ ያግዛል ብለዋል።   የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የአካባቢው ማህበረሰብ ሕይወት እንዲለወጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመድረኩ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተጨማሪ ግብዓቶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያገኝም ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ በማህበራዊ ኃላፊነት ዘርፍ በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ነው
May 2, 2026 31
ሮቤ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመቀናጀት በባሌ ሮቤ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባቸው መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስረክቧል። የተገነቡት 20 መኖሪያ ቤቶች እያንዳንዳቸው የራሳቸው መሰረተ ልማትና የመኖሪያ ቁሶቁሶችን የተሟላላቸው መሆኑም ነው የተገለፀው። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ተቋሙ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ ውስጥም በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ ዜጋ ተኮር ልማቶችና አገልግሎቶችን በማካሔድ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። ዛሬ በባሌ ሮቤ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት እነዚሁ ፕሮጀክቶች የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆናቸውን አመልክተዋል። ፕሮጀክቶቹ በተለይ የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚቀርፉ ከመሆናቸው ባሻገር ፤ በዘርፉ የተያዙ ሀገራዊ ግቦችን ከማሳካት መንፃር ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያካሒደውን የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያጠናክሩና ቀጣይነት ያላቸው መሆናቸውንም አንስተዋል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በራሳቸውና ሌሎች አካላትን በማስተባበር የገነቡትን ዲጂታል መፀሐፍት ቤት ለቀድሞ ትምህርት ቤታቸው የሮቤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስረክበዋል። የመጽሃፍት ቤት ግንባታው የከተማዋን ወጣቶችና ተማሪዎች የንባብ ባህል ይበልጥ የሚያሳድግ ሲሆን የልጅነት ሕልማቸውንም ለማሳካት ያስቻላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዲኖ አሚን በበኩላቸው ፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለከተማዋ እድገትና ለአቅመ ደካማ ዜጎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከተማዋን ለነዋሪው ምቹና የንግድ ማእከል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እገዛ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የገለጹት። ከልማቱ ተጠቃሚዎች መካከል ሼህ አልይ ከድርና ወይዘሮ ፋጡማ አብዳላ በበኩላቸው፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታው ለዓመታት የነበረባቸውን የመጠለያ ችግር የሚቀርፍ መሆኑን ተናግረዋል።  
የሚታይ

ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
May 2, 2026 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በርትተን ከሰራን፣ ጀምረን ከጨረስንና ክፍተቶችን እያየን መሙላት ከቻልን፣ ዘላቂና ተከታታይነት ያለው ዕድገት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብልፅግና በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻንና ሌሎች ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በግል ባለሀብት የተገነባው ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከጅማና ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፣ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር ደግሞ በመጠን የሚስተካከል ነው። የሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሠላሳ ሼዶች ያሉት መሆኑን ጠቅሰው፤ ስፋት ያለው፣ በርካታ ሰዎችን የሚይዝና ለከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የግል ዘርፉ በኢንቨስትመንት መስክ ያለውን ሚና አጎልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በጨርቃጨርቅ ላይ ተመስርቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርት አሁን ላይ እንዲሰፋ በተከናወነው ተግባር፤ ሶላር፣ የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ ጫማና አልባሳትን የመሳሰሉ ምርቶች በኢኮኖሚ ዞኑ እንደሚመረቱ ተናግረዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ባሉ ሼዶች የተለያዩ ምርቶች መመረታቸው የገበያ ዕድልን የሚያሰፋ መሆኑንም አንስተዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ያለው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ አሁን ላይ ሁለት ጊጋ ዋት እያመረተ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ዓመት ተጨማሪ ሁለት ጊጋ ዋት ማምረት ይጀምራል ብለዋል። የሶላር ሴል ምርት በአጭር ጊዜ ውስጥ መመረት የጀመረና አሁን ላይ እየሰፋ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል። ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ የሚገኝና በርካታ ሼዶች ያሉት በመሆኑ፣ በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ዕድል ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ኢንዱስትሪ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢነርጂና ለአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት የሚውል በመሆኑ፣ በበርካታ መንገዶች በኢኮኖሚው ላይ አስተዋፅኦ የሚያበረክት እንደሆነም ገልፀዋል። ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለእውቀት ሽግግርና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የሚውል በመሆኑ፣ ጥቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የተሳካውንና የሚቀረውን በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ ለውጥ እያስመዘገበና የኢንዱስትሪ ሽግሽግን እያመጣ ያለ መሆኑን ገልፀዋል። ይህን ማጠናከር ከተቻለ በቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ራሷን የመቻል ዕድል እንዳላት የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የመጣውን ውጤት በማስፋትና በማሳደግ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ከሁሉም የሚጠበቅ ዐቢይ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት ጥሏል
May 2, 2026 110
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት መጣሉን የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶሳይቲው የበላይ ጠባቂ ደመቀ መኮንን ገለጹ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2004 የተመሰረተው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ትውልድ ትገነባለች የሚለውን መርህ ገቢራዊ ለማድረግ በምታደረገው እንቅስቃሴ ሶሳይቲው ጉልህ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲና በመንግስት ቁርጠኝነት ለሳይንስ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ እንደ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማት በተደራጀ መንገድ እንዲቋቋሙ ተደርጓል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ወጣት የሳይንስ ተመራማሪዎችና አስትሮኖመሮችን ማፍራቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በማፍራትና በምርምር ተስፋ ሰጪ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ ሳይንስ ለግብርና የዲጂታል አብዮት እድገትና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር እኩል ለመራመድ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመኑን የሚዋጅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ወጣቶችን በሳይንስና አስትሮኖሚ ለማብቃት የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር በዘርፉ ከመጠቁ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተወሰኑ ስራዎችና ውጤቶች መርካት የለብንም ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለዚህ ደግሞ የወጣቶች ተሳትፎ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አስረድተዋል።   የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለስፔስ ሳይንስ ዕድገት ትልቅ ባለውለታ መሆኑን አስታውቀዋል። ስፔስ ሳይንስ የሉዓላዊነት፣ የምግብ ዋስትና፣ የዲፕሎማሲ፣ የጤና፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፤ ያለ ስፔስ ሳይንስ መቆም እንደማይቻል ገልጸዋል። የሀገርን ኢኮኖሚና ኅልውና ለማስቀጠል ስፔስ ሳይንስ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ሶሳይቲው ወጣቶችን ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት የተለያዩ ተቋማት መደገፍና በትብብር መስራት አለባቸው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚገኘውን የ“ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ጎበኙ
May 2, 2026 83
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፦‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን የ“ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ዛሬ ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፋብሪካው በ2025 የኢንቨስትመንት ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ መሆኑን አውስተዋል። በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ ነው ብለዋል። ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልም መፍጠር መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።   በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው፣ የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ የተጀመረውን ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም መፍጠሩን ነው ያብራሩት።   በዚሁ የኢንደስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን መመልከታቸውንም በመልዕክታቸው ገልጸዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የኮሪደርና ግዙፍ የልማት ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል
May 2, 2026 121
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደርና ግዙፍ የልማት ሥራዎች ገጽታዋን በመቀየር ረገድ አስደናቂ ለውጥ ማሳየታቸውን የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር ጁሊያ ፓቲካ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ተሠርቶ የታየው ለውጥ ለማመን የሚከብድ ሥራ ነው።   አዲስ አበባ በኮሪደር ልማቱ በተሠራው ሥራ ሰፋፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ለእግር ጉዞ የሚሆኑ ውብ ስፍራዎችና ፓርኮች ያሏት ዘመናዊ ከተማ ሆናለች ብለዋል። ይህ ሥራ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው፤ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጀምሮ በቱሪዝም ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት አድናቆት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሌሃንድሮ ኢቭስ እስቲቪሊ ካስትሮ በበኩላቸው፤ የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ የላቀ ውበት ከመስጠቱም በላይ ለሕዝቡ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ መመልከታቸውን ተናግረዋል።   በከተማዋ ውስጥ ለመዘዋወር፣ ለማሽከርከር እና ለመዝናናት አሁን ያለው ሁኔታ ቀላል እና ማራኪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ በበኩላቸው፤ በቆይታቸው ወቅት የተመለከቱት የኮሪደር፣ የፓርኮች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች አስገራሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።   በከተማዋ የተሠሩት ሥራዎች እጅግ አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከተማዋ ለመኖርም ሆነ ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን እያደረጋት ነው ብለዋል። ለውጡ የታየበትን ፍጥነት አስደናቂ ነው ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ኤር ቫይስ ማርሻል ሲትዋት ናዪማ ናቸው።   ከተማዋን ዓለም አቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች ለማድረግ እየተሠራ ያለው ሥራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑንም አንስተዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ግንቦት 24ን እየጠበቅን ነው - የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 31
ጂንካ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በተመቻቸልን ዕድል ተጠቅመን የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ በመውሰዳችን ግንቦት 24ን በጉጉት እየጠበቅን ነው ሲሉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለፁ።   ተማሪ በቀለ ባሪሶ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ምርጫው የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በንቃት ተሳትፎ ለማድረግ መቻል ልዩ ስሜት አለው። ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድ ሥርዓት አካል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መሳተፍ አለበት ያለው ደግሞ ተማሪ አምሳሉ ዓባይነህ ነው።   በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያበቃውን የድምፅ መስጫ ካርድ በመውሰዱ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አንስቷል።   የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት መቅደስ አድማሱ በበኩሏ አብዛኛው ተማሪ በምርጫው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ ይህም ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድታለች።   ዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽ ኮሙኒኬሽን እና የቤተ ሙከራ ማዕከላትን በበይነ መረብ በማስተሳሰር ተማሪዎች ዲጂታል የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ ዘሮ (ዶ/ር ) ተናግረዋል።
የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ ወስደናል - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 162
አሶሳ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ። ቦርዱ የምርጫ ካርድ ላልወሰዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በካምፕ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በልዩ ሁኔታ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ ነው። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ባገኙት የመራጭነት ዕድል ድምጽ ለመስጠት የሚያበቃቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ መልካሙ መላኩ እንደገለጸው፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም እና ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ፓርቲ እንዲመርጡ ዕድል መመቻቸቱ የሚበረታታ ነው። ተማሪዎች ባሉበት ሆነው በቴክኖሎጂ ታግዘው መመዝገብ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የታየ ትልቅ መሻሻል መሆኑን ጠቁሟል። ተማሪ አበባ የኛነው በበኩሏ፤ ተማሪዎች በምርጫው እንድንሳተፍ መደረጉ የመምረጥ መብታችንን ተጠቅመን ሀገርን በልማትና በሰላም ግንባታ ወደፊት የሚያራምድ ፓርቲ ለመምረጥ ዕድል ይሰጠናል ብላለች። ለተማሪዎች የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የምርጫ ካርድ መውሰዱን የገለጸው ተማሪ አቢያን ኩኩ፤ ባሉበት ሆነው ካርድ ማውጣት መቻላቸው ጊዜና ጉልበት በመቆጠቡ ሊበረታታ ይገባል ብሏል። ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጹን ለሚፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት መዘጋጀቱንም አረጋግጧል።
የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን ነው - የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች
May 2, 2026 127
ሰመራ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ በሆነው ምርጫ ላይ በንቃት በመሳተፍ ለሀገር ግንባታ የሚበጅ ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ኢዜአ በሰመራ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በምርጫ ካርዳቸው የተሻለ ሐሳብ አለው፣ ሀገርና ሕዝብንም ወደፊት ያራምዳል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል።   አቶ ዘይኑ ሙሳ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ምርጫ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለሕዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትና ዘላቂ ሰላም አበክሮ ይሠራል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።   ፓርቲዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮችና ቋንቋዎች ሐሳባቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉ እንደ መራጭ በቂ ግንዛቤ ለመያዝ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። ምርጫ ይበጀኛል ብለን ድምጻችንን ለምንፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ የምንሰጥበት በመሆኑ ሁሉም ሰው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም መዘጋጀት አለበት ያሉት ደግሞ አቶ ሙሳ አብዱ ናቸው። የምርጫውን ቀን እየጠበቁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለሰላምና ልማት መቀጠል የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። አቶ መሐመድ ይመር በበኩላቸው፤ የፓርቲዎችን አማራጭ ሐሳቦች ሕብረተሰቡ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲያገኝ መደረጉ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። የምርጫ ካርዳቸውን በወቅቱ ወስደው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን ለመስጠት መጪውን ግንቦት 24 እየጠበቁ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በተከናወኑ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል
May 2, 2026 110
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ ስታድየም በመካሄድ ላይ ነው።   አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መሠረት መጣሉን አስገንዝበዋል። የሰው ተኮር ሥራዎች የበርካታ ሰዎችን ኑሮ ከመሠረቱ በመቀየር ረገድ ውጤት ማስገኘታቸውን ጠቅሰው፤ የብልጽግና ፓርቲ ለቃሉ የታመነ ለተልዕኮውም የፈጠነ ፓርቲ መሆኑን አስታውቀዋል። አዲስ አበባን ውብ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ሥራዎችም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን የበለጠ ያከናውናል
May 2, 2026 98
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን የበለጠ እንደሚያከናውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ ስታድየም በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አዳነች አቤቤ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ህዝብ ብቸኛው የስልጣን ባለቤት ነው። ያለ ህዝብ ተሳትፎና አጋርነት ብልፅግናን እውን ማድረግ እንደማይቻልም ተናግረዋል።   የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራት ማከናወናቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያቆመው አንዳች ምድራዊ ሀይል እንደሌለ ገልጸዋል። በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ማንንም ያልዘነጉ አካታች መሆናቸውን ጠቁመው፤ እነዚህ ተግባራት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። ብልፅግና ቃሉን የሚጠብቅ ፓርቲ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ የከተማዋን ገጽታም ቃል በገባው መሰረት መገንባቱን ተናግረዋል። በቀጣይም ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ቃል በመግባት "ብልፅግናን ምረጡ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል
May 1, 2026 347
አርባ ምንጭ፤ ሚያዚያ 23/2018 (ኢዜአ)፦ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ኢዜአ በአርባ ምንጭ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ ለመያዝ የተወጡትን ሃላፊነት በምርጫው ቀንም ድምጻቸውን በመስጠት ለመድገም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ያላቸውን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለይተው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።   አስተያታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ አለማየሁ በቀለ እንዳሉት በጠቅላላው ምርጫ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ለመምረጥ የፓርቲዎችን ክርክርና የፖሊሲ አማራጮች ሲከታተሉ ቆይተዋል። ይህም ለሀገር ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲ መጎልበትና ለህዝብ የልማት ተጠቃሚነት በተሻለ ይሰራል ብለው ያሰቡትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። የምርጫው ስኬታማነት በዜጎች ንቁ ተሳትፎ የሚወሰን በመሆኑ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በምርጫው ቀን ድምጻቸውን ይበጀኛል ላሉት ፓርቲ በመስጠት ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። "ለመምረጥ የሚያስችለኝን ካርድ ወስጄ የድምፅ መስጫ ቀኑን በጉጉት እየተጠባበቅኩ ነው" ያለችው ደግሞ ሌላዋ የከተማው ነዋሪ ወጣት ሀና ሸዋ ናት። የምመርጠውን ፓርቲ በስሜት ሳይሆን በጥንቃቄ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ያለችው ወጣቷ፣ በተለይ በቀጣይ የሀገርን ሁለንተናዊ ልማት በማፋጠን ህዝብን ተጠቃሚ ለሚያደርግ ፓርቲ ድምጿን ለመሰጠት መዘጋጀቷን ገልጻለች። ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አብሮነት ይበጃል፤ ሀገርንም ያሻግራል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ እየተዘጋጁ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ኦሳ ፋንታ ናቸው። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ፕሮግራሞቻቸውን በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እንዲያስተዋውቁ መመቻቸቱ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል። በምርጫው ሂደት የእኔ አንድ ድምጽ ዋጋ አለው ያሉት ነዋሪው፣ በምርጫው ቀን ካርዳቸውን በመጠቀም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ከመጠቀም ባለፈ ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻና ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት እንዳለበትም ተናግረዋል።    
በያዝነው የመራጭነት ካርድ የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
May 1, 2026 282
ሰቆጣ ፤ ሚያዝያ 23/2018 (ኢዜአ)፦በመራጭነት ካርዳችን የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ የምርጫ ካርድ በወቅቱ ማውጣታችን በቀጣይ አምስት ዓመት ሀገሪቱን የሚመሩ አካላትን ለመምረጥ ከወዲሁ እንድንዘጋጅ አድርጎናል። የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑት መካከል አቶ ልሳነ ወርቅ መንግስቴ " ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት ሀገርን የሚያስተዳድሩ አካላትን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ አውጥቼ ተዘጋጅቻለሁ" ብለዋል። የመራጭነት ካርድ ለመያዝ ያሳዩትን ተነሳሽነትም በድምጽ መስጫው እለት ለመድገም በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወንም የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ እንደሆነም ነው ያነሱት። የመራጭነት ካርድ ማውጣታቸው በህገ- መንግስቱ የተቀመጠውን ዴሞክራሲያዊ መብት ለመጠቀም እንደሚያስችላቸው የተናገሩት ደግሞ አቶ ሙሃባው ፈረደ ናቸው። ባወጣሁት ካርድ ይበጀኛል ያልኩትን በመምረጥ የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣትና የምፈልገውን አካል ወደ ስልጣን ለማምጣት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ መብራት ውበቱ በበኩለቸው፤ ምርጫው አሳታፊና አካታች እንዲሆን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች ውጤት እየታየባቸው ነው ብለዋል። ማህበሩም ምርጫውን አስመልክቶ አስቀድሞ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በመስራቱ አባላቱ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ በማውጣት ለድምጽ መስጫው ቀን እንዲዘጋጁ አድርጓል ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅትም የፖለቲካ ፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራማቸውን ለማስተዋወቅ በመገናኛ ብዙሃን እያደረጉት ያለው የክርክርና የምረጡኝ ቅስቀሳም በእውቀት ላይ ተመስርቶ በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል።

ማህበራዊ
የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስጋቱን ወደ መልካም አጋጣሚ ቀይሯል -የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ
May 2, 2026 34
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንፃዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።   የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ይህንኑ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል። አፈ ጉባኤው እንደገለጹት ተቋሙ ላለፉት ሰባት ዐሥርተ ዓመታት የመንግሥት ሠራተኛው ዋስትና ሆኖ ቢቆይም፣ የጡረታ ፈንዱን በአግባቡ የማንቀሳቀስ እና ወደ ኢንቨስትመንት የመቀየር አቅም ማጣቱ ለረጅም ጊዜ ስጋት ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት እና በወሰዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች አዳዲስ አዋጆች እና የአስተዳደር ደንቦች እንዲጸድቁ ተደርጓል። ይህም ተቋሙ የነበረበትን ስጋት ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ፈንዱን ከማስጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማራ እና በሀገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል። አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አክለውም፣ ዛሬ የተመረቁት ዘመናዊ ሕንፃዎች ከግዙፍ ቁሳዊ ሀብትነታቸው ባሻገር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ እና የነገው ብሩህ ተስፋ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። "ሕንፃዎቹ የተገነቡት ከድንጋይ እና ከብረት ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ ጡብ ውስጥ የጡረታ ባለመብቶች ክብር፣ የሠራተኞች ላብ እና የሀገራችን ተስፋ ታትሞባቸዋል" ሲሉ የምረቃው ዋና ዓላማ የባለመብቶችን ክብር እና እርካታ ማረጋገጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ለወደፊቱም የፈንዱን ዘላቂነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋፋት እና አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል። አፈ-ጉባኤው መንግሥት ለተቋሙ የሚያደርገው ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት ለስኬቱ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት እየሠሩ መሆናቸውን ሲቪክ ማኅበራት ገለጹ
May 2, 2026 52
መቱ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለመወጠት እየሠሩ መሆናቸውን በኢሉአባቦር ዞን የሚገኙ የሲቪክ ማኅበራት ገለፁ።   የኢሉባቦር ዞን ሴቶች ማኀበር ሊቀ መንበር ወይዘሮ ዓባይነሽ ሙሉነህ እና የዞኑ ሴቶች ፌዴሬሽን ኃላፊ ሀገሬ ሀብታሙ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በየደረጃው ላሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች በምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል። በተለይ በሴት አደረጃጀቶች ውስጥ የታቀፉ ዜጎች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የምርጫ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው ያመለከቱት። ምርጫው፤ ዴሞክራሲያ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጀመሩትን ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል። በሲቪክ ማኅበራቱ የተሰጣቸው ሥልጠና በምርጫው የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ በቂ ግንዛቤ እንዳስያዛቸው የተናገሩት ደግሞ የመቱ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ናሐዊ ደፋር ናቸው። በአሁኑ ወቅትም በምርጫ ታዛቢነት መመረጣቸውን ጠቅሰው፤ ይህንን የሕዝብ አደራ በአግባቡ ለመወጣት ሥልጠናው ዐቅም እንደሆናቸው ነው የሚገልጹት።   ሌላኛዋ የወረዳው ነዋሪ ሙና ኢሳ፤ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሲቪክ ማኅበራቱ እያከናወኑ ያለው ተግባራት መቀጠል ይገባዋል ይላሉ። ማኅበራቱ ባዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ላይ በመሳተፍም፤ በምርጫው ወቅት በታዛቢነት ለመቀመጥ መመረጣቸውን ነው ያመለከቱት።
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያስገነባው ሕንጻ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ዐቅም ይፈጥራል
May 2, 2026 58
ጅማ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጅማ ከተማ ያስገነባው ሕንጻ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ዐቅም እንደሚሆን የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሀ ቀመር ተናገሩ። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጅማ ከተማ የገነባውን ባለ ስምንት ወለል ሕንጻ ዛሬ አስመርቋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሀ ቀመር በዚሁ ወቅት፤ መንግሥት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እና ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል። አስተዳደሩ በጅማ ከተማ የገነባው ሕንጻም ለማኅበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና የሠራተኛውን ተነሳሽነት ለማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።   የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲናኦል ሳቀታ በበኩላቸው፤ የተመረቀው ሕንጻ የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው ብለዋል። ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞችና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምቹ ሆኖ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሟላቱን አረጋግጠዋል።
አስተዳደሩ ያስገነባው ሕንጻ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል- ከንቲባ ጥራቱ በየነ
May 2, 2026 87
ሐዋሳ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሐዋሳ ከተማ ያስገነባው ሕንጻ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ። ከንቲባው የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሐዋሳ ከተማ ያስገነባውን ባለ ስምንት ወለል ሕንጻ ዛሬ መርቀዋል። በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ዓመታት በተደረገ ሪፎርም ተቋሙ አስደናቂ ለውጥ ማስመዝገቡን አንስተዋል። ማኅበራዊ ዋስትናን ከማረጋጋጥ ባለፈ ሀብት መፍጠር በሚችል የኢንቨስትመንት ሥራ ውስጥ በመግባት ያስመዘገበው ውጤት ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ ይሆናልም ብለዋል። ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ሕንጻው፤ ለሐዋሳ ከተማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተጨማሪ ዐቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።   ሕንጻው ለቢሮ አገልግሎት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሕክምና መስጫ ማዕከላትና ለተለያዩ የንግድ አገልግሎቶች እንዲውል ጭምር ተደርጎ መሠራቱን የተናገሩት ደግሞ በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተሾመ ባብሳ ናቸው፡፡ የግንባታ ሥራው በ2015 ዓ.ም መጀመሩንና ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበትም ተመላክቷል።
ኢኮኖሚ
በከተማዋ ‎የተገነባው የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሕንፃ ምቹ የሥራ ሁኔታ ለመፍጠርና ገቢን ለማጠናከር ያስችላል
May 2, 2026 18
ባህር ዳር፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በባህር ዳር ከተማ ‎የተገነባው የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሕንፃ ምቹ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ ገቢን ለማጠናከር እንደሚያስችል የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ። በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በባህር ዳር ከተማ የተገነባው ባለ 9 ወለል ዘመናዊ መንትያ ሕንፃ ወደ ሥራ ገብቷል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በምረቃው እንደገለጹት ከጣና ሐይቅ በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባው ሕንጻ በአካባቢው ከለማው የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ ጋር ተዳምሮ የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ነው። መንትያ ሕንፃው ከቢሮ አገልግሎት በተጨማሪ ለመዝናኛ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ፣ ለስብሰባና ለቱሪዝም አገልግሎት የሚውል መሆኑን አመልክተዋል። ይህም ለተቋሙ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን ኢኮኖሚያዊ አቅምን ከማጠናከር ባለፈ ምቹ የሥራ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። በመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አስቻለው ሞላ በበኩላቸው መንትያ ሕንጻው ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል። በጠቅላላ 2ሺህ 640 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሕንጻ ከቤዝመንት በተጨማሪ ዘጠኝ ወለል እንዳለውና ግንባታውም በተያዘለት ጊዜ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል። ሕንጻው ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውል በርካታ ክፍሎች ያሉትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት መሆኑንም አመልክተዋል። የሕንጻው ግንባታ ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑንም አክለዋል።
ሚኒስቴሩ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ በማህበራዊ ኃላፊነት ዘርፍ በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ነው
May 2, 2026 31
ሮቤ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመቀናጀት በባሌ ሮቤ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባቸው መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስረክቧል። የተገነቡት 20 መኖሪያ ቤቶች እያንዳንዳቸው የራሳቸው መሰረተ ልማትና የመኖሪያ ቁሶቁሶችን የተሟላላቸው መሆኑም ነው የተገለፀው። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ተቋሙ የንግድ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ ውስጥም በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ ዜጋ ተኮር ልማቶችና አገልግሎቶችን በማካሔድ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። ዛሬ በባሌ ሮቤ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁት እነዚሁ ፕሮጀክቶች የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆናቸውን አመልክተዋል። ፕሮጀክቶቹ በተለይ የአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት ችግርን የሚቀርፉ ከመሆናቸው ባሻገር ፤ በዘርፉ የተያዙ ሀገራዊ ግቦችን ከማሳካት መንፃር ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያካሒደውን የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያጠናክሩና ቀጣይነት ያላቸው መሆናቸውንም አንስተዋል። ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በራሳቸውና ሌሎች አካላትን በማስተባበር የገነቡትን ዲጂታል መፀሐፍት ቤት ለቀድሞ ትምህርት ቤታቸው የሮቤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስረክበዋል። የመጽሃፍት ቤት ግንባታው የከተማዋን ወጣቶችና ተማሪዎች የንባብ ባህል ይበልጥ የሚያሳድግ ሲሆን የልጅነት ሕልማቸውንም ለማሳካት ያስቻላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዲኖ አሚን በበኩላቸው ፤ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለከተማዋ እድገትና ለአቅመ ደካማ ዜጎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከተማዋን ለነዋሪው ምቹና የንግድ ማእከል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እገዛ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የገለጹት። ከልማቱ ተጠቃሚዎች መካከል ሼህ አልይ ከድርና ወይዘሮ ፋጡማ አብዳላ በበኩላቸው፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታው ለዓመታት የነበረባቸውን የመጠለያ ችግር የሚቀርፍ መሆኑን ተናግረዋል።  
ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
May 2, 2026 63
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በርትተን ከሰራን፣ ጀምረን ከጨረስንና ክፍተቶችን እያየን መሙላት ከቻልን፣ ዘላቂና ተከታታይነት ያለው ዕድገት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብልፅግና በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻንና ሌሎች ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በግል ባለሀብት የተገነባው ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከጅማና ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፣ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር ደግሞ በመጠን የሚስተካከል ነው። የሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሠላሳ ሼዶች ያሉት መሆኑን ጠቅሰው፤ ስፋት ያለው፣ በርካታ ሰዎችን የሚይዝና ለከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የግል ዘርፉ በኢንቨስትመንት መስክ ያለውን ሚና አጎልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በጨርቃጨርቅ ላይ ተመስርቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርት አሁን ላይ እንዲሰፋ በተከናወነው ተግባር፤ ሶላር፣ የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ ጫማና አልባሳትን የመሳሰሉ ምርቶች በኢኮኖሚ ዞኑ እንደሚመረቱ ተናግረዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ባሉ ሼዶች የተለያዩ ምርቶች መመረታቸው የገበያ ዕድልን የሚያሰፋ መሆኑንም አንስተዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ያለው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ አሁን ላይ ሁለት ጊጋ ዋት እያመረተ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ዓመት ተጨማሪ ሁለት ጊጋ ዋት ማምረት ይጀምራል ብለዋል። የሶላር ሴል ምርት በአጭር ጊዜ ውስጥ መመረት የጀመረና አሁን ላይ እየሰፋ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል። ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ የሚገኝና በርካታ ሼዶች ያሉት በመሆኑ፣ በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ዕድል ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ኢንዱስትሪ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢነርጂና ለአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት የሚውል በመሆኑ፣ በበርካታ መንገዶች በኢኮኖሚው ላይ አስተዋፅኦ የሚያበረክት እንደሆነም ገልፀዋል። ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለእውቀት ሽግግርና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የሚውል በመሆኑ፣ ጥቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የተሳካውንና የሚቀረውን በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ ለውጥ እያስመዘገበና የኢንዱስትሪ ሽግሽግን እያመጣ ያለ መሆኑን ገልፀዋል። ይህን ማጠናከር ከተቻለ በቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ራሷን የመቻል ዕድል እንዳላት የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የመጣውን ውጤት በማስፋትና በማሳደግ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ከሁሉም የሚጠበቅ ዐቢይ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
ለግብርና ኢንቨስትመንት በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ የዘርፉ ውጤታማነት እያደገ ነው
May 2, 2026 100
ቦንጋ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ ለግብርና ኢንቨስትመንት የተፈጠረ ምቹ ሁኔታ የዘርፉን ውጤታማነት እንዳሳደገው ግብርና ሚኒስቴር ገለፀ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በቦንጋ ከተማ መክሯል። በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ደረጀ አበበ እንደገለጹት መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና የግል ባለሀብቱን ለማበረታታት የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ አድርጓል።   ለዚህም ከግብዓት አቅርቦት ጀምሮ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል ለግል ባለሀብቱ በርካታ ማበረታቻዎችን በማድረግ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የግብርና ኢንቨስትመንት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ምርቶችን ለማምረት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል። ባለሀብቶች በገቡት ውልና በፖሊሲው በተቀመጠው መሰረት የወሰዱትን መሬት በአግባቡ ማልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በሰፊው መስራት እና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በትኩረት እንዲሰሩም አሳስበዋል። የመድረኩ ዓላማም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ችግር ለይቶ መፍትሄ ማበጀት፣ ትልልቅ የምግብ ዘይት አምራቾች በእርሻ ዘርፍ እንዲሳተፉ ማድረግና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በመምከር ዘርፉን ይበልጥ ማጠናከር መሆኑንም ገልጸዋል።   ግብርና ለሀገር ኢኮኖሚ ያለዉ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አስራት አስፋ ናቸው። ባለፉት ጊዜያት በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ከፋይናንስ አቅርቦት ጀምሮ በርካታ ድጋፎች በተሻለ መልኩ እየተደረጉ ነው ብለዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት ለኢንቨስትመንት ዘርፍ በተሰጠ ትኩረት 544 ባለሀብቶች በግብርናው ዘርፍ መሰማራታቸውንና የዘርፉ ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች 177ሺህ ሄክታር መሬት መመቻቸቱንና የህግና የአሰራር ማእቀፎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።   በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትልና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሀላፊ ከበደ ተስፋዬ ናቸው። ባለሀብቶቹ በቡና፣ በሰብል፣ በሻይ ልማት እንዲሁም በቅባት እህሎችና በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች መሰማራታቸውን አንስተው፣ ከእነዚህም ውስጥ 93ቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ስራ የገቡ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ናቸው ብለዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ ነው
May 2, 2026 26
ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ። ’’አርብቶ አደሮችና ትምህርት’’ በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ዛሬ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።   በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በኮንፍረንሱ እንደገለጹት፣ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስፋፋት በሰራቸው ተግባራት ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይም የተጀመሩ ኢንሼቲቮችና ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በማህበራዊ ልማት በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል። በዚህ ረገድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውሉ ሲያከናውኑ የቆዩትን ስራዎች ማጎልበት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ለልማት እንዲውል በምርምር በማገዝ የአርብቶ አደሩ ሕይወት እንዲለወጥ በማድረግ በኩል የላቀ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ የሚያግዙ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።   የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ወደ ልማት የሚቀየርበትን አቅም በምርምር እንዲያግዙ ጠይቀዋል። ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስም በቀጣይ ለሚወጡ ሀገራዊ የልማት ፖሊሲዎች ጠቃሚ ግብዓቶች ለማፍለቅ ያግዛል ብለዋል።   የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የአካባቢው ማህበረሰብ ሕይወት እንዲለወጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመድረኩ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተጨማሪ ግብዓቶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያገኝም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት ጥሏል
May 2, 2026 110
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት መጣሉን የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶሳይቲው የበላይ ጠባቂ ደመቀ መኮንን ገለጹ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2004 የተመሰረተው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ትውልድ ትገነባለች የሚለውን መርህ ገቢራዊ ለማድረግ በምታደረገው እንቅስቃሴ ሶሳይቲው ጉልህ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲና በመንግስት ቁርጠኝነት ለሳይንስ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ እንደ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማት በተደራጀ መንገድ እንዲቋቋሙ ተደርጓል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ወጣት የሳይንስ ተመራማሪዎችና አስትሮኖመሮችን ማፍራቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በማፍራትና በምርምር ተስፋ ሰጪ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ ሳይንስ ለግብርና የዲጂታል አብዮት እድገትና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር እኩል ለመራመድ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመኑን የሚዋጅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ወጣቶችን በሳይንስና አስትሮኖሚ ለማብቃት የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር በዘርፉ ከመጠቁ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተወሰኑ ስራዎችና ውጤቶች መርካት የለብንም ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለዚህ ደግሞ የወጣቶች ተሳትፎ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አስረድተዋል።   የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለስፔስ ሳይንስ ዕድገት ትልቅ ባለውለታ መሆኑን አስታውቀዋል። ስፔስ ሳይንስ የሉዓላዊነት፣ የምግብ ዋስትና፣ የዲፕሎማሲ፣ የጤና፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፤ ያለ ስፔስ ሳይንስ መቆም እንደማይቻል ገልጸዋል። የሀገርን ኢኮኖሚና ኅልውና ለማስቀጠል ስፔስ ሳይንስ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ሶሳይቲው ወጣቶችን ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት የተለያዩ ተቋማት መደገፍና በትብብር መስራት አለባቸው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ ቴክኖሎጂ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊነታቸውን የበለጠ እንዲወጡ ያግዛል
May 1, 2026 227
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2018(ኢዜአ)፦ የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና የአስተዳደር ሥርዓት ቴክኖሎጂ፣ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ሥራቸውን በኃላፊነት ስሜት የበለጠ እንዲያከናውኑ እንደሚያስችል የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያለማውን የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓት ቴክኖሎጂ በይፋ ሥራ አስጀምሯል።   የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በርካታ ተቋማትን እየደገፈ ይገኛል። ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ አሻራውን እያሳረፈ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለት ወደ ሥራ የገባው የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓት ቴክኖሎጂ ለሚዲያው ዘርፍ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። በተለይ ግልጽነትና ፍትሐዊነትን ለማስፈን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸው፤ የሚዲያ ተቋማት ኃላፊነትን በተላበሰ መንገድ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።   የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድማሱ ዳምጠው፤ የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓቱ የማኑዋል አሠራርን የሚያስቀር መሆኑን ገልጸዋል። እንዲሁም ትክክለኛነትን የሚያረጋግጥና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል እንዲሁም ለሚዲያዎች ራሱ እንደ ግብረ መልስ ያገለግላል ብለዋል።   የኤን.ቢ.ሲ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ከበደ በበኩላቸው፤ ቴክኖሎጂው የኅብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያረጋግጥና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በመገናኛ ብዙኃን መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ጄይላን አብዲ፤ ቴክኖሎጂው ተጠያቂነት ያለው አሠራርን የሚያረጋግጥ፣ ሥራን የሚያቃል፣ ግልጽነትን የሚፈጥርና የተቋሙን ውጤታማነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመዋል።   በመርሐ ግብሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፣ የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል እውቀቶች ለሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ግብዓት እንሆዲኑ እየሰራ ነው
May 1, 2026 143
አምቦ፤ ሚያዝያ 23/ 2018 (ኢዜአ)፦ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀቶችን ከሳይንስ ጋር በማቀናጀት ለሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ግብዓት እንዲሆኑ በጥናት እያገዘ መሆኑን አስታወቀ ። አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀቶች ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል 11ኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እይካሄደ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባይሳ ለታ (ዶ/ር) በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንገለጹት ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት እየሰራ ነው። በተለይም በምርምር ስራዎቹ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ተጨባጭ ችግሮች እንዲፈቱ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲው በጤና፣ በግብርና፣ በባህልና በአስተዳደር ዘርፎች ያሉ ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ለሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ግብዓት እንዲሆኑ የጥናት ውጤቶችን እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል። የዛሬው የምርምር ከንፍረንስም የማህበረሰቡን ሀገር በቀል እውቀትን በማጥናት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማስተሳሰር ችግር ፈቺ የሚሆንበትን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን ማሾ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በዘንድሮው ኮንፈረንስ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት የተውጣጡ ምሁራንና ተመራማሪዎች ያጠኗቸው በርካታ የጥናት ፅሁፎች ለውይይት እንደሚቀርቡ ገልጸዋል። የቀረቡት ጥናቶች በዋናነት ሀገር በቀል እውቀቶች ላይ ትኩረት ያደረጉና በተግባር ሲተረጎሙም የህብረተሰቡን የእለት ተእለት ችግር የመፍታት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ኮንፈረንሱም እውቀቶቹ ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር ተቀናጅተው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሂደት ለማቀላጠፍና በተመራማሪዎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ለማድረግ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። በመድረኩ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙ ሲሆን፣ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፈረንስ በተመረጡ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ የጥናት ውጤቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተመላክቷል።          
ስፖርት
አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ ስድስት ነጥብ ከፍ ለማድረግ ከፉልሃም ጋር ይፋለማል
May 2, 2026 156
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 አርሰናል ከፉልሃም በኤምሬትስ ስታዲየም ይጫወታሉ።   አርሰናል በ73 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ፉልሃም በ48 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሰሜን ለንደኑ ክለብ ካሸነፈ መሪነቱን ያጠናክራል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ያሰፋል። በ34ኛው ሳምንት አስቶንቪላን 1 ለ 0 ያሸነፈው ፉልሃም ሶስት ነጥብ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን ይበልጥ እንዲያሳድግ ያደርገዋል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት የሊግ ጨዋታ አርሰናል በሊያንድሮ ትሮሳርድ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በሌሎች መርሐ ግብሮች ብሬንትፎርድ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ዎልቭስ ከሰንደርላንድ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ከብራይተን በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ባህር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ 
May 1, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ አንድ አቻ ተለያይተዋል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተካልኝ ደጀኔ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ባህር ዳር ከተማ መሪ ሆኗል። የባህር ዳር ከተማው ሰለሞን ገብረክርስቶስ በራሱ ላይ በ37ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ምድረ ገነት ሽሬን አቻ አድርጋለች። ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል። በዘንድሮው ዓመት በሊጉ በርካታ ጨዋታዎች (16 ጊዜ) አቻ የወጣው ባህር ዳር ከተማ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም። ምድረ ገነት ሽሬ በ30 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ አስቀድሞ በተካሄደው የ29ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል። የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬዎቹ ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል። የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው - አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ
May 1, 2026 242
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኑን በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ገለጹ። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በአረንጓዴ አሻራ፣ የውሃ፣ የንፋስና የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ምንጮችን በማስፋፋት ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ያስገኘ ዕድገት እያመጣ ይገኛል። የበካይ ጋዝ ልቀትን የሚቀንሱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አማራጮችን ማበረታታትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ዘላቂ ግብርናን የሚያሳልጡ ስትራቴጂክ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። ይህ የተቀናጀ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ዕድገትን በማፋጠን ለቀጣዩ ትውልድ አስተማማኝ መሰረት እየጣለ ይገኛል። በኢትዮጵያ የአየርለንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ የትብብር መስኮችን በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ እየሰራች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ተምሳሌትና ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ስኬቶችን እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በተለይም በታዳሽ ኃይልና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተመዘገቡ ውጤቶች የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ መሠረቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም አየርላንድ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። የኢትዮ-አየርላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው የልማት መስኮች በአጋርነት እየተሰራ አንደሚገኝም አምባሳደሯ ገልጸዋል። ኢትዮጵያና አየርላንድ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የበለጠ በማጠናከር በተለያዩ የልማት መስኮች የሚደረጉ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር እንደምታጠናክርም አምባሳደሯ አረጋግጠዋል።
ዘንድሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ ይተከላል
Apr 30, 2026 291
ደብረ ብርሃን፤ ሚያዝያ 22/ 2018 (ኢዜአ)፡- በመጪው ክረምት በሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ እንደሚተከል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል። ለመጪው ክረምት አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚተከሉ 294 ሚሊየን ችግኞች እስካሁን መዘጋጀታቸውን በመምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ቡድን መሪ ጌታነህ ተ/ማርያም ገልጸዋል።   በቀሪ ወራትም ፈጥነው የሚደርሱ ችግኞች ላይ በማተኮር የማዘጋጀት ሥራው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በአጠቃላይም በመጪው ክረምት ከ36 ሺህ 260 ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። ከአሁን በፊት የተተከሉ ችግኞች አርሶ አደሩን በእንስሳት ዕርባታና ማድለብ፣ በንብ ማነብ፣ በመኖ አቅርቦትና በሌሎች የሥራ ዘርፎች በማሰማራት ጥምር ግብርናን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ብለዋል። በዞኑ ባለፉት ዓመታት የለሙ 1 ሺህ 163 ተፋሰሶች የአፈር ለምነትን በማሻሻል፣ የገጸና ከርሰ ምድር ውኃን በማበልጸግና ለመስኖ ልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውንም አክለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ባለማነው የፍራፍሬ ችግኝ ተጠቃሚነታችን አድጓል-አርሶ አደሮች
Apr 29, 2026 239
ሃዋሳ ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኝ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገላቸው በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኞች አድገው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እያስቻሉ ነው፡፡ በወረዳው የፉራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር መሃመድ ቦጋለ እና አርሶ አደር ሄርቲሞ ሬቢሶ የቡና ችግኝ በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡   ችግኞቹን በኩታ ገጠም በመትከል፣ የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀትና ለጥላ የሚሆን እንሰት በመትከል ተገቢውን እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አቮካዶን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ በአቮካዶ ልማት የተሳተፉት አርሶ አደር ሙሴ በቴሾ ናቸው፡፡   ላለፉት ስምንት ዓመታት ሁለት ሄክታር በሚጠጋ ማሳቸው ላይ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው የአቮካዶ ችግኞችን ተክለው በማልማት ምርቱን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚሸጡም አክለዋል። የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ጽህፈት ቤት የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለሙያ አቶ ደሞዜ ሌዳሞ እንዳሉት በወረዳው በዘንድሮው ዓመት ከ726 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።   በተለይም ቡና በክላስተር በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ቡናን ጨምሮ ለፍራፍሬና ለምግብት ለሚውሉ ችግኞች ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት ደግሞ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ናቸው፡፡   በመርሃ ግብሩ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በመርሃ ግብሩም አቮካዶ፣ አፕልና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ለእንስሳት መኖም ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በክልሉ ለዘንድሮ ዓመት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ322 ሚሊዮን በላይ ችግኖች የተዘጋጁ ሲሆን በቡና ችግኝ ተከላ የተጀመረው መርሃ ግብር እስከ መጪው ሃምሌ ወር እንደሚከናወንም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና በታዳሽ ኃይል ያስመዘገበችው ስኬት፤ የአየር ንብረት ጥበቃና ዘላቂ ዕድገት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጠ ነው
Apr 28, 2026 541
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራና በታዳሽ ኃይል ልማት የአየር ንብረት ለውጥ እና ዘላቂ ዕድገት የማይነጣጠሉ ቋሚ አጀንዳዎች መሆናቸውን በተግባር አሳይታለች ሲሉ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል።   በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ለመገምገም ነው። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ እና በኢ-ተገማች የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተስፋና ሥጋት እያስተናገደች ነው። በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው፣ አካታችና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመገንባት አህጉራዊ ለውጥና ሽግግር ያስፈልጋል ብለዋል። ኢነርጂ፣ መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ ከተማ ከማዘመን ባለፈ በሀገራት መካከል የእሴት ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል ጠንካራ እርምጃ እየወሰደች መሆኑን በመግለፅ፤ ለአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ግብ መሳካት ገንቢ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን ለማሳደግ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሏን አስታውሰው፤ በዓለም የደን ልማት ዘርፍ ከፍተኛው ኢኒሼቲቭ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ 95 በመቶ ኃይል ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ወሳኝነት አለው ብለዋል። በአረንጓዴ አሻራ፣ በታዳሽ ኃይልና ከተማ ልማት የተመዘገቡ ስኬቶች ከኢትዮጵያ አልፎ ለሌሎች ሀገራት ዘላቂ ዕድገት ገንቢ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል። ኢኒሼቲቮቹ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የውኃ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ መሰረተ ልማትን ማስፋፋት ያስችላሉ ብለዋል። አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ ግቦችን ለመፈጸም በምታደርገው ጥረት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡   የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሉክ ባሃዱር ታፓ፤ በመላው አህጉሪቱ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚያስችሉ ተግባራት፣ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ፣ በዲጂታል ሽግግርና በቀጣናዊ ትስስር ላይ ቁልፍ አመራር መስጠትና ዕውቀትን ማፍሰስ እንደሚገባ አመላክተዋል። ይህ የአህጉሪቱ አቅም ውጤታማ እንዲሆን ሰፊ ኢንቨስትመንት እንደሚፈልግ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ በተለይም በጤና፣ በትምህርትና በዲጂታል ልማት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ዘላቂ ልማት ያለ እኩልነትና ፍትሐዊ የፋይናንስ ሥርዓት ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል በማንሳት፤ ቀጣይነት ያለው የአየር ንብረት ፋይናንስ ሥርዓት በመዘርጋት ተጎጂዎችን መድረስ እንደሚገባም ገልጸዋል። ለዚህም አባል ሀገራት የውስጥ ሀብት አሰባሰብን ማሳደግ፣ የግሉን ዘርፍ ማበረታታትና ከአጋር አካላት ጋር በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ፕሬዝዳንት ሉክ ባሃዱር ታፓ አሳስበዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት ይገባል 
Apr 28, 2026 511
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት እንደሚገባ የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃጸም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 ጎን ለጎን የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው።   የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድን ሀገር በቀል በማድረግ አካታች ዕድገትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራትም ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን ከአጀንዳው ጋር በማጣጣም የበጀት ድልድልና የፖሊሲ እርምጃዎችን ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦች የበለጸገች አህጉርን እውን ለማድረግም የአባል ሀገራት ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። የአጀንዳ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት የተሳለጠ የለውጥ ሽግግርን ለመፍጠርም ጠንካራና የተሰናሰለ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ የፖሊሲ ፍሰት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በወሳኝ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚኖራቸውን ትብብርና ቅንጅት የሚያበረታታ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።   የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትርና ተሰናባቿ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ ቢሮ ሊቀ-መንበር ሮቢናህ ናባንጃ በበኩላቸው፤ የአፍሪካውያን ድምፅ በወሳኝ የዓለም መድረኮች ላይ መንፀባረቅ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በከፍተኛ ደረጃ ከሚደረግ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ባለፈ በወሳኝ ስትራቴጂክ ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካትም ሎጂስቲክስ፣ ትራንስፖርትና መሰል የትኩረት ዘርፎች ላይ በስፋት በመሰማራት ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ነው
Apr 28, 2026 282
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 በትይዩ የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። በአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድ ሀገር በቀል እንዲሆን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራት ብሔራዊ የልማት ዕቅዶቻቸው ከአጀንዳው ጋር እየተጣጣመ መምጣቱን በማንሳት፤ የበጀት ድልድልና ፖሊሲዎቻቸው ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ የሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን በማሳካት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በሀገራት መካከል ያለው ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸውን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አለባቸው
Apr 27, 2026 310
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦‎ አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸው ላይ እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታንዛኒያ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናትን ለአረንጓዴ የኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ማዋል" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁት የ12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ቅድመ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ እንደ ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ግራናይት እና ሌሎች የከርሰ ምድር ሀብቶችን ጨምሮ የዓለምን 30 በመቶ ማዕድናትን ይዛለች፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻዋን የዓለምን ከፍተኛ የኮባልት ማዕድን የያዘች መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም አፍሪካን የዓለም አቀፍ የኃይል ሽግግር /Energy Transition/ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ዩራኒዬምና ሌሎች የከርሰ ምድር የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ፤ ለዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል አቅርቦት አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ኃይል ልማት እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት ብትሆንም አብዛኛው በጥሬ እቃ መልክ ወደ ውጭ የሚላክ በመሆኑ የአህጉሪቱ የእርስ በእርስ ግብይት ከሁለት በመቶ እንዳማይዘል ተናግረዋል፡፡ በአህጉሪቱ የማዕድናት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን መገንባት ቢቻል በየዓመቱ ከ24 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና ለ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማዕድን ፖሊሲ ለእሴት መጨመር፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ሁሉን አቀፍ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአህጉሪቱ የተቀናጀ ቀጣናዊ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለውን ፍላጎት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አህጉራዊ የማዕድን ሀብቶችን ወደ ዘላቂ ብልጽግና መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጣናዊ እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር የማዕድን ጸጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካዳሪ ሲንጎ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና አካታች ዕድገት ለማስመዝገብ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የሚኖረን ትብብርና ተሳትፎ ስትራቴጂያዊና መዳረሻ ግብ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮት ሽግግርን ለመፈጠር በአቅም ግንባታ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 687
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 26, 2026 392
ክልሎች፤ሚያዝያ 18 /2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር የምንቃኝበት ነው። በዚህ ሳምንትም አንኳር የክልሎች ክንውኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ቀርበዋል። የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተም! ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማት ስራ መደባኛ ስራዋ ካደረገች ወዲህ አያሌ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእቅድ እና በቁርጠኝነት በመከናወኑ ከውጪ የሚገባ ስንዴ ቀርቷል፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቱም ቀጥሏል። ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ሽግግርም ዓመቱን ሙሉ በማልማት እየታጀበ ሲሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ነው። በዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በተያዘው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊማ፣ በጂዳ ወረዳ ሲባ ሲርቲ እና ቂምቢቢት ወረዳ ሰገሌና ደርማሙሳ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ እና በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ አስቃኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፎቶ ጋር ያያዙት መልዕክትም ''ይህ የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተማችን ነው'' ይላል። ብሪክስ -- ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች። መድረኩም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የተካሄደበት፤ በብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የተሰጠበትም መሆኑ ተመላክቷል። ማረም እና ማነጽ የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል እንዲሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነው። የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ “የማረሚያ ተቋማት ለሀገር ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት፣ ከማረሚያ ቤት የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም ከማረም የማነጽ ተሃድሶ ልማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉባኤው በልዩ ሁኔታ የመከረበት ነው። ኢትዮጵያ ማምረቷን ቀጥላለች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክሲፖ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ ነው ብለዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት። ዘንድሮ ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል በኢትዮጵያ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ውኃ የህልውና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ለፍጡራን ሁሉ ውኃ ህይወት ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ግን ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል። በሳምነቱም በአፋር ክልል ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር እና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተከናወነው ልማት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱ በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ መንግስት የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል፤ በተለይም የለውጡ መንግስት ለቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሰራው ስራ የውኃ ተደራሽነት በእጅጉ ማደጉን አንስተዋል። ልምድ ልውውጥ እና ተሞክሮ -ለምክር ቤቶች ሌላው ቅኝታችን በዚህ በተጠናቀቀው ሳምንት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱን የዳሰሰ ነው። የጋራ የምክክር መድረኩ ዓለማ የልምድ ልውውጥና የልማት ሥራዎችን በመመልከት ተሞክሮ መለዋወጫ ነው።የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ መንግስት ሕዝቡ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት ማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ይገባል ብለዋል።የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶች ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል። የጤና ልማት ስራ እስከ አክሞ ማዳን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት የአጋር ድርጅቶች አስተዋጾ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም የተመለከተው በዚህ ሳምንት ነው። ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ መሰል የጤና ዘርፍ የልማት ስራዎች መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ከማሳካት አንጻር እገዛቸው ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።ማዕከሉ ማህበረሰቡ በቅርበት ሕክምና እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ሲታከም ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ ያስቀራል። ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ማሽኖች፣ የመድሃኒት ቤት፣ መኝታ አልጋዎችና የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሟልቶ የተገነባ መሆኑም ታውቋል። የከተሞች ኮሪደር- ከቱሪዝም እስክ ኮንፍረንስ ማዕከልነት በኮሪደር ልማት እጅግ ከተዋቡ እና ከደመቁ የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ ናት። በሳምንቱ የከተማዋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ የምስጋናና ዕውቅና እንዲሁም የአራተኛ ዙር የኮሪደር ልማትና የሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ‎ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርቡ ቀጥሏል ብለዋል። በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሪደር እና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች እንደሚቀጥሉ አንስተው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ምርጫ -የዴሞክራሲ መሰረት ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹበትም ነበር። ኢትዮጵያዊያን መጪውን ጊዜ የተሻለ የሚያደርግላቸውን መንግስት ለመመረጥ ዝግጅታቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 431
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል።   ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል።   በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል።   በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 19, 2026 495
የምግብ ሉዓላዊነት - ከተረጂነት መላቀቂያው መንገድ በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ ከተረጂነትና ጠባቂነት መፋቻ መንገዶች መካከል የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ ብልኀት አድርጋ እየታተረች ነው። ይህን ተከትሎም የዜጎችን የምግብ ፍላጎት በራስ የምርት ዐቅም የመሸፈን ሥራ በመከወን ከጠባቂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ስኬታማ ናቸው። ለዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ከልመና ወጥታ ወደ ውጭ ገበያ መላክ መጀመሯ አሥረጅ ነው። በመሆኑም ከውጭ የኢኮኖሚ ጥገኝነት በመላቀቅ የዜጎችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማስከበር በስንዴ ልማት የተመዘገበውን ስኬት በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለመድገም ርብርብ እየተደረገ ነው። በዚህም መሠረት በሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሻይ ቅጠል እና ሌሎች የተለያዩ ሰብሎች ላይ እየተከናወነ ያለው ሥራ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ የአመራር ቁርጠኝነት የአግሪኮላ ሜዳሊያ በ2016 ዓ.ም ማበርከቱ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረት የተሰጠ ዕውቅና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብን ከማስቀረት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ ጥሬ ሃብቶች፣ተስማሚ የዓየር ንብረት፣ ለሥራ ትጉ የሆነ ወጣት እንዳላት እና እነዚህን ሃብቶች ታሳቢ በማድረግ የታሪክ ዐውራ የሆነችውን ሀገር ልማት ወደፊት ለማራመድ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ እንደከፈልን ሁሉ፤ ከምግብ ጥገኝነት ለመላቀቅ በትጋት መሥራት ይገባል ሲሉ ማስገንዘባቸው ይታወሳል። የምግብ ሉዓላዊነት፣የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፣ የበጀት ሉዓላዊነት ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ መሆናቸውንም አብራርተዋል። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበርም ብሔራዊ ዐርበኝነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ሀገራዊ ትልሙ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያሸጋግር መልካም ጅማሮ ነው።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 19, 2026 377
ክልሎች፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የንፋስ ሃይል በቀጥታ የምናመራው በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ አካባቢ ነው። በኢተያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው የመረቁትን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እንመለከታለን። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 100 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማት ወደ ፊት እየተራመደች መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሥራ ነው። ኢትዮጵያ ዘንድሮ ከጉባ እስከ አሰላ፣ ገናሌ እና አይሻ በሃይል ልማት ዘርፍ ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ፕሮጀክቶች አስመርቃለች። የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ደግሞ በዚህ ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ሥራ ጀምሯል።   ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምርቃቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ከለውጡ በፊት የነበረው 4 ሺህ ሜጋ ዋት የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅም አሁን ላይ ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት በመድረስ ከእጥፍ በላይ እድገት የተመዘገበበትን ትልቅ ስኬት አንስተዋል። የስንዴና ገብስ ሰብሎችን በከፍተኛ መጠን የሚያመርተው አርሲና አካባቢው አሁን ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚመረትበት አካባቢ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም በሁሉም መስክ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እናስቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል። ቢሾፍቱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማም በዚህ ሳምንት በቢሾፍቱ ሀርሰዴ አዳራሽ መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ስኬታማ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። በተለይም የክልሉን ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተሻለ መልኩ ያሳደጉ የከተማ እና የገጠር የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ያስረዱት።   ከዚህ ባለፈ የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማቀላጠፍ የሚያግዙ በቴክኖሎጂ የተደገፉ የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራሮች መተግበራቸውንም ተናግረዋል። የቢሾፍቱ መድረክ በድምሩ የግብርና፣ የገጠርና የከተሞች ልማት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ክንውን በዝርዝር የታየበት ውጤታማ መድረክ እንደነበረም ተመላክቷል። የአሎማ ክላስተር ሌላ የሳምንቱ ዓበይት ጉዳይ ወደ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ይወስደናል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በዚህ ሳምንት ነው። በመስኖ የለማ የስንዴ ክላስተር የተጎበኘበትና በተሁለደሬ ወረዳ በክላስተር ለሚከናወነው የተቀናጀ የፍራፍሬ ልማት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በይፋ የተጀመረበት እንዲሁም የክልሉ የ10 ዓመት የግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታ ይፋ የተደረገበትን ሁነት እናገኛለን።   በእነዚህ ሁነቶች ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የመደመር መንግሥት በሁሉም ዘርፎች ለሀገር እድገትና ማንሰራራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም በግብርና፣ በመስኖ ልማት፣ በቱሪዝምና ሌሎች መስኮች በተግባር የተመለከትናቸው የልማት ሥራዎች ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። የአሎማ ክላስተር የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የሓይቅ ዳር አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የማቻል ጥረት በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን የሚያሳዩ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሀገርን የማሻገር ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የታሪክ መሰነጃ የሳምንቱ በረራችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ የሰው ልጅ መገኛ፣ የኤርታሌ ትኩሳት የሚገነፍልባትና የአዋሽ ወንዝ የተንጣለለባት አፋር ክልል ገብተናል። በአፋር ቆይታችን ትኩረታችንን ሰመራ በማድረግ በስፍራው ሊገነባ የታሰበውን የሉሲ ሙዚየም እንመለከታለን። ሙዚየሙን ለመገንባት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ የፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት አድርገዋል። ለሉሲ አፋር ቤቷ ነው፤ ሀዳር የተባለው ስፍራ ደግሞ መገኛዋ ነው። በመሆኑም በዚህ ከሰው ልጅ መገኛ ጋር የተቆራኘን ስፍራ ሙዚየም ገንብቶ፣ የቱሪስት መስህብ አልምቶና አካባቢውን በስፋት አስተዋውቆ የገቢ ምንጭ ማድረግ ሲቻል ለምን ተዘንግቶ ቆየ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ይሆናል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ አሁን አፋር ሰመራ ላይ በሉሲ የተሰየመ የሀገር ታሪክና ቅርስ ማጣቀሻ፤ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ማሳያ የሆነ ሙዚየም ለመገንባት ዝግጅት መደረጉ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል።   የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ የሚገነባው ሙዚየም የሀገር ታሪክና ቅርስ የሚሰነድበት፣ የአፋር ክልል ህዝብ ቱባ ባህሎች ተጠብቀው የሚዘልቁበት፣ የሰው ልጅ አመጣጥና ዝግመተ ለውጥ የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ የሚካሄድበት ይሆናል ብለዋል። እሳቸው እንዳሉት የሙዚየሙ ግንባታ በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገለግሎት የሚበቃ ይሆናል። የአፋር ክልል በመስኖ ቢያለሙበት፣ የጥጥ እና የቴምር ልማት ቢካሄድበት ተዝቆ የማያልቅ እምቅ አቅም ያለው መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም በለውጡ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን እምቅ የቱሪዝም ሃብቱንም በማልማትና በመጠበቅ የሃገር ሃብት የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሉሲ ሙዚየም ግንባታ ሁነኛ ማሳያ ነው። የሳምንቱ ቅኝታችን እንደቀጠለ ሲሆን አሁን ደግሞ በቀጥታ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ተገኝተናል። አሶሳ በሳምንቱ በሃይማኖት አባቶች ጸሎትና ዱአ ተባርካ ስለ ሰላምና አብሮነት የሚመከርባት ከተማ ሆና እንግዶቿን ተቀብላ አስተናግዳለች። የተለያዩ የኃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ "ሰላምን ይበልጥ ለማስፋት እና ለማስረጽ የሃይማኖቶች ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ አባቶች ስለ ሰላም እና አብሮነት እንትጋ ለትውልድ ግንባታም መስራት ግድ ይለናል በማለት አፅንኦት በመስጠት መክረዋል።   የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኃይማኖቶች ለሰላም እና ለህዝቦች አብሮነት ያላቸውን አስተምህሮ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ሀገራዊ የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን አለባቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ሰላምን ለማጽናት እና የወንድማማችነት ድልድይን ለመገንባት እንስራ በማለትም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ከአሶሳ ወደ ሀዋሳ ስንጓዝ የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት (አግራ-AGRA) ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የኤልቶ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን የሥራ እንቅስቃሴን መጎብኘታቸውን እናገኛለን። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጥምረቱ የቦርድ ሊቀ መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ አርሶ አደሮች ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ተስፋ የተሰነቀበት መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። የግብርና ልማትን የማዘመን፣ ምርታማነትን የማሳደግና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተዋል።   የጥምረቱ ፕሬዚዳንት አሊስ ሩህዌዛ፤ በአፍሪካ የግብርና ስርዓት ሽግግርን ለማጠናከር በተለይም አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል። በአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ሂደት ውስጥ ደግሞ የኢትዮጵያ ለውጥ አስደናቂ ስለመሆኑ አንስተዋል። ሌሎች በዚህ ሳምንት በሁሉም ክልሎች ባደረግነው ምልክታ በተለይም የምርጫ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ ዜጎች የምርጫ ካርዳቸውን እየወሰዱ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችም የምረጡኝ ቅስቃሳ ማድርጋቸውን ቀጥለዋል። የግብርና ልማት ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ዝግጅት እና ሌሎችም የልማት ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ የቀጠሉበት ሳምንት ነበር ማለት ይቻላል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 25, 2026 472
ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥን ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም ገልፀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር መምከራቸው ነው። በዚሁ ወቅትም፤ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር መክረናል ብለዋል። በተመሳሳይም ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት ይዘው ከመጡት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እንዲሁም የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች ሲሉም አስታውቀዋል። • በኢትዮጵያ የበቆሎ መስኖ ውጤታማነት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ፤ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዕርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን ዕውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። • መሶብ የሞባይል አገልግሎት መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሶብ አገልግሎት የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የስራውን ውጤታማነት ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰራሩን ይበልጥ መስፋፋት አስፈላጊነትም ገልጸዋል።ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን ገልጿል። ‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ሥርዓት እንዳለውና የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ማካተቱንም አመላክቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል። በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደኅንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል፤ መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ፣ ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ፣ የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን፣ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ‎በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል። • የ100 ቀናትና የ9 ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት የሥራ ዘመኑ 3ኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ‎የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የዕድገት ሂደትን አስመዝግቧል ብለዋል። ጥረቶቻችን የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ስለ 3ኛው 100 ቀን አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው የ100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ተገምግሟል። በዚሁ ወቅትም አቶ ተመስገን፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ የሚገባትም ትልቅ ሥፍራ ነው፤ እኛ ደግሞ የዚህ ታሪክ ሠሪዎች የመሆን ዕድል በእጃችን ላይ ነው ሲሉ አዝገንዝበዋል። በኮሪደር ልማት፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችና በዲጂታል ኢትዮጵያ ዘርፍ የተካሄደው የመሠረተ-ልማት አብዮት የሀገራችንን እንዲሁም የከተሞቻችንን ገጽታና አገልግሎት ቀይሯል ብለዋል። በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት አማካኝነት የተረጅነትን ቀንበር ሰብረን ወደ ምግብ ሉዓላዊነት እየተጓዝን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዲፕሎማሲው መስክም ኢትዮጵያ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት በመሸጋገር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነቷን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሳድጋለች ብለዋል። • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ፤ በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች፣ በሀገራችን የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የሚመለከት የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ ስምምነት፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ፣ በሥድስት ዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ መክሮ በማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል። • ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች ብሎ ባጋራው መረጃ፤ በመሠረተ-ልማት (የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት)፣ በዲጂታል መሳሪያዎች (ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም)፣ በዲጂታል መንግሥት (በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትሕ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ) የሚሉትን አንስቷል። በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት (‎5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በዕውቀትና በፈጠራ ማብቃት፣ በተቋማት ግንባታ (‎ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር)፣ በሕግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት (በፋይዳ መታወቂያ ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት) የሚሉት ጉዳዮችን ጠቅሷል። • የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ሀገራዊ የስንዴ ልማትን በተመለከተም ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል ብሏል። ‎‎ከሌማት ትሩፋት አንጻርም፤ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው፤ የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። ዲጂታል ኢትዮጵያን አስመልክቶም፤ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው ብሏል። ‎‎የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትም፤ የከተሞች መሠረተ-ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት አኳያም፤ የማምረት ዐቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው ብሏል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ስለመሆኑም አመላክቷል። እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ሲልም በአጽንዖት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 420
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል።   በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ኢትዮጵያ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መንገድ
Apr 21, 2026 1646
(በዮሐንስ ደርበው) ታሪክ እንደሚነግረን፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ያገኘው የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን በሚመለከተው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1883 በተፈረመው የፓሪስ ስምምነት እንዲሁም፤ በ1886 የተፈረመውን የሥነ-ጽሑፍና ሥነ-ጥበብ ሥራዎች ጥበቃን የተመለከተውን የበርን(ስዊዘርላንድ) ስምምነት ተከትሎ ነው። እነዚህ ስምምነቶችም በዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት የሚተዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣንን፤ በ2022 ዓ.ም ፈጠራንና ኢኖቬሽንን በማበረታታት የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ዕሴት በመለወጥ ሂደት ለሀገራዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና የሚጫወት በአፍሪካ ተምሳሌት የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ለማድረግ እየታተረች ነው። ለዚህ ርዕይ መሳካትም፤ ተቋሙ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለሀገራዊ ፈጠራ መጎልበት፣ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሊጂ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደግ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀገራዊ የመዋቅር ሽግግርን መደገፍ የሚል ተልዕኮ አንግቦ እየሠራ ይገኛል። የእስካሁኑ የንግድ ምልክት፣ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ምዝገባ   የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ወርቅነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም እስከ ያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ድረስ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና በፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) 20 ሺህ 476 ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ 14 ሺህ 729 የንግድ ምልክቶች፣ 5 ሺህ 254 የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም 1 ሺህ 781 የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ምዝገባ በተቋማችን አማካኝነት ተከናውኗል። የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምንድን ናቸው? አዕምሯዊ ንብረት ማለት በሰው ልጅ አዕምሮ የሚፈጠሩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚመለከት መሆኑን የገለፁት አቶ ብሩክ፤ እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በንብረትነት የሚታወቁበትን አግባብ የያዘው ሥርዓት ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት መብት እንደሚሰኝ ያስረዳሉ። በዚህ አግባብ፤ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ንብረት ሁሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ባለመብቶች የሚሰጡ የባለቤትነት መብቶች መሆናቸውን እንረዳለን። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ ወጥ ሥራዎችን ለማመንጨት የፈጠራ ባለመብቶች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ከብዙ ድካም በኋላ ያገኟቸው የፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ነው። ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንድም፤ የሰው ልጅ ቀጣይ ዕድገትና የኑሮ ደኅንነት ዋስትና መሠረት የሚያርፈው በቴክኖሎጂና ባሕል ዘርፎች በሚያሳርፋቸው ፈጠራዊ ብቃቶቹ በመሆኑ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ ሀብት የሚያስገኝ በመሆኑና ይህም የኢኖቬሽን ሥርዓቱን ስለሚያሳድግ ነው ይላሉ አቶ ብሩክ። እንዲሁም፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና ዘርፉን ለሕዝብ የማስተዋወቅ ተግባር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ የድርሻውን ስለሚወጣና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በአጠቃላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲቆም ስለሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ሀገራት ጠንካራ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠሩ ቁጥር ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የልማት መሣሪያ መሆኑን ይገነዘባሉ። ጠንካራና ፍትሐዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠራ ባለቤቶችና በተጠቃሚው ሕዝብ ዘንድ ሚዛናዊ ነው ያሉት አቶ ብሩክ። በአጠቃላይ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአጽነዖት አንስተዋል። ዜጎች በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት እንዴት ተጠቃሚ ይሆናሉ? ባለብዙ ቢሊየን ዶላር የፊልምና ድምጽ ሪከርድስ አሳታሚዎችና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎች ለብዙ ሚሊየኖች የመዝናኛ ሥራዎች የሚያበረክቱት የቅጅ መብት ጥበቃ በመኖሩ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አቶ ብሩክ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን ምርቶችና አገልግሎቶችን መለየት የሚያስችላቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ምልክቶች ጥበቃና የመብት ማስከበር ሥርዓቶች ባይኖሩ ኖሮ ተመሳስለው በሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች መታለልና ሌሎችም ችግሮች ያጋጥማቸው እንደነበርም ጠቁመዋል። ስለዚህ ምርቶችን በመሸመት ሂደትም በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያለምንም ግራ መጋባት ግብይቱን ማከናወን እንደሚያስችላቸው መገንዘብ ይቻላል። እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ ለፓተንት የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ በመደረጉ መሰጠት የሚገባቸው ማበረታቻዎች የማይሰጡ ከሆነ፤ የፈጠራ ባለሙያዎች ቀጣይ የምርምር ሥራዎችን ማሳደግና ማስፋት እንደማይችሉ ይገመታል። በቀጣይነት የሚገኙ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎች አለመኖራቸው ደግሞ፤ በምርቶች ተጠቃሚና አጠቃላይ የኑሮ መሻሻል ሂደት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ዓይነቶች እንዴት ይመደባሉ? የአዕምሯዊ ንብረት፤ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት (Industrial Property) እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች (Copyright and Related Rights) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚመደብ ያስረዳሉ። አክለውም፤ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት በውስጡ፤ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ እና የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች የተሰኙ አራት ክፍሎችን እንደሚይዝ ያብራራሉ። ፓተንት ምንድን ነው?፡- ፓተንት ማለት በአንድ ቴክኒካዊ ባሕርይ ባለው የፈጠራ ሥራ ላይ የሚኖር የፈጠራ ባለቤትነት ብቸኛ መብት መሆኑን አቶ ብሩክ አስረድተዋል። የፓተንት መብት በአንድ ምርት (ለምሳሌ ማሽን ወይም የአመራረት ሂደት (Process) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ፈጠራውም ለአንድ ቴክኒካዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል ይላሉ። ከፈጠራ ሥራው አመንጪ ይሁንታ ውጭ ሥራውን ገበያ ላይ ማዋል፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወዘተ… እንደማይቻልም አክለዋል። ፓተንት ለባለ መብቱ የጥበቃ መብት የሚያስገኝ ሲሆን፤ የጥበቃው ዘመንም በአጠቃላይ እስከ 20 ዓመት ሊደርስ ይችላል። ፓተንት የሚያስገኛቸው ሕጋዊ (የጥበቃ) መብቶች፡- የፈጠራ ሥራውን መጠቀም የሚችሉና የማይችሉ ሰዎችን መወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ሥራውን እንዲጠቀሙ የመፍቀድ ወይም የፈቃድ ውል ስምምነት የመስጠት እንዲሁም የፈጠራ ሥራውን የመሸጥ (ለአዲስ የፓተንት ባለመብት) የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። የፓተንት ሥራዎች ለምን ያስፈልጋሉ?፡- ይህን ሲያብራሩም፤ ፓተንት ለፈጠራ ባለመብቶች ዕውቅናንና ሽልማቶችን (ማበረታቻዎችን) የሚሰጥ በመሆኑ፣ ፈጠራዎቹ የኢኖቬሽን ሥራዎችን ስለሚያጠናክሩና በዚህም ቀጣይነት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት መሻሻልን የሚያረጋግጥ በመሆኑ እና በሌሎችም በጎ አስተዋጽዖዎች ፓተንት በዕጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የንግድ ምልክት ምንድን ነው?፡- የንግድ ምልክት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌላው ምርትና አገልግሎት እንዲለይ ለማስቻል በንግድ ምልክት ባለቤቶች ለምርታቸውና አገልግሎታቸው መለያ እንዲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ልዩ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ምልክት ሸማቹ ሕብረተሰብ የሚፈልገውን ምርትና አገልግሎት በቀላሉ ለይቶ እንዲገዛ ከማስቻሉም በላይ በሚገዛው ምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ በመተማመን ፍላጎቱን እንዲያሟላ ያደርጋል። የንግድ ምልክት ለባለመብቱ ምን ጥቅም ያስገኛል?፡- ምርቶቹ (አገልግሎቶቹ) በተጠቃሚዎች እንዲለዩለት ወይም እንዲታወቁለት ያደርጋል፣ ክፍያን መሠረት አድርጎ ሦስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የንግድ ምልክቶች በራሳቸው ዋጋ አላቸው (የአዕምሯዊ ንብረት ዋጋ ትመና (IP Valuation) ለምሳሌ በፈረንጆቹ በ2026 የመጀመሪያ ወራት አፕል (Apple) 600 ቢሊየን ዶላር፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) 565 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር፣ ጉግል (Google) 433 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ግምት እንደነበራቸው ተብራርቷል። በተጨማሪም፤ የንግድ ምልክት በሕግ በሚቀመጥ የጊዜ ገደብ መሠረት እየታደሠ ለዘላለም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ የንግድ ምልክት ባለቤቱን በማስተዋወቅ ዕውቅናና የገንዘብ ትርፍን ያስገኛል፤ የንግድ ምልክት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (ተመሳስለው የሚሠሩና ለገበያ የሚቀርቡ ሥራዎችን (Counterfieited Products) ለመዋጋት ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ ምልክት ሰዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ሚዛናዊ በሆነ አግባብ እንዲያቀርቡ በማድረግና በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽዖው የላቀ ነው ብለዋል። ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ምንድን ነው?፡- ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በምርቶች ሥነ-ውበት (Esthetics) ላይ ተመስርቶ ቅርጽን፣ መስመሮችን ወይም ቀለምን በመጠቀም ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የገዥዎችን (ሸማቾችን) ቀልብ ለመሳብ እንዲችሉ በምርቶች ላይ የሚገለጽ የንድፍ ጥበብ ዘርፍ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፤ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች በኢንዱስትሪና ዕደ-ጥበብ ምርቶች ላይ ተዘጋጅተው ሊወጡና ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ ይላሉ። ዘርፉ ከቴክኒካልና ሕክምና መሣሪያዎች አንስቶ እንደ ሠዓት፣ ጌጣጌጦችና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ዕቃዎችን ሊያካትት ይችላልም ብለዋል። የቤት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የሕንጻ ንድፎችን እንዲሁም የጨርቃጨርቅ ንድፍ ውጤቶች በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ሥር የሚወድቁ ይሆናሉ ይላሉ። ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች ጥበቃ የሚደረግላቸው አዲስ ወይም ወጥ ከሆኑ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በዲዛይኑ ውስጥ ከሚገለጸው ምርት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ጥበቃ እንደማይደረግላቸው አስታውቀዋል። ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?፡- በምርቶች ውበት ላይ የሚገለጽ በመሆኑ የተጠቃሚውን ዐይን ይስባል፣ የምርቶችን ዋጋ ይጨምራል፣ ፈጠራንና ውድድርን ያበረታታል፣ ለባለመብቱ ብቸኛ መብትን ያጎናጽፋል፣ በኢንዱስትሪዎች፣ ባሕላዊ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ ፈጠራ በማሻሻል ኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርጋል፣ የወጭ ንግድን (Export Trade) ያሳድጋል በማለት የኢንዱስትሪ ንድፍ ጥበቃ አስፈላጊነትን ያብራራሉ። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካች ምንድን ነው?፡- የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች በምርቶች ላይ የሚቀርቡ ምልክቶች ሆነው እነዚህ ምልክቶች አንድ የተወሰነ አካባቢን በምርቱ ምንጭነት የሚያመላክቱና ጥራትንና ዝናን ከቦታው ጋር አስተሳስረው የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን አቶ ብሩክ ያስረዳሉ። በአብዛኛው የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች ልዩ ምርቱ የሚገኝበትን የቦታ ስም (Specific Local Geographyical Factors – Climate, Soil) ይይዛሉ። ለምሳሌ፡- Roquefort for Cheese -France፣ የማረቆ በርበሬ፣ የሸኖ ቅቤ፣ የዓድኣ ጤፍ … የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሾች ናቸው። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾችን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?፡- ተጠቃሚዎች ምርቶች የሚገኙበትን ሀገር ወይም አካባቢ በቀላሉ ለመለየት፣ ሕጋዊነት በሌላቸው ወገኖች የምርቱ መገኛ አካባቢ እና የምርቱ ዝና በተሳሳተ መልኩ ለሌላ ምርት መጠሪያ እንዳይውል ለመከላከል ይረዳል ይላሉ። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምንድን ናቸው?፡- የቅጅ መብት በሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ ወጥ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ደራስያን፣ አርቲስቶች ወዘተ… የባለቤትነት መብት የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም ነው ሥራ አስፈጻሚው የሚያስረዱት። በአንጻሩ ተዛማጅ የቅጅ መብት ማለት ይላሉ አቶ ብሩክ፤ በወጥ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተመስርተው የሚሠሩ ተዛማጅ (Related) የፈጠራ ሥራዎችን ያካትታል። ለምሳሌ፡- ከዋኞቹ (ተዋንያን እና ዘፋኞች)፣ ድምጽ ሪከርዲንግስ፣ አሳታሚዎች (ኮምፓክት ዲስኮች)፣ የብሮድካስት ተቋማት፣ (ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ዘርዝረዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምን ዓይነት መብቶች ያስገኛሉ?፡- ባለመብቶች ሥራዎቻቸውን ለመጠቀም ወይም ሦስተኛ ወገኖች እንዲጠቀሙባቸው የመፍቀድ፣ ሥራዎች እንዲባዙ፣ ለሕዝብ እንዲዳረሱ፣ እንዲሠራጩ፣ እንዲተረጎሙ ወይም ወደሌላ ሥራ እንዲቀየሩ የመፍቀድ ወይም የመከልከል፣ የደራሲነት (የአመንጭነት) መብት ዕውቅና እንዲያገኙ፣ በብዕር ስም የመጠቀም መብት፣ ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ የሥራ መዛባት እንዳይኖር የመጠበቅ ወይም የሥራው ወደሌላ መቀየር የሚያስከትለውን ጉዳት የመቃወም ወዘተ መብቶችን ያስገኛሉ ብለዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?፡- የሰውን ልጅ የፈጠራና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ያሳድጋል፣ ለፈጠራ አመንጭዎች መበረታታትን ይፈጥራል፣ የሕጋዊ ተፈጻሚነትን በማረጋገጥ አመንጭዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈሱ የፈጠራ ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን የሥርጭት ሽፋን ያሳድጋል ነው ያሉት አቶ ብሩክ። የፓሪስ ስምምነት አባል ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር ለመሆን ለዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ያስገባችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማጽደቁ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ለስምምነቱ ተገዢ ሆናለች። አቶ ብሩክ እንዳብራሩት፤ የፓሪስ ስምምነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪያዊ ንብረቶችን ጥበቃ የሚመለከት ነው። የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የግልጋሎት ሞዴል (በአንዳንድ ሀገራት ሕግ ኢትዮጵያን ጨምሮ “የአነስተኛ ፈጠራ የባለቤትነት መብት” በመባል የተደነገገ)፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም (የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ስያሜዎች)፣ ጂኦግራፊያዊ አመላካች እና ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድርን መከላከል ያካተተ ነው። የስምምነቱ መሠረታዊ ድንጋጌዎች በሦስት ዋና ዋና መርሆዎች እንደሚከፈሉ ጠቁመው፤ እነሱም፡- የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር መሆን በሌሎች አባል ሀገራት ውስጥ እንደ ዜጋ የመስተናገድ መብት፣ የቀዳሚነት መብት የማግኘት፣ በቀላሉ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የማግኘት አሠራር እና መሰል ጉልህ ጥቅሞችን የማግኘት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ይገልጻሉ። በመሠረቱ የፓሪስ ስምምነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃን በማቀላጠፍ አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን እንዲሁም የንግድ ሥራዎች ድንበር ሳይገድባቸው የፓተንትና የንግድ ምልክት መብቶች በቀላሉ እንዲጠበቁ በማድረግ ፈጠራን፣ ንግድን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እውን ያደርጋል ብለዋል። የዘንድሮው የአዕምሯዊ ንብረት ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም “አዕምሯዊ ንብረትና ስፖርት፤ እንዘጋጅ፣ እንጀምር፣ እንፍጠር!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በስፖርት ዓለም ውስጥ የሚከሰቱ ተወዳዳሪዎች የግልና የጋራ ፈጠራዎች፣ ንድፎች፣ ብራንዶችና የመልካም ዝና ታሪኮችን ለመጠበቅና ሀገራትን ጭምር ለማስተዋወቅ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል። ምክንያቱም ስፖርት በባሕርይው በውድድር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፤ ከሀገራት ዝና፣ ከፋሽን ዲዛይን፣ ከመዝናኛ፣ ከሚዲያ ሥርጭት፣ ከጤናና ከዕለት ተዕለት መገልገያ ቁሶች ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።  
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 18, 2026 1121
ከሚያዝያ 5 እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ ‎በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ ዕቅድ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ዕውን አድርጋለች ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ-ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል ሲሉም ገልጸዋል። ይህም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ አብነት ነው ብለዋል በወቅቱ። በሁሉም ዘርፎች የምናስመዘግበው የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ ተጠናክሮ እየቀጠለ ይበልጥም እየለማ ይሄዳል፤ ከምንጊዜውም በላይ ታላቅ የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉም አመላክተዋል። • ከኮፕ32 አስተናጋጅነት ጋር በተያያዘ ምክክር መደረጉ የኮፕ32 አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ‎ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅቷን ቀደም ብላ መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ከብሔራዊ ኮሚቴው ጋር በነበረን ስብሰባ፤ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም ክፍተቶችን የመለየት እና ሁሉም ጥረቶቻችን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተዳሷል ሲሉ ገልጸዋል። ከግምገማ ባሻገር የቀጣይ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰው፤ ትኩረታችን ግልጽ ነው፤ በጠንካራ ትብብር፣ በተዋሃደ ታላቅ ርዕይ እና የጋራ ጽኑ ትጋት ተናበን ይህን ዓለም አቀፍ ሁነት በልኅቀት በማስተናገድ የሀገርን ታላቅነት ዳግም ማሳየት ነው ብለዋል። • የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከዚያም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይትም፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቅኝ ያልተገዙ፣ ለአኅጉሩ ነፃነትና አንድነት ድምፅ በመሆን ከጋራ የጽናት ታሪክ የሚመነጭ ጥልቅና ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት አላቸው ያሉት ጠላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬም እንደ ሁሌው ኢትዮጵያ ከሰፊ ገበታዋ ያላትን ታላቅ ዐቅምና ዘላቂ ወዳጅነት አብረዋት ለሚጓዙ ሁሉ ለማካፈል ዝግጁ ናት ብለዋል። ጉብኝቱም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን የቆየ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት ወሳኝ ምዕራፍን ከፍቷል ሲሉ ገልጸዋል። ከሁለትዮሽ ስብሰባው በመቀጠልም በሁለቱ ሀገራት በኩል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳካት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስምምነቶቹ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማካፈል እንዲሁም ከአጋሮቻችን የተለያዩ ዕይታዎችን በመቅሰም ለአኅጉሩ ዕድገት ዘላቂና አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በጋራ ለማፍለቅ እንደ ወሳኝ መሠረት ያገለግላሉ ነው ያሉት። • የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ባሳለፍነው ሳምንት በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ቀጣይ ትብብሮችን በምናጠናክርባቸው ቁልፍ መስኮች ላይ መክረናል ብለዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም፤ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ፣ የተሻገረ ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ በበቂ ሁኔታ ዜጎችን ሥራ ለማስያዝ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሚና አይተኬ መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ሥራ ይፈጥራል፣ ኢኮኖሚ ያሸጋግራል፣ ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመሻገር እንደ መስፈንጠሪያ ሆኖ ያገለግላል በማለት አብራርተዋል። በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነት አንዱ አንጓ ነው በማለት አስረድተዋል። የብዙ መንግሥታትና የእኛም ትኩረት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ላይ የሆነበት ዋናው ምክንያት፤ ኢንዱስትሪ ማደግ ለሚያስብ ሀገር በጣም ወሳኝ ነገር ስለሆነ ነው ብለዋል። አክለውም፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ልብ መሆኑን አስገንዝበዋል። አንድ ሰው ልቡ ካልሠራ ሌላው አካላቱ ጤነኛ ቢሆንም ውጤታማ እንደማይሆን ሁሉ፤ ኢኮኖሚን ኢኮኖሚ የሚያደርገው የኢኮኖሚ ልብ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ነው ብለዋል። እንዲሁም የከተማ እና የከተሜነት እሳቤ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ስኬት ያለውን ወሳኝ ሚና አንስተው፤ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሊከናወንና ሊሳካ የሚችለው በጥግግት የሚኖሩ ሰዎች ሲኖሩ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሕዝብ ጥግግት ለልማት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልማትንና ብልጽግናን የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ከተማን፣ ከተሜነትን፣ ግብር መክፈልንና አገልግሎት መስጠትን ማዕከሉ ካላደረገ ልማት ሊያመጣ እንደማይችል አብራርተዋል። ከተማ አያስፈልግኝም፤ የእኔ ትኩረት አርሶ አደር ብቻ ነው የሚል እሳቤ ካለ ልማትን ማሰብ እንደማይቻልም አመላክተዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በወሎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ በጎበኙበት ወቅት፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ሥር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተመለከትነው የስንዴ ልማትም የራዕያችንን ውጤት፣ የሐሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው በማለት ገልጸዋል። እንዲሁም በ "ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር የተገነባውን የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ሥራ ማስጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ጸጋን የመለየት፣ የማልማትና ወደ ሀብት የመቀየር ማሳያ እና የወሎ የብልጽግና ተስፋ ነው ብለዋል። ይህ ፕሮጀክት ከግንባታው ጅማሮ እስከ ፍጻሜው የ"መደመር" ዕሳቤ በተግባር የታየበት፣ የመንግሥት ሐሳብ፣ የባለ ሀብቱ ታታሪነት እና የሕዝቡ ትጋት የተሰባጠረበት ድንቅ ውጤት ነው ሲሉም ገልጸል። ያየነው ልማት የሰላም ውጤት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ሰላማቸውን አጥብቀው እንዲጠብቁ አደራ በማለት፤ በአንድነት እና በትጋት ከሠራን ይህ ቀጣና የዕድገትና ብልጽግና መዳረሻ መሆኑ አይቀሬ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። እንዲሁም የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንትን የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ በዚሁ ወቅት መሠረተ-ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብዓቶችን በማመላለስ የኢኮኖሚያችን የደም ሥር፣ የብልጽግናችን መሠረት ነው ብለዋል። በዐውደ ርዕዩ የተመለከትነውም ወሳኝ የልማት ተቋሞቻችን፣ መሠረተ-ልማትን እንደ ሀገር በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆናቸው ነው ሲሉም ገልጸዋል። መንግሥት በመንገድ፣ በኃይል፣ በመስኖ፣ በባቡርና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፍ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል። አሁን ያለንበት ወቅት የሥራ፣ የውጤት እና የተስፋ ዘመን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ትናንት የተገነባው ለዛሬ፣ ዛሬ የምንገነባው ደግሞ ለነገው ትውልድ ኩራት እና የብልጽግና ዋስትና ነው ብለዋል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 4189
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2845
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8633
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7116
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 61397
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 55239
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35729
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 33328
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 28169
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 27469
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26962
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26464
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 61397
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 55239
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35729
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 33328
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 494
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው።   በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል።   የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል።   የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል።   ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 730
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም