የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብሩን “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ስታዲየም እያካሄደ ነው።
በቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ብልጽግና ፓርቲን በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ተገኝተዋል።