አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ ስድስት ነጥብ ከፍ ለማድረግ ከፉልሃም ጋር ይፋለማል - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ያለውን ልዩነት ወደ ስድስት ነጥብ ከፍ ለማድረግ ከፉልሃም ጋር ይፋለማል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 አርሰናል ከፉልሃም በኤምሬትስ ስታዲየም ይጫወታሉ።
አርሰናል በ73 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ፉልሃም በ48 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ካሸነፈ መሪነቱን ያጠናክራል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ያሰፋል።
በ34ኛው ሳምንት አስቶንቪላን 1 ለ 0 ያሸነፈው ፉልሃም ሶስት ነጥብ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን ይበልጥ እንዲያሳድግ ያደርገዋል።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት የሊግ ጨዋታ አርሰናል በሊያንድሮ ትሮሳርድ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ብሬንትፎርድ ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ ዎልቭስ ከሰንደርላንድ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ከብራይተን በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።